Z=Amhara ዘ አማራ

Z=Amhara ዘ አማራ ሰላም ፍቅርና ወንድማማችነት !!

ጽንፈኛዉ ቡድን ተሞክሮ የከሸፈዉን የትህነግ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በራሱ ህዝብ ላይ ሞክሮት እንደ እሳት ራት በገባበት ቀልጦ ቀርቷል።ከሰሞኑ ጽንፈኛው ቡድን መካነሰላም እና አካባቢዉ ፎቶ ተነስቶ...
04/10/2025

ጽንፈኛዉ ቡድን ተሞክሮ የከሸፈዉን የትህነግ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በራሱ ህዝብ ላይ ሞክሮት እንደ እሳት ራት በገባበት ቀልጦ ቀርቷል።

ከሰሞኑ ጽንፈኛው ቡድን መካነሰላም እና አካባቢዉ ፎቶ ተነስቶ ለቀጣሪዎቹ እና ለማህበራዊ ሚዲያ ክንፉ ለመላክ ሰተት ብሎ ገብቶ ነበር። እንደገባም በፍቅርና በአንድነት በሃይማኖት ሳይለያይ ሰዉነት ብቻ በሚያኖረው የወሎ ህዝብ መካከል የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት መስጅድ ዉስጥ ገብቶ አማኞች ላይ ተኩሶ ገድሏል።

ይሄን ድርጊቱን በመንግስት እና በሌሎች የሃይማኖት ተከታዮች እንደተደረገ ለማስመሰል ሞክሮ ከሽፎበታል።

ቡድኑም በቅርብ ወልድያ እና አካባቢዉ እንደሆነዉ ሁሉ የመካነ ሰላም ህዝብ በነቂስ ወጦ ባሉበት እየጠቆመ ከገቡበት ገብቶ አዉጥቷቸዋል። የመካነ ሰላም ምድርም እነሱ እንዳሰቡት ሳይሆን የረገጡት ሁሉ እንደ እሳት አቃጥሏቸዉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፉ ቀርተዋል። በህይወት የተረፉትም ለመንግሥት እጃቸዉን ሰጠዋል።

የመካነሰላም ህዝብም በማይመጣ መጣችሁ ብሎ በገቡበት እየገባ እያሳደዳቸዉ ነዉ።

እዉነት ተደብቆ አይቀርም!

በሀሰተኛ መረጃዎች የአማራን ህዝብ  ማደናገር አይቻልም !!!****በምዕራብ  ጎጃም ዞን በቋሪትና በደጋ ዳሞት ወረዳ ልዩ ልዩ ቦታዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንና ጥምር ሀይል አከርካሪው...
02/07/2025

በሀሰተኛ መረጃዎች የአማራን ህዝብ ማደናገር አይቻልም !!!
****
በምዕራብ ጎጃም ዞን በቋሪትና በደጋ ዳሞት ወረዳ ልዩ ልዩ ቦታዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንና ጥምር ሀይል አከርካሪውን የተመታው የትህነግና የሻቢያ ተላላኪዎች የተለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ማስተጋባት ጀምረዋል ።

በእርግጥ የአማራ ክልልን ህዝብ በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ማሳሳት አይቻልም ። ለዚህ ደግሞ የዚህ ሀይል መሠረታዊ ሁኔታ ከመላእክት መከካል እንደገባ ሰይጣን ከሆነ ከርሞበታል።

ፅንፈኛው የመከላከያ ሠራዊት ያወደመው የግለሰቦች ሞተር የሚለው የኬንያን የወደሙ ሞተሮች ነው

በእርግጥ መከላከያ ሠራዊታችንም የግለሰብ ሞተር ቀርቶ የማንንም አያወድምም እንጂ አውድሞስ ቢሆን ኖሮ ከሩጫና መሹለክለክ ውጭ መች አቅም ኖሮት ነው ምስልስ የሚይዘው ብለን ብንጠይቅ ሀቁን እናውቀዋለን።

የሀሰት ፎቶ እየተዋሳችሁ የእውነት ከምትወገሩ እጅ ስጡ። የአማራ ሕዝብ እንደሁ ለክቶ ተማሮ ተፀይፎ ተፍቷችኋል።

የጃማ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት 14 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ስራ መስራቱን ገለጸ።********የጃማ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በህብረተሠብ ተሳትፎና በወረዳው የካፒታል...
17/05/2025

የጃማ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት 14 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ስራ መስራቱን ገለጸ።
********
የጃማ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በህብረተሠብ ተሳትፎና በወረዳው የካፒታል በጀት 14 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ስራ መስራቱን ገልጿል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አስናቀ ፀጋው በወረዳው በተያዘ የካፒታል በጀትና የወረዳውን ህዝብ በማስተባበር በህብረተሠቡ ላይ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ሲነሳ የነበረ 14 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና ስራ መስራት መቻሉን ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም በወረዳው ካፒታል በጀት ከደጎሎ ሽላፋፍ ካለው መንገድ ላይ አራት ኪሎ ሜትር በ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የጥገና ስራ ሰርቶ በማጠናቀቅ ርክክብ ተደርጎ መንገዱ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በህብረተሠብ ተሳትፎ ከደጎሎ ቦረን ካለው መንገድ ላይ 10 ኪሎ ሜትር 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በጀት በመያዝ የጥገና ስራ እየተሠራ መሆኑን አቶ አስናቀ አብራርተዋል።

ከደጎሎ ቦረን ካለው መንገድ ላይ ከሚሠራው 10 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራ ውስጥ አምስት ኪሎ ሜትር የድችና የቦይ ጠረጋ እንድሁም አምስት ኪሎ ሜትር የጠጠር ማልበስ ስራ እየተሠራ መሆኑን አቶ አስናቀ ተናግረዋል።

ለመንድ ስራ ከህብረተሰብ ተሳትፎ 13 ሚሊዮን ብር ለመሠብሠብ ታቅዶ እስካሁን በተሠራው ስራ 7 ሚሊዮን ብር መሠብሠብ መቻሉን ኃላፊው ገልጸዋል።

እስካሁን የተሠሩ የመንገድ ጥገና ስራዎች የህዝቡን ችግር የፈቱ መሆናቸውን ኃላፊው ጠቁው በቀሪ ወራት ከቢለው አንዷቤት ያለውን መንገድ በህብረተሰብ ተሳትፎ የጥገና ስራ ይሰራል ብለዋል።

የጃማ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ለወጠኝ ጸጋው የወረዳው ህዝብ አንገብጋቢ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች መካከል መንገድ አንዱ ነው ብለዋል።

አብዛኞቹ ቀበሌዎች ከወረዳው ማዕከል ጋር በመንገድ የተሳሰሩ ቢሆንም ለብዙ ጊዜ አገልግሎት በመስጠታቸው ህብረተሠቡ የጥገና ስራ እንድሰራለት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እያቀረበ በመሆኑ ከነዚህ መካከል የበለጠ ችግር ያለባቸውን መንገዶች በመለየት ህብረተሰቡን በማስተባበርና በወረዳው የካፒታል በጀት የጥገና ስራ መሠራቱን አቶ ለወጠኝ አብራርተዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም በቀጣይ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠሩ ያሉ መንገዶችን በቅደም ተከተል በመለየት የወረዳውን ህዝብ በማስተባበርና ወረዳውም በጀት በመያዝ የሚሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የተሠራውን የመንገድ ጥገና ሥራ የደቡብ ዞን መንገድ መምሪያ ኃላፊ አቶ እብራሂም ሀሰን፣ የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱ መሀመድ፣ የጃማ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለወጠኝ ፀጋው፣ የጃማ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መጣለም አበበና ሌሎችም የወረዳው አመራሮች በመሥክ ተገኝተው ጎብኝተዋል።

ጃማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
https://t.me/anrsRoadBureau/151

የደብረብርሃን - ደነባ - ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር - ደነባ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ፕሮጀክት በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው*********በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ...
07/05/2025

የደብረብርሃን - ደነባ - ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር - ደነባ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ፕሮጀክት በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው
*********
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው 108.25 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ከደብረ ብርሃን - ደነባ - ለሚ መገንጠያ እና ከደነባ - እነዋሪ - ጅሁር እየተገነባ የሚገኘው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የአስፋልት ማልበስ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ።

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት መነሻውን ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ በማድረግ ለሚ መገንጠያ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን እንዲሁም ከጅሁር ከተማ በመነሳት መዳረሻውን ደነባ ከተማ ላይ ያደርጋል።

በእስካሁኑ የመንገድ ግንባታ ስራ የአስፋልት ንጣፍ፣ አፈር ቆረጣ እና ሙሌት ፣ የድሬኔጅ ስራዎች፣ ሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣ ቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ እንዲሁም የስትራክቸር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

ለግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውለውን ገንዘብ 3,613,766,908.69 (ሶስት ቢሊዮን ስድስት መቶ አስራ ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስምንት ብር ከ ስልሳ ዘጠኝ ሣንቲም) ብር የሚሸፈ ነው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን እያከናወነ የሚገኘው አገር በቀሉ ሰንሻይን የስራ ተቋራጭ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ኤቢኤም ኢንጂነርስ እና ንዑስ ኮንሰልታት ፕላስ ኮንሰልት ሃ/የተ/የግ/ማህበር በጋራ እያከናወኑ ይገኛሉ።

የመንገድ የግንባታ ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለአካባቢዉ ህብረተሰብም ሆነ ለመስመሩ ተጠቃሚዎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥን በማምጣት ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

በለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሚመረተውን ሲሚንቶ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ የግንባታ ኢንዱስትሪውን እድገት ከማፋጠኑም ባሻገር የዋጋ ግሽበትን ያረጋጋል።

በአካባቢው የሚገኙት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደ ገበያ ለማውጣት እና የኢንዱስትሪ ውጤቶችንም ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ ተደራሽ በማድረግ የገበያ ማረጋጋት ስራ ማከናወን ያስችላል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ የጎን ስፋት ትከሻን ጨምሮ በዞን ከ25.5 - 32.1 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር፣ በወረዳ 19.45 ሜትር ሲሆን በገጠር 11 ሜትር ነው።

መረጃው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ነው

ፕሮጀክትላንጨርስአንጀምርም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/share/1C4hcGQmsq/
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau

በጋዞ ወረዳ ከደረቅ ወንዝ ሶሎናጅ -ዋሮ ህዝብ ጥያቄ የነበረው የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ ተጀመረ።*********,በሰሜን ወሎ ዞን የጋዞ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ፅ/ቤት  ከወረዳው አስተ...
03/05/2025

በጋዞ ወረዳ ከደረቅ ወንዝ ሶሎናጅ -ዋሮ ህዝብ ጥያቄ የነበረው የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ ተጀመረ።
*********,
በሰሜን ወሎ ዞን የጋዞ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ፅ/ቤት ከወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት እና በወረደ ግብርና ፅ/ቤት ከCALM P4R በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን ከደረቅ ወንዝ ሶሎናጅ -ዋሮ 6 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ጥገና ስራን የወረዳው ስራ አስፈፃሚዎችና የወረዳው የካልም ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የማስጀመር ስራ ተሰርቷል።

በማሰጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃብቴ ካሳው እንደገለፁት መንገዱ ከተሰራ ረጅም ጊዜ በማስቆጠሩና በክረምትም ጭቃ እየሆነ ተሽከርካሪ እንደልብ ባለማስገባቱ የሚወልዱ እናቶችን በፍጥነት ወደ ጤና ጣቢያ ለማድረስ በማስቸገሩና አርሶ አደሩም በቀላሉ ወጥቶ ለመግባት መቸገሩን ተናግረው የወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት ካለው ውስን በጀት 2 ሚሊዮን 1 መቶ ሽህ ብር ቅድሚያ ለዚሁ ተግባር እንድመደብ በማደረግ እና ከካልም P4R 2 ሚሊዮን 370 ሽህ ብር በድምሩ 4 ሚሊዮን 470 ሽህ ብር ወጭ ሆኖ የመንገድ ጥገና ስራው መጀመሩን ገልፀዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ዝናቡ ገረመው በበኩላቸው ካለው ውስን በጀት መድቦ የህዝብ ጥያቄዎችን ምላሽ መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀው አንዱና ዋናው ተግባራችን በመሆኑ መንገዱም የአካባቢውን ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚፈታ በመሆኑ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንድጠናቀቅ ሁሉም የሚመለከተው አካል ርብርብ ማድረግ አለበት ብለዋል።

የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አስራት ሰጠ በበኩላቸው የካልም ፕሮጀክት የተፋሰሶችን ዘላቂነት በማረጋገጥ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን የህዝብ አንገብጋቢ የሆኑ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት እያገዘ መሆኑን ገልፀዋል።

የወረዳው መንገድና ትራንስፖርት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ደሴ አባይ በበኩላቸው መንገዱ የረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ ስለነበር ከወረዳው አስተዳደር ምክር ቤትና ከካልም በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ ማሽነሪ ገብቶ ስራ መጀመሩንና ስራውን ባለሙያ ተመድቦ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ፕሮጀክትላንጨርስአንጀምርም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/share/1C4hcGQmsq/
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok!

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኽምራ ብሔረሰብ  ዞን የመንገድ ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን ማስጀመሪያ ሥነሥርዓትና አሀዛዊ መረጃዎች !!!******1ኛ/ በፌዴራሉ  መንግስት አማካኝነት ከ5....
02/05/2025

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን የመንገድ ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን ማስጀመሪያ ሥነሥርዓትና አሀዛዊ መረጃዎች !!!
******
1ኛ/ በፌዴራሉ መንግስት አማካኝነት ከ5.1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል።

2ኛ/ በሁለት ዞኖች( በዋግኽምራ ብሔረሰብና በሰሜን ወሎ ዞን መካከል የሚገኙ ከሰባት በላይ የሚሆኑ ወረዳዎችን ያገናኛል ።

3ኛ/ 204 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመትን ይሸፍናል ።

4ኛ/ የመንገዱ ስፋት ከ10 እስከ 30 ሜትር ይሰፋል ።

5ኛ/ የግንባታው ወጭ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፍን ሲሆን ፕሮጀክቱ ሚያዝያ 2019 ዓ.ም ይጠናቀቃል ።

6ኛ/ በግንባታው ሂደት በሺህ ለሚቆጠሩ የአካባቢው ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጠራል ።

ፕሮጀክትላንጨርስአንጀምርም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/share/1C4hcGQmsq/
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok!

የመንገድ ግንባታው መጀመር በአካባቢው  ባለው ሀብት  የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት  ለማረጋገጥ  ብሎም ለሀገር ልማት  በተገቢዉ  መልኩ  ለማዋል ጠቀሜታዉ ከፍ ያለ ነዉ  ክቡር አረጋ  ከበደ  ...
02/05/2025

የመንገድ ግንባታው መጀመር በአካባቢው ባለው ሀብት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብሎም ለሀገር ልማት በተገቢዉ መልኩ ለማዋል ጠቀሜታዉ ከፍ ያለ ነዉ ክቡር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
*********
በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኘው የኮንትራት 1 የጋሸና - ቢልባላ እና የኮንትራት 2 ፡ የቢልባላ - ሰቆጣ የአስፋልት ኮንክሪት ቀሪ ሥራዎችን የማጠናቀቂያ ፕሮጀክት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መሐመድ አብዱራህማን ፣ የክልሉ የዞን እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአካባቢዉ ማህበረሰብ በእዉቀቱ፣ በባህሉ እና ባለዉ የተፈጥሮ ሀብት ለሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ነዉ። በመሆኑም አካባቢው ባለዉ ሀብት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብሎም ለሀገር ልማት በተገቢዉ መልኩ ለማዋል ዛሬ በይፋ ያስጀመርነዉ መንገድ ጠቀሜታዉ ከፍ ያለ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን በበኩላቸው መንገዶቹ ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ፋይዳ አንጻር ተጠናቀው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ይችሉ ዘንድ ፕሮጀክቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ግንባታው በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።

የፕሮጀክቶቹን ከፍተኛ ጠቀሜታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በተገቢው የጊዜና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

የኮንትራት 1 እና 2 ፕሮጀክት በአጠቃላይ 204.8 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍን ነው።

በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወን የተቻለ ሲሆን ፣በቀጣይም ያልተጠናቀቁ ስራዎች ማለትም የውሃ ማፋሰሻ ትቦዎች ፣ የሰቤዝ ፣ የቤስኮርስ እና የአስፋልት ስራዎችን በአፋጣኝ ለማጠናቀቅም እየተሰራ ይገኛል፡፡

የመንገዱን ግንባታ የአማራ ክልላዊ ብሄራዊ መንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ያከናውናሉ።

የኮንትራት 1 ፕሮጀክትን የማማከርና ቁጥጥሩን ሥራ ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድር ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚያካሂድ ሲሆን በተመሳሳይ የኮንትራት 2 ደግሞ ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ኃ/የ/የግ/ማህበር ከቤዛ ኢንጂነሪንግ ኬኒያ ሊሚትድ ጋር በጣምራ ያካሂዱታል፡፡

ለግንባታው የሚውለው 5,119,831,284 ( አምስት ቢሊዮን አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ብር የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ የላሊበላ ከተማን ፣ የላስታ ፣ የመቄትን እና የዋድላ ወረዳዎች እንዲሁም ፣ በዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን ጋዝጊብላና ሰቆጣ ወረዳን የሚያገናኝ ነው፡፡

በተጨማሪም በዓለም የቅርስ መዝገብ (UNESCO) ተመዝግቦ የሚገኘውና ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ያለበት የላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያኖች እና የተለያዩ አብያተ መዛግብት የሚገኙት በዚሁ የመንገድ ኮሪደር ውስጥ መሆኑ የመንገዱን አስፈላጊነት ከፍ ያደርገዋል፡፡

ፕሮጀክትላንጨርስአንጀምርም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/share/1C4hcGQmsq/
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok!

ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የተመድበለታልን  ከሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ  የአስፋልት ኮንኮሪት  መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ሥራ ተጀመረ። ******ርእሰ መሥ...
02/05/2025

ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የተመድበለታልን ከሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ የአስፋልት ኮንኮሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ሥራ ተጀመረ።
******
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጋሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ሥራን አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱረህማን፣ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኀላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የጋሸና- ላሊበላ- ብልባላ- ሰቆጣ የአስፋልት መንገድ የረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ ቆይቷል። ታሪካዊቷን እና የቱሪዝም መዳረሻ የኾነችውን ላሊበላን አቋርጦ የሚሄደው መንገዱ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

የቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ፕሮጄክቱ በሁለት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተመላክቷል። ለፕሮጄክቱ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል።

#ፕሮጀክት ላን ጨርስ አንጀምርም!

#ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61564040788841
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok!!

የመካነሰላም ከተማ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ  የአስፓልት ማንጠፍ ስራ ተጀመረ።*********የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር   ባለ 2 አካፋይ መንገድ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ የአስፓልት...
24/04/2025

የመካነሰላም ከተማ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ የአስፓልት ማንጠፍ ስራ ተጀመረ።
*********
የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ባለ 2 አካፋይ መንገድ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ የአስፓልት ማንጠፍ ስራ ተጀምሯል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክት ስራው በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በኮምቦልቻ ዲስትሪክት ጽ/ቤት አማካኝነት በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ለማድረግ የክልሉ መንግስት በትኩረት እየተሰራ ነው።

በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የፕሮጅክት ስራ መጀመር፣ አሁን ለደረሰበት መልካም አፈጻጸምና ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ የዞኑ አስተዳደር፣ የከተማ አስተዳደሩ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ፣ ክትትል እና ትብብር ከፍተኛ በመሆኑ ቀጣይም ይህንን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል።

ፕሮጀክትላንጨርስአንጀምርም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/share/1C4hcGQmsq/
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok!

የአብክመ መንገድ ቢሮ ኃላፊ ጋሻዉ አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) የአብክመ መንገድ ቢሮ ኃላፊ ትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት መልእክት******ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እና ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች...
19/04/2025

የአብክመ መንገድ ቢሮ ኃላፊ ጋሻዉ አወቀ ትኩዬ (ዶ/ር) የአብክመ መንገድ ቢሮ ኃላፊ ትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት መልእክት
******
ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እና ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልኩኝ መልካም ምኞቴን ስገልጽ ላቅ ያለ ኮራት ይሰማኛል።

የአብክመ መንገድ ቢሮ የያዛቸውን የመንገድና ተያያዥ መሰረተ ልማት ስራዎችን በውጤታማነት በመፈፀም ከተቋሙ ባሻገር በክልል ደረጃ ፕሮጀክቶችን በጥራት በማዕቀድና በውጤታማነት መምራት የሚያስችል አቅምና ተቋማዊ ባህል እየፈጠር ያለ ተቋም፡፡

የተፈጠረውን አቅም የበለጠ ማጠናከር የሚያስችል 7/24 በመስራት ፕሮጀክቶችን በጊዜና በጥራት መፈፀም አለብን የሚል አመለካከትና ቁርጥኝነት ተፈጥሯል፡፡

ለዚህ ደግሞ ቢሮ ሦስቱን አቅሞች ማለትም የመንግስትን ፤የህዝብንና የድርጅትን አቅሞች አሟጦ በመጠቀም የክልሉን ሁለተናዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን በስፋት እና በጥራት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ በሦሰቱም አቅሞች በያዝነው በጀት ዓመት ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በማንቀሳቀስ ከ761 በላይ ፕሮጀክቶችን ወደሥራ በማስገባት እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየስራ ነው፡፡

በክልላችን በገጠርም ሆነ በከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት ዘላቂነትን በማስቀጠል፣ ፍትሐዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ፕሮጀክቶች በሁሉም አካባቢዎች በስፋትና በጥራት እየተሰሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ፕሮጀክቶችን በዉጤታማነት የመምራትና የማስፈጸም አቅማችንን በማሳደግ በገጠርም ሆነ በከተማ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን እናረጋግጣለን፡፡

መንገድ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት ነው። በመሆኑም በገጠርም ሆነ በከተማ በዘርፉ የህዝባችንን የበርካታ ዓመታት ጥያቄዎች የመለሰ፣ የህዝብን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ባለፉት የለውጥ ሰባት ዓመታት ሰፋፊና ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በማቀድ ወደ ተግባር በመግባት የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስራ ተሰርቷል ። በመሰራትም ላይ ይገኛል።

የለውጡ መንግስት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ውሰጥ ቁልፍ ማሳለጫና መስፈንጠሪያው የመሠረተ ልማት መሆኑን በውሉ በመገንዘብ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ መልካም ፍሬዎች ታይተዋል። ለአብነትም ፦ ባለፉት የለውጥ አመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመንገድ መሰረተ ልማት ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ ፈሰስ ተድርጓል። የፌደራል መንግሥቱ ባለፋት ሰባት አመታት ብቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ45 ሺህ ኪ.ሜ በላይ መንገድ መገንባት ተችሏል ።

የመንገድ አውታር ሽፋን እንደ ሀገር ከነበረበት 126 ሺህ ኪ.ሜ ወደ171 ሽህ ኪ.ሜ ማድረስ ተችሏል። የመንገድ ተጠቃሚ ያልሆኑ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እና በ2 ኪ.ሜ ልዩነት ውስጥ መንገድ እንድያገኙ ተችሏል ። በየአመቱ በሀገር ደረጃ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና ሂደት ውስጥ ይሳተፋሉ። የስራ ዕድልንም ይፈጥራል።

በተለይም የክልሉን የፕሮጀክት አፈፃፀም በውጤታማነት፣ በጥራትና በጊዜ የማጠናቀቅና የመምራት ችግሮችን በማረምና የማስፈፀም አቅማችንን በማሳደግ ለራሳችንና ለመጪው ትውልድ በመታመን የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ህዝባችንን የሚክስ ተግባር ልናከናውን ይገባል።

የትንሳኤ በዓል የመታደስና የንስሀ በዓል ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የሞት ደብዳቤ የተቀየረበት የበዓላት ሁሉ ምሶሱ የሆነ በዓል ነው፡፡ የመንገድ መሰረተ ልማት ደግሞ የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ በዘርፉ ለምንሰራቸው ተግባራት ስኬታማነት መነሳሳትና ቁጭት የምንፈጥርበትና የህዝባችንን ጥያቄዎች የመንመልስበት ቁልፍ ተግባር ነው፡፡

በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን !!
መልካም የትንሳኤ በዓል !!!
ጋሻዉ አወቀ ትኩዬ(ዶ/ር)
አመሰግናለሁ

የባህር ዳር ከተማ  ምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት ሥራ የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ  በተገኙበት ተጀመረ ። ******** የባህርዳር ከተማ አስተዳደር 2ኛ ምዕራፍ የኮሪ...
17/04/2025

የባህር ዳር ከተማ ምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት ሥራ የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ በተገኙበት ተጀመረ ።
********
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር 2ኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ከአማራ ልማት ማህበር እስከ ዋተር ፍሮንት ኢንተርናሽናል ሆቴል ደረጃውን የጠበቀ 800 ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 40 ሜትር ስፋት ኮንክሪት አስፓልት መንገድና ሌሎች የመሠረተ ልማት ስራዎች ይገነባሉ ።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያው ምዕራፍ ከ22 ኪ.ሜ በላይ የተለያዩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

#ፕሮጀክትላንጨርስአንጀምርም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://www.facebook.com/share/1C4hcGQmsq/
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok

"የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ዉጤታማነት በትኩረት በመሰራት ላይ ይገኛል። "ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)********ባሕር ዳር:  መጋቢት 08/2017 ዓ.ም የአብክመ መንገ...
16/04/2025

"የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ዉጤታማነት በትኩረት በመሰራት ላይ ይገኛል። "ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)
********
ባሕር ዳር: መጋቢት 08/2017 ዓ.ም የአብክመ መንገድ ቢሮ በገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም (Rural connectivity for food Security program - RCFSP) ዙሪያ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና ስልጠና አዘል የምክክር መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ በገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም (Rural connectivity for food Security program - RCFSP) ዙሪያ የአፈፃፀም፤ የአሰራር፤ ተጠባቂ ውጤቶች ዙሪያ አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት የቢሮው የዲዛይንና ኮንስትራክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የፕሮግራሙ ተወካይ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ መኳንንት ሲሆኑ የገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተፈፃሚነትና ዝርዝር ተግባራትን አስመልክተው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የመንገድ ቢሮ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር) ለገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ዓላማና ተፈፃሚነት የባለድርሻ አካላትን አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ፕሮግራሙ በተገቢው ሁኔታ መሬት እንዲነካ በቀጣይ በየደረጃው ለሚገኙ የክልል ተቋማት፤ የዞንና የወረዳ አመራርና ባለሞያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍሎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሠጥና ተግባሩን በትኩረት እንደሚተገበር የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ቢሮ ኃላፊው አያይዘው የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ዙሪያ በየደረጃው ላሉ ፈፃሚ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱ በስራ ላይ ያለውን የአሰራር ግልፀኝነት በቂ ግንዛቤ እንድኖራቸው ያስችላል ብለዋል።

በመድረኩ የአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀለሙ ሙሉነህ፣ የሁለቱ ተቋም ምክትል ኃላፊዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ በልስቲ፣ በየተቋሙ የሚገኙ የፕሮግራሙ ፎካሎችና አጠቃላይ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን በቀጣይም በተደራጀ አግባብ ለታችኛው መዋቅር የአቅም ግንባታ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት ተነስቷል።

#ፕሮጀክት ላን ጨርስ አንጀምርም!

#ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61564040788841
Telegram ፡ https://t.me/anrsRoadBureau
You Tube: https://www.youtube.com/
TikTok Amhara Regional Road Bureau () | TikTok!

Address

Amhara
Bahir Dar
3

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Z=Amhara ዘ አማራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Z=Amhara ዘ አማራ:

Share

Category