Abebaw Ambaye-አበባው አምባዬ

Abebaw Ambaye-አበባው አምባዬ ሰላም🕊 ለኢትዮጵያ🇪🇹

" እኛ ለውቧ ሙሽራችን ጎንደር ልብሷን በልኳ የምንሰፋ አገልጋዮቿ ነን!!"                ቻላቸው ዳኛውየጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ
20/06/2026

" እኛ ለውቧ ሙሽራችን ጎንደር ልብሷን በልኳ የምንሰፋ አገልጋዮቿ ነን!!"

ቻላቸው ዳኛው
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

አሜሪካ ሰላምን በሚያደፈርሱ የህወሓት አክራሪ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ እገዳ ጣለችዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን በማደፍረስ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ባለቻቸው የህዝባዊ ወ...
18/06/2026

አሜሪካ ሰላምን በሚያደፈርሱ የህወሓት አክራሪ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን በማደፍረስ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ባለቻቸው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አክራሪ አመራሮች እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያነጣጠረ የቪዛ እገዳ መጣሏን አስታወቀች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቶማስ ፒጎት ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የቪዛ እገዳው በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በሰላም ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በማደናቀፍ ኃላፊነት ባለባቸው እና ተባባሪ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህግ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ይህንን እርምጃ መውሰዳቸው ተገልጿል።

ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ፍርሃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ጠቁሟል።

በመጨረሻም ዩናይትድ ስቴትስ በሰላም መኖር ከሚፈልገው የኢትዮጵያ እና የትግራይ ህዝብ ጎን መቆሟን እንደምትቀጥል ያረጋገጠው መግለጫው፤ በቀጠናው ሰላም ላይ አደጋ በሚጥሉ የህወሓት ባለስልጣናት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን ሁሉንም አማራጮች እንደምትጠቀም አስጠንቅቋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል(ሰኔ 11/2018 ዓ.ም)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዘንድሮው በጋ...
18/06/2026

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል

(ሰኔ 11/2018 ዓ.ም)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በዘንድሮው በጋ መስኖ ከለማው ስንዴ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ማግኘቱ ተገልጿል።

በዞኑ ግብርና መምሪያ የመስኖ አጠቃቀም አግሮኖሚስት ዘሩ ገረመው እንደገለጹት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አርሶ አደሩ በምግብ ራሱን ከመቻል ያለፈ ምርት እንዲያመርት አስችሏል።

በበጋው ወራት የተለያዩ የመስኖ አማራጮችን በመጠቀም 51 ሺህ 966 ሄክታር መሬትን በስንዴ በማልማት ከ2 ሚሊየን 147 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል።

ምርታማነቱን ለማሳደግም በባለሙያዎች ድጋፍ የማዳበሪያ፣ የምርጥ ዘርና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን አርሶ አደሩ በአግባቡ እንዲጠቀም ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

በዚህም የዞኑ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርታማነት በሄክታር በአማካይ 60 ኩንታል እንዲደርስ ማስቻሉን አስረድተዋል።

አርሶ አደሮቹ ያመረቱትን ስንዴ ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባሻገር ለኢንዱስትሪዎች ግብዓትና ለአካባቢው ገበያ በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ስራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የሰብልና ኢንዱስትሪ ግብይት ባለሙያ ጌታው ሙሉ፤ በዞኑ በዘንድሮው በጋ በጥራትና በብዛት ስንዴን በማምረት ለገበያ እየቀረበ ነው ብለዋል።

እስካሁንም 200 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ የስንዴ ምርት በአካባቢው ለሚገኙ አንዱስትሪዎችና ሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት መቅረቡን ጠቁመው የገበያ ማረጋጋቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በዚህም አሁን ላይ የስንዴ ዋጋ መቀነሱን ጠቁመው ይህም የዱቄት ፋብሪካዎች በቂ ዱቄት በማምረት ለዳቦ አምራቾች እንዲያቀርቡ እድልን ፈጥሯል ብለዋል።

በዞኑ በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ አርሶ አደር ታፈሰ ቱሉ፤ የበጋ መስኖ ልማት ስራ ምርታማነታችንን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሃብት እንድንፈጥር አስችሎናል ነው ያሉት።

በዘንድሮው በጋም አራት ተኩል ሄክታር ማሳቸው ላይ ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በመተባበር ስንዴን በኩታ ገጠም በማልማት ከ200 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ያመረቱትን ምርትም በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር በአካባቢው ለሚገኙ አንዱስትሪዎች በማቅረብ የተሻለ ገቢ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ሌላው የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር ደርቤ ፈለቀ በበኩላቸው አንድ ሄክታር ማሳቸውን በበጋ ስንዴ በማልማት 60 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ገልፀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

18/06/2026
ደባርቅ - ቧሂት አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ለማፋጠን እየተሰራ ነው። (ሰኔ 11/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎችን ከበየዳ ወረዳ የሚያ...
18/06/2026

ደባርቅ - ቧሂት አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ለማፋጠን እየተሰራ ነው።

(ሰኔ 11/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎችን ከበየዳ ወረዳ የሚያገናኝው የደባርቅ - ቧሂት አስፋልት መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል።

አጠቃላይ የግንባታ ስራው 63 ነጥብ 21 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በስካሁኑ የስራ እንቅስቃሴ የአስፓልት ማንጠፍ፣ የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የድሪኒጅ ፣ የሰብ ቤዝ ፣ የቤዝኮርስ ፣ የቤዝ ቦርስ መፍጨት፣ የአስፓልትና ኮንክሪት ጠጠር መፍጨት፣ ፓይፐ ማምረት እንዲሁም በርካታ የስትራክቸር ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ጅማሮውን ደባርቅ ከተማ ላይ አድርጎ ቧሂት ከተማ ድረስ የሚዘልቅ ነው፡፡

ግንባታው በ4,174,470,239.57 (አራት ቢሊዮን አንድ መቶ ሰባ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ ሰባት ሳንቲም) በሆነ ወጪ በፌደራል መንግስት ነው የሚሸፈነው።

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ግንባታውን እያካሄደ ሲሆን የግንባታውን ጥራት የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ደግሞ አይ.ዲ.ኮን ኢንፍራስትራክቸር ደቬሎፕመንት ኮንሰልታንትስ ኃ.የተ.የግ ማህበር እያከናወነው ይገኛል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በአስፋልት ኮንክሪት መገንባቱ ለአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ ለመስመሩ ተጠቃሚዎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥን ያመጣል።

አርሶ አደሮች ምርታቸውን ካለምንም ችግር በአፋጣኝ ወደ ማዕከላዊ ገበያ በማውጣት አምራችና እና ሸማቾችን በቀላሉ በማገናኘት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።

የሰሜን ብሔራዊ ፓርክን ለውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ምቹ እንዲሆን ከማስቻሉም ባለፈ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በተጨማሪም በተሽከርካሪ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን የ4 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 1 ሰዓት ያሳጥረዋል።

ፕሮጀክቱ በከተማ 19 ሜትር፣ በወረዳ 20.5 ሜትር እንዲሁም በገጠር 7 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጉ እየተገነባ መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 #አሸነፉ!ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተወዳደሩበት ምርጫ ክልሎች ማሸነፋቸው ተገለፀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል ለፓርላማ በተወዳደሩበት ጎማ ሁለት ...
17/06/2026

#አሸነፉ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተወዳደሩበት ምርጫ ክልሎች ማሸነፋቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል ለፓርላማ በተወዳደሩበት ጎማ ሁለት ምርጫ ክልል ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ ዛሬ ማምሻውን ይፋ አድርጓል።

በምርጫ ክልሉ ብልፅግና ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወዳድረው እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም በክልሉ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘው ብልፅግና መሆኑን ነው ቦርዱ ያስታወቀው።

በተጨማሪም በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሸንፈዋል ተብሏል።

16/06/2026

ሰርክ አዲስ ባሕርዳር‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰማይ የአፍሪካ ኩራትና መመኪያ ሆኖ ዘልቋል፤ አሁን ደግሞ መሬት ላይ በቢሾፍቱ ሌላ አፍሪካም ዓለምም ሊማሩበት የሚገባ ፕሮጀክት እያሣለጠ ይገኛል። ምክትል ጠቅላይ ...
16/06/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰማይ የአፍሪካ ኩራትና መመኪያ ሆኖ ዘልቋል፤ አሁን ደግሞ መሬት ላይ በቢሾፍቱ ሌላ አፍሪካም ዓለምም ሊማሩበት የሚገባ ፕሮጀክት እያሣለጠ ይገኛል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

15/06/2026

በአርቲስት ሰማኸኝ በለው ሕልፈት ሕይወት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል።

አርቲስት ሰማኸኝ በለው ባሕላዊ ይዘት ያላቸውን ስራዎች በመስራት ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ አርቲስት ነበር።

በኢትዮጵያ አይዶል በዳኝነት በመሳተፍ ለዘርፉ ተተኪ ወጣቶች በማፍራት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

የባሕል አምባሰደር የነበረው አርቲስት ሰማኸኝ በለው ባሕልና እሴቱን ጠብቆ በሰራቸው ሀገራዊ የኪነጥበብ ስራዎቹም በአድናቂዎቹ ዘንድ "ባለ ሀገሩ" በሚል ተወዳጅነትን አትርፎ ያለፈ አርቲስት ነው።

በአርቲስት ሰማኸኝ በለው ሕልፈተ ሕይወት የተሰማኝ ጥልቅ ሃዘን እየገለጽኩ፦ ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abebaw Ambaye-አበባው አምባዬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Abebaw Ambaye-አበባው አምባዬ:

Share