30/04/2025
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም መሠረት ለአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ የተሠጡ ተግባርና ኃላፊነት
1. የክልላዊ መንግሥቱን ረቂቅ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከአቻ የፌደራል መንግሥት ማዕቀፎች ጋር በማገናዘብና በማስተሳሰር ይነድፋል፣ ያበለጽጋል፣ ያስጸድቃል፤
2. የኢኮኖሚና የልማት ፖሊሲ ትንተናና ጥናቶችን ያካዳል፣ ስትራቴጅካዊ የሶሾ-ኢኮኖሚ ጉዳዮችን ይለያል፣ በትንተናና ጥናቶች በሚገኙ ውጤቶች መሠረት የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያካሒዳል፤
3. የክልሉን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶችን ለማዘጋጀት የሚረዱ የኢኮኖሚ ጥናትና ምርምሮችን ያካሂዳል፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ መለኪያዎችንና መመዘኛዎችን ያዘጋጃል
4. በሀገሪቱ የልማት ስትራቴጂዎች ላይ የተመሠረተና በክልሉ መንግሥት የሚፈጸም የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
5. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የክልሉን ሕዝብ ፍትሐዊ የመልማትና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
6. ለክልሉ መንግሥት አካላት በተለይም ለክልሉ ከፍተኛ አስፈጻሚና አስተዳደራዊ አካል የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ዝግጅት፣ ክትትል፣ አተገባበርና ግምገማ ማዕከል ሆኖ ይሠራል፤
7. የብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተቋማትን የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅዶችን አተገባበር፣ ውጤታማነትና ጥረት በላቀ ሙያዊ ኃላፊነትና በሀቀኝነት ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ለዚህም ያመቸው ዘንድ በስትራቴጅካዊ የትኩረት መሥኮች ከፋፍሎ የየዘርፉን ዕቅዶችና ሪፖርቶች ይቀበላል፣ ለበላይ አመራሩ የሚቀርበውን የተጠቃለለ ሪፖርት ያዘጋጅል፤
8. በክትትልና በግምገማው የተገኙትን ውጤቶች በጥልቀት በመመርመርና በመተንተን ከተገማች እንድምታዎቻቸው ጋር ለበላይ አመራሩ እናአግባብ ላላቸው ፈጻሚ አካላት በወቅቱ ያስተላልፋል፤
9. የእርስ በርስ ግንኙነቶችን በማጠናከር በክልሉ ውስጥ የተደራጁትን ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ተቋማት፣ የግል ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሰፊው የሚያሳትፉበት ተጠያቂነትን ያሰፈነ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት ይዘርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተል፤
10. የክትትልና ግምገማ ሥርዓቱን ለማስተዋወቅና በክልሉ መንግሥታዊ ተቋማት ዘንድ ለማስረፅ የሚያግዙ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ያከናውናል፣ ሥርዓቱን በማላመድና በማስተግበር ረገድ የየደረጃው ፈጻሚ አካላት ክህሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚገነባበትን ስልት ይቀይሳል፤
11. የልማት ዕቅድን ለማሳካት እንዲሁም የመንግሥትን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከርና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አቅም እንዲፈጠር የሥርዓት ማሻሻያ ጥናት ያካሂዳል፣ በጥናቱ ላይ ተመሥርቶ የተቋማትን አደረጃጀት በተመለከተ የውሳኔ ሐሳብ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
12. በመንግሥት በጀት፣ በመንግሥት ዋስትና ብድር እንዲሁም በሌሎች ተመሳሳይ የበጀት ምንጮች እንዲከናወኑ የታቀዱ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የአዋጭነትና አስፈላጊነት ግምገማ በማከናወን ወጤቱን ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
13. የልማት ፕላን ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች አዘገጃጀት ሥርዓት በመዘርጋት በሥራ ላይ እዲውል ያደርጋል፣ የቴክኒካል ምክር አገልግሎትና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል፤
14. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት አካላት ጋር በመመካከር በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶች ውስጥ ሊንፀባረቁ የሚገባቸውና በክልሉ መንግሥት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች እንዲጠኑና እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ይገመግማል፤
15. በክልሉ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የልማት ዕቅዶችን ለማሳካት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ሪፖርት ያዘጋጃል፤
16. አለም ዓቀፍና ሀገራዊ የስታትስቲክስና የጅኦ ስፓሻል መረጃ ስታንዳርዶችን መሠረት በማድረግ መረጃዎች በክልሉ እንዲሰበሰቡ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ይከታተላል፣ ያሰፈጽማል፤
17. የክልሉን የተፈጥሮ ሀብት፣ የጂኦ-ስፓሻል፣ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የምርት፣ የአገልግሎትና የመሳሰሉትን መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ለሚመለከታቸው ያስተላልፋል፤
18. ለክልሉ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ፋይዳ ያላቸው የቅየሳ፣ የካርታና የጂኦግራፊ ጥናት ሥራዎችን ያከናውናል፣ እንዲከናወን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤
19. የተቋማትን የመረጃ የመሰብሰብ ተግባራት ይቆጣጠራል፣ የአሠራር ስታንዳርድ እና የናሙና ዘዴዎችን ያጸድቃል፣ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ይሰጣል፤ 2
20. በክልሉ ውስጥ በወሰን ተለይተው ለሚቋቋሙ የከተማና የገጠር አስተዳደራዊ እርከኖች የአስተዳደር ወሰን ይሠራል፣ መለያ ኮዶችን በመስጠት የካርታ ሥራ ይሠራል፣ የሥነ ሕዝብ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎችም ያሰራጫል፤ ያደራጃል፣
21. በክልሉ ውስጥ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጃዎችን ያመነጫል፣ ለተጠቃሚዎችም ያሰራጫል፤
22. የሥነ-ሕዝብ ጉዳዩችን አስመልክቶ ጥናትና ምርምር ያካሒዳል፣ መረጃዎችን ያደራጃል፣ ለተጠቃሚዎችም ያሰራጫል፤
23. መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በብሔራዊው የሥነ-ሕዝብ ፖሊሲ አፈጻጸም ረገድ የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ከነዚሁ አካላት ጋር በመቀናጀት ይሠራል፤
24. በክልሉ መንግሥት አካላት እየተዘጋጁ የሚቀርቡትን የመደበኛና የካፒታል በጀት ጥያቄዎች ከክልሉ የልማት እቅድ ጋር ተገናዝበው እዲዘጋጁና ፍትሐዊ የሆነ የበጀት ቀመር እንዲኖር የሚያስችል መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ከአስተያየት ጋር ለገንዘብ ቢሮ ያስተላልፋል፤
25. ከሀገር ውስጥና ከውጭ በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ሆነ በበይነ መንግሥታት የሚቀርቡ የልማት ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ከክልሉ የልማት እቅድ ጋር ተመጋጋቢ እዲሆኑ ያደርጋል፤ እንዲሁም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን በመሰብሰብ ከአጠቃላይ የክልሉ ሪፖርት ጋር በማገናዘብ ጥቅል ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
26. የአየር ንብረት ለውጥን የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ ይከታተላል፡፡
Website:-http://anrsbopd.gov.et
Telegram:-https://t.me/planpdb2014
Facebook:-https://www.facebook.com/ANRSPADB
YouTube channel: - https://www.youtube.com/-2014
Instagram :- https://www.instagram.com/plan_and_development_bureau/
x-account:- https://x.com/logout
tiktok:- https://www.tiktok.com/?lang=en-GB
gmail address:- [email protected]
Welcome to the official website of the Amhara National Regional State Plan and Development Bureau! The Plan and Development Bureau plays a major role in drafting and enriching the regional state’s draft policies and strategies, conducting economic studies and research to help prepare development...