Amhara Prosperity Party /APP/

Amhara Prosperity Party /APP/ "የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ቴሌግራም ▶https://t.me/amharaapp

''የመጀመርያው አለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ የጋራ ብልፅግና፣ ፍትህና ርትዕ የተረጋገጠበት ዓለም ለመፍጠር አዲስ ምዕራፍ ከፋች ነው'' ክቡር አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ...
07/09/2026

''የመጀመርያው አለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ የጋራ ብልፅግና፣ ፍትህና ርትዕ የተረጋገጠበት ዓለም ለመፍጠር አዲስ ምዕራፍ ከፋች ነው'' ክቡር አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በሴኡል ደቡብ ኮሪያ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ICDPP) የምክክር መድረክ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር (ICDPP) ከኤሺያ፣ ከአፍሪካ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ የተወጣጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መሪዎችን የሚያገናኝ መድረክ ነው።

የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ በልዩ ልዩ የፖለቲካ ባህሎች መካከል የእርስ በእርስ ግንዛቤን ማሳደግ፣ እምነትን ማጠናከር፣ በጋራ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መለዋወጥ እና ቀጣይነት ያለው አለም አቀፍ ትብብር የሚደረግባቸውን መንገዶችን ማመላከት ነው።

በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ፣ የምክክር መድረኩ ሊኖረው ስለሚገባው ተልዕኮ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዲፕሎማሲ ሚና፣ አወቃቀር፣ ሊከተላቸው የሚገቡ መርሆዎች እና በብልፅግና ፓርቲ የመደመር እሳቤ ተሞክሮዎች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል።

ክቡር አቶ አደም በንግግራቸው፣ የምክክር መድረኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝብን ፍላጎት የሚያንፀባርቁ መሪዎችን የሚያፈሩና ፖሊሲዎችን የሚቀርፁ መሆናቸውን ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት አንስተዋል።

መድረኩም በመንግስታት መደበኛ ዲፕሎማሲ እና በሕዝቦች መካከል ባለው ግንኙነት መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ ወሳኝ የጋራ መድረክ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተለይም ዋና ትኩረቱ እምነትን መገንባት፣ የርዕዮተ-ዓለም ውጥረትን መቀነስ፣ ተቋማዊ ልምድ ልውውጥን ማጠናከር፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው መሪዎች ማፍራት ላይ መተባበር፣ ግጭቶችን መከላከል እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር መሆን እንዳለበት አብራርተዋል።

በተጨማሪም የሃሳብ ብዝሃነት፣ ሉዓላዊ እኩልነት፣ አካታችነት፣ ተቋማዊነት እና ተጨባጭ ትብብር መርሆዎች ሊመራ እንደሚገባም አክለዋል።

የምክክር መድረኩ በዋናነት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸውም ዋና ዋና ጉዳዮች ሶስት መሆናቸውንም አንስተዋል።

የመጀመሪያው ዲሞክራሲያዊና ተቋማዊ ጥንካሬ ማረጋገጥ ሲሆን በዚህም ሰላማዊ ምርጫን፣ የህግ የበላይነትን እና ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ማተኮር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁለተኛው አካታች ልማትና ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን ማምጣት ሲሆን ከዚህ አኳያ ብልፅግና ፓርቲ የሚመራበት የመደመር እሳቤ መሰረት በማድረግ፣ ሁሉንም አቅሞች ተጨማሪ እሴትና አቅም በሚፈጥር አኳኃን ደምሮ በመጠቀም በማጎልበት የምግብ ሉዓላዊነትን፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና ዘርፈ ብዙ ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል አንስተዋል።

ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል በሶስተኛነት ያነሱት ሰላም ግንባታና ቅድመ-ግጭት መከላከልን ማጠናከር ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግጭትንና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ለመከላከል የሚያስችሉ ምክክሮች ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በአጠቃለይ ክቡር አቶ አደም፣ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች መርህን መሰረት ያደረገና በተግባር ላይ ያተኮረ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ካስቻለ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት፣ የጋራ ብልፅግና፣ ፍትህና ርትዕ የተረጋገጠበት ዓለም ለመፍጠር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት እምነታቸው መሆኑን አንስተዋል።



~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

07/09/2026
ጳጉሜን 2  የማንሰራራት ቀን ነው። ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት!  ~•~•~•~•🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊   "የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን...
07/09/2026

ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን ነው። ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት!
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

ፓርቲው ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ያከናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ ነው ፦  አቶ ነብዩ ስሑልየብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ልዑክ በቻይና እያካሄደ ያለው የልምድ ልወውጥ እ...
07/09/2026

ፓርቲው ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ያከናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ ነው ፦ አቶ ነብዩ ስሑል

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ልዑክ በቻይና እያካሄደ ያለው የልምድ ልወውጥ እንደቀጠለ ሲሆን የፓርቲ አደረጃጀትና ተቋም ግንባታን የሚያሳዩ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ተቋማትን ጎብኝቷል።

ፓርቲያችን ብልፅግና በመደመር እሳቤ በመመራት የተዛቡ ትርክቶችን በማረም ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ባከናወናቸው ተግባራት ወንድማማችነትና አህትማማችነት እየጎለበተ እንዲመጣ ማስቻሉን የሉዑኩ ቡድን መሪ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሑል ገልፀዋል።

የልዑኩ አባላትም በሁለትዮሽ ውይይት መድረኮች ባነሷቸው ሀሳቦች ብልፅግና ፓርቲ ባዘጋጀው ስትራቴጂክ ፕላን መሠረት በመፍጠርና መፍጠን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እንዲሁም በዲፕሎማሲ መስክ እየመጡ ያሉ ለውጦች የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በተጨባጭ እያስመሰከረ ነው ብለዋል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአገራችን የዴሞክራሲ ባህል እየጎለበተ መምጣቱን እንዲሁም ጠንካራ ተቋማትን እየተፈጠሩ መሆናቸውን ማሳያ ነው ያሉት ።

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የእሳቤ እና የተግባር አንድነት እንዲሁም የፓርቲ ግንባታ ዙሪያ ልምድ የመውሰድና የመደመር እሳቤ ተሞክሮዎችን ማጋራት የተቻለ ሲሆን ከላይ እስከ ታችኛው ድረስ ተቀናጀና የተናበበ መዋቅር በመፍጠር የሀገርን ዘላቂ ጥቅም በማስከበር እና የጋራ ዓላማን ለማሳካት ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

የሲፒፒሲሲ ኮሚቴ አባልና የሲፒፒሲሲ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሊን ሶንግተን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደችው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በወሳኝ ሀገራዊ ወሳኝ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ ብልፅግና ፓርቲ ያደረገውን በሳል አስተዋጽዖ በአድናቆት እንደሚመለከቱ ገልጸዋል።

እንዲሁም በአጠቃላይ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ) አመራርነት እየተመዘገበ ያለው ለውጥ አስደናቂ መሆኑን በመጥቀስ ሁለቱ ፓርቲዎች በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ያላቸዉ አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ልዑኩ ከሚያካሂደው የስራ ጉብኝት በተጨማሪ የሁለቱን ፓርቲዎች ወዳጅነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይም ውይይት አካሂዷል።

''እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!"‎‎በሰሜን ጎጃም ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀን"በአንድነትና በትብብር ሃገርን እናሻግራለን" እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!በሚል መሪ ...
06/09/2026

''እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!"

‎በሰሜን ጎጃም ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀን"በአንድነትና በትብብር ሃገርን እናሻግራለን" እመርታ ፣ለዘላቂ ከፍታ!በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ ነው።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

ግብርናና ኢንዱስትሪን በማመጋገብ ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተሰራ ነው "የእመርታ ቀን"ን አስመልክቶ በደብረ ብርሃን ከተማ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተከናወኑ የ...
06/09/2026

ግብርናና ኢንዱስትሪን በማመጋገብ ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተሰራ ነው

"የእመርታ ቀን"ን አስመልክቶ በደብረ ብርሃን ከተማ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች በከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተጎብኝተዋል።

በዕለቱ በአንጎለላ ቀበሌ በ605 ሄክታር መሬት ላይ በኩታ ገጠም አሰራር የለማ የስንዴ ማሳ፣ እንዲሁም የጁሹ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ጉብኝት ተደርጓል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደገለጹት፣ ደብረ ብርሃን በግብርናውም ሆነ በኢንዱስትሪው ዘርፍ በርካታ የመልማት አማራጮች ያሏት ከተማ ናት። በክልሉ መተግበር የጀመረው የዘላቂ ልማትና የአሻጋሪ ዕቅድ ዋነኛ ዓላማ የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ መሆኑን ጠቅሰው፣ ግብርናና ኢንዱስትሪን በማመጋገብ ምርታማነትን በመጨመር የኑሮ ውድነቱን ለማቅለል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም በአብነት በጎሸባዶ፣ በአንጎለላ፣ በቢርቢሳና በጽጌሬዳ ቀበሌዎች ሰፋፊ የስንዴ ክላስተሮች በዘመናዊ መካናይዜሽን እየለሙ ሲሆን፣ ከተማዋ በወተትና በዶሮ እርባታም አርአያ የሚሆኑ አሰራሮች እንዳሏት ተገልጿል። ይህ እንቅስቃሴ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያፋጥን መሆኑን የገለጹት ከንቲባው፤ በከተማዋ የግብርና ምርቶችን እንደ ጥሬ ዕቃ የሚጠቀሙ በርካታ ፋብሪካዎች መኖራቸውንም አብራርተዋል።

ወደፊትም መልካም ተሞክሮዎችን አጠናክሮ ማስፋት እንደሚገባ ያስገነዘቡት ተቀዳሚ ከንቲባው፤ አርሶ አደሮች የባለሙያዎችን ምክረ ሀሳብ በመተግበር ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና የሚተርፋቸውን ምርት ለገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን የመቀነስ ድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ምርታማነት ሲያድግ ኢኮኖሚው እንደሚረጋጋ፣ የኑሮ ውድነት እንደሚቀንስና የከተማዋና የአካባቢው ልማት እንደሚፋጠን ያመለከቱት አቶ በድሉ፤ የተቀመጠው ግብ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየተሰማሩበት ሙያ ጉልበታቸውን አፍስሰው፣ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

በደሴ ከተማ አስተዳደር «የኢትዮጵያ መንሰራራት!» በሚል መሪ ቃል የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን»ን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶች አጠቃላይ የመስክ ጉብኝት ተካ...
06/09/2026

በደሴ ከተማ አስተዳደር «የኢትዮጵያ መንሰራራት!» በሚል መሪ ቃል የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን»ን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶች አጠቃላይ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

​የደሴ ከተማ ብልፅግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዓለማየሁ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት የመደመር መንግሥት ያስመዘገባቸውን የልማት ውጤቶች መነሻ በማድረግ በከተማዋ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በጥቅል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የታዩትን እመርታዎች የከተማው ሕዝብ በግንባር ተገኝቶ እንዲገነዘብ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

​በዚሁ የምርት እና የልማት እንቅስቃሴ ምልከታ ​በኢንዱስትሪ ፓርክ ሼዶች ውስጥ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በእንጀራ ዝግጅት እና በሌሎች የምግብ ማቀነባበሪያ ዘርፎች ከተሰማሩ ወጣቶች በተጨማሪ በልብስ ስፌት፣ በቅባት እና ኮስሞቲክስ እንዲሁም በመድኃኒት ምርት ስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችና ሴቶች ምርታማነት ተጎብኝቷል።

​በግብርናው ዘርፍ ደግሞ የመኸር የስንዴ ልማት እንቅስቃሴ እና የተገኙ ተጨባጭ ውጤቶችና ድሎች ተገብኝተዋል።

​አቶ አሸናፊ አክለውም በስንዴ ልማት ዘርፍ የታየው እመርታ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ስኬታማነት የሚያረጋግጥ አቢይ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

​በከተማዋ ከተረጅነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት በርካታ መሆናቸውን የጠቆሙት ኃላፊው በአረንጓዴ አሻራ፣ በግብርና፣ በኢንቨስትመንት መስክ እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ የተመዘገቡት ድሎች የደሴን የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ትልልቅ እመርታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለባቸው ሠይድ በከተማችን 121 መካከለኛና ከፍተኛ አምራቾች መኖራቸውን ጠቁመው ለአምራቾቹ የጥሬ እቃን የሃይል ችግር ተፈቶላቸው የማምረት አቅማቸው እየጨመረ መንጣቱን ተናግረዋል።

አቶ አለባቸው አያይዘው በ2018 ለ2318 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል እንደተፈጠረና በቀጣይ ከዚህ በተሻለ እደሚሰራ ተናግረዋል።

የደሴ ከተማ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ እዩኤል ሙልዬ በግብርናው ዘርፍ በሰብል ልማት በአረንጓዴ አሻራና በአትክልት ልማት በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸው በተለይ ተረጂነትን በመቀነስ ምርታማነትን በማሳደግ ምግብ እጥረት ያጋጠማቸውን ለመደገፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በጉብኝቱ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ አለማየሁ፣የከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣የመምሪያ አመራሮች፣የክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

በዞኑ 14 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል።የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በጉብኝት በመቃኘት «የዕ...
06/09/2026

በዞኑ 14 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በጉብኝት በመቃኘት «የዕመርታ ቀንን» በፍኖተ ሰላም ከተማ አክብሯል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መንገሻ እንኳሆነ እንደገለጹት በከተማ አሥተዳደሩ ምርት እና ምርታማነትን የሚያሳደጉ ሥራዎች ተጠናክረው እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ሰብልን በመኸር ወቅት ከማልማት ባለፈ ያሉትን ፀጋዎች በመጠቀም በበጋ መስኖ የማልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱንም አብራርተዋል።

አክለውም የቡና እና ፍራፍሬ ልማትን ወደ ሰፊ የኩታ ገጠም አሠራር ለማሳደግ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመው የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅም ሳይታረሱ የቆዩ ከ31 ሄክታር በላይ የቆዩ መሬቶች መልማታቸውን ተናግረዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ሰውመኾን ተገኘ በበኩላቸው የግብርናውን ዘርፍ ከነበረበት ኋላቀር አሠራር ለማውጣት የክላስተር አደረጃጀቶችን የማጠናከር እና ምርታማነትን የሚያሳድጉ አማራጮችን የመጠቀም ሥራዎች ትኩረት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በመኸር ወቅት ከሚለማው ከ266 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በተጨማሪ ጾም ሲያድሩ የነበሩ መሬቶችን በሰብል የመሸፈን ውጤታማ ተግባር መከናወኑንም አንስተዋል።

ኀላፊው አክለውም በዞኑ ባለፈው ዓመት ከተገኘው 13 ሚሊዮን ኩንታል ምርት በዘንድሮው የምርት ዘመን ወደ 14 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት ዘመናዊ ግብርናን እውን ለማድረግ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ እንቅስቃሴዎች የሚያበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር በተለያዩ ወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች ጳጉሜ-1 የእመርታ ቀን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በልዩ ልዩ  መርሃ ግብሮችና ዝግጅቶች  ተከብሯል።   ...
06/09/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር በተለያዩ ወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች ጳጉሜ-1 የእመርታ ቀን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮችና ዝግጅቶች ተከብሯል።

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

ጳጉሜ 1 "የእምረታ ቀን" በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የመስክ ሰብል ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ተካሄደ በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ "እመርታ...
06/09/2026

ጳጉሜ 1 "የእምረታ ቀን"

በደቡብ ወሎ ዞን በአልብኮ ወረዳ "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የመስክ ሰብል ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው «የእምርታ ቀን» በደመቀ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን፤ የግብርና ልማት ሥራዎችንና የልምድ ልውውጥን ያካተተ የመስክ ሰብል ጉብኝት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በእለቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ እንደገለጹት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ራስን መቻልን ለማረጋገጥ፣ ለአግሮ-ፕሮሰሲንግ ፋብሪካዎች የግብርና ምርቶችን ለማቅረብ እና የውጭ ምርቶችን በመተካት ኤክስፖርት የማሳደግ ሦስት ዋና ዋና ግቦችን ታስበው የተከናወኑ ናቸው።

አቶ አህመድ አያይዘውም ባለፉት ዓመታት ከ96 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ማስመረቅ የተቻለ ሲሆን፣ በያዝነው ዓመትም ከ261 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ለማስመረቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም 14 ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ከምግብ ዋስትና ችግር ነፃ የሚያደርጉበት የትኩረት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ማሾ፣ ባቄላ እና አኩሪ አተር ያሉ ኤክስፖርት የሚደረጉ ሰብሎችን የማምረት ሥራ የተጀመረ ሲሆን፤ ያልታረሱና የጋራ መሬቶችን በማረስ ለመጠባበቂያ የሚሆን ምርት የማከማቸት አሰራር ተዘርግቷል።

በዚህም በዞኑ ከ293 ሄክታር በላይ የወል መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን፣ ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ እህልና 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ከማኅበረሰቡ በማሰባሰብ የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።

የአልብኮ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብደላህ ሰይድ በበኩላቸው፤ በወረዳው የሕዝቡን የተረጅነት አስተሳሰብ በመቀየር የመሬት፣ የውኃና የሰው ኃይል ጸጋዎችን አቀናጅቶ ለመጠቀም ሰፊ የመግባባት ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል። በወረዳው ከ14 ሺህ 952 ሄክታር በላይ የሚታረስ መሬት የሚገኝ ሲሆን፣ ከ553 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገመትም ጠቁመዋል።

በወረዳው ከተረጅነት ማላቀቅ ጋር ተያይዞ በ03 ፈላና ቀበሌ እስካሁን ታርሶ የማይታወቀውን 39 ሄክታር የወል መሬት ከማኅበረሰቡ ጋር በመስማማት በትራክተር የማረስ ሥራ የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 7 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት በባቄላ፣ በጤፍ፣ በስንዴና በበቆሎ ዘር ተሸፍኖ በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል።

በምልከታው ወቅት ያናገርናቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች አራጋው ይመር እና ሰይድ ሙሀመድ፤ ከዚህ ቀደም ለእንስሳት ማገጃነት ይውል የነበረውን የወል መሬት በጋራ በመስማማትና በትራክተር ማረስ መጀመራቸው ከእርዳታ ጠባቂነት ለመውጣት ትልቅ ተስፋ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ የግብርና ባለሙያዎችን ምክር፣ ኮምፖስትና ዘመናዊ ግብአቶችን በመጠቀም በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ በማምረት የኑሮ ደረጃቸውን እያሻሻሉ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Prosperity Party /APP/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share