Amhara Region President Office

Amhara Region President Office Amhara National Regional State president office is one of the Amhara region Governmental office that is established for public service delivery.
(1)

05/06/2026
05/06/2026
የባሕር ዳር የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ነው በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት ፕሮጀክት፤ ከተ...
03/06/2026

የባሕር ዳር የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ነው

በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት ፕሮጀክት፤ ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለቱሪስቶች ደግሞ ተመራጭ እያደረጋት ይገኛል።

የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስኬቶች እና ፋይዳዎች፦

🔹የቱሪዝም መነቃቃት፦ የዐይን ማረፊያ የኾኑ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የጣና ዳርቻ ዘመናዊ መንገዶች፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መስመሮች የጎብኚዎችን ቆይታ ያራዝማሉ።
የዘንባባ ፓርክም ሙሉ በሙሉ ሳቢ ኾኖ ተጠናቅቋል።

🔹ውበት እና ደኅንነት፦ ለአረንጓዴ ልማት የተሰጠው ትኩረት ከተማዋን ውብ እና ንጹሕ ከማድረጉ ባለፈ፣ የዘመናዊ መንገድ መብራቶች መገጠማቸው የምሽት እንቅስቃሴን እና ደኅንነትን አሳድጓል።

🔹የኢኮኖሚ ዕድገት፦ የቱሪስት ፍሰቱ መጨመር ለሆቴሎች፣ ለትራንስፖርት እና ለአካባቢው ነጋዴዎች ሰፊ የሥራ ዕድል እና ከፍተኛ ገቢ እየፈጠረ ይገኛል።

🔹"የባሕር ዳር ኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ ለትውልድ የሚተርፍ አሻራም ነው።

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው ሕዝባችን ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል"         ክቡር አረጋ ከበደየአማራ ክልል ርእ...
03/06/2026

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው ሕዝባችን ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል"

ክቡር አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር

"ሚሊሻው የሕዝባዊነትን ትርጉም በተግባር ያሳየ ኃይል ነው" ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ  (ግንቦት 26/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በክልል ደረጃ የሚ...
03/06/2026

"ሚሊሻው የሕዝባዊነትን ትርጉም በተግባር ያሳየ ኃይል ነው" ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ

(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን ግንቦት 29/2018 ዓ.ም በክልል ደረጃ የሚካሄደውን የሚሊሻ 30ኛ ዓመት የምሥርታ በዓል እና የእውቅና መርሐ ግብር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል የሚሊሻውን ታሪካዊ ተጋድሎ እና መስዋዕትነቱን ለመዘከር የታሰበ ነው ብለዋል።

በዓሉ ለሚሊሻ አባላት እና ለቤተሰቦቻቸው ክብር እና ምስጋና ለማቅረብ፤ ተቋማዊ ሪፎርም እና ዝግጁነቱን ለማረጋገጥ፤ የሕዝቡን እና የሚሊሻውን ትስስር ለማጥበቅ እና ሌሎች ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳሉትም አንስተዋል።

ግንቦት 29/2018 ዓ.ም የአማራ ክልል ሚሊሻ የ30 ዓመታት የጀግንነት እና የሕዝባዊነት ጉዞ የሚከበርበት ልዩ ቀን እንደኾነም ገልጸዋል።

የሚሊሻ 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ሲባል የሚሊሻ ምስረታ ዕድሜው 30 ዓመት ነው ለማለት ሳይኾን በክልል ደረጃ የተቋቋመበትን ለመግለጽ እንደኾነም ተናግረዋል። ሚሊሻ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ጀምሮ ዘመናዊ ወታዳር ባልነበረት ወቅትም ነበር ብለዋል።

ባለፉት ሦሥት አስርት ዓመታት የክልሉ ሚሊሻ በርካታ ታሪካዊ ምዕራፎችን ማለፉንም ገልጸዋል።

ሚሊሻው መደበኛ የሥራ ድርሻውን ሳያስተጓጉል በአንድ እጁ አምራች በሌላ እጁ ደግሞ የሰላም ዘብ በመኾን "የሕዝባዊነትን ትርጉም በተግባር ያሳየ ኃይል ነው" ብለዋል።

ሀገራዊ የሉዓላዊነት ፈተናዎች እና ክልላዊ የጸጥታ ስጋቶች ባጋጠሙ ጊዜያት ሚሊሻው ከመከላከያ ሠራዊት እና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰለፍ በደም እና በአጥንቱ ደማቅ ታሪክ መጻፉን ገልጸዋል።

በክልሉ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ የበኩሉን ሚና ተጫውቷልም ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን 30ኛ ዓመት በዓል ሲያከብር ወደፊት የክልሉን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማስከበር እና የሰላም ጥሪ ተግባራት ላይ በትኩረት ለመሥራት ታሳቢ አድርጓል ነው ያሉት ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክ...
03/06/2026

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው፡፡

መንግሥትም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የታለመውን ዘላቂ ዕድገት እና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን አሻሽሏል፡፡ አሠራሮችን ዘርግቷል፡፡ ማበረታቻዎችን አድርጓል።

የዚህ ሪፎርም አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም ፍሬው በግልጽ እየታየ ነው።

በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊየን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማር ምርት ተገኝቷል*******በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ...
03/06/2026

በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊየን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማር ምርት ተገኝቷል
*******
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊየን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማር ምርት መገኘቱን የዞኑ እንስሳትና ዓሳ ሃብት መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የንብና ሃር ልማት ባለሙያ ስማቸው ዳምጤ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በንብ ማነብ ስራ በማሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው።

በበጀት ዓመቱ በማነብ ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን በመደገፍና በማበረታታት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ ማር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።

በዞኑ የሚገኙ ከ48 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ባሏቸው ከ200 ሺህ በላይ የንብ ቀፎዎች እስካሁን ከ2 ነጥብ 9 ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ ማር ተመርቷል ነው ያሉት።

የተመረተውን ማር ለገበያ በማቅረብ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉንም ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ(ግንቦት 25/2018 ዓ.ም) ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላ...
02/06/2026

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

(ግንቦት 25/2018 ዓ.ም) ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷንና በአማራ ክልልም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ ማሸነፋቸውን ጠቅሰዋል።

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው የክልላችን ሕዝብ ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል፤ በአማራ ክልል ምርጫ ማካሄድ ድምጽ ከመስጠት ባሻገር ነው" ብለዋል።

በክልላችን ምርጫ እንዳይካሄድ፤ ዜጎች መብታቸውን እንዳይጠቀሙ፤ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግሥት እንዳይመሠርት፣ ክልሉ ሁልጊዜ በድህነት እና በግጭት ውስጥ እንዲኖር የሚፈልጉ የውይይት እና የሰላም ተቃራኒ ኃይሎች ብዙ ጥረት ማድረጋቸውንም አንስተዋል። "ይሁን እንጂ በሕዝባችን አስተዋይነት እና በጸጥታ ኃይላችን ጀግንነት እነርሱ የፈለጉት ሳይኾን ሕዝብ የፈለገው ኾኗል" ነው ያሉት።

የክልሉ ሕዝብ ትናንት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያሳየው ተሳትፎ፣ ጽናት እና ትዕግሥት የብልሃት እና የጥበብ ምንጭ መኾኑን ያሰመሰከረበት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ምርጫው ሕዝቡ ለፈተና የማይበገር፤ በዛቻ እና በማስፈራሪያ የማይሰበር፣ ለሰላም እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የትኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል ያሳየበት እንደሆነ አስታውቀዋል። "የክልላችን ሕዝብ በትናንትናው ምርጫ የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በሕዝብ ድምጽ እንጂ በኃይል አለመኾኑን ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈበት ነው" ብለዋል።

የአማራ ክልል ሕዝብ ሰላም ወዳድነቱን፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ፈላጊነቱን፤ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ ለሚጸና መንግሥት ቀናዒነቱን በግልጽ እንዳሳየም አብራርተዋል። ለዚህ ደግሞ የከበረ ምስጋናዬን ከጥልቅ አክብሮት ጋር ማቅረብ እወዳለሁ ነው ያሉት።

"ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ምርጫው በክልላችን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገው ለሀገር መከለካያ ሠራዊት፣ ለክልላችን የጸጥታ ኃይል፣ በየደረጃው ለሚገኙ የክልላችን አመራሮች እና ለመላው የክልላችንን ሕዝብ በራሴ እና በአማራ ክልል መንግሥት ስም የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ለሀገር እና ለሕዝብ በአንድነት መሥራት ምን አይነት ስኬታማ ውጤት እንደሚያስገኝ ምርጫው ሕያው ምስክር መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በምርጫው ጫፍ ረገጥ አስተሳሰቦች እስከ አደረጃጀቶቻቸው በሕዝብ ደምጽ ከሽፈዋል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሸንፋለች ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት መልእክት።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ************* ‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ...
02/06/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
*************

‎ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል።

‎ይህ ትልቅ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል።

‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፤ የማይቆራረጥ የልማት ስራችን ህያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሃገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በአማራ ክልል በስኬትና  በታላቅ ድል መጠናቀቁ ተገለጸ።በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በከፍተኛ ስኬት ስልጡን እና ህዝባዊ ተሳትፎ በጎላ...
02/06/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በአማራ ክልል በስኬትና በታላቅ ድል መጠናቀቁ ተገለጸ።

በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በከፍተኛ ስኬት ስልጡን እና ህዝባዊ ተሳትፎ በጎላበት መልክ በታላቅ የህዝብ ድል መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተወዳዳሪ የሌለው ሚና ለተጫወቱት የክልሉ ፖሊስ፣ ለጀግናዉ የመከላከያ፣ የፌደራል ፀጥታና የደህንነት አካላት ፣ለመላዉ ህዝባችን እና ለሌሎች የክልላችን የጸጥታ መዋቅሮች በሙሉ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የላቀ ምስጋናና እውቅና አቅርቧል።

ሁሌም ሰላምና ልማትን ቀዳሚ የሚያደርገው የክልሉ ህዝብ የምርጫ ካርድ ከመውሰድ ጀምሮ በምርጫው ዕለት በታላቅ ትዕግስት እና ስነ-ስርዓት ድምፅ እስከመስጠት ድረስ ያሳየው ፍቅርና ሀገር ወዳድነት የታሪክ ማህደር የማይረሳው መሆኑን ገልጿል።

በምርጫው ዕለት ህብረተሰቡ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በነቂስ በመውጣት በክልሉ በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ያከናወነው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ያለምንም መሰላቸት እስከ ምሽት ሰአት መከናወኑን አረጋግጧል።

ህብረተሰቡ ረጅም ሰልፎችን በታጋሽነት በመሰለፍ፣ የመምረጥ መብቱን በአግባቡ መጠቀሙ የሰለጠነ ዴሞክራሲያዊ ባህሉን ያሳየበትና ለምርጫው ስኬታማነት ትልቁን ድርሻ ያበረከተበት መሆኑንም ጠቁሟል።

ምርጫው የክልሉን ህዝብ ብስለት፣ ሰላም ወዳድነት እና ለሀገር ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት ዳግም ለዓለም ያስመሰከረበት ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑንም ዋና ጠቅላይ መምሪያው አመላክቷል።

ሀገራዊ ምርጫው በስኬት ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሌት ከቀን የህግ ማስከበር ስራቸውን በብቃት ለተወጡት ለክልሉ ፖሊስ አባላት፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለፌዴራል ፖሊስ፣ለብሔራዊ ደህንነት አካላትና ለሌሎች የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ታላቅ አክብሮትና እውቅና ሰጥቷል።

የጸጥታ ኃይሉ ሂደቱን በበላይነት በመምራትና የእያንዳንዱን አካባቢ ህብረተሰብ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ በማንቀሳቀስ፣ ከህዝብ የተውጣጡ የሰላም ኮሚቴዎችንና አደረጃጀቶችን ከራሱ የጸጥታ መዋቅር ጋር በማስተሳሰር የጋራ የሰላም ግንባር መፍጠር በመቻሉ ሰላሙን ማረጋገጥ መቻሉንም አረጋግጧል።

ይህንን ስራ ስኬታማ ለማድረግ የጸጥታ ኃይሉ አባላት ሌት ከቀን ያሳዩት ከፍተኛ ልፋት፣ ድካም እና ተጋድሎ በአንዳንድ ቦታዎች የምርጫውን ሂደት ለማደፍረስና ሁከት ለመፍጠር አልመው የተንቀሳቀሱ ህገ-ወጥ አካላትን የጥፋት ሴራ ቀድሞ በተዘጋጀ ስልታዊ የመከላከል እቅድ ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ መቻሉንም አመላክቷል ።

የጸጥታ ኃይሉ የተጣለበትን ታሪካዊ አደራ የመወጣት ጀግንነት፣ ሙያዊ ብቃት እና የገባውን ቃልኪዳን በታማኝነት በመፈጸም የህዝቡን ደህንነት በልዩ ጥንቃቄ የማስጠበቅ ስራ፤ ከተቋማዊ ኩራት ባሻገር ለክልሉና ለሀገሪቱ ታላቅ ክብርን ያጎናጸፈ ተግባር በመሆኑ ላቅ ያለ ምስጋናና እውቅና ሰጥቷል።

ምርጫውን ለማወክ የሞከሩ ማናቸውንም የፀረ-ሰላም ኃይሎች የጥፋት አጀንዳ ሙሉ በሙሉ ያከሸፈ ታላቅ የህዝብ ድል የተመዘገበው ህዝቡ ያሳየው አስተዋይነት እና የሰላም ባለቤትነት ስሜት በመኖሩ እንደሆነም አክሏል።

ለታሪካዊ ድሉ መገኘት ህዝቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም፣ መረጃዎችን በወቅቱ በመለዋወጥ እና ለሰላም ጥበቃው ግንባር ቀደም ጠባቂ በመሆን ያሳየው ጠንካራና የተቀናጀ ጥምረት ዋነኛ መሠረት ነበር ተብሏል።

በምርጫው ወቅት የታየውን መልካም የህዝብና የፖሊስ ቅንጅታዊ አሰራርና አደረጃጀት ይበልጥ በማጠናከር የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ቀጣይም በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።

ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ለሲቪክ ማህበራት፣ ለብዙሃን መገናኛ አካላት ፣ ለዉጭና የአገር ዉስጥ ታዛቢዎች እና ለሰላም ወዳዱ ማህበረሰብ በሙሉ በድጋሚ የላቀ ምስጋና በማቅረብ፤ የተጀመረውን የሰላምና የዴሞክራሲ ጉዞ በጋራ ለማስቀጠል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጥሪ አስተላልፏል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region President Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Region President Office:

Share