የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ/East gojjame zone pp women league

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ/East gojjame zone pp women league

የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ/East gojjame zone pp women league Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ/East gojjame zone pp women league, Political organisation, D. markos, Bahir Dar.

ወ/ሮ አትክልት አሳቤ የምስ/ጎ/ዞን ብልጽግና ፖርቲ ፖለቲካ ዘርፋ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን
12/10/2021

ወ/ሮ አትክልት አሳቤ የምስ/ጎ/ዞን ብልጽግና ፖርቲ ፖለቲካ ዘርፋ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን

ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ የምስ/ጎ/ዞን ብልጽግና ፖርቲ አደረጃጀት ዘርፋ ሀላፊ ሆና ተሹማለች።  ጀግኒት መልካም የስራ ዘመን ይሁንልሽ!!!
10/10/2021

ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ የምስ/ጎ/ዞን ብልጽግና ፖርቲ አደረጃጀት ዘርፋ ሀላፊ ሆና ተሹማለች። ጀግኒት መልካም የስራ ዘመን ይሁንልሽ!!!

10/10/2021

የሹመት መረጃ!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሹመት የተሰጣቸው የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ
አመራሮች!
1. ደቡብ ወሎ ዞን!
1. የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ---አብዱ ሁሴን ኢብራሂም(እጩ ዶ/ር)
2. ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ---አቶ አሊ መኮንን አስፋው
3. ምክትል አስተዳዳሪ------አቶ ተስፋ ዳኛው
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ----አቶ አሊ ይማም ሁሴን
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ--ወ/ሮ ሀና አለባቸው
2. ምስራቅ ጎጃም ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ---አቶ አብርሃም አያሌው
2. የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ---አቶ ዋለ አባተ
3. ምክትል አስተዳዳሪ--አቶ መንበሩ ዘውዴ
4. የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ--ወ/ሮ አትክልት አሳቤ
5. የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ--ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ
3. ምዕራብ ጎጃም ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ------አቶ መልካሙ ተሾመ
2. ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ----አቶ ደጀኔ ልመንህ
3. ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ--------አቶ ጥላሁን አለምነህ
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ------አቶ አለባቸው ገነት
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ---ወ/ሮ ሰርካዲስ አታሌ
4. ሰሜን ሸዋ ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ------አቶ ታደሰ ገ/ጻዲቅ
2. ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ----አቶ ካሳሁን እምቢአለ
3. ምክትል አስተዳዳሪ--------አቶ ሲሳይ ወ/አማኑአል
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ-------አቶ ዘውገ ንጉሴ
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ----ወ/ሮ ሰዓዳ ኢብራሂም
5. ሰሜን ጎንደር ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ-------አቶ ያለአለም ፈንታው
2. ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ---አቶ አባይ መንግስቴ
3. ምክትል አስተዳዳሪና ከተማና መሰረት ልማት መምሪያ ኃላፊ---ወ/ሮ
ደብረወርቅ ይግዛው
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ-----አቶ ብርሃኑ ዘውዱ
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ----አቶ ሸጋው ውቤ
6. ምዕራብ ጎንደር ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ---አቶ ደሳለኝ ጣሰው
2. ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ---አቶ ቢክስ ወርቄ
3. ምክትል አስተዳዳሪና ጤና መምሪያ ኃላፊ
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ-------አቶ እያሱ ይላቅ
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ----አቶ አብደላ ኑሩ
7. ደቡብ ጎንደር ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ----አቶ ይርጋ ሲሳይ
2. ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ---አቶ ታደሰ ይርዳው
3. ምክትል አስተዳዳሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ
4. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ----አቶ አገኘሁ ካሳ
8. ማዕከላዊ ጎንደር ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ----አቶ ወርቁ ኃ/ማርያም
2. ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ---አቶ ፈንታው ስጦታው
3. ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ-------------ወ/ሮ እየሩስ
መንግስቱ
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ----------አቶ ገድፍ ጌትነት
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ-------አቶ ነጋ ይስማው
9. ሰሜን ወሎ ዞን!
1. ዋና አስተዳዳሪ--------ተስፋው ባታብል
2. ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ----ከድር ሙስጠፋ
3. ምክትል አስተዳዳሪና ትም/መምሪያ ኃላፊ---ጋሻው አስማሜ
4. ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ---------ዮሃንስ ተሰሜ
5. አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ-----ወ/ሮ ጀነቴ አያሌው
ሁነው ተሹመዋል።
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤትም ለሁሉም ዞን ተሿሚወች መልካም የስራ
ዘመን እንዲሆን ይመኛል።

08/10/2021
26/09/2021

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን !!

የመስቀልን በዓል ስናከብር የአመፃ ዘመን አብቅቶ የነፃነት ዘመን እንደሚመጣ ፤ የውሸት ፀሃይ ጠልቆ የእውነት ፀሃይ እንደሚወጣ ፤ የተከመረው የቆሻሻ ክምር ተንዶ የንፁሃን ደመራ እንደሚያበራ ፤ የክፉዎች ሴራ ተበትኖ የደጋጎች ጥላ እንደሚሰበሰብ የምናስታውስበት የትዕግስት ፣ የመተማመን ፣ የፍቅርና የፅናት ተምሳሌት ነው ።

የአዳኝነትና እውነትነት ምልክት የሆነውን መስቀል በቀበሩት ጊዜ የፀሃይ መጨለም ፤ የጨረቃ ደም መልበስ ፤ የከዋክብት መርገፍ ፤ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ መቀደድ ፤ የምድር መናወጥና የሙታን መነሳት ዓለምን በአዲስ ክስተት እንዳጎናፀፉት ሁሉ ታላቋን እና የቃል ኪዳን ምድር የሆነችውን ኢትዮጵያን ከሃዲዎች ከጀርባዋ በወጓት ጊዜ የሴረኞች ፀሃይ እየጠለቀች ፣ የአመፀኞች ዕይታ እየደበዘዘ ፣ የዘረኞች የጎጥ መጋረጃ እየተቀደደ ፣ የቆሙበት መሬት ሁሉ እየከዳቸው ፣ የሙት መንፈሳቸው ጠልፎ ከአፈር በታች እያዋላቸውና የእውነት ዘመን መበሰር አይቀሬ ስለመሆኑ አመላካች ክስተቶችን እያየን ነው ።

አመፀኞች የእውነት ተምሳሌት የሆነውን መስቀል ለመሰወርና ስሙም ዳግም እንዳይጠራ ኑ እናጥፋው ብለው 90 ክንድ ጥልቀት በመቆፈር ጠንካራና ጠማማ ድንጋዮችም ቢጭኑበትም በ300 ዓመታት ፅናትና ትዕግስት መስቀሉን ከመገኘት ጠማማውን ድንጋይ ከመሰበር አላዳነውም ነበር ። ዛሬ ላይም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የተዘረጋውን የውሸት ክምር ለመናድ ፣ የዘር ትብታብ ለመበጣጠስ ፣ መንገድ የዘጉ ጠማማ ድንጋዮችን ለማስወገድ እና የተሰበሰቡ የክፋት ማህበርተኞችን ለመበተን ምንም እንኳን የ30 ዓመታት ስቃይና መከራን ቢፈጅም በ90 ክንድ ጥልቀት በ500 ክንድ ስፋት የቆሻሻ ክምር እና በጠማማ ድንጋዮች የተሸፈነው ግማደ መስቀል በተገኘ ጊዜ ከዓጥናፍ እስከ ዓጥናፍ የፈካው ትልቅ ብርሃን እንደተከሰተ ሁሉ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ታላቅ የተስፋና የብልጽግና ብርሃን መጣሁ እያለ ስለመሆኑ የሚያሻማ ጉዳይ አይደለም ።

ከሃዲዎች የመዳኛውን እና የእውነት መስቀሉን ለማድበስበስ ቀለንጢስ ከሚባል እንጨት የውሸት መስቀል ሰርተው ቢያስቀምጡም ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ሁሉ በጁንታዎች የተዘጋጁ የውሸት ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብኩም ሆነ አሸናፊነትን የሚያቀነቅኑ ድምፆችን በማስተጋባት ለሚያሰሙት የገደል ማሚቶ ለአንድ አፍታም እንኳን መዘናጋት የለብንም ።

ሊነጋ ሲል ይጨልማል እንዲሉ አሁን ያለንበት ወቅት ሃገራችን ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም በጠላቶቿ ክፉኛ እየተፈተነች ያለችበት የታሪክ መታጠፊያ ወቅት ነው ። የውስጥ ባንዳዎች ከኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ የራሳቸውን ሆድ ለመሙላት የቋመጡበት ፤ የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ደግሞ በኢትዮጵያ መበታተን ላይ ድንኳን ሰርተው የሰርግና ምላሻቸውን ካፓ ለብሰውና ደምቀው ለመታየት የተቅበዘበዙበት የቅዠት ወቅት ነው ።

ዳሩ ግን እውነትን ታግሎ ማሸነፍ ፤ ታሪክን በአጓጉል ቅዠት መቅበር ከቶም አይቻልምና አሸናፊነቷ ቀድሞ የተፃፈዋን የጀግኖች አገር ኢትዮጵያ ይፈትኗት ይሆናል እንጅ ይረቷት ዘንድ በፍፁም አይቻላቸውም ፤ ይነቀንቋት እንደሆነ እንጅ ሊጥሏት አቅም የላቸውም ።

የመስቀሉ መገኘት በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን በዓንድ መዓድ እንዳሰባሰበ ሁሉ የባንዳዎች እና የውጭ ተስፈኞች በኢትዮጵያ ላይ መነሳት ተዳፍኖ የኖረውን ኢትዮጵያ አንድነት በዳግም መግነጢሳዊ ሃይል እንዲገነፍል አድርጎታል ፤ ደብዝዞ የነበረውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቋ ከፍ ብሎ በኩራት እንዲውለበለብ አስችሎታል ፤ በወንዝና ሸንተረር የታጠረውን ህዝቧን በአንድ ቅላፄ እንዲያዜሙ አስገድዷቸዋል ። ለዚህም ነው የዘረኞች ፣ ባንዳዎችና ከፋፋዮች ፀሀይ እየጠለቀች የኢትዮጵያዊያን ቀን እየመጣ ነው ብለን አንገታችንን ቀና አድርገን የምንናገረው ።

ውድ የምስራቅ ጎጃም ህዝቦች ሆይ በዓሉ የእውነት ፣ የአንድነት ፣ የመቻቻል ፣ የመተባበር ፣ የመተሳሰብ ፣ የማሸነፍ ፣ የአልበገርም ባይነት ፣ የፅናት እና የድል ምልክት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ስለ ውዷ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ሲሉ በየጦር ግምባሩ እየተዋደቁ ያሉ ጀግኖችን ፤ በውሸት ባለሟሎች የጭካኔ በትር ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ፤ በአመፀኞች የፈረሱ ተቋማትን ፤ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አረጋዊያንን እና አላሳዳጊ የቀሩ እምቦቀቅላ ህፃናትን በማሰብ እንዲሆን አደራ እያልኩ የህዝባችን የደስታ ቀን ለሴረኞች ደስታ አይሰጥምና በሁሉም አካባቢ ፀጉረ ልውጦችንና ሰርጎ ገቦችን በአራት አይና እይታ መቃኘት ያለባችሁ መሆኑን እያሳሰብኩ በድጋሜ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ ፤ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ ።

አቶ አስቻለ አላምሬ

የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ

24/09/2021

Address

D. Markos
Bahir Dar

Telephone

0581785115

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ/East gojjame zone pp women league posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share