25/05/2023
አብክመ መሬት በ2015 በጀት ዓመት በክልሉ በተለያያ አዞኖችና ወረዳዎች ሚገኙ ነፃ የእርሻ ኢንቨስትመንት መሬቶች የተሻለ የማልማት አቅም ላላቸው ባለሀብቶች ለማስተላለፍ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ።
ዝርዝሩን በበኩር ጋዜጣ ግንቦት 14/2015 እትም ገፅ 24 እና 25 እንዲሁም በቢሮውና በዞኖች የውስጥ ማስታወቂያ መመልከት ይችላሉ።
የመሬት ቢሮ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በመሬት ባንክ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት መሬቶችን በገጠር መሬት የሊዝ ህግ በውድድር ስርአት ለባለሃብቶች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የግብርና ኢንቨስትመንት መሬት ፈላጊዎች በሙሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን መስፈርቶች ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የተዘጋጀ የኘሮጀክት ሀሳብ ሰነድ እና አሰፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን አያይዞ በማቅረብ መመዝገብና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በግብርና ኢንቨስትመንት መሬት የሚፈልግ ባለሃብት (ድርጅት) ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የበዓል ቀናትን ጨምሮ አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ የኘሮጀክት ሀሳብ (Business plan) ከማመልከቻ ጋር ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ ማቅረብ አለበት፡፡
አመልካቹ የኘሮጀክት ፕሮፓዛል (ሃሳብ) በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ቋንቋ አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት፡፡ የሚወዳደርበትን መሬት ለይቶ ማቅረብ አለበት (ማለትም መሬቱ የሚገኝበት ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ ልዩ-ቦታ ወይም ብሎክ፣ የመሬቱ ስፋት በሄ/ር እና ለምን አገልግሎት እንደሚውል/የመሬት አጠቃቀሙ/ እና በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሰውን የቦታው ተራ ቁጥር መግለጽ አለበት)፡፡
2. አንድ ተወዳዳሪ ባለሀብት መወዳደር የሚችለው ሁለት መሬቶችን ብቻ በመምረጥ ነው፡፡ ነገር ግን ከሁለት በላይ በሆነ መሬት አመልክቶ ቢገኝ ሙሉ በሙሉ ከውድድር ውጭ /የሚሰረዝ/ ይሆናል፡፡
3. ተወዳዳሪ ባለሀብቶች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን በፊት ባሉት 3 ተከታታይ ወራት ጊዜ ውስጥ የፋይናንስ አቅማቸውን የሚያሳይ የባንከ ስቴትመንት በባንኩ ዲስትሪክት ኃላፊ በተፈረመበት መሸኛ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. አመልካቹ አካል ማህበር ከሆነ በሚመለከተው አካል የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና ህጋዊ ሰውነት ያገኘበትን ሰነድ ማቅረብ አለበት፡፡
5. አመልካቾች ጠቃሚ ናቸው የሚሏቸውን ሌሎች ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
6. አመልካቾች የተንቀሳቃሽ ንብረት ማለትም እንደ እርሻ መገልገያ ማሽነሪ እና የመሳሰሉትን ያላቸው ተወዳዳሪዎች የባለቤትነት ማስረጃዎች ህጋዊ ስልጣን ካለው ተቋም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ከዚህ በፊት መሬት ወስደው በማልማት ላይ ያሉ ማስጠንቀቂያ ያለባቸው ባለሃብቶች እና መሬታቸው ወደ መሬት ባንክ የገባባቸው ባለሃብቶች በዚህ ውድድር ተሳታፊ አይሆኑም፡፡
8. የውጭ ሃገር የባንክ ስቴትመንት የሚያቀርቡ ባለሃብቶች የሚያቀርቡትን የባንክ ተቀማጭ የገንዘብ አቅም በሃገር ውስጥ ጉዳዩ በሚመለከተው ህጋዊ ተቋም የተገናዘበ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. በአንድ መሬት ላይ ብቸኛ ተወዳደሪ በሚቀርብበት ጊዜ፣ የቴክኒክ ግምገማ ከ60% እንዲሁም የፋይናንስ አቅም የሚያሳይ ትራንዛክሽን ደግሞ ከ40% የሚያዝላቸው ሁኖ በሄ/ር የተቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት/ስታንደርድ/ አሟልቶ ሲገኝ እና በሁለቱም የመገምገሚያ መስፈርቶች በድምሩ ውጤት 50% (ሃምሳ ከመቶ) እና ከዛ በላይ ነጥብ ካመጣ የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡
10. ከላይ በተራ ቁጥር 8 እንደተጠቀሰው የተጠበቀ ሆኖ በአንድ መሬት ላይ ከአንድ በላይ ተወዳዳሪ በሚኖርበት ጊዜ፣ ተወዳዳሪዎች በሚያገኙት የነጥብ ብልጫ የሚለዩ ይሆናል፡፡ ሆኖም ተወዳዳሪዎች በቴክኒክ እና በፋይናንስ ግምገማ ውጤት ከ50% በታች ካመጡ ፕሮጀክቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
በአንድ መሬት ላይ ከአንድ በላይ ተወዳደሪዎች ተወዳድረው እኩል ውጤት ካገኙ ለሴት ተወዳደሪዎች፣ በንግድ ማህበራት (አክሲዮን፣ሽርክና፣ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና የመሳሰሉት) ተደራጅተው ለቀረቡ ባለሃብቶች እንደቅደም ተከተላቸው ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
11, ሆኖም በአንድ መሬት ሴት ተወዳዳሪዎች ከሴት ተዎዳዳሪዎች፤ወንድ ተወዳዳሪዎች ከወንድ ተወዳዳሪዎች እና በንግድ ማህበር የተደራጁ ተወዳዳሪዎች ከንግድ ማህበር ከተደራጁ ተወዳዳሪዎች እኩል ውጤት ካገኙ በባንክ ስቴትመንት የተሻለ የገንዘብ መጠን ያሳየው (በባንክ ስቴትመንት የተሸለ ነጥብ የተሰጠው) ቅድሚያ ይሰጠዋል ፡፡
12. በተራ ቁጥር 11 ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በሁሉም መስፈርቶች እኩል ውጤት ቢያመጡ ተወዳዳሪዎች በተገኙበት በዕጣ የሚለዩ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ
1, ቀሪዎቹን የማወዳደሪያ መስፈርቶች በተመለከተ ለኢንቨስትመንት እንዲውል ተሻሽሎ በወጣው የገጠር መሬት አሰጣጥ እና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 13/2013 ዓ.ም መመልከት ይቻላል፡፡
2, ለውድድር የሚቀርቡ አስፈላጊ መረጃዎችን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3, ለውድድር የሚቀርብ የባንክ ስቴትመንት ማስታወቂያው እስከ ወጣበት ቀን ድረስ ያለው ያልተቆራረጠ ወደ ኋላ የ3 ተከታታይ ወራት የባንክ እንቅስቃሴ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ከተጠቀሰው ቀን ወደፊትም ሆነ ወደኋላ ጨምሮ ቢቀርብ ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
4, በግሉ ለመወዳደር ጥያቄ ያቀረበ አመልካች ለውድድሩ ያቀረበውን የባንክ ስቴትመንት ድጋሚ ይሄው ተወዳዳሪ በአባልነት የተካተተበት ማህበር ተወዳዳሪ ሆኖ ቢቀርብ ለማህበሩ በማወዳደሪያነት አይያዝም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በግሉ የእርሻ ማሽነሪ ያለው አካል በአባልነት የተካተተበት ማህበር ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ ይሄው የግል ማሽነሪ ለማህበሩ በማወዳደሪያነት አይያዝም፡፡
5, ማስታወቂያው ከወጣ ከአስራ አምስተኛው ቀን በኋላ የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
6, በተራ ቁጥር 4 እና 5 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የምዝገባው ቀን ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ እና ተወዳደሪዎች ከተመዘገቡ በኋላ የምዝገባ ጊዜ ባይጠናቀቅም የተጨማሪ ሰነድ ይያዝልኝ ወይም ቀድሞ ገቢ የተደረገ ሰነድ ይቀየርልኝ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡
7, አመልካቾች ለውድድር የሚያቀርቡት የኘሮጀክት ሃሳብ፣ ለመወዳደር ካመለከቱበት ዞን፣ ወረዳ፣ የመሬት ስፋት፣ የመሬት አጠቃቀም እና ተራ ቁጥር ጋር መገናዘብ የሚገባው ሲሆን ከተዘረዘሩት ውስጥ በአንዱም ቢሆን ካልተጣጣሙ ውድቅ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዳቸው ለውድድር የቀረቡ መሬቶች ለየብቻቸቸው የፕሮጀክት ሀሳብ ሊዘጋጅላቸው ይገባል፡፡
8, አመልካቾች የፕሮጀክት ሃሳባቸውን እና ሌሎች ለውድድር አሰፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን የሚያቀርቡት ማስታወቂያው አየር ላይ በዋለበት ጊዜ ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
9. የኘሮጀክት ሃሳብ (Business plan) እና ሌሎች ጠቃሚ ማስረጃዎችን ቢቻል የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት እና የባለሀብቱ ፊርማ ተፈርሞበት ለአብክመ መሬት ቢሮ በውስጥ ማስታወቂያ በሚገልጸው ቢሮ ቁጥር በስራ ሰዓት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
Awelachew Diaspora, [5/24/2023 5:03 PM]
10. የምዝገባው ጊዜ በተጠናቀቀ በ30 የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊዎችን እና ውጤታቸውን በተቋሙ የውሰጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
11, በውጤቱ ቅሬታ ያለው አመልካች ቢኖር ጊዜያዊ ውጤቱ በተገለጸ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ቅሬታውን በጽሁፍ ለአብክመ መሬት ቢሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
12, አሸናፊ የሆነው ባለሃብት/ድርጅት/ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልያዘ መብቱን መጠቀም እንዳልፈለገ ተቆጥሮ በነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አሸናፊ ባለሃብት ወይም ድርጅት ውል እንዲወስድ ይደረጋል፡፡
13, ከባለሃብት ተመልሰው ለውድድር የወጡ መሬቶች በካሳ ህጉ መሰረት ካሳ የሚያስከፍል ንብረት /ግንባታ፣አት/ፍራፍሬ እና መሰል ንብረቶች/ ካሉ አሸናፊው ግለሰብ/ድርጅት በካሳ ህጉ መሰረት ውል ከመውሰዱ በፊት ተገቢውን ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
14, ቢሮው ውድድሩን እንደ አሰፈላጊነቱ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የአብክመ መሬት ቢሮ
ባህር ዳር