Bahir Dar Customs Branch - ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ

Bahir Dar Customs Branch - ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ year of excellence!

29/05/2026
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡ግንቦት 11/2018ዓ.ምበጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት በጎንደር ከተማ ከአጋርና ባለድርሻ አካል የሆኑ አመ...
20/05/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

ግንቦት 11/2018ዓ.ም

በጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት በጎንደር ከተማ ከአጋርና ባለድርሻ አካል የሆኑ አመራርና የፀጥታ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ከማዕከላዊ ጎንደር አስተዳደር ዞን ፣ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ፣ ከታች አርማጭሆ ወረዳ አስተዳደር፣ ከላይ አርማጭሆ ወረዳ አስተዳደር፣ ከጠቅላይ አቃቢ ህግ ጎንደር ቅርንጫፍ፣ ከፌደራል ፖሊስ ሬጅመንት 10 እና ከመረጃና ደህንነት የተውጣጡ የአመራር እና የጸጥታ አካላት እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት የተሳተፉ ሲሆን መድረኩን የቅ/ጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ አባቡ ፀጋ የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የውይይት መድረኩን ከፍተዋል።
በመቀጠል የውይይቱ መነሻ ጽሁፍ በቅ/ጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ አባቡ ፀጋ ቀርቦ ውይይቱን አቶ አየልኝ ደሳለኝ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ፣ አቶ አንተነህ ታደሰ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ እና አቶ አባቡ ፀጋ የቅ/ጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ያወያዩ ሲሆን ከውይይቱ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች በሚመለከታቸው ተሳታፊዎችና አወያዮች ምላሽ ተሰጥቷል። በውይይቱም በትኩረትና በስፋት የተነሱ ሀሳቦች ፌ/ፖሊስ ወደ ጣቢያዎች አለመግባቱና ለቁጥጥር ስራው ውስንነት መታየቱ፣ የአሰራር ብልሹነትና የስነ ምግባር ችግሮች መታየታቸው፣ በአቋራጭ መበልፀግና ለህገ ወጥ ተግባራት ያለው የተባባሪነት ፍላጎት፣ የኮንትሮባንድ እቃን ይዞ ለጉምሩክ አለማስረከብ እና በራስ መሸጥ፣የይለፍ ወረቀት መስጠትና ሽፋን መሆን፣ የጠ/አቃቢ ህግና ፌ/ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተደራሽነት ችግር፣ የሁመራ ቀጠና ከጉምሩክ ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ተጋላጭነታችን መስፋቱ፣ የኮንትሮባንድ እቃ እና የጦር መሳሪያ ጉዳይ፣ የቅንጅት ስራዎች ማነስ፣ የህግና አሠራር ጥሰቶች እና ብልሽቶች መኖር እና ሌሎች ሀሳቦች በስፋት ተነስተዋል።

በመጨረሻም በመድረኩ ለተነሱ ሀሳቦች በመድረክ መሪዎች ምላሽና ቀጣይ የማስተካከያ አቅጣጫዎች ከተሰጡ በሗላ አቶ አባቡ ፀጋ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰሩ የሚገባቸው ስራዎች በቅንጅትና በአጋርነት መስራት፣ የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮችን በጋራ መስራት፣ ለታችኛው መዋቅር በክልሉ የቅንጅት ደረጃ በማድረስ ትኩረትን ማሳደግ ፣ አሰራሮችና ህጎች እንዲከበሩ ተገቢ ድጋፍ ማድረግ፣ ጥናትን በማጠናከር የተቀናጀ እርምጃ መውሰድ፣ ኢ-ስነ ምግባራዊ ድርጊትን እና ሌብነትን በጋራና በተናጠል መከላከል፣ ተጠርጣሪዎችን አስተማሪና ተቀራራቢ የጥፋተኝነት ውሳኔ በመስጠት አጥፊዎች ከጥፋታቸው እንዲማሩ የምርመራ ጥራትን ማረጋገጥ፣ የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዙ የተያዙ ተሸከርካሪዎችን ወዲያውኑ ለጉምሩክ ማስረከብ እና ለውሳኔ ግልፅ የሆነ ማስረጃ መላክ፣ የኬላ ፍተሻ ስራዎችን ማጠናከር፣ የኬላ ስራ በማይኖርበት ሰዓት የሚመጣ ተሸከርካሪ ጠብቆና ተፈትሾ እንዲያልፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት ለነበረው አመርቂ አፈፃፀም ምስጋና አቅርበው በቀጣይ ሁሉም አመራር ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ላይ በትኩረትና በቅንጅት ከመስራት ባሻገር ህግን ተከትሎ መስራት ይገባል የሚል መልዕክት አስተላልፈው መድረኩን ዘግተዋል፡፡

"ተቋምን በልህቀት ገቢን በስኬት!"
ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

12/05/2026
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄደ፡፡ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ቡድን ባዘጋጀው በየሩብ ዓመቱ ...
07/05/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም

የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ቡድን ባዘጋጀው በየሩብ ዓመቱ የሚካሄደዉን የደም ልገሳ ፕሮግራም አስመልክቶ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮችና ፈጻሚዎች ደም ለሰዉ ልጅ በህይወት ለመኖር እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ እና ደም መስጠት ለጤናም ጥሩ መሆኑን በመረዳት እንዲሁም ሆስፒታል ገብተዉ በደም እጦት ምክንያት የሚሰቃዩ ወገኖቻችን "ኑ! በደም እጦት ምክንያት የሚሞቱ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ እናትና አባቶቻችንን እንታደጋቸው" በሚል መሪ ቃል የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮችና ፈጻሚዎች ደም ለግሰዋል፡፡

"ተቋምን በልህቀት ገቢን በስኬት!"
ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር
ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et.
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/...

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የዉይይት መድረክ አካሄደሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ባህር ዳር- ኢትዮጵያ የገበያ አረጋጊ፣ ህገ ወጥ ንግድ እና ፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ግብረ ...
06/05/2026

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የዉይይት መድረክ አካሄደ

ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ባህር ዳር- ኢትዮጵያ

የገበያ አረጋጊ፣ ህገ ወጥ ንግድ እና ፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ግብረ ሃይል የወንጀል ጉዳዮች ክትትል የቴክኒክ ኮሚቴ የ 9 ወር አፈፃፀም ግምገማ ዉይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩን የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም የከፈቱ ሲሆን የዉይይት መነሻ ጽሁፉን የኮንትሮባንድ ፣ ንግድ ማጭበርበር እና ህገ-ወጥ ንግድ ነባራዊ ሁኔታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ አባቡ ፀጋ አቅርበዉ መድረኩን በመሩት የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም፣ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታዉ (ዶ/ር) እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው አማካኝነት ዉይይት ተደርጓል፡፡

በመድረኩ ለተነሱ ሃሳቦች በቤቱና በመድረክ መሪዎች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ በመሆኑ ለዉጥ መምጣቱ ተመላክቷል በመጨረሻም በ9 ወሩ የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ድክመቶችን ማስተካከል እንደሚገባ በማሳሰብ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

"ተቋምን በልህቀት ገቢን በስኬት!"
ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!!
ከደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ባህር ዳር

ጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤትን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/BahirDarCustomsBranch
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et.
በቴሌግራም፦ https://t.me/BahirDarCustoms
በኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/invites/contact/...

04/05/2026
https://www.facebook.com/share/1Mei5gNWeY/
01/05/2026

https://www.facebook.com/share/1Mei5gNWeY/

የዩኒቨርሲቲያችን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የPhD ዲግሪያቸውን አጠናቀቁ

አርብ፣ ሚያዚያ 23 2018 ዓ.ም፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
***********************************************************************************************************************

የዩኒቨርሲቲያችን ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በማጠናቀቅ ለምርቃት በቅተዋል።

የመመረቂያ ጽሑፋቸው "Modernizing Ethiopian Customs: A Qualitative Analysis of Organizational Efficiency, Digital Transformation, Human Capital Development and Stakeholder Collaboration on Trade Facilitation and Economic Growth" በሚል ርዕስ ላይ አተኩሯል።

በቢዝነስ አስተዳደር የትምህርት መስክ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በኪይ ዊስት ዩኒቨርሲቲ ሲከታተሉ የቆዩት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ፤ ትምህርቶን አጠናቀው በመመረቆ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማኔጀመንት እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሰማውን ልባዊ መልካም ምኞት ይገልጻል።

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶክተር) እንኳን ደስ አሎት! እንኳን ለዚህ ስኬት አበቃዎት!

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ከሁለት ወር በፊት የአፍሪካ አመራር አካዳሚ በአመራር ዘመናቸው ላስመዘገቡት የላቀ ስኬት የአፍሪካ የዓመቱ ስኬቴማ ሰው በሚል እውቅና እና ሽልማት መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) በድጋሚ እንኳን ደስ አሎት!

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!

ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

Www.wku.edu.et

_______________________/////////////////////////////////////////___________________________
_______________________/////////////////////////////////////////___________________________

The Chairperson of our University's Governing Board completed his Ph.D. Degree

Friday, May 01/ 2026 (Wolkite University)
***********************************************************************************************************************

Debele Kabeta (Dr), Chairperson of our University's Governing Board and Commissioner of the Customs Commission, completed his (PHD) Degree.

Commissioner Debele Kabeta (Dr) completed a PHD degree from Key West University in the field of Business Administration.

His PHD Research Title is on: "Modernizing Ethiopian Customs: A Qualitative Analysis of Organizational Efficiency, Digital Transformation, Human Capital Development and Stakeholder Collaboration on Trade Facilitation and Economic Growth"

Wolkite University Management and the University Community would like to say Congratulations.

Commissioner Debele Kabeta (D/r) Congratulations!

It is notable that two months ago Commissioner Debele Kabeta (Dr) recognized and awarded as African Leadership Person of the year by African Leadership Organization for the Outstanding Achievements in his Leadership accomplishments.

Commissioner Debele Kabeta (Dr) Congratulations on your Remarkable Achievement!

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International Relation!

To know more about us, please visit our website!

www.wku.edu.et

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bahir Dar Customs Branch - ባሕር ዳር ጉምሩክ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share