South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ

South Gondar  zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ Quality Education for All !!

የ2018/2019 ዓ.ም  የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ዝውውር አጭር  መረጃ ስለመስጠት ***********የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018/2019 የመምህራን እና ትምህርት አመራሮች ዝ...
30/05/2026

የ2018/2019 ዓ.ም የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ዝውውር አጭር መረጃ ስለመስጠት
***********
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018/2019 የመምህራን እና ትምህርት አመራሮች ዝውውር በጥራት፣ ፍትሐዊነቱን በጠበቀ መንገድ ሲሰራ ቆይቶ ተጠናቋል። ቀሪ ስራዎችንም የክልሉ ትምህርት ቢሮ እየሰራ ይገኛል።
ስለሆነም ክቡራን የክልላችን መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የተሰራው ዝውውር በቀጣዮቹ አጭር ቀናት ውስጥ ይፋ ስለሚደረግ በትዕግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።

#ትምህርትለትውልድ

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየም አካሄደ። *********************ደብረታቦር ፤ ግንቦት 21/2018ዓ.ም(ደ/ጎ/ትም/መ)የደቡብ ጎንደ...
29/05/2026

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየም አካሄደ።
*********************
ደብረታቦር ፤ ግንቦት 21/2018ዓ.ም(ደ/ጎ/ትም/መ)የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየም አካሄደ።
በጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየሙ የደቡብ ጎንደር ዞን የትምህርት መምሪያ ምክትል ኋላፊ አቶ ተፈሩ መላኩ በመክፈቻ ንግግራቸው ትምህርት ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ባጋጠመን የውስጥ የፀጥታ ችግር ምክንያት የትምህርት ዘርፉ በከፍተኛ ሁኔታ ስብራት ደርሶበታል ብለዋል፡፡ ።ኃ
ላፊው አክለውም የትምህርት ባለሙያዎች በተለይም መምህራን በትምህርት ቤት ደረጃ በመማር ማስተማር ሂደት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች የሚለዩበትና መፍትሄ የሚፈልግበት መንገዶች አንዱ ጥናት እና ምርምር ነው ያሉ ሲሆን ፤ ትምህርታዊ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማለትም በትምህርት ጥናትና ምርምር የመፍታት ተሞክሮ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ሌላው የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየሙ አሰተባባሪው አቶ ጋሻው ያለው እንደገለፁት የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየሙ ዋና አላማው መማማር ነው ሲሉ ለተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በዕለቱ ለጥናት አቅራቢ መምህራኖች የእውቅና የተሰጠ ሲሆን ጥናት አቅራቢወች እንደገለፁት የጥናት እና ምርምር ሲምፖዚየም መካሄዱ ተገቢ እና ጥሩ እውቀት የበለጠ ለመስራት ተነሳሽነት እንዲኖረን ያግዛል ብለዋል።

✅ለተጨማሪ አዳዲስ እና ወቅታ መረጃ:-
የፌስ ቡክ ገጻችን :- https://www.facebook.com/southgedu/
በቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/southgedu
ያገኙናል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ !!

29/05/2026
ግጭት ያልበገረው ልማት በእስቴ ወረዳ። ============================ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም  በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ካለው የትምህርት ፍላጎት አኳያ ያለው የትም...
27/05/2026

ግጭት ያልበገረው ልማት በእስቴ ወረዳ።
============================
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ካለው የትምህርት ፍላጎት አኳያ ያለው የትምህርት ቤቶች ቁጥር ሲታይ አነስተኛ እንደኾነ ይታመናል።ለዚህ ማሳያ የሚኾነው ደግሞ በየቀበሌው የሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ መኾናቸው እና በወረዳው በቂ ሁለተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ትምህር ቤት አለመኖራቸው ነው።

በአብዛኛው የወረዳው ቀበሌዎች የሚገኙ ተማሪዎች የሁለተኛና መሠናዶ ትምህርታቸውን በመካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር በሚገኘው እና በሌሎች ውስን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ረጅም እርቀት ተጉዘው ሲማሩ ቆይተዋል።

አሁን ላይ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየተሠራ መኾኑን የእስቴ ወረዳ አሥተዳደር አስታውቋል።

በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች 39 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የመማሪያ፣ አሥተዳደር እና መሰል ግንባታዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መኾናቸውን የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አዱኛው ጎቤ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶቹ በ2017 ዓ.ም ተጀምረው በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

የተገነቡት ሕንጻዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እና ምቹ በመኾናቸው የሕፃናትን የመማር ፍላጎት እንደሚጨምሩ እና የትምህርት ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩ ነው የተናገሩት።

የእስቴ ወረዳ አሥተዳዳሪ ማንተፋርዶ ሞላ ፕሮጀክቶቹ በመንግሥት፣ በአማራ ልማት ማኅበር እና በሕዝብ ተሳትፎ የተገነቡ መሆናቸውን አንስተዋል።

የተገነቡት ተቋማት የነገ ሀገር ተረካቢው ትውልድ የሚቀረጽባቸው ናቸው ያሉት አሥተዳዳሪው ማኅበረሰቡ በጥንቃቄ በመያዝ ባለቤትነቱን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል።

እስቴ ወረዳ ተደጋጋሚ ግጭት የሚነሳበት እና በርካታ ጉዳቶችን ያስተናገደ አካባቢ መኾኑን ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ የወረዳው አሥተዳደር ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የተለያዩ የልማት ሥራዎች እያከናወነ መኾኑን ገልጸዋል።

​በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች፣ የእስቴ ወረዳ እና የመካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች፣ መምህራን እና የወላጅ መምህራን ህብረት አባላት መገኘታቸው ተገልጿል።

#አሚኮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ600 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገዙ ኮምፒውተሮችን ለዞን ትምህርት መምሪያዎች አስረከበ። ====================ግንቦት19/2018 ዓ.ም // የ...
27/05/2026

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ600 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገዙ ኮምፒውተሮችን ለዞን ትምህርት መምሪያዎች አስረከበ።
====================
ግንቦት19/2018 ዓ.ም // የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ600 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገዙ ከ2 ሽህ በላይ ኮምፒውተሮች አስረከቧል።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ
በትምህርት መዋቅሩ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አኳያ በተደጋጋሚ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካካል የትምህርት ቤት ኮምፒውተር ማሟላት ጥያቄ አንዱ ነው ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጠው በበይነ መረብ በመሆኑ እና ትሞህርት ቤቶችን ድጅታል ከማድረግ አንጻር የኮምፒውተር ግብዓት ማሟላት አስፈላጊነት በመመልከት የክልሉ መንግስት በልዩ ውሳኔ ከ600 ሚሊዬን ብር በላይ በመመደብ ከ2 ሽህ በላይ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች እና 135 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን መግዛቱን ተናግረዋል።
የቀረቡት ኮምፒውተሮች 14ኛው ትውልድ ዘመናዊ ኮምፒውተሮች በመሆናቸው ለትምህርት ቤቶች ድጅታላይዜሽን አገልግሎት እና የበይነ መረብ ፈተና ለመስጠት ምቹ መሆናቸውን አኃላፊው አመላክተዋል።
በዚህ ዙር በዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች ለተመረጡ 85 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለእያንዳንዳቸው 25 ኮምፒውተር መመደቡን ኃላፊው ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ትምህርት ላይ ኢንቨስት በማድረግ በኩል ትልቅ ስራዎችን እየሰራ ነው። በዚህም ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ድጅታል ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ /PhD/ ፈጣን፣ ፈጣሪ አለም አቀፍ እሳቤ ያለው ትውልድ ለማፍራት መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ከአለም ጋር መወዳደር እንደሚገባ ገልጸዋል። በዚህም መንግስት ለትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰው ተኮር ተግባር እያከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።
የባህር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ /PhD/ ድጋፉ የትምህርት ቤቶችን የኮምፒውተር ግብዓት ችግር የሚቀርፍ ታሪካዊ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል። ኮምፒውተሮቹ ስማርት መማሪያ ክፍሎችን እና ድጅታል ቤተመጽሐፍት ለማዘጋጀት እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል።
የሰሜን ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ የሽወርቅ ድረስ ትምህርት ቢሮ ለጥያቄያቸው ፈጣን ምላሽ የሰጠበት እንደሆነ ተናግረዋል።ለ12ኛ ክፍል የበይነ መረብ ፈተና ለመስጠት በወቅቱ መድረሱን ገልጸዋል።

25/05/2026

በአማራ ክልል 100 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እንደሚወስዱ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የፊታችን ሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በስኬት ለማስኬድ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኀላፊ እየሩስ መንግሥቱ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቢሮው ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው ብለዋል።

በዚህ የትምህርት ዘመን ላይም 99 ሺህ 897 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ነው ያሉት።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን ተማሪዎችን በበይነ መረብ የመፈተን ዕቅድ በክልሉ ለመተግበር ርብርብ እየተደረገ ስለመኾኑም አስረድተዋል።

በክልሉ የሚገኙ 539 ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚያስፈትኑም ምክትል ኀላፊዋ ገልጸዋል።

ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 315ቱ በበይነ መረብ አማካኝነት ለተማሪዎቻቸው ፈተናውን ይሰጣሉም ብለዋል። በበይነ መረብ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስፈትኑት መካከልም 215 ትምህርት ቤቶች በክልሉ በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚያስፈትኑ ይኾናል ነው ያሉት።

ቀሪ 100 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ማዕከላት እና በአይ ሲ ቲ ማዕከላት እንደሚያስፈትኑ ነው የተናገሩት።

ቀሪዎቹ ትምህረት ቤቶች ደግሞ በተለመደው የወረቀት ፈተና አሰጣጥ ሂደት ፈተናውን እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል።

በበይነ መረብ አማካኝነት ተማሪዎችን በስኬት ለማስፈተን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ስለመኾኑም ምክትል ኀላፊዋ አንስተዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎቹ ቴክኖሎጅውን እንዲለማመዱት የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት።

የበይነ መረብ ፈተና ሥርዓት ኩረጃን በማስቀረት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል።


#ትምህርትለትውልድ

ማስታወቂያየሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ።ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና...
21/05/2026

ማስታወቂያ
የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ።
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የምሰጥባቸው ቀናት እንደምከተለው የተሸጋሸጉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

21/05/2026

Address

Debre Tabor
Bahir Dar

Telephone

+251584412987

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Gondar zone Education Department /ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ:

Share