ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office

ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ  ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office, Government Organization, Bahir Dar.

25/03/2026
የወጪ ማስረጃ ውድቅ ሲደረግ ተቀናሽ ስለሚደረግ ወጪ  የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ማንኛውም ግብር ከፋይ ያቀረበው የወጪ ማስረጃ በታክስ ባለስልጣኑ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምክንያት ውድቅ ሲደረግ የ...
25/03/2026

የወጪ ማስረጃ ውድቅ ሲደረግ ተቀናሽ ስለሚደረግ ወጪ

የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ማንኛውም ግብር ከፋይ ያቀረበው የወጪ ማስረጃ በታክስ ባለስልጣኑ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምክንያት ውድቅ ሲደረግ የሚከተሉት ሁኔታዎች ከተሟሉ ወጪው በከፊል ይያዝለታል፡-

👉 ወጪው ገቢን ለማመንጨት የወጣ ከሆነ
👉 ወጪው የድርጅቱን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ከሆነ
👉 ለድርጅቱ ህልውና ወይም ዋስትና ለመስጠት የወጣ ከሆነ

የሚፈቀደው የወጪ መጠን (የመቶኛ ቀመር)

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጪ ማስረጃውን ውድቅ ቢያደርገውም፣ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ከተረጋገጡ በገበያ ዋጋ ተሰልቶ ከታች ባለው መጣኔ መሰረት ወጪው ይያዝለታል፡-

👉 ለቋሚ ንብረት የገበያ ዋጋው ——— 70%
👉 ለሌሎች ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች የገበያ ዋጋው ——— 65%

ወጪው ሙሉ በሙሉ ውድቅ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች

👉ወጪው ለድርጅቱ ስራ አስፈላጊ መሆኑ ካልተረጋገጠ።
👉የሀሰት ደረሰኝ (Illegal Receipt)፤ ምንም አይነት የንግድ ልውውጥ ሳይኖር የተቆረጠ ደረሰኝ ከሆነ።
👉 ህገ-ወጥ ደረሰኝ፤ በህግ እውቅና ከሌለው አካል የተገኘ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ከሆነ።

ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ •  በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤ •  የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ፤ •  ...
25/03/2026

ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ

• በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤
• የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ፤
• መንግሥት ባጸደቃቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና ኮንቬንሽኖች መሠረት ሰነዶች ነጻ ሊደረጉ ይችላሉ፤
• ተመሳሳይ መብት የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ገንዘብ ሚኒስቴር ኢምባሲዎችን፣ ቆንስላዎችን እና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችን ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ሊያደርጋቸው ይችላል፤

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/FUukO

ቀን29/06/2018ዓ/ምየባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በገቢ ግብር አዋጆች፣ደንቦች እና ሰራሮች እንዲሁም ህገ-ወጥነትን በመከላከል ወረዳችን የሚያመነጨውን ኢኮኖሚ እንዴት እንሰብስብ...
09/03/2026

ቀን29/06/2018ዓ/ም
የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በገቢ ግብር አዋጆች፣ደንቦች እና ሰራሮች እንዲሁም ህገ-ወጥነትን በመከላከል ወረዳችን የሚያመነጨውን ኢኮኖሚ እንዴት እንሰብስብ በሚሉና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከንግዱ ማህበረሰብ እና ከአጋር አካላት ጋ ር ውይይ እና ምክክር አካሄደ።
የገቢ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ እንዳለ አይነቱ አያይዘውም ግብር መሰብሰብ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚሰጥ ተግባር ባለመሆኑ የንግዱ ማህበረሰብም ሆነ አጋር አካላት ትኩረት ሰጥተን በመረባረብ በእቅድ ዘመኑ መሰብሰብ ያለብንን የገቢ እቅድ በመሰብሰብ የማህበረሰቡን የልማት ፍላጎት ማርካት፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን በመገንባት ተደራስነትን ማስፋት እና ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።
በማያያዝም የገቢ ተቋሙ እና አጋር አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ ትስስርን በማጠናከር ህገ-ወጥነትን መከላከል፣ግብርን በወቅቱ መክፈል የሚችል የንግድ ማህበረሰብ መፍጠር፣ታክስ ማጭበርበርንና ስዎራን የሚጠላ የንግድ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የሀገራችን ሰላም የሚረጋገጠው እና ነግዶ ማትረፍና ውሎ መግባት የሚቻለው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ሰላምን ለማረጋገጥ ደግሞ ከታክስ ማጭበርበርና ስወራ ወጥተን የሚጠበቅብንን ግብር/ታክስ ስንከፍል እንደሆነ ሃላፊው አጽእኖት ሰጥተው ገልጸዋል።
ግብር ከፋዮችም የገቢ ተቋሙ ከአሁን በፊት ሲያደርገው ከነበረው በበለጠ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ በማተኮር ተገልጋዩን ማህበረሰብ ማገልገል እንዳለበት በመግለጽ የገቢ ተቋሙ እና የንግዱ ማህበረሰብ ለሃገራችን የቀጣይ የማደግና የመበልጸግ ራዕይ በሰራ እና በስራ ብቻ የተመሰረተ የመገናኛ ድልድይ በመገንባት አገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ በማሳደግተደራሽነትን መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት እና ሌት ተቀን ሳንታክት በመስራት ወረዳው የሚያመነጨውን ኢኮኖሚ መሰብሰብ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

05/12/2025

ተቋምን በማዘመን ሙስናን መከላከል
ማንኛውም ተቋም ሲመሰረት ሊያሳካ የሚጠበቅበት ግብና ዓላማዎች ይኖሩታል። በመሆኑም የጠራ ራዕይ እና ተልዕኮ ቀርጾና በረጅም ፣በመካከለኛና በአጭር ጊዜ የሚፈፅማቸውን ከግቦቹና ዓላማዎቹ የተቀዱ ተግባራትን ያካተተ እድቅ ይኖሩታል። በዚህ አጭር ጹህፍ ግን ትኩረት የምናደርገው የመንግስትና የህዝባዊ ድርጅቶች ተቋማትን ብቻ ይሆናል።
ተቋማት ወርቃማ ግቦችንና ዓላማዎችን ይቀርፁና ጥርት ያለ ርዕይ እንዲሁም የማያሻማና አስጎምጅ ተልዕኮ ቢያዘጋጁ የአገልግሎት አሰጣጣቸው ቀርፋፋና ኋላቀር፣ ተቋማቱም ለስራ የማያመቹ ከሆኑ ውጤታቸው ከባዶው የሚዝል አይሆንም። ተቋማት ዘመኑን የዋጀ፣ዓላማዊና ሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎችን ያገናዘበ እንዲሁም ሀገራዊና ባህላዊ እሴቶችን ከግምት ያስገባ እንዲሆን ይጠበቃል።
የተቋማት መዘመንን በተመለከተ በዋናነት በሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን።ይኸውም ተቋማዊ የስራ አመችነት እና የአገልግሎት አሰጣጡን ማለት ነው።አንድ ተቋም ለሰራተኞቹ በሚያመች መልኩ የተገነባና በፅዱ አካባቢ የተከበበ መሆን ይኖርበታል። የስራ ቦታ አመችነት የቢሮዎቹ አወቃቀር፣ የክፍሎቹ ለሰራተኞች አመችነትን እንዲሁም የመገልገያ እቃዎች መሟላትንና መዘመንን ያጠቃልላል። ዘመኑን የሚዋጅ የመገልገያ መሳሪያዎች፣የክፍሎቹ የብርሃን ሁኔታ እና የአየር ተደራሽነት በዚህ ክፍል የሚካተቱ ጉዳዮች ናቸው። ውብ አካባቢና ቢሮ፣አመቺ መቀመጫዎችና የእቃ ማስቀመጫዎች ያልተጨናነቀ፣ የማይከብድና ቀለል ያለ የስራ ክፍል ከምቹ የስራ አካባቢ የሚመደቡ ጉዳዮች ናቸው።
በሌላ በኩል የአንድ ተቋም የአገልግሎት አሰጣጥ መዘመንና አለመዘመን ጉዳይ ነው።የተቋማት የስራ አመቺነት፣የአመራሩና አጠቃላይ የተቋሙ የአሰራር ስርዓት ዘመናዊነት እንዲሁም የሰራተኞች የእርስ በዕርስ ግንኙነት ጤነኝነት መጠበቅም በዚህ የሚካተቱ ነጥቦች ናቸው። ሰራተኞች ሲወጡም ሲገቡም ሲሰሩም ደስ ብሏቸው ስራቸውን እንዲያከናውኑ አመቺና የማይጎረብጥ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት አለበት።የተቋሙ ቢሮክራሲያዊ አወቃቀርና የአሰራር ስርዓት መዘመን ለቀልጣፋና ጥራት ላለው አገልግሎት አሰጣጥ የራሱ አስተዋጽኦ አለው።
እንደሚታወቀው አገልግሎት የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዓላማ ተኮር ተግባር ነው።አገልግሎት በመጠን ፣በወጭ፣በጥራት እና በተገልጋይ እርካታ ይለካል። በአጠቃላይ አገልግሎት በተቀባዩ ዘንድ ፋይዳ ያለው እሴት የሚጨምር ሊሆን ይገባል።በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚሰጠው አገልግሎት አምስት ዋና ዋና ባህሪያት አሉት እነርሱም የማይጨበጡ እና የማይታዩ (intangible) መሆኑ ፣የማይነጣጠል (ሰጭ እና ተቀባይ) /Inseparable/ መሆኑ ፣ተለዋዋጭ (ጊዜን የሚዋጅ) /variable/ መሆኑ፣ ለብልሽት /ለብክነት ተጋላጭ መሆኑ /perishable/ (ይቆየኝ ተብሎ የሚቀመጥ አለመሆኑ) እና የተገልጋይን ተሳትፎ የሚጠይቅ /customer participation/ መሆኑ ናቸው።ስለሆነም ማንኛውም አገልግሎት እነዚህን መሰረታዊ ባህርያቱ ሳይፋለሱ መከወን አለበት።
በአንድ ተቋም ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ከአመራሩ እስከ ምንዝሩ በሙያዊ ስነ-ምግባራቸው የታነፁ በምግባራቸው የላቁ እንዲሆኑ ይጠበቃል።የቅርብ ጊዜ ሀገራዊ ጥናቶች እንደሚገልፁት ለሙስና እና ብልሹ አሰራሮች መንስኤዎች በዋናነት የስነ-ምግባር ዝቅጠት እና በአቋራጭ የመበልፀግ የላቀ ፍላጎት ቢሆኑም የሚከተሉት ከኋላቀር አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችም አሉበት።
ይኸውም በየተቋማቱ ህዝብና መንግስትን ለማገልገል በግልፅ የተቀመጡ አሰራሮች መሸርሸር ወይንም ይስሙላ ተቋማዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አንዳንድ ተገልጋዮች ቅድሚያ ለመስተናገድ ወይንም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የተቋም መሪዎቸን፣የስራ ኃላፊዎችን እና ሰራተኞችን በጥቅም መደለል፣የተቋማት የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ጠንካራ አለመሆን፣የተወሰኑ የስራ ኃላፊችና ባለሙያች የስነ-ምግባር ችግር መኖር፣ህግና አሰራርን በጣሰ መልኩ ውሳኔ መስጠት እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በተቋማት ሙስና እንዲንሰራፋ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ። ሀገራዊ ጥናቶቹ ጨምረው እንዲሚገልጹት በሀገር ደረጃ በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች በቀጥታ ከተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ጋር መያያዛቸውን ነው።ከእነዚህ የሙስና ወንጀሎች መካከልም፣ስልጣንን አላግባብ መገልገል፣ጉቦ መቀበል ወይም መስጠት፣ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት እና መገለገል፣የመንግስትን ወይም የህዝባዊ ድርጅትን ስራ በማያመች ሁኔታ መምራት የስራ ሚስጢር ማባከን፣ ከባድ የስነ-ምግባር ጥሰት መፈፀም፣ከባድ እምነት ማጉደል ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራት፣ወዘተ ተዘርዝረዋል። በመሆኑም እነዚህንና መሰል የሙስና ወንጀሎችን ለመከላከል የተቋማትን አሰራር ማዘመን በእጅጉ ወሳኝ ይሆናል። የተቋማት አሰራርን ማዘመን ሲባል በሁሉም ዘርፎችና ተቋማት ውስጥ ለሙስና ተጋላጭ ሆኑ የውስጥ አሰራር ስርዓቶችን በማስተካከል በተቋማት አሰራር ሂደት ግልፅነትንና የተጠያቂነትን ከማስፈን በተጨማሪ በቴክኖሎጅ /በድጅታል አሰራር መጠቀም ያካትታል። ማለትም የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ከዕጅ ንክኪ በማላቀቅ ዘመኑ የደረሰበትን የድጅታል አሰራር መጠቀም ሙስናን ለመከላከል ጠቀሜታው የሚተካ አይደለም።በሌላ በኩል ደግሞ በቅርቡ የተጀመረው የአንድ ማእከል (የመሶብ) አገልግሎት በማስፋፋት ጥቅም ላይ ማዋል ሌላው የሙስና መከላከያ ዘዴ መሆኑ ተረጋግጧል። ከነዚህ አገልግሎች የማዘመን ወሳኝ ተግባራትን በተጨማሪና ጎን ለጎን ተቋማት የማይጠቅሙና ለአገልግሎት አሰጣጥ የማያመቹ እንዲሁም ጊዜን የሚበሉ አወቃቀሮች በዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሁም ጊዜ ቆጣቢ በሆኑ አወቃቀር ማደራጀት ይገባል። በአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን ሂደት ሌላው መዘንጋት የሌለበት ተግባር ሰራተኞችን ከሙያቸው ብቃትና ሙያዊ ሥነ-ምግባራቸውን ማዳበርና ማዘመን በተጨማሪ ሁሉም ሰራተኞች በፀረ-ሙስና ትግሉ እንዲሳተፉ በታቀደ መልኩ የስልጠና እና የማነቃቂያ ሥልጠናዎች ሊሰጣቸው ግድ ይላል።
እንደ በርካታ ሀገሮች ተሞክሮ ከሆነም የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት ተቋማት ከፓርቲ ፖለቲካ እሳቤ ጸድተው በነፃነትና በገለልተኝነት ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበት ሥርዓትና አሰራር መፍጠር ለፀረ-ሙስና ትግሉ የላቀ አስተዋጽኦ አለው።
በመሆኑም ተቋምን ማዘመን ሲባል እነዚህን ሁሉ በቁርጠኝነት መተግበር ነው፣ለዚህም ነው ተቋምን በማዘመን ሙስናን መከላከል ይቻላል የሚባለው።
ተቋምን ማዘመን ሙስናን መከላከል
የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት
የግብር ት/ኮ/ዋና የስራ ሂደት
ህዳር//2018 ዓ/ም
ባህር ዳር

04/12/2025

በየደረጃው ለምትገኙ የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ግብር ከፋዮች፣
የታክስ ክፍያ ማራዘሚያ መመሪያ 29/2017ዓ/ም መሰረት የክፍያ ጊዜን ለማርዘም የተቀመጡ ማራዘሚያ ጊዚዎች በሚከፍሉት እዳ መጠንና በግብር ከፋይ ደረጃ የተወሰነ ነው፣
በዚህ መሰረት፣
1.የታክስ ስሌት ውሳኔ ማስታወቂያ የደረሰው የደረጃ ሀ በሁሉም የታክስ አይነቶች የሚፈለግበት ጠቅላላ ፍሬ ግብር ታክስ፣መቀጫ እና ወለድ እዳ፣
 ከ200,001 እስከ 500,000 ከሆነ እስከ 3 ወር
 ከ500,001 እስከ 1.5 ሚሊየን ከሆነ እስከ 6 ወር
 ከ1.51 ሚሊየን እስከ 3 ሚሊየን ከሆነ እስከ 8 ወር
 ከ3.1 እስከ 5 ሚሊየን ከሆነ እስከ 10 ወር
 ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ከሆነ እስከ 12 ወር
2.የታክስ ስሌት ውሳኔ ማስታወቂያ የደረሰው የደረጃ ለ በሁሉም የታክስ አይነቶች የሚፈለግበት ጠቅላላ ፍሬ ግብር ታክስ፣መቀጫ እና ወለድ እዳ፣
 ከ50,000 እስከ 125,000 ከሆነ እስከ 3 ወር
 ከ125,001 እስከ 750,000 ከሆነ እስከ 6ወር
 ከ750,001 እስከ 2,500,000 ከሆነ እስከ 8 ወር
 ከ2,500,001 እስከ 3,750,000 ከሆነ እስከ 10 ወር
 ከ3,750,000 ብር በላይ እስከ 12 ወር
 3.የታክስ ስሌት ውሳኔ ማስታወቂያ የደረሰው የደረጃ ሐ በሁሉም የታክስ አይነቶች የሚፈለግበት ጠቅላላ ፍሬ ግብር ታክስ፣መቀጫ እና ወለድ እዳ፣
 ከ2,500 እስከ 25,000 ከሆነ እስከ 3ወር
 ከ25,001 እስከ 50,000 ከሆነ እስከ 6ወር
 ከ50,001 እስከ 75,000 ከሆነ እስከ 8ወር
 ከ75,001 እስከ 100,000 ከሆነ 10ወር
 ከ100,001 ብር በላይ ከሆነ እስከ 12 ወር

21/11/2025

ቁጥር፡ባ/ዙ/ወ/ገቢ /5760/ 55/5
ቀን፡ 11/03/2018 ዓ/ም

የዜና መግለጫ፣

የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከ 89 ሚሊየን ብር በላይ ሰበሰበ፣
የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ2017/2018 የግብር ዘመን ከሶስቱ የገቢ አርእስቶች ማለትም ከንግድ፣ ከእርሻ እና ለልዩ ልዩ ገቢዎች ብር 260,675,822 ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሲሆን ከዓመቱ የገቢ እቅድ አኳያ እስከ ጥቅምት 30/2018 ድረስ ብር 89,721,089.40 በመሰብሰብ የእቅዱን 34.42% ያሳካ ሲሆን የአራት ወሩን የገቢ እቅድ አፈጻጸም ለይተን ስንመለከት ደግሞ ከሶስቱ የገብ አርእስቶች ብር 92,425,306 ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም ድረስ ብር 89,721,089.40 በመሰብሰብ የእቅዱን 97.07% ለማሳካት ተችሏል።
የተሰጠን የገቢ እቅድ እጅግ በጣም የተለጠጠ ቢሆንም አገራችን ፣ክልላችን፣ዞናችን እና ወረዳችን እያጋጠመው ያለውን የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ ገቢ መሰብሰብ ዋነኛ አማራጭ መንገድ መሆኑን በመገንዘብ ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከአጋር አካላት ጋር በጋር በመግባባትና የጋራ አቋም በመያዝ አንጻራዊ ሰላም በተፈጠረባቸው ቀበሌዎችና ቀጠናዎች ሙሉ አቅማችንን በመጠቀም መንቀሳቀስ በመቻላችን እና የወረዳ አመራሩ ፣አጋር አካላት እና የጸጥታ መዋቅሩ እያደረጉት ያለው ድጋፍና ክትትል የጎላ በመሆኑ ከአራት ወሩ የገቢ እቅድ አፈጻጸም አኳያ ሲታይ 97.07% ማሳካታችን ይበል የሚያሰኝ እና የስራ ተነሳሽነትን የበለጠ የሚያጠናክር ስለሆነ በቀጣይም ተደራሽ ያልሆንባቸውን ቀበሌዎችና ቀጠናዎችን በስልክና በተለያዩ አማራጮች በመቀስቀስና የአስተምህሮትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን አጠናክረን በመቀጠል እና በመስራት ግብር ከፋዩ የሚጠበቅበትን ግብር/ታክስ እንዲከፍል አጠናክረን የምንሰራ ሲሆን የወረዳ አመራሩ፣የጸጥታ መዋቅሩ፣በየደረጃው የምተገኙ ባለሙያዎች እና አጋር አካላት ላደረጋችሁልን ድጋፍ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ከሶስቱ የገቢ አርእስቶች የ4 ወሩ የገቢ እቅድ አፈጻጸም እስከ ጥቅምት 30/2018 ድረስ፣
ተ.ቁ የገቢ አርዕስት እቅድ ክንውን አፈፃፀም
1 ከንግድ 33,296,898 27,785,043.7 83.45%
2 ከዕርሻ 1,067,844 1,236,573 115.80%
3 ከልዩ ልዩ 58,060,564 60,699,472.7 104.54%
ድምር 92,425,306 89,721,089.4 97.07%

የግ/ት/ኮ/ዋ/የስ.ሂደት አስ/ባለሙያ

የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ23/02/2018 ዓ.ም ከነጋዴው ማህበረሰብ እና አጋር አካላት ጋር ስለ ገቢ አሰባሰብ እና በወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የውይይት እና የምክክር መ...
03/11/2025

የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ23/02/2018 ዓ.ም ከነጋዴው ማህበረሰብ እና አጋር አካላት ጋር ስለ ገቢ አሰባሰብ እና በወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የውይይት እና የምክክር መድረክ አካሄደ

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት/Bahir Dar Zuria Woreda revenue office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share