የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

18/09/2026

ልጆቻችንን በወቅቱና በሙሉ በመከተብ ጤናማ ትውልድን አብረን እንገንባ!

ይህ ቪዲዮ የህፃናትን የቀዳማይ እድገት ክትትልና የክትባት አስፈላጊነት በግልፅ ያሳያል :: ይመልከቱት፣ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!

#የልጆችጤና #ክትባት #ጤናማትውልድ #የቀዳማይእድገት #የህፃናትእንክብካቤ

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 8/2019 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

መንግስታዊ ያልሆነ  Simprints  eCHIS Project ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከ 4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ታብሌቶችን ድጋፍ አደረገ::        የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ መስከ...
16/09/2026

መንግስታዊ ያልሆነ Simprints eCHIS Project ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከ 4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ታብሌቶችን ድጋፍ አደረገ::

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ መስከረም 6/2019 ዓ.ም

Simprints eCHIS Project በጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የሚሰጡ የማኅበረሰብ ጤና አገልግሎቶችን ወደ ወረቀት አልባ (Paper-free/Paperless) የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚያግዙ ከ 4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 77 ታብሌቶችን ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ለዳሌና ወንዶ ገነት ወረዳዎች የተደረገ ሲሆን፣ በወረዳዎቹ በሚገኙ የጤና ኬላዎች የሚሠሩ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የሚሰበስቡትን የማኅበረሰብ ጤና መረጃ በዲጂታል ሥርዓት በወቅቱ እንዲመዘገብና እንዲደራጅ በማድረግ የኤሌክትሮኒክ የማኅበረሰብ ጤና መረጃ ሥርዓት (eCHIS) ትግበራን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ድጋፉን የተረከቡት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በመልዕክታቸው፦ የጤና መረጃ ጥራት በጤና ሥርዓቱ ውስጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ከማኅበረሰቡ የሚሰበስቡት መረጃ በወቅቱና በጥራት መመዝገቡ የጤና አገልግሎትን በመረጃ ለመምራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ ድጋፍ ትልቅ ነው፤ ለተደረገው ድጋፍ Simprints e-CHIS እናመሰግናለን” ያሉት አቶ በላይነህ፣ ታብሌቶቹ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ በአግባቡ እንዲውሉ እንደሚጠበቅና በቀጣይም ከድርጅቱ ጋር በትብብር እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

አቶ በላይነህ አክለውም፣ በክልሉ የeCHIS ትግበራ ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው፣ የዲጂታል ጤና ሥርዓቱን በማጠናከር የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የሚያከናውኑትን የማኅበረሰብ ጤና ሥራ ይበልጥ ቀልጣፋና በመረጃ የሚመራ ለማድረግ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

የSimprints e-CHIS ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ቃልኪዳን ካሳሁን የተደረገውን ድጋፍ ሲያስረክቡ፣ ድርጅቱ ዳሌንና ወንዶ ገነት ወረዳዎችን ከወረቀት ነፃ የማድረግ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀምር ገልጸዋል። በተጨማሪም በክልሉ ሌሎች ሰባት ተጨማሪ ወረዳዎችም የe-CHIS ትግበራን ለማጠናከር የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገላቸው እንደሚገኙ አስረድተዋል። አቶ ቃልኪዳን አክለውም፣ ፕሮጀክቱ በቀጣይ በጤና መረጃ ሥርዓቱ ላይ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት፣ የጤና ሴክተሩን ዲጅታላይዜሽን ለማጠናከር እና የe-CHIS ትግበራን በቀጣይነት ለማስፋት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የዳሌና ወንዶ ገነት ወረዳዎች በበኩላቸው፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሥራን ከወረቀት አልባ የመረጃ አሠራር ጋር ለማጠናከር የተደረገውን ድጋፍ በማድነቅ፣ የeCHIS ትግበራን በቁርጠኝነት ለማስፋፋትና ታብሌቶቹን ለታለመላቸው ዓላማ በአግባቡ ለመጠቀም እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

የSimprints Technology LTD eCHIS Project ድጋፍ የጤና ኤክስቴንሽን ሥራን ከወረቀት አልባ የመረጃ አሠራር ጋር በማገናኘት፣ የማኅበረሰብ ጤና መረጃ በወቅቱ እንዲሰበሰብ፣ እንዲደራጅና ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲውል ከማስቻል ባለፈ፣ በቀጣይ የተሻሉ የዲጂታል ጤና አሠራሮችን ለማስፋፋት መሠረት የሚጥል መሆኑ ተብራርቷል ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 6/2019 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇Sidama National Regional State Health BureaudJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

15/09/2026

እናት ደህና፣ ልጅም ጤና!

የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በእናቶችና ሕፃናት ጤና ያስመዘገበውን ለውጥና ውጤት የሚያሳይ ይህንን አጭር ዶክመንተሪ ቪዲዮውን ይመልከቱ
ሀሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉ ።

ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ !

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 4//2019 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የጤናው ዘርፍ አጋር የሆነው JSI ለሲዳማ ክልል ጤና ተቋማት   ግምታቸው 3 ሚሊዮን የሚሆኑ የህክምና መሣሪያዎችን ድጋፍ አደረገ ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣  መስከረም 4/2019 ዓ.ም የ...
15/09/2026

የጤናው ዘርፍ አጋር የሆነው JSI ለሲዳማ ክልል ጤና ተቋማት ግምታቸው 3 ሚሊዮን የሚሆኑ የህክምና መሣሪያዎችን ድጋፍ አደረገ ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ መስከረም 4/2019 ዓ.ም

የጤናው ዘርፍ አጋር የሆነው JSI በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የአለታ ወንዶ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ለ2ኛ ሞጊሣ ጤና አ/ጣቢያ ግምታቸው 3 ሚሊዮን የሚሆኑ የህክምና መሣሪያዎችን ድጋፍ አድርጓል ።

በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ የጤና ቢሮው ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት ፥

የክልሉ ጤና ቢሮ ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመፍጠር ከወትሮው በተለየ መልኩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ ፣ የዚሁ አካል የሆነውን የህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ለማሻሻል ከጤና አጋሮች ጋር በመሆን መጠነ ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አውስተው ፣ እንደ ክልል ዛሬ የተገኘው ድጋፍም የጨቅላ ህጻናትን ጤና ለማሻሻል ትልቅ ትርጉም ያለው እንደሆነ ገልጸዋል ። ድጋፉ የተደረገላቸው የአለታ ወንዶ ጠ/ ሆስፒታልም ሆነ 2ኛ ሞጊሣ ጤና አ/ጣቢያ የህ/መሣሪያዎቹንና መገልገያዎችን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ። JSI ከልማት ማህበር ጋር በመሆን ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

በJSI የሲዳማ ክልል Health System Strengthening Service delivery አስተባባሪና የሕክምና መሣሪያዎቹን ያስረከቡት ወ/ሮ ምንትዋብ ዘነበ በበኩላቸው ፣ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመሆን ለተለያዩ ወረዳዎችና ጤና ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመው ፣ ዛሬ የተደረገው ድጋፍም የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ በተለይም ህብረተሰብ ተኮር የጨቅላ ህጻናት የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥተው የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልጸው ፤ ጤና ተቋማትም ንብረቶቹን ለታለመላቸው ዓላማ ማዋል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የ Momentum health Resilience (JSI ) የደቡብ ኤሪያ ማኔጀር አቶ አገኘው ገብሩ በበኩላቸው አጋር ድርጅቱ በክልሉ ለሚገኙ ጤና ተቋማት ከዚህ በፍትም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበረ ገልጸው ፣በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የሲዳማ ልማት ማህበር ምክትል ኃላፊ አቶ ያለው ተከስቴ በበኩላቸው ፣ ከJSI ጋር በመሆን ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የክልሉ ጤና ቢሮ እያደረገ ላለው ጥረት ትልቅ ድጋፍ እንደሆነ በመግለጽ ድጋፍ ያደረገውን አጋር ድርጅቱን አመስግነዋል።

በመጨረሻም አቶ በላይነህ በቀለ ከግብረ- ሰናይ ድርጅቱ የተገኘውን ድጋፍ ለአለታ ወንዶ ጠ/ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ለአቶ ፍጹም ዳንጉራ ርክክብ በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
መስከረም 4//2019 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤናና በደስታ አደረሳችሁ! አደረሰን! በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።    የሲዳማ ክልል ጤና ቢ...
10/09/2026

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤናና በደስታ አደረሳችሁ! አደረሰን! በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም

አዲሱ ዓመት ካለፈው በተሻለ ተስፋ፣ በአዲስ ራዕይ፣ በአዲስ ህልምና በአዲስ ጅማሬ የሚታደስበት፤ የሰላምና የአብሮነት እሴቶች የሚጠናከሩበት፤ ሕዝቦች በጤና፣ በደስታና በብልጽግና የሚያድጉበት የስኬት ዘመን እንዲሆን ቢሮው ምኞቱን ይገልጻል።

በጤና ዘርፉ ባለፉት ዓመታት በተቀናጀ አመራር፣ በጤና ባለሙያዎች ትጋትና ቁርጠኝነት፣ በማኅበረሰቡ ተሳትፎና በአጋር ድርጅቶች ድጋፍ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። ከበሽታ መከላከል ባሻገር የሕክምናና የማዳን አገልግሎቶችን በማጠናከር፣ የጤና አገልግሎቶችን ጥራትና ተደራሽነት በማሻሻል የተመዘገቡ ለውጦች ለቀጣይ ስኬት ጠንካራ መሠረት ፈጥረዋል።

በ2019 በጀት ዓመትም ይህንን እድገት በማስቀጠል፣ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ መካከለኛ ዘመን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ (HSDIP-II) እና የጤና ዘርፍ ሪፎርምን በተግባር በማስፈጸም፣ ፍትሃዊ፣ ጥራት ያለው፣ ውጤታማና ለሁሉም ተደራሽ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ከጤና ዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ ከማኅበረሰቡና ከአጋር ድርጅቶች የጋራ ግብን ሰንቆ እየተጓዘ ይገኛል፡፡

ጤናማ ምርታማ እና የበለጸገ ህብረተሰብ ተፈጥሮ የማየት ራዕይን ለማሳካት ፣የሕዝብ ጤናና ደህንነትን ማስጠበቅ የጤና ዘርፉ ቀዳሚ ተልኮውንም ከግብ ለማድረስ ፤የማኅበረሰብ ጤና ስጋቶችን በፍጥነት በመለየት፣ ተገቢና ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት የሕዝቡን ጤና ለመጠበቅ ቢሮው እየተጋ ይገኛል !ትጋቱንም በህብረት ያስቀጥላል፡፡

የአዲስ ዓመት በዓልን በጤናና በደስታ ለማክበር እያንዳንዱ ዜጋ የራሱንና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ እንደሚገባው የሚያወሳው ጤና ቢሮ በተለይም በዓሉን ለማክበር በሚደረጉ የእርድ ሥርዓቶች የእንስሳት ጤና መረጋገጡን ማረጋገጥና የእንስሳት ጤና ምርመራ በእርድ ወቅት ተገቢውን ቦታ እንዲያገኝ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻል፡፡

በበዓላት ወቅትም ሆነ ከበዓላት በኋላ ጤናማ የአኗኗር ልምዶችን ማስቀጠል የራሳችንን፣ የቤተሰባችንንና የማኅበረሰባችንን ለሰው ልጅ ጤና ሊያሰጉ ከሚችሉ ስጋቶች ራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን መጠበቅ ተገቢ መሆኑን የሚያስገነዝበው ቢሮው፤

በተለይም ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ለተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የስኳር ሕመም፣ ሥር የሰደደ የመተንፈሻ አካል ችግር፣ ካንሰርና የልብ ሕመም የሚያዙና በእነዚህ ሕመሞች ሳቢያ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያጎላዋል፡፡

በበዓላት ወቅት የተለያዩ ምግቦች በብዛት ስለሚዘጋጁ፣ ምግብን በመጠኑ መመገብ፣ ቅባትና ጨው የበዛባቸውን ምግቦች ከመጠን በላይ ከመመገብ መቆጠብና ለጤናማ አመጋገብ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ እየገለፀ ፤የበዓሉ ደስታ በጤና እንዲደምቅ የግልና የቤተሰብ ጤናን መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን ቢሮው ያሳስባል፡፡

አዲሱ 2019 ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ፣ የስኬትና የብልጽግና ዘመን እንዲሆን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤናና በደስታ አደረሳችሁ! አደረሰን!

መልካም አዲስ ዓመት!

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

 #ምስጋና ለክልሉ ጠ/ሆስፒታሎች !በሲዳማ ክልል በሚገኙ ጠ/ሆስፒታሎች  ባለፉት ሁለት ወራት  ሲካሄድ በነበረው የክረምት በጎ አገልግሎት ለ 366 ዜጎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጠ::የሲ...
10/09/2026

#ምስጋና ለክልሉ ጠ/ሆስፒታሎች !

በሲዳማ ክልል በሚገኙ ጠ/ሆስፒታሎች ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ በነበረው የክረምት በጎ አገልግሎት ለ 366 ዜጎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጠ::

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም

በሲዳማ ክልል በሚገኙ ጠ/ሆስፒታሎች ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ በነበረው የክረምት በጎ አገልግሎት ለ 366 የቀዶ ሕክምና ተጠባባቂ (Surgical Backlog) ታካሚዎችን ማስተናገድ/ማጽዳት ችለዋል።

ሆስፒታሎቹ ባለፉት ሁለት ወራት ከዚህ በፊት በቀጠሮ ላይ የነበሩትን ጭምር በልዩ ድጋፍ ማዕቀፍ በመደገፍ ፤ በተፈጥሮና ድንገተኛ አደጋዎች የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ፣ እንዲሁም የውስጥ ደዌ እና የአፈጣጠር ችግር ላለባቸው ዜጎች አገልግሎቱን የሰጡ ሲሆን ፣
አፈጻጸማቸውም ፥
1. አለታ ወንዶ ጠቅላላ ሆስፒታል – ለ177 ታካሚዎች ፣
2. አዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል –ለ 67 ታካሚዎች ፣
3. ቦና ጠቅላላ ሆስፒታል – ለ47 ታካሚዎች ፣
4. ቱላ ጠቅላላ ሆስፒታል –ለ43 ታካሚዎች ፣
5. ዳዬ ጠቅላላ ሆስፒታል – ለ 32 ታካሚዎች ፣
በድምሩ ለ366 ዜጎች ዘመናዊ የቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠታቸው ታውቋል ።

ሆስፒታሎቹ አገልግሎቱን በክረምቱ ዘመቻ ፕሮግራም ከጤና አጋሮች ጋር በመተባበር የሰጡ እንደሆነ ታውቋል ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ሆስፒታሎቹ በጤና ሴክተር በክረምቱ በጎ አገልግሎቶች ደረጃ ሊሰጡ የታቀዱ ቁልፍ ስራዎች ዙሪያም ትርጉም ያለውን አገልግሎት ሲሰጡ ቆይቷል ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሆስፒታሎቹ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና ጤናማ ኑሮ እንዲኖራቸው ለማስቻል ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ስላከናወኑት የተለያዩ ቀዶ ህክምና እና ሌሎች ሰው ተኮር አገልግሎቶች ከልብ የመነጨ ምስጋና ያቀርባል ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

ምስጋና !በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል  ባለፉት ሁለት ወራት  ሲካሄድ በነበረው የክረምት በጎ አገልግሎት ለ1541  ዜጎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጠ::...
10/09/2026

ምስጋና !
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ባለፉት ሁለት ወራት ሲካሄድ በነበረው የክረምት በጎ አገልግሎት ለ1541 ዜጎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጠ::

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ባለፉት ሁለት ወራት በተፈጥሮና ድንገተኛ አደጋዎች የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም የውስጥ ደዌ እና የአፈጣጠር ችግር ላለባቸው :-
1.Cleft lip and palate ችግር ላለባቸው ለ87 ሰዎች ፣
2.Tonsil ችግር ላለባቸው ለ150 ሰዎች ፣
3.Neurosurgery ለ38 ሰዎች ፣
በድምሩ ለ275 ዜጎች ዘመናዊ የቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል ።

ሆስፒታሉ አገልግሎቱን የሰጠው በተቋሙ በመደበኛው ፕሮግራሙ እና ከግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሲሆን፤ ሕክምናው የተከናወነው በሆስፒታሉ ውስጥ ቀደም ተብሎ በተቋቋመው ዘመናዊ የቀዶ ህክምና ማዕከል ውስጥ ነው።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሆስፒታሉ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና ጤናማ ኑሮ እንዲኖራቸው ለማስቻል ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ስላከናወነው የተለያዩ ቀዶ ህክምና እና ሌሎች ሰው ተኮር አገልግሎቶች ከልብ የመነጨ ምስጋና ያቀርባል ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታልና ሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል ጋር  በመቀናጀት ለሕፃናት የነፃ ሕክምና አገልግሎት መስጠታቸው ተገለጸ። የሲዳማ ክልል ...
09/09/2026

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታልና ሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል ጋር በመቀናጀት ለሕፃናት የነፃ ሕክምና አገልግሎት መስጠታቸው ተገለጸ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ከአለታ ወንዶ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታልና ከሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል ጋር በመቀናጀት ለሕፃናት የአፍንጫና የጉሮሮ ቶንሲል ነፃ ቀዶ ሕክምና ዘመቻ አካሂዷል።

በዘመቻው 45 ሕፃናት ነፃ የቶንሲል ቀዶ ሕክምና ያገኙ ሲሆን፣ በተለይም የሕክምና ወጪን ለመሸፈን አቅም ላጡ ቤተሰቦች ከፍተኛ የጤናና የኢኮኖሚ እፎይታ መፍጠር ተችሏል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ፣ መንግሥት፣ የግሉ ዘርፍና ማኅበረሰቡ በትብብር ሲሠሩ የማኅበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ይበልጥ ማስፋት እንደሚቻል ገልጸዋል።

ዶ/ር ሰላማዊት በክረምት ወራት የተካሄዱ የጤና በጎ ፈቃድ ሥራዎች ነፃ ሕክምና ከመስጠት ባለፈ፣ በሽታን በመከላከል፣ ቀድሞ ምርመራን በማጠናከርና የጤና ግንዛቤን በማሳደግ ጤናማ ማኅበረሰብ ለመገንባት ትልቅ አቅም የፈጠሩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በክረምት በጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎት መርሐ ግብር ለሕፃናቱ ነፃ ሕክምና እንዲሰጥ ያቀረበውን ጥያቄ በአጭር ጊዜ በመቀበልና ለመርሐ ግብሩ ድጋፍ በማድረግ ለተሳተፉት የሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል።

የጤና በጎ ፈቃድ ገንዘብ መለገስ ብቻ ሳይሆን ሙያን፣ ጊዜንና እውቀትን ለሌሎች ማጋራትም መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ሰላማዊት፣ ማኅበረሰቡ በአቅሙ ሁሉ ለጤና ልማት እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል።

የሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል የአንገት በላይ ስፔሻሊስትና የጆሮ ቀዶ ሕክምና ሰብስፔሻሊስት ዶ/ር ሙሉቀን በቀለ በበኩላቸው፣ በዘርፉ ያላቸውን የሙያ እውቀትና ልምድ በመጠቀም 45 ሕፃናትን በነፃ ማከም በመቻላቸው ታላቅ የመንፈስ እርካታ እንዳገኙ ገልጸዋል።

የአለታ ወንዶ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ዳንጉራ፣ ለሕፃናቱ ነፃ የቀዶ ሕክምና ዕድል በመፍጠር ለዘመቻው ስኬት አስተዋፅዖ ያደረጉትን የግል ጤና ተቋሙን የሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል የጤና ባለሙያዎች አመስግነዋል።

ነፃ የቶንሲል ቀዶ ሕክምናው በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር የማኅበረሰቡን የጤና ችግሮች በተግባር መፍታት እንደሚቻል ያሳየ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

የዘመቻው ተጠቃሚ የሆኑ የሕፃናት ወላጆችም በልጆቻቸው ጤና መሻሻል ደስታቸውን ገልጸው፣ በነፃ የተሰጣቸው የቀዶ ሕክምና ድጋፍ በቤተሰቦቻቸው ላይ የነበረውን የጤና፣ የጊዜና የኢኮኖሚ ጫና ለማቃለል እንደረዳቸው ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታልና ከሩህ የአንገት በላይና የቀዶ ሕክምና ማዕከል ባለሙያዎች እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ለዘመቻው ስኬት አስተዋፅዖ ላደረጉ የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞችም ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

የሲዳማ ክልል  ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገለጸ። የሲዳማ ክልል  ጤና ቢሮ ፣ ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም. የሲዳማ ብሔራዊ ክ...
09/09/2026

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገለጸ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም.

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት በድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፣ ህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት ፣ በምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና በመረጃ አያያዝ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገልጿል ።

በዛሬው ዕለት ኢንስቲትዩቱ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን የገመገመ ሲሆን፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዋና ዋና ግቦችንና የትኩረት መስኮችንም አስተዋውቋል ።

በመድረኩ የቀረበውን የአፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግም ከተሳታፊዎች ገንቢ አስተያዬቶች ከመሰጠታቸው ባሻገር አንዳንድ በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ተግዳሮቶችን እና በ2019 ዓ.ም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉም ታውቋል ።

በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ 2018 በጀት ዓመት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ መሻሻሎችና ለክልሉም ሆነ ለሀገር ምሳሌ የሚሆኑ በርካታ ሥራዎች የተከናወኑበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል።

የተሻለ አፈጻጸም ከተመዘገበባቸው የስራ ዘርፎችን የቢሮ ኃላፊዋ ሲጠቅሱ ፥በድጂታላይዜሽን አተገባበር ላይ የታዩ ለውጦች ፥ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ቴክኖሎጂ (ዲ. ኤች. አይ.ኤስ-2) አፈጻጸም ወደሚፈለግበት ደረጃ መድረሱ እንዲሁም ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በጤና ተቋማት ገብራዊ ማድረግ ፣ የህብረተሰብ ጤና የላብራቶሪ አገልግሎትን በዘመናዊ መሣሪያዎች ማሻሻል እና ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን ምርመራዎች ማስጀመር እንዲሁም ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምር ስራዎች በዓመቱ ከተመዘገቡ ዋና ዋና ውጤቶች መካከል መሆናቸውን ዶ/ር ሰላማዊት ገልጸዋል ።

ኃላፊዋ አያይዘውም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የውስጥ አቅሙን በማጎልበት ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመግታት በተሠራው ሥራ በተለይ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝን ባጠረ ጊዜ በመከላከልና በመቆጣጠር ያሳየው ብቃት ለሀገሪቱም ተሞክሮ ሊሆን የሚችል አንደሆነ በአድናቆት አንስተዋል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ በበኩላቸው፣ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የሚከሰቱ የጤና አደጋዎችን ቀድሞ ለመለየትና ተገቢውን ምላሽ በፍጥነት ለመስጠት የቅኝትና የአሰሳ ሥራዎችን በማጠናከር በሽታዎች በሕብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሳያስከትሉ ባጠረ ጊዜ እንዲቆጣጠሩ ማስቻሉን ገልጸዋል። በታችኛው እርከን ያሉ መዋቅሮች ሪፓርታቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንድልኩ ለማስቻል ከ110 በላይ ዘመናዊ ኮምፕተሮችን ለወረዳዎች እና ለጤና ተቋማት መሠራጨቱንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ በበጀት ዓመቱ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተጣሉ ግቦችን በአግባቡ የፈጸሙ እና የመሩ መዋቅሮች እና ግለሰቦች የዕውቅና ምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን ፤

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ የዓለም አቀፍ የጤና ኢንስቲትዩቶች መስፈርት በማሟላት የሚፈለጉ ቅድመ - ሁኔታዎችን በሚፈለገው ደረጃ ማሟላት በመቻሉ ባሳለፍነው በጀት ዓመት በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ International Association of National Public health Institute (IANPHI) አባል መሆን መቻሉን ምክንያት የቢሮ ኃላፊዋና የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች በጋራ በመሆን ይህንኑ አስመልክቶ የተዘጋጀውን የኬክ ቆረሣ ተደርጎ ደስታቸውን አጣጥመዋል ።

በመድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማኔጅመንት አባላት ፣ የፌደራል ተቋማት ኃላፊዎች ፣ የዞንና የወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት አስተባባሪዎችና ኃላፊዎች ፣ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች፣ አጋር አካላትና እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ

Website: https://www.shb.gov.et

Facebook:
👇👇👇👇

https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/

Telegram : https://t.me/SidamaRHB

Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau

WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71

YouTube:

https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX

Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa/

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share