18/07/2023
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ
*********************************
ኢትዮ ቴሌኮም የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀሙን በተመለከተ ለሚዲያዎች መግለጫ እየሰጠ ነው።
ተቋሙ በ2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።
ተቋሙ 18.7 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱም ተነስቷል።
የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም 101 ከመቶ ስኬት የተገኘበት ሲሆን፣ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ23 በመቶ ብልጫ የታየበት መሆኑ ተነስቷል።
164 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የተገኘበት ዓመት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 203 የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶችን ለደንበኞች ያቀረበ ሲሆን፤ 116ቱ አዳዲስ አገልግሎቶች ናቸው ተብሏል።
ግዙፉ የቴሌኮም ተቋም ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ተደራሽ ለማድረግ ‘ሊድ ግሮውዝ ስትራቴጂ’ አሰራሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጠቁመዋል።
በአሚር ጌቱ