Bahir Dar International Stadium Center

Bahir Dar International Stadium Center This is the official page of Bahir dar international stadium center LETS DO !!!

የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል በክፍት የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድር ለመቅጠር የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ
28/05/2026

የባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል በክፍት የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድር ለመቅጠር የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ

03/05/2026
የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።ሚያዝያ 20/2018የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እስከ መጪው ...
28/04/2026

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ሚያዝያ 20/2018

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለሀገር እና ለአህጉር አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለፀ።

የቢሮው ኃላፊ መልካሙ ፀጋዬ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ የባህር ዳር ስታዲየም ታላላቅ የእግር ኳስ ውድድሮችን ማካሄድ እንዲችል ርብርብ እየተደረገ ነው።

ስታዲየሙ ሀገር እና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በዚህም ካፍ እንዲስተካከሉ አስተያየት የሰጠባቸው የመጫወቻ ሜዳው ሣር፣ የክብር እንግዶች መቀመጫ ወንበሮች፣ የተጫዋቾች መልበሻ፣ የሚዲያና የህክምና ክፍሎች እንዲሁም መብራቶችና ሌሎችን ለማሟላት ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በመሆኑም ስታዲየሙን እስከ መጪው ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለውድድር ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የልምምድ ሜዳዎችና የመዋኛ ገንዳዎች ደረጃቸውን በጠበቀ አግባብ እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች ለቅሞ በመያዝም አብዛኞቹ ስራዎች መጠናቀቃቸውን ጠቅሰዋል።

የተሟሉትን መስፈርቶች በተመለከተ የካፍ ገምጋሚ ቡድን እንደሚገመግመው ገልጸዋል።

ታዳጊ ስፖርተኞችን በማነቃቃት ብቃት ያላቸውን ተተኪ ስፖርተኞች በሁሉም ዘርፍ ለማፍራት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመላክተዋል።

ኢዜአ

የአማራ ሊግ ውድድር ሊመለስ ነው።ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ምተወዳጅ የኾነው የአማራ ሊግ ውድድር በሁለት ቀጣናዎች ተከፍሎ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።የፌዴሬሽኑ ...
25/04/2026

የአማራ ሊግ ውድድር ሊመለስ ነው።
ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም

ተወዳጅ የኾነው የአማራ ሊግ ውድድር በሁለት ቀጣናዎች ተከፍሎ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ብርሃኔ ጌትነት የአማራ ሊግ ውድድር በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ከተቋረጠ ከሦሥት ዓመታት በኋላ በቅርብ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ውድድሩ በምሥራቅ እና በምዕራብ ቀጣና ተከፍሎ ይከናወናል ነው ያሉት። የምሥራቅ ቀጣና በደሴ ከተማ አስተናጋጅነት ከሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 09/2018ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል ብለዋል።

በደሴ ሆጤ ስታድየም በሚከናወነው የአማራ ሊግ ውድድር 10 ክለቦች እንደሚሳተፉም ገልጸዋል።
በውድድሩ አሸናፊ የኾኑ ክለቦች አማራ ክልልን ወክለው በኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ይሳተፋሉ ነው ያሉት።

በምዕራብ ቀጣናም ውድድሩን ለማከናወን ፌዴሬሽኑ እየሠራ ይገኛል ያሉት አቶ ብርሃኔ ክለቦችን የመመዝገብ ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም አንስተዋል።

ተወዳዳሪዎች በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲወዳደሩ አሳስበዋል። የደሴ እና አካባቢው ነዋሪዎች በሆጤ ስታድየም ተገኝተው ጨዋታዎችን እንዲታደሙ እና ክለቦችን እንዲያበረታቱም ጥሪ አቅርበዋል።

አሚኮ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ ፀደቀ።መጋቢት 13/2018 ዓ.ምበኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት ታሪክ ውስጥ፣ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋ...
21/04/2026

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ ፀደቀ።
መጋቢት 13/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት ታሪክ ውስጥ፣ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመሉ ድምፅ ፀድቋል።

ይህ አዋጅ ዘርፉን በማዘመን፣ የአሰራርና የህግ ስርዓቶችን በመዘርጋትና ተጠያቂነትን በማስፈን ለኢትዮጵያ ስፖርት ልማት ዕድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ውድድሮች ክልሉ አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገለፀ።ሚያዝያ 8/2018 ዓ.ምበሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር እና 23ኛው የኢትዮጵ...
16/04/2026

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ውድድሮች ክልሉ አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገለፀ።
ሚያዝያ 8/2018 ዓ.ም

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር እና 23ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ውድድር የተሳተፈው የአማራ ክልል ስፖርት ልዑካን አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገለፀ።

የአብክመ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ክልሉ በውድድሮቹ የነበረውን ተሳትፎና ውጤት ቢሮ ኃላፊው አቶ መልካሙ ፀጋየ እና ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ ጋሻው ተቀባ በተገኙበት ገምግሟል።

በግምገማው በሁለቱም ውድድሮች የነበረው የክልሉ ተሳትፎና ውጤት በዝርዝር ቀርቦ ተገምምግሟል።

በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት አዳማ ከተማ በተካሄደው የ2018 የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር ክልሉ በ10 የስፖርት አይነቶች ወደ 146 ስፖርተኞችን በማሳተፍ 40 ወርቅ፣ 22 ብርና 31 የነሃስ ሜዳሊያ በድምሩ 93 ሜዳሊያወችን በመሰብሰብ 1ኛ ሆኖ እንዳጠናቀቀ በሪፖርቱ ተገልጿል።

በሀረሪ ክልል አስተናጋጅነት ሀረሪ ከተማ በተካሄደው 23ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ፌስቲቫል የተሳተፈው የአማራ ክልል ስፖርት ለዑካን ብርቱ ፋክክር በማድረግ 6 ዋንጫወችን ማንሳት የቻለ ሲሆን በአጠቃላይ 53 ነጥብ በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁም ተገልጿል።

በውድድሮቹ የተገኘው ውጤት የሚበረታታ ሲሆን በተናጠል ውጤት ያልተገኘባቸው ስፖርቶች ላይ በልዩ ሁኔታ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ተገልጿል።

በቀጣይ በጠንካራ ክትትልና የውስጥ ውድድርን ከታች ጀምሮ በማካሄድ ተተኪወችን ማፍራት በሚቻልበት አግባብ መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል።

ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ስናወራ የደሴ ከተማን ስም ሳናነሳ ማለፍ አይቻልም። አቶ መልካሙ ፀጋየ የአብክመ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊየደሴ ከተማ ስፖርት ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊ...
15/04/2026

ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ስናወራ የደሴ ከተማን ስም ሳናነሳ ማለፍ አይቻልም። አቶ መልካሙ ፀጋየ የአብክመ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

የደሴ ከተማ ስፖርት ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሚያደርገው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆኑን አስመልክቶ ቢሮ ኃላፊው የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ደሴ ከተማ ገና ከጥንቱ ጀምሮ ለብሔራዊ ቡድንና ለታላላቅ የሀገሪቱ ክለቦች ድንቅ ተጫዋቾችን አፍርታለች። በሜዳ ላይ ባላቸው ከፍተኛ የቴክኒክ ብቃት እና በስፖርታዊ ጨዋነታቸው የሚታወቁ በርካታ አንጸባራቂ ኮከቦች መነሻቸው ደሴ ነው።

ደሴ ዛሬም እንደ ትላንቱ ለእግር ኳሳችን ትንሳኤና እድገት የራሷን የላቀ ድርሻ እየተወጣች ትገኛለ።

የደሴ ስፖርት ቤተሰቦች ትጋትና ፍቅር ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ሁሌም ኩራት ነው! ብለዋል ቢሮ ኃላፊው።
ለክልላችን ተጨማሪ የእግር ኳስ ፈርጥ የሚሆነው ደሴ ከተማ ዛሬ ወሳኝ ፍልሚያውን ያደርጋል! በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

መልካም ዕድል!

ደሴ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ከመሪው ያለውን ልዩነት አጠበበ።ሚያዝያ 2/2018 ዓ.ምየ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግን ለመቀላቀል በሚደረገው ፋክክር በምድብ 'ለ' የተደለደለው ደ...
10/04/2026

ደሴ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን በማሸነፍ ከመሪው ያለውን ልዩነት አጠበበ።
ሚያዝያ 2/2018 ዓ.ም

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግን ለመቀላቀል በሚደረገው ፋክክር በምድብ 'ለ' የተደለደለው ደሴ ከተማ ከመሪው ሀላባ ከተማ ጋር ያለውን ልዩነት ወደ አንድ ነጥብ ዝቅ የሚያደርግበትን ወሳኝ 3 ነጥብ አዲስ አበባ ከተማን 2ለ1 በማሸነፍ አስመዝግቧል።

በጨዋታው የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋየ እና ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ ጋሻው ተቀባ በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም በመገኘት ቡድኑን አበረታተዋል።

የባህር ዳር ስታዲየምን ለአፍሪካ ዋንጫ ብቁ ለማድረግ በፍጥነት እየተሰራ ነው*****************የካፍ የስታዲየም ኢንስፔክተር አምሀ ተስፋየ ከስለ ስፖርት ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የባህ...
28/03/2026

የባህር ዳር ስታዲየምን ለአፍሪካ ዋንጫ ብቁ ለማድረግ በፍጥነት እየተሰራ ነው
*****************

የካፍ የስታዲየም ኢንስፔክተር አምሀ ተስፋየ ከስለ ስፖርት ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የባህር ዳር ስታዲየም ቀደም ሲል ከነበረበት ሁኔታ አሁን ወደ ተሻለ ደረጃ የተሸጋገረበትን ሂደት "መሰረታዊ ለውጥ" ሲሉ ገልጸውታል።

ስታዲየሙን ከካፍ መስፈርት ጋር ለማጣጣም የመጫወቻ ሜዳውና የልምምድ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ተወግደው በአዲስ መልክ ተገንብተዋል ብለዋል።

ስታዲየሙ ትክክለኛውን ጥራት እንዲይዝ ለማድረግ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ፈርሶ እንዲሰራ መደረጉም ተገልጿል።

ከሜዳው ግንባታ በላይ ፈታኝ የነበሩት የተያያዥ መሰረተ ልማቶች እንደ ተጫዋቾች መቀያየሪያ ክፍል፣ የሚዲያ ማእከልና የቪአይፒ ቦታዎች በአሁኑ ወቅት መስፈርቱን በሚያሟላ መልኩ መሰራታቸው ተመላክቷል።

የካፍ ህግ የአፍሪካ ዋንጫን ለማሰናዳት ስድስት ስታዲየሞችና 12 የመለማመጃ ሜዳዎች እንዲኖሩ ያስገድዳል።

ለግማሽ ፍጻሜና ለፍጻሜ ጨዋታዎች ከ40 ሺህ በላይ ደጋፊ የሚይዙ ስታዲየሞችን የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ለሌሎች ጨዋታዎች ግን እስከ 18 ሺህ ደጋፊ የሚይዙ ስታዲየሞች እንዲካተቱ ይፈቅዳል።

የባህር ዳር ስታዲየም ሲጠናቀቅ ሁሉንም ቴክኒካዊ መስፈርቶች አሟልቶ ለታላቁ አህጉራዊ ውድድር ዝግጁ እንደሚሆን ይጠበቃል።

EBC

"ታዋቂ ሰዎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ማድረግ የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት ያስችላል" አቶ ኢሳያስ ጅራ ጥር 24/2018 ዓ.ምየቀድሞው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ የባ...
01/02/2026

"ታዋቂ ሰዎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ማድረግ የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት ያስችላል" አቶ ኢሳያስ ጅራ
ጥር 24/2018 ዓ.ም

የቀድሞው የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ የባሕር ዳር ስታዲየምን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ከባካሪ ሳኛ በተጨማሪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል። ባካሪ ሳኛ በባሕር ዳር ስታዲየም ከታዳጊዎች ጋርም እግር ኳስ ተጫውቷል።

የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ጋሻው ተቀባ የባሕር ዳር ስታዲየም የካፍ እና የፊፋን ደረጃዎችን መሠረት በማድረግ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ስታዲየሙ ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶችን እያሟላ መኾኑንም ተናግረዋል።

የስታዲየሙ ግንባታ ወደ መጨረሻው መኾኑንም አንስተዋል። የባካሪ ሳኛ ጉብኝትም ጥሩ አጋጣሚ መኾኑን አንስተዋል።

ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የካፍ ቡድን መጥቶ የስታዲየሙን ደረጃ እንደሚገመገም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ የባሕር ዳር ስታዲየም የካፍ ደረጃዎችን የማሟላት ሥራ እየተሠራለት ነው ብለዋል። ባየሁት ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ ያሉት ፕሬዝዳንቱ የተተከለው ሣር፣ የመልበሻ ክፍሉ፣ የቪአይፒ እና የቪቪአይፒ መቀመጫዎች ሥራ የሚያስደስቱ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ስታዲየሙ እንዲጠናቀቅ መሪዎች እያሳዩት ያለው ጥረት እና ቁርጠኝነት የሚደነቅ መኾኑንም ገልጸዋል። ስታዲየሙ ማንኛውም ውድድር ማድረግ የሚችል አቅም እንዳለውም ተናግረዋል።

ከባሕር ዳር ስታዲየም ትምህርት በመውሰድ ፕሮጄክትን በተገቢው መንገድ ማስተዳደር እንደሚገባ አንስተዋል።

ስታዲየሙ በደረሰበት ደረጃ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ደስታችን ሙሉ የሚኾነው ስታዲየሙ ተጠናቅቆ፣ በካፍ ፈቃድ አግኝቶ ብሔራዊ ቡድናችን ወደ ሀገር ሲመለስ ነው ብለዋል። የቀረውን ጠንከር ብሎ ማጠናቀቅ እንደሚገባም አንስተዋል። የቀሩት ሥራዎች ሲጠናቀቁ ብሔራዊ ቡድናችን ወደ ሀገራችን ይመለሳል ነው ያሉት።

ስታዲየሙ እዚህ እንዲደርስ ላደረጉ መሪዎች እና ባለሙያዎች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። ስፖርት ለገጽታ ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ እንደ ባካሪ ሳኛ አይነት ታዋቂ ተጫዋቾች የሚያደርጉት ጉብኝት ትርጉሙ ትልቅ መኾኑን ተናግረዋል።

ታዋቂ ሰዎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ማድረግ የኢትዮጵያ ገጽታ በአወንታዊ መልኩ ለመገንባት ያስችላል ብለዋል። የባካሪ ሳኛ ጉብኝት ገጽታን ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

በጋራ ከሠራን ነገ የእኛ ልጆች ታላላቅ ተጫዋቾች የማይኾኑበት ምክንያት የለም ነው ያሉት።

አሚኮ

Address

Bahirdar
Bahir Dar

Telephone

+251582202202

Website

and sport face book.

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar International Stadium Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share