SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ, Government Organization, Meskel Square, Awassa.

ጾታ ተኮር ጥቃትን የመከላከል ሥራ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለፀግንቦት 27/2018ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጾታ ተኮር ጥቃት ህክምና በሁሉም አከባቢዎች ለማጠናከር እየተ...
04/06/2026

ጾታ ተኮር ጥቃትን የመከላከል ሥራ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

ግንቦት 27/2018ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጾታ ተኮር ጥቃት ህክምና በሁሉም አከባቢዎች ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የህግ አገልግሎቶችን ማጠናከር እንደሚገባም አቶ ዳዊት መንግስቱ ገልፀዋል።

በጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዳዊት መንግስቱ እንደገለፁት የጾታ ተኮር ጥቃት ህክምና ባልተጀመረባቸው ሆስፒታሎች ስራውን ለማስጀምር እና የጾታ ተኮር ጥቃት የመከላከል ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራት ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ጠቁመዋል።

የጊዶሌ፣ ሶያማ እና አማሮ ኬሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የጾታ ተኮር ጥቃት ህክምና ለማስጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውንም አውስተዋል።

በውይይት መድረኩ የጾታ ተኮር ጥቃት ጫና በክልሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታን በመዳሰስ የዘጠኝ ወር የጾታ ተኮር ጥቃት ህክምና እና መከላከል ስራ ሪፖርትን ተመልክተዋል።

በጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጆሹዋ አየለ በበኩላቸው የአንድ ማዕከል ህክምና አገልግሎትን በመስጠት ፆታ ተኮር ጥቃት ለመከላከል ከዚህ በበለጠ ልሰራ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተቀናጀ የአንድ መዕከል አገልግሎት አሰጣጥና ተሞክሮ ልምድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ፍትህ ቢሮ የሴቶችና ህጻናት ልዩ ምርመራና ክስ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ለማላ አበረሃም የተቀናጀ የአንድ መዕከል አገልግሎት፣ ማቆያና ማገገሚያ ተቋማት ላይ ዝርዝር ተግባራትና መረጃ አቅርበው ተወያይተውበታል።

በቱርሚ፣ ጊዶሌ፣ ሶያማ እና አማሮ ኬሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የጾታ ተኮር ጥቃት የተቀናጀ የአንድ መዕከል አገልግሎት መጀመር እንዳለባቸውም ተመክሯል።

‎ለጥቃት ተጋላጭና ተጎጂ የሆኑ ሕጻናትን ለመንከባከብ እና ወደነበሩበት ሁለንተናዊ ደህንነት ለመመለስ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የህጻናት ባለሙያዎችን፣ የፖሊስ አካላትንና የማህበራዊ ሳይንስ ...
03/06/2026

‎ለጥቃት ተጋላጭና ተጎጂ የሆኑ ሕጻናትን ለመንከባከብ እና ወደነበሩበት ሁለንተናዊ ደህንነት ለመመለስ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የህጻናት ባለሙያዎችን፣ የፖሊስ አካላትንና የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት ያለመ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

‎የሚኒስቴሩ የህፃናት መብት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ ባስተላለፉት መልዕክት፤ሕፃናት በተዛቡ አመለካካቶች፣ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ምክንያት ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ የሚሆኑባቸው እድሎች ሰፊ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

‎በተለይም በህፃናት ላይ የሚፈፀም አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ስሜታዊ ጥቃት በሕጻናት የአሁንና የወደፊት ሕይወት ላይ ጥልቅ የሆነ ሥነ-ልቦናዊ ጠባሳ፣ የማህበራዊ መገለል እና የጤና እክሎችን ከማስከተሉም በላይ ውድ ህይወትን ሊያሳጣ እንደሚችል ተናግረዋል።

‎ሕጻናት በአካል፣ በሥነ-ልቦና እና በማህበራዊ ተጠቃሚነት ረገድ ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ያሉት ወ/ሮ ዘቢደር የህጻናትን ጥበቃ ለማጎልበት የሚያስችሉ የህግ፣ የፖሊሲ ማእቀፎችን ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ እና የአሰራር ስርዓቶችን ከመዘርጋት ባሻገር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የመከላከልና ምላሽ የመስጠት ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

‎በተጨማሪም የባለሙያዎችን /front line workers/ እውቀት በማሳደግ የህጻናትን ጥቃትና ተጋላጭነት መቀነስ፤ ለጥቃት ሲጋለጡም ፈጣን ምላሽ የተናበበና የቅብብሎሽ አገልግሎት የሚያገኙበትን ተቋማዊ አሰራሮች ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

‎ከጥቃት የተረፉትን ሕጻናት ለመንከባከብ፣ ምላሽ ለማመቻቸት እና ወደነበሩበት ሁለንተናዊ ደህንነት ለመመለስ የሚከናወኑ ተግባራት ልዩ ጥንቃቄን፣ ሙያዊ ክህሎትን እና ርህራሄን ይጠይቃል ብለዋል።

‎በዘርፉ የሚሰሩ አገልግሎት ሰጪዎችንም ከስራው ጋር ተያይዞ ከገቡበት የስነልቦና ጫና እንዲወጡ እና የህጻናትን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

‎በስልጠናው ከሁሉም ክልልና ከተማ እስተዳደር የተውጣጡ የህጻናት ባለሙያዎች፣ የፖሊስ አካላት፣ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
‎ #ሴማጉሚ

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በመገኘት ድምፃቸውን ሰጡ‎‎ግንቦት 24/2018 ዓ.ም‎‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴ...
01/06/2026

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በመገኘት ድምፃቸውን ሰጡ

‎ግንቦት 24/2018 ዓ.ም

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በመገኘት የዜግነት አሻራቸውን አኑረዋል።

‎ቢሮ ኃላፊዋ በሶዶ ዙሪያ ምርጫ ክልል-2፣ በፋና ወምባ አፈር ምርምር አበል ጭናሾ ምርጫ ጣቢያ በአካል ተገኝተው ነው ድምፃቸውን የሰጡት።

‎ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ለሚዲያ አካላት በሰጡት መግለጫ፤ መላው የመራጭ ሕዝብ በእጁ ያለውን የምርጫ ካርድ በአግባቡ በመጠቀም፣ ራሱን በታማኝነትና በብቃት ማስተዳደር የሚችልን ፓርቲ መምረጥ እንዳለበት አሳስበዋል።

‎ቢሮው ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች በተመለከተም ኃላፊዋ ሲያብራሩ፤ በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ሴቶች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ያለምንም እንግልትና ጫና ቀድመው ድምፃቸውን እንዲሰጡ የሚያስችል ምቹና አካታች ዝግጅት እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ።

‎በመጨረሻም፣ ማንኛውም መራጭ መብቱና ግዴታው የሆነውን ይህንን ታሪካዊ ዴሞክራሲያዊ መብት በአግባቡ ሊጠቀምበት እንደሚገባ የገለጹት ወ/ሮ ካሰች፤ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል እስከ ፍጻሜው ድረስ በሰላማዊና በጨዋነት መንፈስ ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

‎ስለ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉ ገፆቻችንን ይጎብኙ!

‎For more information follow the Women and Social Affairs Bureau Pages

‎ድረ ገጽ፦ https://www.wcya.gov.et/
‎ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064714717786
‎ቴሌግራም፦ https://t.me/WcyaEthiopia
‎ዩትዩብ፦ women and social affairs bureau

‎ቀጠሮው ከታሪክ ጋር ነው፦ ድምፅ ለመስጠት 1 ቀን ብቻ ቀረው!‎‎"የእኔ ድምፅ የሀገሬ መጻኢ ዕድል ነው፤ ዋጋ ስላለው እኔ ለመምረጥ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅቻለሁ፤ እናንተስ?"‎‎አዎ! ያ በጥንቃ...
31/05/2026

‎ቀጠሮው ከታሪክ ጋር ነው፦ ድምፅ ለመስጠት 1 ቀን ብቻ ቀረው!

‎"የእኔ ድምፅ የሀገሬ መጻኢ ዕድል ነው፤ ዋጋ ስላለው እኔ ለመምረጥ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅቻለሁ፤ እናንተስ?"

‎አዎ! ያ በጥንቃቄ ስንጠብቀው የነበረው፣ የነገዋን ውብና የበለጸገች ኢትዮጵያ መሠረት የምንጥልበት ታላቅ ቀን ለመድረስ "አንድ ቀን ብቻ" ቀረው። ሰዓታት እንጂ ቀናት የማይቆጠሩበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን።

‎🗳️ የእርስዎ ድምፅ፦ ለሰላምዎ ዋስትና ነው!
‎🗳️ የእርስዎ ድምፅ፦ ለልጆችዎ የተሻለ ነገ ነው!
‎🗳️ የእርስዎ ድምፅ፦ የሀገርን ሉዓላዊነትና ጽናት የሚያረጋግጥ የአልማዝ አሻራ ነው!

‎የወሰድነውን ካርድ በእጃችን ይዘን፣ በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመገስገስ ጨዋነታችንን እና የሰለጠነ ዴሞክራሲያዊ ባህላችንን ለዓለም የምናሳይበት ጊዜ አሁን ነው። እኔ የዜግነት ኃላፊነቴን ለመወጣት ተዘጋጅቻለሁ፤ የእናንተስ ዝግጅት እንዴት ነው?

‎ነገ ማለዳ ላይ እንገናኝ! በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ — ድምፅዎ የነገ ተስፋዎ ነው!





‎ #ኢትዮጵያ

‎ !

የታሪክ ምዕራፍ ላይ ቆመናል፦ የሰላምና የዕውቀት ውሳኔ ከሴቶችና ወጣቶች ይጠበቃል!‎‎መላው የሀገራችን ሴቶችና ወጣቶች!‎‎የሀገራችንን የነገ ተስፋ፣ ሰላምና ብልጽግና በገዛ እጃችን የምናረጋግ...
30/05/2026

የታሪክ ምዕራፍ ላይ ቆመናል፦ የሰላምና የዕውቀት ውሳኔ ከሴቶችና ወጣቶች ይጠበቃል!

‎መላው የሀገራችን ሴቶችና ወጣቶች!

‎የሀገራችንን የነገ ተስፋ፣ ሰላምና ብልጽግና በገዛ እጃችን የምናረጋግጥበት ያ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ እነሆ ደረሰ። ይህ ቀን መሪ የምንመርጥበት ብቻ ሳይሆን፣ የሰላም አምባሳደርነታችንን በተግባር የምናሳይበት ታላቅ መድረክ ነው።

‎በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ከእያንዳንዱ የሀገራችን ሴትና ወጣት የሚጠበቁ ሁለት ወሳኝ እሴቶች አሉ፦

በጥንቃቄ ማሰላሰል ነገን፣ የልጆቻችንን መጻኢ ዕድል እና የሀገራችንን ቀጣይነት ቆም ብሎ ማሰብ።

በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ መስጠት በስሜታዊነት ሳይሆን በዕውቀት፣ በእውነትና በተጨባጭ ሥራዎች ላይ ተመስርቶ "ይበጀኛል" ለሚሉት ምርጫ ድምፅን መስጠት።

‎ሴቶች የቤተሰብና የማህበረሰብ ምሰሶዎች፣ ወጣቶች ደግሞ የሀገር ጉልበትና ጋሻ ናችሁ። ጨዋነትንና ሰላምን በማስቀደም፣ የበሰለ ዴሞክራሲያዊ ባህላችንን ለዓለም የምናሳይበት ጊዜ አሁን ነው።

‎በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ —በጥንቃቄ ያስቡ፣ በመረጃ ይወሰኑ፣ የሰላም አምባሳደርነታቸውን ያረጋግጡ!

‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1 ሺህ 64 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።‎‎ግንቦት 22/ 2018 ዓ.ምበሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 64 ኢትዮ...
30/05/2026

‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1 ሺህ 64 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

‎ግንቦት 22/ 2018 ዓ.ም

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 64 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

‎በሳምንቱ 3 ቀናት በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 64 ወንዶች ብቻ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 27 ተመላሾች እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

‎መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ75 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

‎ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

‎በተጨማሪም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።

‎ወደፊትም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት ሚኒስቴሩ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ቀኑ ደረሰ! የታሪክ ባለቤት ለመሆን ተዘጋጅታችኋል?‎‎መላው የሀገራችን ሴቶችና ወጣቶች!‎‎የነገዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ለመወሰንና የልማታችንን ቀጣይነት በአለት ላይ ለመቅረጽ ቀጠሮ የተያዘለ...
29/05/2026

ቀኑ ደረሰ! የታሪክ ባለቤት ለመሆን ተዘጋጅታችኋል?

‎መላው የሀገራችን ሴቶችና ወጣቶች!

‎የነገዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ለመወሰንና የልማታችንን ቀጣይነት በአለት ላይ ለመቅረጽ ቀጠሮ የተያዘለት ያ ታላቅ ቀን እነሆ ደረሰ!

‎የሀገራችን ደም-ስሮች የሆናችሁ ሴቶችና ወጣቶች፤ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በአስተዋይነት፣ በሰለጠነና ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ፣ ነገን በጥንቃቄ በማሰላሰል "ይበጀኛል" የምትሉትን ለመምረጥ ዝግጁ ናችሁ?

‎🗳️ ውሳኔዎ፡ የነገው ሰላምዎ ነው!
‎🗳️ ምርጫዎ፡ የልጆችዎ መጻኢ ዕድል ነው!
‎🗳️ አሻራዎ፡ የጸናች ሀገር መሠረት ነው!

‎ስሜታዊነትን አውጥተን በዕውቀትና በብስለት፣ ለሀገራችን አንድነትና ብልጽግና ስንል ድምፃችንን እንስጥ። ጨዋነትንና ሰላምን አስቀድመን የዜግነት አሻራችንን በኩራት እናኑር!

‎በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅዎ የነገ ተስፋዎ ነው!

የሴቶች ልማት ህብረት አባላትን በተለያዩ የሙያ መስኮች በማሳተፍ ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ  ግንቦት 19/2...
27/05/2026

የሴቶች ልማት ህብረት አባላትን በተለያዩ የሙያ መስኮች በማሳተፍ ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

ይህም የተገለፀው በክልሉ የ3ተኛ ዙር የሞዴል ሴቶች የልማት ህብረት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ4ተኛ ዙር የልማት ህብረት የማስጀመሪያ መድረክ ላይ ነዉ።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ፣ሴቶችን ያላሳተፈ ልማትና እድገት ውጤታማ አይሆንም ብለዋል።

ሴቶችን ወደ ሥራ ማስገባትና በተለያዩ የሙያ መስኮች ማሳተፍ በክልሉ የሚገኙ ሴቶችን በህብረት በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ሴቶች በራስ የመተማመን ብቃታቸው እንዲዳብርና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውም እንዲረጋገጥ በትምህርት፣ በስልጠናና በመሳሰሉት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም ወ/ሮ ካሰች አመላክቷል ።

የሴቶች ተሳትፎ በሀገሪቱ ዕድገት ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ፣በክልሉ በልማት ህብረት የተደራጁ ሴቶች ከራስ አልፈው ለሌሎች አቅም መሆን ይገባቸዋል ብለዋል።

በክልሉ ይህንኑ ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው የገለፁት ኃላፊዋ ፣በልማት ህብረቱ በተደራጁ ሴቶች የሚተገበሩ ተግባራት በውጤት መታጀብ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥቷል።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ምህረት በላይ በበኩላቸው ፣የሴቶች የልማት ህብረት የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ ለሀገሪቱ ዕድገትና ለዘላቂ ልማት አቅም ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ሴቶች የሁሉም ስራ ማሳለጫ ስለመሆናቸው የገለፁት ወ/ሮ ምህረት ወደፊት እንዲመጡ እየተደረገ ላለው ጥረት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል ።

በወቅቱ አስተያየታቸውን የሰጡት የመድረኩ ተሳታፊዎች ፣መንግስት ሴቶች ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲያሳድጉ እየተተገበረ ያለው ተግባር የተሻለ ውጤት እንድናይ አስችሎናል ብለዋል።

በጋራ በመስራት በጋራ ማደግ ይገባል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ፣ይህንኑ ዕሳቤ ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፣በቀጣይም ከዚህ ቀደም ከነበሩ ክፍተቶች ትምህርት በመውሰድ ለሚፈለገው ውጤት ይበልጥ መትጋት እንደሚገባ አስረድተዋል ።

መንግስት ለሴቶች ያመቻቸውን ዘርፈብዙ ዕድሎችን ወደ ዕድል በመቀየር የገቢ ማስገኛ አማራጮችንና የቁጠባ ባህልን ማሳደግ እንደሚገባ በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል ።

በክልሉ ከ 40 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሴቶች ህብረት በማህበር ተደራጅተው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ስለመሆናቸውም ተጠቁሟል ።

ስለ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉ ገፆቻችንን ይጎብኙ!

‎For more information follow the Women and Social Affairs Bureau Pages

‎ድረ ገጽ፦ https://www.wcya.gov.et/
‎ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064714717786
‎ቴሌግራም፦ https://t.me/WcyaEthiopia
‎ዩትዩብ፦ women and social affairs bureau

‎ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገለፀ ‎‎ግንቦት 19/2018 ዓ.ም‎‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ...
27/05/2026

‎ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገለፀ

‎ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
‎ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል ።

‎በክልሉ ከ 40 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሴቶች ህብረት በማህበር ተደራጅተው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ስለመሆናቸውም ተጠቁሟል ።

‎በክልሉ የ3ተኛ ዙር የሞዴል ሴቶች የልማት ህብረት ዕቅድ አፈፃፀምና የ4ተኛ ዙር የልማት ህብረት የማስጀመሪያ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

‎የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ በዚህ ወቅት መንግስት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች በማሰማራት በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

‎የሴቶችን አቅም መገንባትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ለማህበረሰብ እድገት ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ካሰች በክልሉ ይህንኑ ይበልጥ ለማጠናከር እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል ።

‎በክልሉ ሴቶችን በልማት ህብረት በማደራጀት በኢኮኖሚ እንዲበቁ በተደረገው ጥረት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንም የቢሮ ኃላፊዋ አስረድተዋል ።

‎የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ፣በክልሉ ባለፉት ጊዜያት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

‎በዚህም ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሞዴል ሴቶች በልማት ህብረት ተደራጅተው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ስለመቻሉ ጠቁመዋል ።

‎በቀጣይም ይህንኑ ለማጠናከር እንዲቻል በ3ተኛ ዙር በነበሩት ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ወ/ሮ ካሰች ገልጸዋል ።

‎በመድረኩ የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ይሆናል ።

‎ስለ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉ ገፆቻችንን ይጎብኙ!

‎For more information follow the Women and Social Affairs Bureau Pages

‎ድረ ገጽ፦ https://www.wcya.gov.et/
‎ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064714717786
‎ቴሌግራም፦ https://t.me/WcyaEthiopia
‎ዩትዩብ፦ women and social affairs bureau

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የቀሩን 5 ቀናት ብቻ ናቸው። ሰኞ ግንቦት 24 ቀን መላው ኢትዮጵያውያን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ያቀናሉ።የአገርዎን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን የድምፅ መስጫ ካ...
27/05/2026

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የቀሩን 5 ቀናት ብቻ ናቸው።

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን መላው ኢትዮጵያውያን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ያቀናሉ።

የአገርዎን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን የድምፅ መስጫ ካርድዎን አዘጋጅተዋል?

ድምፅዎን በመስጠት በዴሞክራሲያዊ ጉዟችን ላይ የራስዎን አሻራ ያኑሩ!

Address

Meskel Square
Awassa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to SERS Women and Social affairs Bureau በደ/ኢ/ክ/መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ:

Share