16/03/2022
በሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት
በግብር ትምህት ኮሙኑኬሽን
ዋና የስራ ሂደት
ለግብር ከፋዮች እና ለተለያዩ
የማህበረሰብ ክፍሎች የተዘጋጀ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ
መጋቢት/2014 ዓ.ም
ሮቢት
የገቢ ሰንጠረዥ
አምስት አይነት የገቢ ሰንጠረዦች አሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ሰንጠረዥ ”ሀ” ከመቅጠር የሚገኝ ገቢ (Personal Income Tax)
ከመንግስት መስሪያቤቶች እና ከግል ድርጅቶች ተቀጥረው ከሚሰሩ የሚቆረጥ ግብር ነው፡፡
ከ600 ብር በታች የወር ደመዎዝ ያላቸውን አይጨምርም፡፡
1.ከመ ቅጠር የሚገኝ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የወር ደመወዝ ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 600 0% 0
601 1,650 10% 60
1,651 3,200 15% 142.50
3,201 5,250 20% 302.50
5,251 7,800 25% 565
7,801
10,900 30% 955
ከ10,900 በላይ 35% 1500
ለምሳሌ አቶ ሮቤል የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ ሲሆን በወር 9014 ብር ይከፈላቸዋል፡፡ አቶ ሮቤል በወር እና በዓመት ምን ያህል ብር ይከፈላሉ፡፡
የተሰጠ
ጠቅላላ የወር ደመዎዝ =9014
የግብር መክፈያ ምጣኔ =30%
ተቀናሽ ብር=955
የተጠየቀ
በየወሩ የሚከፍለው ግብር ስንት ነው?
ቤዓመቱ የሚከፍለው ግብር ስንት ነው?
መፍትሔ/አሰራር
የሚከፈል ግብር ጠቅላላ ደመወዝ= (ጠቅላላ የወር ደመዎዝ×የግብር መክፈያ ምጣኔ)- ተቀናሽ ብር
የአቶ ሮቤል የወር ደመወዝ የስራ ግብር ስኬል ከወር ደመወዝ 7,801 እሰከ 10,900 ብር መካከል ስለሚገኝ ምጣኔዉ 30% ነዉ፡፡
አቶ ሮቤል የሚከፍሉት ግብር በወር =(9014×30%)-955 = 2704.2 ብር በወር ይከፍላሉ፡፡
አቶ ሮቤል የሚከፍሉት ግብር በዓመት =2704.2 ×12 = 32,450.4 ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡
2. ሰንጠረዥ “ለ” ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ (Rental Income Tax)
• የመኖሪያ እና
• የድርጅት ቤት
ከኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የዓመት ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 7,200 0% 0
7,201 19,800 10% 720
19,801 38,400 15% 1,710
38,401 63,000 20% 3,630
63,001 93,600 25% 6,780
93,601
130,800 30% 11,460
ከ130,800 በላይ 35% 18,000
ለምሳሌ፡- አንድ የመኖሪያ ህንፃ የሚከራይ ግብር ከፋይ በየወሩ ብር 200,000.00 ቢያከራይ ዓመታዊ ገቢው ብር 200,000.00×12=ብር 240,000.00
ግብር የሚከፈልበት ገቢ ብር 240,000.00×50%=ብር 120,000.00
ዓመታዊ ግብር ብር 120,000.00×30%=ብር 36,000.00
36,000.00-11,460.00=24,540
ዓመታዊ ግብር ብር=24,540
3. ሰንጠረዥ “ሐ” ከንግድ ትረፍ የሚገኝ ገቢ (Business Income Tax)
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢን አይጨምርም፡፡
ዓመታዊ ገቢያቸው ከ7200 ብር እና በታች የሆነን አይጨምርም፡፡
ድርጅት ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የንግድ ስራ ገቢ የግብር ምጣኔ 30% ነው፡፡
ከንግድ ስራ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
የዓመት ገቢ የግብር መክፈያ ምጣኔ ተቀናሽ
ብር
ከብር እስከ ብር
0 7,200 0% 0
7,201 19,800 10% 720
19,801 38,400 15% 1,710
38,401 63,000 20% 3,630
63,001 93,600 25% 6,780
93,601
130,800 30% 11,460
ከ130,800 በላይ 35% 18,000
ለምሳሌ፡- XYZ ተቋራጪ ድርጅት በዓመት የተጣራ ትርፍ 280,000 ብር ቢያገኝ ሚከፍለው ግብር 280,000×30%=84,000
4. ሰንጠረዥ “መ” ሌሎች ገቢዎች (Other Income Tax)
o ሮያሊቲ
o ትርፍ ድርሻ ክፍፍል
o የስራ አመራር ክፍያ
o የቴክኒክ አገልግሎት ክፍያ
o ንፋስ አመጣሽ ትርፍ
o ያልተከፋፈለ ትርፍ
o ወለድ ወዘተ…..ናቸው፡፡
5. ሰንጠረዥ “ሠ” ከገቢ ግብር ነጻ የሆኑ ገቢዎች (Free From Income Tax)
• የውሎ አበል
• የወር ደመወዛቸው ከ600 ብር በታች የሆነ
• የማበረታቻ ሽልማት
• የአየር ጸባይ አበል እሰከ 30% የሚከፈል
• ስጦታ የመሳሰሉት ናቸው፡፡