20/12/2023
የሀዘን መግለጫ
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳
የቅርንጫፋችን የስራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሆሴ ጌቴ ከሰኔ 6 ቀን 2006 ዓ.ም እስከ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የመጋዘን ሀላፊ በመሆን እዲሁም ከሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ህይወታቸው ህልፈት ድረስ የመድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ስርጭት ባለሙያ በመሆን በአዳማ ቅርንጫፍ አዳማ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ አቶ ሆሴ ጌቴ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዳማ ሆስፒታል እና ሜዲካል ኮሌጅ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናቱን እንመኛለን።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዳማ ቅርንጫፍ