09/06/2021
በትራፊክ አደጋ የሠው ህይወት አለፈ
******************
በምስራቅ ጎጃም ዞን በፈለገ ብርሃን ንዑስ ወረዳ ፈለገ ብርሃን ከተማ ቀጠና አራት ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ሰኔ 02/2013ዓ/ም ከጥዋቱ 1:30 ከባህርዳር ወደ አድስ አበባ ሲሄድ የነበረ ኢ.ት ኮድ 3 ሠሌዳ ቁጥር 85203 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ አባይ ባስ መንገድ አቋርጠው በመሄድ ላይ ያሉ ሁለት ሠዎችን በመግጨት አንድኛዋ እዚያው ላይ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ሁለተኛዋ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባታል።
ስለሆነም አሽከርካሪዎች ፍጥነታችሁን ቀንሳችሁ አሽከርክሩ እያልን እግረኞች ደግሞ መንገድ ከማቋረጣችሁ በፊት ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ ማቋረጥ እንዳለባችሁ እና ግራ መስመር ይዛችሁ እንድትጓዙ እንዲሁም ማቋርጥ ያለባችሁ በዘብራ መንገድ መሆኑን አውቃችሁ ለህብረተሰቡ ት/ት በመሥጠት እራሣችንን እና ህብረተሠባችንን ከትራፊክ አደጋ እንከላከል እያልን መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ።
የፈለገ ብርሃን ንዑስ ወረዳ ፖሊስ የኮሚኒኬሽን ክፍል
Send a message to learn more