የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues, Government Organization, Bahir Dar.

የታክስ ደረሰኝ ሽልማት ዕጣ እንዲኖር መመሪያ ለማውጣት በተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደግንቦት 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)የታክስ ደረሰኝ ሽልማት ዕጣ እንዲኖር መመሪያ ...
29/05/2026

የታክስ ደረሰኝ ሽልማት ዕጣ እንዲኖር መመሪያ ለማውጣት በተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የታክስ ደረሰኝ ሽልማት ዕጣ እንዲኖር መመሪያ ለማውጣት በተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ በገቢዎች ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ

አቶ ፍቃዱ ታደሰ ዘላቂ ገቢ ማግኘት የሚቻለው አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ከመውጣታቸው በፊት የበሰሉ እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በረቂቅ ሰነዶች ላይ ግብዓት ማሰባሰብ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው በሰነዱ ላይ የተሰጠው አስተያየትም ተገቢ እና ገንቢ ነው ብለዋል፡፡

በእለቱ በውይይቱ ወቅት የተሰጡ አስተያየቶች ታክለውበት ሰነዱ ዳብሮ ለሚመለከታቸው አካላት መቅረብ እንዳለበት የተናገሩት አቶ ፍቃዱ ይህም ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

የሚኒስቴር መ/ቤቱ የታክስ ሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አበረ አስፋው ረቂቅ ሰነዱን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በማብራሪያቸው የሰነዱን ዓላማዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በማብራሪያቸውም የሸማቾችን ደረሰኝ የመጠየቅ ባህልን፣ የታክስ ህግ ተገዢነትን እና ታክስን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህልን ለማሳደግ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡

አቶ አበረ በረቂቅ ሰነዱ ላይ ለሽልማት ብቁ ስለሚያደርጉ መስፈርቶች፣ የምዝገባ አማራጮች፣ የዕጣ ድልድል እና የግብይት መጠን፣ የዕጣ አወጣጥ እና የቅሬታ አፈታት ሂደቶች፣ የውጤት ማሳወቂያ ዘዴዎች፣ ሽልማት የማይሰጥባቸው ሁኔታዎች፣ የሽልማት ሀብት አስተዳደር እና የባለድርሻ አካላት ተግባራት እና ኃላፊነቶች የሚሉ ጉዳዮች ካቀረቧቸው ነጥቦች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ረቂቅ ሰነዱን አስመልክቶ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የሚኒስቴሩ የዋናው ሚኒስቴር መ/ቤት የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም ምክትል ሥራ አስኪያጆች ተገኝተዋል፡፡

በሽመልስ ሲሳይ
ፎቶ:- ክፍሌ አዳፍሬ

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!የአረፋ በዓል ታላቅ መስዋዕትነት፣ ታማኝነት፣ መተሳሰብና አብሮነት የሚንጸባረቅበት የተቀደሰ ዕለት ነው። አማኞች አላህ...
26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የአረፋ በዓል ታላቅ መስዋዕትነት፣ ታማኝነት፣ መተሳሰብና አብሮነት የሚንጸባረቅበት የተቀደሰ ዕለት ነው። አማኞች አላህን በመፍራትና በትዕዛዛቱ በመገዛት የሚያሳዩት እውነተኛ ታማኝነት፣ ማህበረሰባዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ በጎ ምግባራት የሚዘከሩበት በዓል በመሆኑ ዘመናትን የተሻገሩ ውድ እሴቶቻችን መገለጫ ነው።

ይህ ታላቅ በዓል የሚያስተምረን የመሰጠት፣ የሀላፊነትና የታማኝነት እሴት ከግብር ከፋይነት ተግባራችን ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው። ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል፤ ግብርን በታማኝነት መክፈል የማህበረሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከፈል የዜግነት መስዋዕትነት ነው።

በአረፋ በዓል ደካሞችንና የተቸገሩትን በመርዳት የምናሳየው መተሳሰብ፣ በግብር አሰባሰብ ሂደት ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው። የምንሰበስበው ገቢ ለትምህርት ቤቶች፣ ለጤና ተቋማትና ለንጹህ መጠጥ ውሃ መሠረተ ልማቶች መዘርጋት የሚውል በመሆኑ፣ እርስ በርስ የመደጋገፊያችን ትልቁ መድረክ ነው።

ስለሆነም የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ፣ መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ የተለመደውን ታማኝነትና ህጋዊነት በተግባር ክልላችንን ለማበልጸግና የህዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪውን ያቀርባል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የልማት እንዲሆንላችሁ በድጋሚ ይመኛል!
ዒድ ሙባረክ

በአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ መረጃዎችን ለማግኘት፣
አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ

Facebook፡-
1. የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues and
2. Amara region Revenue Bureau

ቴሌግራም፦ https:// Amara Region revenue bureau

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/ገቢያችን

Website: - https://www.abor.gov.et/

Email: - [email protected] or
[email protected]

ስልክ ቁጥር 058 226 5774
95 04
ፖ.ሣ.ቁ 746

ግብር መክፈል፡ የግዴታ ቀንበር ወይስ የሉዓላዊነት ኩራት?የግብር ሕግ ተገዥነት ከቅጣትና ማስገደድ ባለፈ በማህበረሰብ ውስጥ ሊሰርጽ የሚገባው ጥልቅ "ማኅበራዊ ባህል" መሆን አለበት፡፡ብዙዎች ...
25/05/2026

ግብር መክፈል፡ የግዴታ ቀንበር ወይስ የሉዓላዊነት ኩራት?

የግብር ሕግ ተገዥነት ከቅጣትና ማስገደድ ባለፈ በማህበረሰብ ውስጥ ሊሰርጽ የሚገባው ጥልቅ "ማኅበራዊ ባህል" መሆን አለበት፡፡

ብዙዎች የግብር ሕግ ተገዥነት (Tax Compliance) ሲባል ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ሕጋዊ ግዴታ፣ የኦዲት ፍተሻ እና ከባድ ቅጣቶች ናቸው። ይሁን እንጂ የግብር አስተዳደርን በቁጥጥርና በቅጣት ላይ ብቻ መሥራት ለገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ፣ በግብር ከፋዩና በመንግሥት መካከል ያለመተማመን ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል።

እውነተኛና ዘላቂ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት የሚገነባው፣ ግብር መክፈልን እንደ ዜግነት ግዴታና ማኅበራዊ ኃላፊነት የሚመለከት ማኅበረሰብ ሲፈጠር ብቻ ነው።

ባህል በትምህርትና በልምድ የሚወረስ እንደመሆኑ፣ ስለ ግብር ምንነትና ጥቅም ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ለሕፃናት፣ ለወጣቶችና ለግብር ከፋዮች በተደጋጋሚ ማስተማር ይገባል።

የግብር ሕግጋትና አሠራሮች ቀላል፣ ግልጽና በቴክኖሎጂ የተደገፉ መሆን አለባቸው። የወረቀትና የቢሮክራሲ መደራረብ ባህሉን ያዳክማል።

የግብር ተገዥነት ባህል በሆነበት አገር ውስጥ፣ መንግሥት የግብር ስወራን ለመቆጣጠር የሚያወጣው ወጪ ይቀንሳል። ይህም አገር በውጭ ዕርዳታና ብድር ላይ ያላት ጥገኝነት ቀርቶ በራስ አቅም እንድትቆም ያደርጋታል።

ስለሆነም የግብር ሕግ ተገዥነትን ማሳደግ የአንድ ሰሞን ዘመቻ ወይም የሕግ ማሻሻያ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ ነጋዴም ሆነ ተቀጣሪ ሠራተኛ፣ ግብር መክፈልን የሀገር ባለቤትነት መገለጫ አድርጎ የሚያስብበት ሥርዓት ያስፈልጋል። ይህ ባህል ሲዳብር፣ ግብር መክፈል የግዴታ ቀንበር መሆኑ ቀርቶ የኩራትና የሉዓላዊነት መሠረት ይሆናል።

ስለሆነም ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃንና መላው ማኅበረሰብ ይህንን በጎ ባህል ለመገንባት በጋራ ሊረባረቡ ይገባል።

የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው? በአገራችን የግብር አከፋፈል የግዴታ ቀንበር ሳይሆን የፈቃደኝነት ባህል እንዲሆን ምን መደረግ አለበት ይላሉ? በኮመንት መስጫው ላይ ያጋሩን።

✍️፡- ሲሳይ አስማማው
አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ
በፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/AmraNews
https://www.facebook.com/profile.
በቴሌግራም:- Amhara Region revenue bureau
በዩትዩብ:- https://www.youtube.com/ ገቢያችን
Website:- https://www.abor.gov.et/
እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በ 9504 ይደውሉ
መደበኛ ስልክ ቁጥሮች 058 22

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከ1 ቢልዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበግንቦት 12 /2018 (የኦሮሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ /ከሚሴ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ኦሮሞ ብ/ሰ/...
23/05/2026

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከ1 ቢልዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ግንቦት 12 /2018 (የኦሮሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ /ከሚሴ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ኦሮሞ ብ/ሰ/አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከመደበኛ ገቢ ብር 1,166,394,679 እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 359,959,734 በድምሩ ብር 1,526,354,413 ገቢ ለመሰብሰብ መልካም ውጤት እያሳየ ይገኛል።

መምሪያው እስከ ሚያዚያ 30/2018 ዓ/ም ከመደበኛ ገቢ 839,059,092.62 ብር ወይም የዕቅዱን 71.9 በመቶ እንዲሁም ከከተማ አገልግሎት ገቢ 263,893,855.08 ብር ወይም የዕቅዱን 73.3 በመቶ በድምሩ ብር 1,102,952,947.70 ወይም ከዓመቱ ዕቅድ በአማካይ 72.26 በመቶ መሰብሰቡን የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ገቢዎች መምሪያ የግብር ትምህርት እና ኮሙኒኬሽን ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ገመዳ ጉታ ገለፁ።

ገቢው በ2017 ተመሳሳይ ወር ከተሰበሰበው 721,931,840.06 ብር ጋር ሲነፃፀር የብር 381,021,107.64 ወይም የ 52.77 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አስታውሰዋል።

የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳዳግ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ፣ የህግ ተገዢነትን ደረጃ ለማሳደግ በተደረገው የቤት-ለቤት እና የመድረክ ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ የግብር ከፋዮች አመለካከትና አስተሳሰብ እየተሻሻለ መጥቷል።

አሁንም ግን ታክስ ለመሰወር፣ በግብይት ወቅት ደረሰኝ አለመቁረጥ እንዲሁም በራስ ፈቃደኝነት የግብር ግዴታን በወቅቱ ያለመወጣት ክፍተቶች መኖራቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ግብር ከፋዩን ማስተማርና ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ መምከር ቅድሚያ ተግባሩ ያደረገው መምሪያው የሕግ ተገዢነትን ለማረጋገጥ በተደጋጋሚ ጊዜ ትምህርትና ምክር እየሰጠ ቢሆንም የህግ ጥሰቶችን ማስቆም አልተቻለም።

በምምሪያው ባደረገው ክትትል በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ ግዴታ ያለባቸው 30 ግብር ከፋዮች ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈፀሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘው የ50 ሺህ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት መቀጣታቸውን አቶ ገመዳ አብራርተዋል።

በሚቀጥሉት ወራት የደረሰኝ ክትትልን ከማጠናከር በተጨማሪ በኦዲት ግኝትና እንቨስትጌሽን፣ በዳግም ውሳኔ፣ በውዝፍ ገቢ አሰባሰብ፣ በ3ኛ እና በ2ኛ ሩብ ዓመት 25% ቅድመ-ግብር ክፍያ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራም አስታውሰዋል።

ዘገባው ፡- የኦሮሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ የግ/ትም እና ኮሙኒኬሽን ዋና የሥራ ሂደት ነው።

ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት እየተሠራ ነው፡፡ አቶ ፍቅረማርያም ደጀኔ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ም/ኃላፊባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (የአማራ ...
22/05/2026

ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት እየተሠራ ነው፡፡ አቶ ፍቅረማርያም ደጀኔ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ም/ኃላፊ

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ የሚያስችለውን የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አስተዳደር ስርዓት (e-TAS) ሁለተኛ ምዕራፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥልጠና ለባለሙያዎቹ በባህር ዳር ከተማ ሰጠ።

በሥልጠናው መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማርያም ደጀኔ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ራሱን ከዘመኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር ለማስማማት ሰፊ ሪፎርሞችን እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

ቢሮው ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሙሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ለመሆን የያዘው ግብ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰነቀውን የዲጂታል ስትራቴጂካዊ ራዕይ ለማሳካት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አስገንዝበዋል።

የቴክኖሎጅው የመጀመሪያ ምዕራፍ የግብር ውሳኔን ለግብር ከፋዩ ማሳወቂያ መላክና የክፍያ ቢል ኮድ (Bill Code) ጀነሬት ማድረግ እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ኃላፊው፤ በሁለተኛው ምዕራፍ የገቢ ግምት መመዝገብ፣ አወሳሰን፣ የተወሰነውን የማፅደቅ ሂደት እንዲሁም የታክስ ቅሬታና ተያያዥ አሠራሮች በዲጂታል ሥርዓት እንዴት እንደሚሰሩ እንደሚሸፈን ጠቁመዋል።

የገቢ ተቋሙን አሠራር ለማዘመን እየለማ የሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አስተዳደር ስርዓት (e-TAS) የገቢ አሰባሰብ ስራን ግልጽ እና ቀላል እያደረገ መሆኑን ተነግሯል፡፡

የሲስተም ግንባታ በሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፍሎ እየተከናወነ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ ከግብር ከፋዮች ምዝገባ እና ተያያዥ ሥራዎችን ያካተተው የመጀመሪያው ምዕራፍ የማልማት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ሁሉንም ዓይነት የግብር አወሳሰን ሥራዎችን ያቀፈው ሁለተኛው ምዕራፍ በአሁኑ ወቅት ከ95 በመቶ በላይ መከናወኑንና በማጠናቀቅ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተብራርቷል። የግብር/ታክስ ኦዲት እና ተያያዥ አሠራሮችን በቴክኖሎጂ ለማገዝ የታቀደው የሦስተኛው ምዕራፍ ሥራ በተወሰኑ ዘርፎች ላይ መጀመሩ ተገልጿል።

የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አስተዳደር ስርዓት (e-TAS) ተቋማዊ አሠራርን ከማቀላጠፉም በላይ፣ በክልሉ የሚካሄደውን የግብር አሰባሰብ ሂደት ፍትሐዊ፣ ፈጣን እና ግልፅ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ስልጠናው በባህር ዳር ከተማ በሁለት ማዕከላት ተሰጥቷል፡፡

በአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ መረጃዎችን ለማግኘት፣
አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ

Facebook፡-
1. የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues and
2. Amara region Revenue Bureau

ቴሌግራም፦ https:// Amara Region revenue bureau

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/ገቢያችን

Website: - https://www.abor.gov.et/

Email: - [email protected] or
[email protected]

ስልክ ቁጥር 058 226 5774
95 04
ፖ.ሣ.ቁ 746

21/05/2026

#ታሪክ የሚሰራው በዕቅድ ብቻ ሳይሆን በፈጻሚው ቁርጠኝነት ጭምር ነው።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት 100.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታላቅ ግብ አስቀምጦ ሌት ተቀን በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። እስከ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 72 ነጥብ 078 ቢሊዮን ብር ወይም ከዕቅዱ ከ71.81 በመቶ በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

ይህ አበረታችና ትልቅ ስኬት ቢሆንም፣ ከታለመው የመጨረሻ ግብ ለመድረስ አሁንም ያልተሻገርነው ወሳኝ ምዕራፍና ያልተጠናቀቀ የቤት ስራ ከፊታችን ይገኛል። ምክንያቱም የታቀደው እያንዳንዱ ሳንቲም ሳይሰበሰብ ቢቀር፣ ዋጋው በቀጥታ የሚከፈለው በክልላችን ሁለንተናዊ ዕድገትና በማህበረሰባችን ህይወት ላይ ነው፡፡

የታቀደው ገቢ ሙሉ በሙሉ አለመሰብሰብ ማለት ቁጥሮች ጎደሉ ማለት ብቻ አይደለም፤ በክልላችን ህዝብ ላይ የሚከተሉትን ተጨባጭ ተፅዕኖዎች ያሳርፋል፡፡ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባትና ያሉትን ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ የተያዘው በጀት ይስተጓጎላል። ይህ ማለት ልጆቻችን ጥራት ያለው ትምህርት በአቅራቢያቸው የማግኘት ዕድላቸው ይዘጋል ማለት ነው።

በአሁኑ ወቅት ንጹህ መጠጥ ውሃን በናፍቆት ለሚጠባበቁ የክልላችን ነዋሪዎች የተጀመሩ የውሃ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለማስረከብ የፋይናንስ እጥረት ይፈጠራል፤ ይህም የማህበረሰቡን ጤናና የዕለት ተዕለት ኑሮ አደጋ ላይ ይጥላል። ባጭሩ የገቢ እቅድ አለመፈጸም ማለት በትምህርት ቤት ግንባታ፣ በጤና እና በንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ላይ ቀጥተኛ ጫና ይፈጥራል ማለት ነው፡፡

"ዕቅድ ማትረፍ ነውር ነው!" ከማን ምን ይጠበቃል?
ይህንን ክልላዊ የልማት ግብ መቶ በመቶ (100%) ለማሳካት የሶስቱ ወገኖች የተቋሙ፣ የግብር ከፋዩ እና የማህበረሰቡ ቅንጅታዊ እርብርብ ወሳኝ ነው። የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ በእያንዳንዱ ቀን ዕቅድ ላይ በቂ ቁርጠኝነት ማሳየት ይገባል። ተገቢውን ህግ በማስከበር ጭምር በሚከተሉት ቁልፍ የገቢ አርእስቶች ላይ ያላሰለሰ ጥረት መደረግ አለባቸው፡፡

# ያልከፈሉ ግብር ከፋዮችን ማስከፈልና ውዝፍ የመደበኛ ዕዳዎችን ማጠናቀቅ፣
# የ25% ቅድመ ግብር እና የ2.5% አማራጭ አነስተኛ ግብር አፈጻጸምን ማሳደግ፣
# በዳግም ውሳኔ፣ ታክስ በልዩነት፣ ሮያሊቲ፣ በዕርሻ ግብር እና በግል ድርጅት ስራ ግብር ላይ በትኩረት መስራት፣

# በውዝፍ ሊዝ፣ የዘመን ሊዝ፣ ቦታ ኪራይ፣ እንዲሁም በንግድና ሙያ አገልግሎት ገቢዎች ላይ ያለውን አሰባሰብ ማጠናከር ተገቢ ነው፡፡

ግብር ከፋዩች የዜግነት ግዴታን በወቅቱ መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል የበለጸገች ሀገር የመገንቢያ መሰረትና የመልካም ዜግነት ዋነኛ መገለጫ ነው። ውዝፍ ዕዳዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የክልላችንን የልማት ጉዞ ማፋጠን ከእያንዳንዱ ነጋዴና ባለሀብት ይጠበቃል።

እያንዳንዱ ዜጋ ህጋዊ ደረሰኝ የመጠየቅ ባህልን ማሳደግ አለበት። ግብር የመክፈልን አስፈላጊነት በየአካባቢው በማስተማርና በማንቃት የልማቱ የጋራ ባለቤትነቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል።

የታቀደውን ገቢ ሙሉ በሙሉ በመሰብሰብ የክልላችንን የብልጽግና ጉዞ እናፋጥን!
እቅዳችንን ለማሳካት ሁላችንም በጋራ እንረባረብ!
✍️፡- ሲሳይ አስማማው
📸፡- በኤአይ የተሰራ
በአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ መረጃዎችን ለማግኘት፣
አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ
Facebook፡-
1. የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues and
2. Amara region Revenue Bureau

ቴሌግራም፦ https:// Amara Region revenue bureau

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/ገቢያችን

Website: - https://www.abor.gov.et/

Email: - [email protected] or
[email protected]

ስልክ ቁጥር 058 226 5774
95 04
ፖ.ሣ.ቁ 746

የከተማቸን የገቢ አቅም በሳይንሳዊ ምርምር መደገፍ አለበት!ክቡር አቶ ጎሹ እንዳላማዉየባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባግንቦት 2018 ዓ.ም ባህር ዳር በአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ...
18/05/2026

የከተማቸን የገቢ አቅም በሳይንሳዊ ምርምር መደገፍ አለበት!
ክቡር አቶ ጎሹ እንዳላማዉ

የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ
ግንቦት 2018 ዓ.ም ባህር ዳር በአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት እና በሚመለከታቸዉ የክልል ቢሮዎች አማካኝነት የተቋቋመዉ የገቢ አቅም ጥናት ቡድን ስራዉ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ የክፍለ ከተማ፤ የስቴት የኒቨርሲቲዉ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት አጭር ሪፖርት ቀርቦ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የስቴት ዩኒቨርሲቲዉ ሥልጠና ማማከርና ሀብት ማፈላለግ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ እሱባለዉ መሠለ የተጀመረዉ የማማከር ስራ ጥራት ያለዉ መረጃ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁላችንም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በኃላፊነት መንፈስ የምንሰራዉ ተልዕኮ ነዉ ብለዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጎሹ እንዳላማዉ በበኩላቸዉ የተጀመረዉን የከተማችን ሁለንተናዊ ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለንን የገቢ አቅም በጥናት መለዬት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ከንቲባዉ አክለዉም የከተማችን የገቢ ዓቅም በትክክል ለማወቅ በሳይናሳዊ ምርምር መደገፍ እንዳለበት አመላክተዉ የተጀመረዉን ስራ በየደረጃዉ ያለዉ የከተማ አመራርና ባለሙያ ከስቴት ዩኒቨርሲቲዉ እና ከሚመለከታቸዉ ክልል ቢሮዎች ጋር ተቀናጅቶና ባለቤት ሆኖ መስራት እንዳለበት ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዉ ሂደቱም ትኩረት የሚሻና የተደራጀ አመራር የሚጠይቅ ትልቅ ተግባር መሆኑን አመላክተዋል፡፡

14/05/2026

Address

Bahir Dar
746

Opening Hours

Monday 08:30 - 05:30
Tuesday 08:30 - 05:30
Wednesday 08:30 - 05:30
Thursday 08:30 - 05:30
Friday 08:30 - 05:30
Saturday 08:30 - 12:30

Telephone

+251582265774

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአብክመ ገቢዎች ቢሮ -ANRS Bureau's of Revenues:

Share