28/05/2026
አንጎት የደገራ -የወረዳ -ወልማደግ 14 ነጥብ 5ኪሎ ሜትር መንገድ ከ17 ማሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት እየተጠገነ እንደሆነ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ መንገድ፣ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ጽ/ቤት ገለፀ።
መንገዱ 5 ቀበሌዎችን የሚያገናኝ እና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መንገድ መሆኑን የገለፁት የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ዳዊት መንበር እንደተናገሩት የመንገዱ መጠገን የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ የሚፈታ ነው ብለዋል።
የመንገድ ጥገናው በወረዳ በጀትና በህብረተሰብ ተሣትፎ የሚሰራ መንገድ እንደሆነ ሃላፊው አክለው ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ በወረዳው ቀደም ብሎ ጥገና የጀመረውን ደምበጫ- የገሊላ -ዋዳን ቀበሌ አገናኝ መንገድ ጨምሮ አንጎት የደገራ-የወረዳ-ወልማደግ መንገድ ጥገና እየተካሄደ እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ ዳዊት አክለውም የመንገድ ጥገና ዘላቂነት እንዲኖረው ማህበረሰቡ በባለቤትነት ስሜት እንዲጠብቀውና ጥራቱን እንዲከታተል አሳስበዋል።
Dembecha zuria Communication