ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር
እናሻግራት ሁላችንም በመደመር
መድረሻችን ጫፍ እስከ ጫፍ እንዲሰማ
እንለኩሰው ይቀጣጠል የድል ሻማ።

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣  በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ...
27/05/2026

ትናንት፣ ዛሬና ነገ....

በሀገራችን ውስጥ በሚዛን ሊያዝ የሚገባው ነገር በትናንት፣ በዛሬና በነገ መካከል ያለው ምልከታ ነው፡፡ ትናንትን ፈፅሞ የመቀደስም ሆነ ትናንትን ፈፅሞ የማርከስ ጉዞ ሀገርን ያለ ወረት ያስቀራል።

ዛሬንና ነገን ማቃለልም ሆነ ዛሬና ነገን የሁሉም ነገር መጀመሪያ ማድረግ ሀገርን ያለ መነሻ ያስቀራል፡፡ ብልፅግና ትናንት ከዛሬና ከነገ ጋር በሚዛን የሚታይበትን መርሕ ይከተላል፡፡

• ከትናንቱ መልካሙን መውሰድ፤ እንከኑን ማረም
• ዛሬን፣ በትናንት መሠረት ላይ ገንብቶ በሚገባ መጠቀም
• ለነገ ተግባብቶ ወረት ማቆየት

ትናንትን ከዛሬና ነገ ጋር በሚዛን ለማየት እንዲቻል፣ የትናንት ቁርሾዎችን የምናክምባቸው፣በትናንትጉዞ ላይ የምንግባባባቸው ፤ ነገን በጋራ የምንተልምባቸው መንገዶችን መከተል አለብን ብሎ ያምናል፡፡

እነዚህም፡-
👉በሰከነ ምክክር አዲስ ቃል ኪዳን ማሠር ፤

ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፣ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ፓርቲያችን በቀዳሚነት አስቀምጧል፡፡ለዘመናት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እንኳን ያላግባቡን ጉዳዮች በሀገራዊ ምክክር ምላሽ እንዲያገኙ ቁርጠኛ አቋምም አለው። ፓርቲያችን ብሔራዊ መግባባት ለሀገረ መንግሥቱ ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ እንደሆነ ያምናል።

የፖለቲካ ማኅበረሰቡ የትናንት ቅራኔዎችን በመግባባትና በዕውቅና፣ በዕርቅና በሽግግር ፍትሕ መፍታት እንዳለበት እናምናለን፡፡ ስለዚህም በስክነትና በዕውቀት፣ ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሠምር ሕዝባችንና የፖለቲካ ልሂቃን አዎንታዊ ሀገራዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አናቀርባለን።

በዚህ የጸና እምነታችንና መሻታችን የተነሣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋም ሂደት እንደ ፓርቲና እንደ መንግሥት የሚጠበቅብንን አድርገናል፡፡

የሕዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ፣ ለኮሚሽኑ ሥራ አስፈላጊ የሆኑትን የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክስና የመረጃ አቅርቦቶችን ያለተዐቅቦ በማሟላት፣ እንዲሁም ነጻነቱን በማክበር ባለፈው ምርጫ ዘመን ቃል የገባንውን በተግባር ፈፅመናል።

በቀጣይ አምስት ዓመታትም፡-

በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መሪነት በሂደት የሚደረስባቸው ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ይኖራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

እነዚህን ውሳኔዎችና ምክረ ሐሳቦች ወስደን ለሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች፣ ለፖለቲካ ሥርዓት ማሻሻያዎች፣ ለሰብአዊ መብቶች ማሻሻያዎች እና ለቀደሙ በደሎች የመፍትሔ መንገዶች አድርገን እንደ ፓርቲና መንግሥት ለመፈጸምና ለማስፈጸም እንሠራለን።

👉በሽግግር ፍትሕ መሥመር፤ ቁርሾን መሻር ፤

በኢትዮጵያ ለዘመናት የኖሩ በደሎች፣ ቁርሾዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አሉ፡፡ እነዚህን በተመለከተ ፈውስ የሚሰጥ ፍትሕን እና ይቅርታን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ እንደሚያስፈልገን ፓርቲያችን ያምናል። ይህንን መሠረት በማድረግም ባለፉት ዓመታት ሕጋዊና ተቋማዊ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

በቀጣይ ዓመታትም፡-

ለተፈጸሙ በደሎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ የወንጀል ምርመራና ክስ፣ እውነትን የማፈላለግ እና ይፋ የማውጣት ተግባር፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ግለሰባዊ እና ማኅበረሰባዊ ዕርቅ ለማስፈን እንሠራለን፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሕጋዊና ባህላዊ መንገዶችን እንጠቀማለን፤ ማካካሻና ተቋማዊ ማሻሻያን ይተገበራል።በዚህም ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደ ሀገር እንዲተገበር እንሠራለን።

የብሔራዊ መግባባት፣ የዕርቅና የፍትሕ ሂደት እንዲሠምር የሀገራትን ተሞክሮ ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር አስማምተን እንጠቀማለን። እንዲሁም ባሕላዊ የግጭት አፈታትና የዕርቀ ሰላም ሥርዓቶችን እንደየአካባቢው እንተገብራለን፡፡ ይህንንም በማድረግ ሀገራዊ አንድነታችንን እና ብሔራዊ መግባባታችንን እናጠናክራለን፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከተፅዕኖ እና ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲከናወን እናደርጋለን፡፡ ተአማኒነቱን እና ቅቡልነቱን ለማረጋገጥ፣ ሐቅ አፈላላጊ ኮሚሽን፣ ልዩ ዐቃቤ ሕግና ልዩ ችሎት ይቋቋምለታል፡፡

በእነዚህ ተቋማት በሚመራ ምርመራና ዳኝነት አማካኝነት እንዲከናወን በማድረግ፣ የሽግግር ፍትሕ ያስቀመጣቸውን ብሔራዊ ግቦች እንዲመታ እናደርጋለን።

👉የተሐድሶ ፕሮግራም ፤

በተለያዩ አካባቢዎች ነፍጥ አንግተው ጫካ የገቡ አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ፓርቲያችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ መንገድም በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

እነዚህ ታጣቂዎች በተሐድሶ ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ ይገባናል፡፡ ታጣቂ ቡድኖች እንዲበተኑ፤ ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲያወርዱ እና ወደ ሰላማዊው መንገድ እንዲቀላቀሉ ለማድረግ የቦታ፣ የገንዘብ፣ የቴክኒክ እና የሥነ ልቦና ዝግጅት ይፈልጋል፡፡

ለዚህ ታላቅ ተግባር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ የበጀትና የቁሳቁስ ዝግጅት በማከናወን የተሐድሶን ፕሮግራም በተሟላ መልኩ ለማከናወንና የጸና ሰላምን ለመመሥረት ፓርቲያችን ይሠራል፡፡



#ኢትዮጵያንወደተምሳሌትሀገር
#ብልፅግናፓርቲንይምረጡ

27/05/2026
27/05/2026
  👌👌👌 #ወ/ሮ_ሰላማዊት_አለማየሁ_በቀለ የብልጽግና ፓርቲ የባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል ''የክልል ምክር ቤት'' እጩ !!  !   !  !Selamawit Alemayehu
27/05/2026

👌👌👌
#ወ/ሮ_ሰላማዊት_አለማየሁ_በቀለ
የብልጽግና ፓርቲ የባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል ''የክልል ምክር ቤት'' እጩ !!

!

!
!
Selamawit Alemayehu

ለመቄት እድገትና አንድነት!የመቄትን ህዝብ ታላቅነትና ታሪክ የሚመጥን፣ በቁርጠኝነትና በዕውቀት የሚያገለግል መሪ መምረጥ የወደፊት እጣ ፈንታችንን የመወሰን ጉዳይ ነው። ብልፅግና ፓርቲ የመቄት...
27/05/2026

ለመቄት እድገትና አንድነት!

የመቄትን ህዝብ ታላቅነትና ታሪክ የሚመጥን፣ በቁርጠኝነትና በዕውቀት የሚያገለግል መሪ መምረጥ የወደፊት እጣ ፈንታችንን የመወሰን ጉዳይ ነው። ብልፅግና ፓርቲ የመቄትን ህዝብ ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ለመመለስና አካባቢያችንን የሰላምና የልማት ተምሳሌት ለማድረግ አቶ ፍስሃ ደሳለኝን በዕጩነት አቅርቧል።

መቄትን ህዝብ ትክክለኛ ፍላጎት፣ ባህልና እሴት ጠንቅቀው የሚያውቁና ከህዝቡ መሃል የበቀሉ መሪ ናቸው።

የመሠረተ ልማት፣ የግብርና፣ የትምህርትና የጤና ጥያቄዎችን በቁርጠኝነት በማስፈጸም የመቄትን ብልፅግና ያረጋግጣሉ።
የወጣቶችንና የሴቶችን ድምፅ በማድመጥ፣ ሁሉንም ያካተተ ፍትሃዊ አሰራርን የሚያሰፍኑ ቁርጠኛ መሪ ናቸው።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለክልላችን ምርጫ ብቻ አይደለም። የዘላቂ ሰላም ግንባታ መሰረታችን ጭምር ነው። አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን ከጠመንጃ ይልቅ በሃሳብ የበላይነት መመራትና ለዴሞክራሲ መርሆዎ...
27/05/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለክልላችን ምርጫ ብቻ አይደለም። የዘላቂ ሰላም ግንባታ መሰረታችን ጭምር ነው። አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን ከጠመንጃ ይልቅ በሃሳብ የበላይነት መመራትና ለዴሞክራሲ መርሆዎች መገዛት ግድ ይላል።

ብልጽግና ደግሞ ይህንን ደጋግሞ በተግባር አሳይቷል። ዛሬም ፥ ነገም ወደፊትም መርሁ የሕዝባችንን ሰላምና የመልማት መብትና ፍላጎት ማሟላት ነው።

ሲመርጡን አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን እየመረጡ ነው። ሲመርጡን ልማትንና ብልጽግናን ሀብት እያደረጉ ነው።

ብልፅግናን ይምረጡ!
Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ
Arega Kebede Legas/አረጋ ከበደ ለጋስ
Selamawit Alemayehu

ክቡር ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)በፍኖተ ሰላም ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩምሁራዊ ዕይታ፣የህዝብ ፍላጎት የሚረዱ፣የመሪነት ጥበብ እናየዳበረ እውቀት ያላቸው ቆራጥ መሪ ናቸው!ኢትዮጵያን ወደ ...
27/05/2026

ክቡር ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
በፍኖተ ሰላም ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ

ምሁራዊ ዕይታ፣
የህዝብ ፍላጎት የሚረዱ፣
የመሪነት ጥበብ እና
የዳበረ እውቀት
ያላቸው ቆራጥ መሪ ናቸው!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር
#ብልጽግናን ይምረጡ!

በከተሞቻችን ተጠናክረው የሚቀጥሉ ልማቶቻችን!🏙 የኮሪደር ልማት🏙 ዲጂታላይዜሽን🏙 የተማሪዎች ምገባ🏙 ምቹ መኖሪያ🏙 የስፖርት ማዘውተሪያ🏙 አምራች ኢንዱስትሪ🏙 ምቹ ትራንስፖርትእነዚህንና ሌሎችን...
27/05/2026

በከተሞቻችን ተጠናክረው የሚቀጥሉ ልማቶቻችን!
🏙 የኮሪደር ልማት
🏙 ዲጂታላይዜሽን
🏙 የተማሪዎች ምገባ
🏙 ምቹ መኖሪያ
🏙 የስፖርት ማዘውተሪያ
🏙 አምራች ኢንዱስትሪ
🏙 ምቹ ትራንስፖርት

እነዚህንና ሌሎችንም
አጠናክረን እንቀጥላለን!
ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
በባሕር ዳር ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ
ብልጽግናን ይምረጡ !
#ኢትዮጵያን ወደተምሳሌት ሀገር!

ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህበባሕር ዳር ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ🏆 ሀቀኛና ትሁት፣🏆 ቆራጥና ትጉህ፣🏆 ታማኝ፣🏆 አሻጋሪ ፣ ባለራዕይ እና🏆 በዕውቀት የዳበረ ልምድ      ...
27/05/2026

ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ
በባሕር ዳር ምርጫ ክልል
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ
🏆 ሀቀኛና ትሁት፣
🏆 ቆራጥና ትጉህ፣
🏆 ታማኝ፣
🏆 አሻጋሪ ፣ ባለራዕይ እና
🏆 በዕውቀት የዳበረ ልምድ
ያላቸው መሪ ናቸው!

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ድንቁበአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ምርጫ ክልልለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪ                ኢትዮጵያ ወደ ተምሳ...
27/05/2026

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ድንቁ
በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪ

ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!

ብልፅግናን ይምረጡ !!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!!


#ምርጫ2018

27/05/2026

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918768463

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share