Ministry of Revenues Bahir Dar Branch/የገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት/

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Ministry of Revenues Bahir Dar Branch/የገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት/

Ministry of Revenues Bahir Dar Branch/የገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት/ Ministry of Revenues Bahir Dar Branch is one of many branches of the Ethiopian Ministry of Revenues

18/01/2026
19/11/2025

ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑት መጣኔዎች

ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጠዋል፡፡

በመቀጠር በሚገኝ ወርሃዊ ገቢ ላይ ለሚጣለው ግብር ተፈጻሚ የሚሆኑት መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፦

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

19/11/2025

ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎች

ሕዳር 9/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር መጣኔዎች ተቀምጠዋል፡፡

እነኚህ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

20/08/2025

የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል

ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል አለ፡፡

ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከምጣኔ ውጭ ሌሎች ማሻሻያዎችን በማካተት ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ በ2017 በጀት አመት ስራ ላይ መዋሉን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከነበረው ከ12 በመቶ በላይ ድርሻ በየዓመቱ በተከታታይ እየቀነሰ ከ7 በመቶ በታች መድረሱን ጠቅሶ፥ ከዚህ ጠቅላላ ቅናሽ 44 በመቶው የተጨማሪ እሴት ታክስ ድርሻ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ህጉን አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ የቀጣይ ዓመታት ለውጦች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በመካከለኛ ዘመን የገቢ ስትራቴጂው መሰረት ተሻሽሎ በ2017 በጀት ዓመት ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብሏል፡፡

በማሻሻያው መሰረት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ነው የገንዘብ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

ዘገባውን ያገኘነው ከኤፍ ኤም ሲ ነው

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም

14/07/2025
23/12/2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ዙሪያ የመግባቢያ ስነድ ተፈራረመሕዳር 30/2017 ዓ....
09/12/2024

የገቢዎች ሚኒስቴር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ዙሪያ የመግባቢያ ስነድ ተፈራረመ
ሕዳር 30/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ሥነ-ስርዓት በገቢዎች ሚኒስቴር እና በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት መካከል በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን ዓላማውም ከታክስ ደረሰኝ ህትመት ጋር በተያያዘ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) ተካቶ ማተም፤ የህትመት ጥያቄ መቀበል፣ ከታተመ በኋላ የስርጭት እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ማስራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እና የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ሽታሁን ዋለ ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እንደ ሀገር ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ገቢን በብቃት መሰብስብ እና ሀገራዊ ወጪን በሀገራዊ ገቢ ለመሽፈን የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑን ጥቁመው ላለፉት በርካታ ዓመታት ለግብር ከፋዩ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ምቹ እና ቀልጣፋ ለማድረግ በርካታ ማሻሻያዎችን አከናውኗል ብለዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት የማንዋል ደረሰኝ አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ ብዙ ርቀት ለመሄድ የተሞከር ቢሆንም የሀሰተኛ ደረሰኝ ህትመት መበራከት በግብር አሰባበሰቡ ላይ ፈተና ሆኖ የቆየ በመሆኑ የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያን ለማሻሻል የወጣ መመሪያ ቁጥር 188/2017ን አጽድቆ ስራ ላይ በማዋል ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ እያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ሲታተም ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) ተካቶ መታተም እና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ በህትመት ዘርፉ ፈርቀዳጅ የሆነና የአንድ መቶ አራት ዓመት ልምድ ካለው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በጋር ለመስራት ከስምነት ላይ ተደርሷ ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ አያይዘውም ደረሰኝ እንዲታተም ፍቃድ ከመስጥት ጀምሮ ያሉ አገልግሎቶችን ማስተናግድ እንዲቻል የራሱ የሆነ ዲጂታል ፕላትፎርም የተዘጋጀ ስለሆነ ደረሰኝ የሚያሳትም ማንኛውም ግብር ከፋይ በዚሁ መንገድ መስተናገድ የሚችል መሆኑን ጠቁመው ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ የማንዋል ደረሰኝ የመሳተም ጥያቄያቸውን ማቅረብ የሚቻል መሆኑን አመላክተው ከየካቲት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተም የማንዋል ደረሰኝ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ሽታሁን ዋለ በበኩላቸው የገቢዎች ሚኒስቴር የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት እንዲችል በተለይም ከገቢ አሰባስቡ ጋር በተገናኛ ያሉ ማነቆዎችን ማፈታት እንዲቻል ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አጋር ተደርጎ በመታየቱ እና በጋራ ለመስራት በመመረጡ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ድርጅቱ ሚስጥራዊ ህትመቶችን በማተም ካለው የካበት ልምድ በመነሳት ደረጃውን የጠበቀ፣ ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) የተካተተበት እና አስመስሎ መስራት በማይቻል መልኩ የህትመት ሥራውን ለማከናወን በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
አክለውም ግብር ከፋዮች ለገቢዎች ሚኒስቴር በሚያቀርቡት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ መሠረት የሚቀርቡ የህትምት ትዕዛዞችን ተቀብሎ ደረሰኞችን ለማተም በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጸው ድርጅቱም ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት በመወጣት በተገባው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚቀርብለትን የደረሰኝ ህትመት ትዕዛዝ በሙሉ ኃላፊነት የሚተገብረው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

24/11/2024

በታክስ አከፋፈል ላይ ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ውስጥ የሚያስገቡ ጥፋቶች

👉ትክክለኛውን ክፍያ እና በወቅቱ አለመክፈል፣
👉 የግብር ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሳቸው በኃላ ክፍያ አለመፈጸም፣
👉 በጊዜ ስምምነት ለመክፈል ስምምነት ከገቡ በኃላ ማቋረጥ፣
👉 በግብር ተመላሽ ወቅት የሚቀርቡ የታክስ መጠን በስህተት ወይንም ሆን ብሎ በትክክል ያለማቅረብ፣
👉አግባብ ያልሆነ ተመላሽ መጠየቅ፣
👉 ግብር የመክፈል አቅም ያላቸው ግብር ከፋዮች በግብር ሥርዓት መረብ ውስጥ ያለመታቀፍ፣

የስጋት ደረጃን ለማሻሻል የሚረዱ ሁኔታዎች

👉 በግብር ከፋይነት መመዝገብ እና በግብር ስርዓቱ መታቀፍ
👉 ትክክለኛውን መረጃ ለግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ማሳወቅ
👉 ለግብር አወሳሰን የሚረዱ የሂሳብ ሰነዶችን በአግባቡ መያዝ
👉 የሚጠበቀውን ግብር በወቅቱ ማስታወቅ እና መክፈል
👉የተቀመጡ የተመላሽ፣ ኪሳራ የማሳወቅ መብቶችን በአግባብ መጠቀም

የስጋት ደረጃን ማሻሻል ምን ጠቀሜታ አለው?

👉 ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በማሻሻል ገቢ በወቅቱ እና በትክክል ተሰብስቦ ለስራ እንዲውል ያግዛል፤
👉የህግ ማስከበር ወጪዎችን ይቀንሳል፤
👉ግብር ከፋዩም ሆነ ግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ስራቸው ላይ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ በማድረግ ምቹ አሰራር ይፈጥራል፤
👉 ተቋሙ ለተሻለ የህግ ተገዢነት ላላቸው ግብር ከፋዮች ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ በዚህ ደረጃ ያሉ ግብር ከፋዮች ያለ ወረፋ ይስተናዳሉ፤ በሌሎች መስሪያ ቤቶችም የቅድሚያ አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎች እየተመቻቹ በመሆኑ ከአላስፈላጊ ጊዜና ገንዘብ ብክነት ይድናሉ፡፡

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 ገቢያችን ህልውናችን ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎️ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን መጠየቅ ወይንም ማግኘት ይችላሉ፡፡

Address

Abdisa Aga Road
Bahir Dar
508

Opening Hours

Monday 08:00 - 05:00
Tuesday 08:00 - 05:00
Wednesday 08:00 - 05:00
Thursday 08:00 - 05:00
Friday 08:00 - 11:30
Saturday 08:00 - 12:00

Telephone

+251582263409

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Revenues Bahir Dar Branch/የገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ministry of Revenues Bahir Dar Branch/የገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት/:

Share