ANRS Disaster Risk Management Commission

Directions Website Contact the organization

ANRS Disaster Risk Management Commission ለአደጋ የማይበገርና የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን!

በደዌ ሀረዋ ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ ሊከሰት የሚችልን የአደጋ ስጋት ለመግታት የሚያስችል ጥናት ተካሄደ​ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በደዌ ሀረዋ ወረዳ የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ...
09/10/2026

በደዌ ሀረዋ ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ ሊከሰት የሚችልን የአደጋ ስጋት ለመግታት የሚያስችል ጥናት ተካሄደ

​ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በደዌ ሀረዋ ወረዳ የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የአደጋ ስጋት አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል አስቸኳይ የዳሰሳ ጥናት ተካሂዷል።

​የዞኑ አደጋ ስጋት አይበገሬነት ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በወረዳው የተከሰተው የዝናብ እጥረት በኅብረተሰቡ፣ በሰብልና በእንስሳት ሀብት ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በቦታው ተገኝተው የዳሰሱ ሲሆን፣ ከመስክ ምልከታው መልስም ከደዌ ሀረዋ ወረዳ ስቲሪንግ እና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር ጥልቀት ያለው የምክክር ውይይት አካሂደዋል።

​በመድረኩ ላይ ከመስክ ዳሰሳ ጥናቱ የተገኙ መረጃዎችና የምልከታ ውጤቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ ሁለቱ ወገኖች በጋራ በመምከር በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና የመከላከል እርምጃዎች ላይ ሙሉ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

​ይህ ቅንጅታዊ የመስክ ምልከታና የተደረገው የጋራ ውይይት በወረዳው የዝናብ እጥረቱ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ፈጣን የቅድመ ማስ his warning (የቅድመ ማስጠንቀቂያ) እና የቁስ ድጋፍ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የማህበረሰቡን አይበገሬነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጻል።

Harawa

"በሩብ ዓመቱ የታዩ ስኬቶችና መልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል" — አቶ አለሙ ይመርየሰሜን ወሎ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ጽሕፈት ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመርያ...
09/10/2026

"በሩብ ዓመቱ የታዩ ስኬቶችና መልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል" — አቶ አለሙ ይመር

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ጽሕፈት ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመርያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

በመድረኩ የጽሕፈት ቤቱ የዕቅድና በጀት ክትትል ባለሙያ ወጣቷ ኤልሳቤጥ አየነው ያቀረቡት አጠቃላይ ሪፖርት፤ ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑ ቁልፍና አበይት ተግባራትን፣ በምግብ ራስን ለመቻል የተደረጉ ጥረቶችን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በዝርዝር ዳሷል። የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግም በየደረጃው ከሚገኙ የዞኑ ባለሙያዎች ጋር ሰፊና ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል።

የምክክርና የግምገማ መድረኩን የመሩት የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር፤ የሩብ ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም በወቅቱ መገምገም መቻሉ ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑትንና ያልተከናወኑትን ተግባራት በጥብቅ ዲስፕሊን ለመቃኘትና ራስን ለመፈተሽ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል።

ኃላፊው አክለውም በሩብ ዓመቱ የታዩ መልካም ልምዶችና ስኬቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተመሳሳይ መልኩ ያልተፈጸሙና ትኩረት ያላገኙ አበይትና ቁልፍ ተግባራት ተለይተው በቀጣዩ ሩብ ዓመት የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ የማረም እርምጃ እንዲወሰድ በማሳሰብ፣ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የግምገማ መድረኩ ፍጻሜ አግኝቷል።

በሰሜን ወሎ ዞን የኤሊኖ ክስተት እና የዝናብ እጥረት ትንበያን ተከትሎ በተወሰዱ ቅድመ-ዝግጅቶች ምክንያት የሰብል አዝመራው በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።የቆቦ...
09/10/2026



በሰሜን ወሎ ዞን የኤሊኖ ክስተት እና የዝናብ እጥረት ትንበያን ተከትሎ በተወሰዱ ቅድመ-ዝግጅቶች ምክንያት የሰብል አዝመራው በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

የቆቦ ከተማ ከንቲባ ኃይለአብ ወንድሙ እና የከተማዋ ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት እንዳስረዱት ከአርሶ አደሮች ጋር በተደረገ ቅድመ-ተግባቦት ድርቅን የሚቋቋሙ እና በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት ውጤታማ መኾን ተችሏል።

በዚህም 200 ሄክታር የቦሰት ጤፍ እና 200 ሄክታር የመልካም ማሽላ በኩታ ገጠም የለማ ሲኾን ከዚህ ውስጥ 100 ሄክታሩ (50 ሄክታር ጤፍ እና 50 ሄክታር ማሽላ) ለቀጣይ መኸር የዘር ምንጭ የሚኾን የዘር ብዜት ታሳቢ ተደርጎ የተዘራ ነው።

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተገኝ አባተ በበኩላቸው የዝናብ እጥረቱን ለመቋቋም ሦሥት ቁልፍ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
👉የመስኖ አማራጮችን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ዝግጁ ማድረግ፤
👉የዝናብ ውኃን በማቀብ የአፈር እርጥበትን ማቆየት እና
👉ፈጥነው የሚደርሱ እና ድርቅን የሚቋቋሙ የሰብል ዝርያዎችን መዝራት ከተወሰዱ እርምጃዎች ዋናዎቹ ናቸው።
ኀላፊው አክለው እንደገለጹት በዞኑ ከሚገኘው ከ231 ሺህ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት ውስጥ ከአፋር ክልል ጋር በሚዋሰኑ ቆላማ አካባቢዎች ዝናብ ባለመጣሉ 40 ሺህ ሄክታሩ በድርቅ ተጎድቷል። ኾኖም ቀሪው መሬት በጥሩ የሰብል ቁመና ላይ የሚገኝ በመኾኑ በመኸሩ ለማግኘት የታቀደውን 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማሳካት ይቻላል ተብሎ ይጠበቃል።
North Wollo Communication ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን

09/10/2026
09/10/2026
09/10/2026
09/10/2026
09/10/2026
09/10/2026

‎ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ይከበራል።
‎
‎የቀኑን አከባበር በማስመልከት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል፦
‎
‎19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የኢፌዴሪ መንግሥት ፕሬዘዳንት በተገኙበት በድምቀት ይከበራል፡፡
‎
‎19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡
‎
‎የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሠረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ይደነግጋል፡፡
‎
‎ይህ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩት ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር የመስጠትና የማክበር ኃላፊነትና ግዴታ አለበት፡፡
‎
‎ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ በዋናነት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫና አርማ ነው፡፡ ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሠንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበትና በሀገራዊ አንድነትና ህብረ ብሔራዊነት መግባባትን የሚፈጥሩበት ሀገራዊ በዓል በመሆኑ ነው፡፡
‎
‎ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ከጀመረ እነሆ አስራ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ዘንድሮ ለአስራ ዘጠነኛ ጊዜ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነትና አስተባባሪነት በመላ ሀገሪቱ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድምቀትና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከበራል፡፡
‎
‎በዚህም መሠረት ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዕለቱን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን መልዕክት በማስተላለፍ በንግግር ከከፈቱ በኋላ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት በመላው ሀገሪቱ ዜጎች በሠንደቅ ዓላማው ፊት ቃለ መሃላ የሚፈጸምበት ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡
‎
‎ከዚያም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ እና ክብር ዘብ ታጅበው በክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት አማካኝነት ሠንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።
‎
‎በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት፣ ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
‎
‎ይህ በዓል በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች በተመሳሳይ ሰዓትና ድምቀት ይከበራል።
‎
‎የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት!
‎
‎
‎ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/
Ticktock: https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8uQMisH1Hd7&_r=1
Website: https://www.amharacomm.gov.et

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለድህነት ቅነሳ የለማውን ሰፊ የማሽላ ሰብል ጎበኙ መሰከረም 28/2019 የቀወት ወረዳ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለድህነት ቅነሳና አደጋ ስጋት መጠባበቂያ የ...
08/10/2026

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለድህነት ቅነሳ የለማውን ሰፊ የማሽላ ሰብል ጎበኙ
መሰከረም 28/2019 የቀወት ወረዳ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለድህነት ቅነሳና አደጋ ስጋት መጠባበቂያ የለማውን ሰፊ የማሽላ ሰብል ጉብኝት አካሄዱ ።
በጉብኝቱ ያገኘናቸው ወ/ሮ ማህሌት እደግልኝ የቋሚ ኮሚቴው የኢኮኖሚ ጉዳዮች አባል መሆናቸውን ገልጸው ኮሚቴውድጋፍና ክትትል ከሚያደርጋቸው የኢኮኖሚ ጉዳዮች መካከል ግብርና አንዱና ዋነኛው መሆኑን ነግረውናል ።
ወ/ሮ ማህሌት አክለውም ለአደጋ ስጋት መጠባበቂያ በለማው 32 ሄክታር ሰፊ የማሽላ ሰብል ያለበትን ቁመና ምልከታ አድርጎ ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለፍሬ የሚያበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማከናወን መሆኑን አብራርተዋል ።
በዚህም ሰብሉ በጥሩ ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን በዝናብ እጥረት ምክንያት የሚገጥሙ ችግሮችን ለማቃለል የግብርና ጽ/ቤት የመስኖ እና ሰብል ልማት ቡድን ትኩረት ሰጥተው በውኃ መሳቢያ ሞተር በመጠቀም የማጠጣት ስራ እናከናወኑ መሆኑ ተገልጿል ።
ቋሚ ኮሚቴው የኤፍራታና ግድም ወረዳ ላበረከተው የልማት አጋርነት ምስጋና አቅርቧል ።
ምንጭ፣ ቀወት ወረዳ See less

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Disaster Risk Management Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Disaster Risk Management Commission:

Shortcuts

Share