የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ, Public & Government Service, snnprsrevenuea@gmail. com, Awassa.

https://www.facebook.com/share/18gnRXEsDY/
14/05/2025

https://www.facebook.com/share/18gnRXEsDY/

የበጀት ዓመቱን የገቢ ዕቅድ ከወዲሁ ለማሳካት ሁሉን አቀፍ ርብርብ ማድረግ ይገባል - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች

ግንቦት 06/2017 ዓ ም
በክልሉ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት የገቢ ስራን በስኬት ለማጠናቀቅ እንዲቻል እንደ ተቋም "በዳግም ዘመቻ እምርታዊ የግብ ስኬት እናረጋግጥ "በሚል መሪ ሀሳብ ለማከናወን የታቀደውን የገቢ ፊዚካልና ፋይናንሻል ስራዎችን ወደ ላቀ ስኬት ለማሸጋገር እንዲቻል የድጋፍና ክትትል ስራዎች በክልሉ በሁሉም የገቢ መዋቅሮች ተግባራዊ እየተካሄደ ይገኛል ።

በክልሉ እየተደረገ ያለው የድጋፍና ክትትል ስራ በ4 የድጋፍ ሰጪ ቡድኖች እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት ወራት 8 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ በክልሉ በመሰብሰብ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ይገኛል ።

ይህንንም ዕቅድ ለማሳካት በተጀመረው የድጋፍና ክትትል ተግባር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመከተልና በማጠናከር የጋራ ርብርብ ማድረግን የሚጠይቅ በመሆኑ በዚህ ላይ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል ።

ያለ ገቢ ልማትን ማረጋገጥ አይቻልም ።

👉"በዳግም ዘመቻ እምርታዊ የግብ ስኬት እናረጋግጥ"!!

፡-

👇👇👇👇👇

የፌስቡክ ገፅ (https://www.facebook.com/profile.php?id=61562204634443

የቲክቶክ ገፅ (https://vm.tiktok.com/ZMkhEJbMb/

የቴሌግራም ገፅ (https://t.me/SNNPRS_Revenue_Bereau

የዩቲዩብ ገፅ (https://youtube.com/?si=ELneJRp2Lj7xJ8GK

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

https://www.facebook.com/share/18dDN5XsMX/
28/04/2025

https://www.facebook.com/share/18dDN5XsMX/

የግብር ከፋዩች /ተገልጋዩች/ መብት

ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

👉ተገልጋዩች በሥራ ላይ ሰላሉ የግብር እና ቀረጥ ድንጋጌዎች፣ ተቋሙ
ሰለሚሰጣቸው አገልግሎቶችና ቅድመ ሁኔታዎች ተገቢውን መረጃ እንደ
አግባብነቱ በስልክ፣ በድረ ገጽ እና በአካል በመቅረብ መረጃዎችን የመጠየቅ፣
ምላሽ የማግኝት እና አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው፡፡

👉ማንኛውም የተቋሙ ተገልጋይ በጾታ፣ በዘር፣ በቋንቋ ፣በሃይማኖት ፣
በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃው እና መገለል አድልዎ ሳይደርስበት በተገቢው
ሁኔታ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፡፡

👉ማንኛውም ተገልጋይ ክብሩና ስብዕናው ተጠብቆ የመስተናገድ እና
ለሚያቀርባቸው አግባብነት ያላቸው የአገልግሎት ጥያቄዎች እንደሁኔታው
አዎንታዊ ይሁን አሉታዊ ምላሽ የማግኘት መብት አለው፡፡

👉ተገልጋዩች ለሚያቀርቡት የአገልግሎት ጥያቄ ወዲያው ምላሽ ለመስጠት
የማይቻልበት ሁኔታ ሲኖር እና ቀጠሮ የሚሰጥባቸው ከሆነ በሂደት ላይ
የሚገኘው ጉዳያቸው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እና የት ክፍል እንደሚገኝ
(ጉዳዩ እስኪጠናቀቅ በሚስጥር መያዝ የሚገባቸውን ጉዳዩች ካልሆነ በስተቀር)
ጠይቀው የመረዳት መብት አላቸው፡፡

👉የተቋሙን ተገልጋዪች በተቋሙ አሠራር ፣ በሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥነ
ምግባር እና በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን
የማቅረብ ፣ ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ የማግኘት የመደመጥ መብት አላቸው፡፡

👉በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥና አሠራር ዙሪያ የታዘቡትንና ቢሆን ይሻላል
የሚሉትን ተገቢ አስተያየት በማመስገንም ሆነ በመተቸት በነፃነት የመግለጽ
መብት አላቸው፡፡

፡-

👇👇👇👇👇

የፌስቡክ ገፅ (https://www.facebook.com/profile.php?id=61562204634443

የቲክቶክ ገፅ (https://vm.tiktok.com/ZMkhEJbMb/

የቴሌግራም ገፅ (https://t.me/SNNPRS_Revenue_Bereau

የዩቲዩብ ገፅ (https://youtube.com/?si=ELneJRp2Lj7xJ8GK

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

https://www.facebook.com/share/p/198ePFSvxu/
22/04/2025

https://www.facebook.com/share/p/198ePFSvxu/

ለግንዛቤዎት!

ሚያዚያ 14/2017ዓም

የታክስ ሕግ ተገዥነት ማለት መንግስታት የታክስ ገቢን ለመሰብሰብ የወጡትን የታክስ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እና መርሆዎችን በፈቃደኝነት በማክበር የግብር እና ቀረጥ ግዴታዎችን በተገቢው ጊዜ እና መንገድ መወጣት ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ የታክስ አስተዳዳር ከግብር ከፋዮቹ የሚጠብቀው መሠረታዊ ግዴታዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም፡-

1. በግብር ከፋይነት መመዝገብ፣
2. ግብርን በወቅቱ እና በትክክል ማሳወቅ፣
3. በትክክል ሪፖርት ማድረግ ወይም ትክክለኛ ደጋፊ ማስረጃዎች ማቅረብ እና
4. ግብርን መክፈል ናቸው፡፡
1. በግብር ከፋይነት መመዝገብ፡-

እያንዳንዱ በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኝ እና በግብር ከፋይነት መመዝገብ የሚጠበቅበት ግለሰብ እና ተቋም በሙሉ በራሱ ተነሳሽነት ወደ ታክስ መረቡ መምጣት እና በግብር ከፋይነት መመዝገብ ይገባዋል፡፡

መመዝገብ ለሚመለከተው የታክስ ዓይነት ሁሉ መመዝገብን ይጨምራል፡፡ ለአንዱ የታክስ ዓይነት ተመዝግቦ ለሌላው አለመመዝገብ የህግ ተገዥ አያሰኝም፡፡

በእኛ አገርም ያለው የግብር ከፋዮች ምዝገባ ሥርዓት የጣት አሻራ መስጠትን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማውጣትን እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የሂሳብ መዝገብ መያዝን የሚያካትት በመሆኑ እያንዳንዱ ግብር ከፋይ እነዚህን ሥርዓቶች አሟልቶ በግብር ከፋይነት መመዝገብ ይጠበቅበታል፡፡

2. ታክስ ማስታወቅ፡- በሌላ በኩል ከአንድ በግብር ከፋይነት የተመዘገበ ግብር ከፋይ የሚጠበቀው ሌላኛው ግዴታ የግብር ሰብሳቢው ተቋም ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እና ባስቀመጠው ግብርን የማሳወቂያ መንገድ ተጠቅሞ ለግብር ሰብሳቢው ተቋም መክፈል የሚገባውን የታክስ መጠን ማሳወቅ ነው፡፡ ይህም ማለት ከነበረው የሽያጭ መጠን እና በህግ የተፈቀዱ ተቀናሽ ወጪዎች አንጻር እንዲሁም በህግ በተቀመጡ የታክስ ቀመሮች አንጻር ለገቢ ሰብሳቢው መክፈል የሚገባው የታክስ መጠን በራሱ አስልቶ ግብር ሰብሳቢው ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እና ባዘጋጀው መንገድ ማሳወቅ ነው፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር እንደ ታክሶቹ ዓይነት የማሳወቂያ የጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠ ሲሆን በተቀመጠው አግባብ ማሳወቅ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ለየታክስ/ግብር አይነቱ የተለያየ ማስታወቂያ ቅጾች የተዘጋጁ በመሆኑ ቅጾቹን በአግባቡ ሞልቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ጀምሮም ተቋሙ ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ግብራቸውን የሚያሳውቁበት ስርዓርአትንም ዘርግቷል፡፡

3. ሪፖርት ማድረግ፡- የሚጠበቅበትን የግብር መጠን ያሳወቀ ግብር ከፋይ ያሳወቀው የታክስ መጠን ትክክለኛ ስለመሆኑ በደጋፊነት ሊያስረዱለት የሚችሉ የተለያዩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

እነዚህም ሪፖርቶች በዋናነት የገቢ መግለጫ /income statement/፣ የሂሳብ መዝገብ /balance sheet/፣ የገንዘብ ፍሰት /cash flow/ እና የመሳሰሉትን ያካትታሉ፡፡

4. ታክስ መክፈል፡- በአራተኛ ደረጃ ከአንድ ግብር ከፋይ የሚጠበቀው ግዴታ በራሱ ፈቃድ መክፈል ይገባኛል በማለት አምኖ ያሳወቀውን እንዲሁም በተለያዩ ሪፖርቶች ያረጋገጠውን የታክስ መጠን በግብር ሰብሳቢው ተቋም በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መክፈል ነው፡፡

ይህም ማለት አመታዊ የሆኑትን በየዓመቱ በተቀመጠው ጊዜ፣ ወርሃዊ እና ሌሎቹንም በተቀመጠላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት መክፈል ነው፡፡

፡-

👇👇👇👇👇

የፌስቡክ ገፅ (https://www.facebook.com/profile.php?id=61562204634443

የቲክቶክ ገፅ (https://vm.tiktok.com/ZMkhEJbMb/

የቴሌግራም ገፅ (https://t.me/SNNPRS_Revenue_Bereau

የዩቲዩብ ገፅ (https://youtube.com/?si=ELneJRp2Lj7xJ8GK

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

https://www.facebook.com/share/p/1AbjwcLTkz/
20/04/2025

https://www.facebook.com/share/p/1AbjwcLTkz/

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ይመኛል!
መልካም በዓል!
***********
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች

https://www.facebook.com/share/1KcmSmDtkN/
15/04/2025

https://www.facebook.com/share/1KcmSmDtkN/

የቴምብር ቀረጥ የሚከፈልባቸው ሰነዶች

ሚያዚያ 07/2017 ዓ.ም

በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 110/90 በአንቀጽ-3 መሰረት በሚከተሉት 12 ሰነዶች የቴምብር ቀረጥ እንዲከፈልባቸው ያዛል፡-

1. የማህበር መመስረቻ ፅሁፍና መተዳደሪያ ደንብ
2. ግልግል ሰነድ
3. ማገቻ
4. የዕቃ ማከማቻ ማረጋገጫ ሰነድ
5. ውል፣ ስምምነትና የእነዚህ መግለጫ
6. የመያዣ ሰነዶች
7. የሕብረት ስምምነት
8. የስራ ቅጥር ውል
9. የኪራይ፣ የተከራይ አከራይ ማረጋገጫ
10. ማረጋገጫ
11. የውክልና ስልጠና
12. የንብረት ባለቤትነት ማስመዝገቢያ ሰነድ
፡-

👇👇👇👇👇

የፌስቡክ ገፅ (https://www.facebook.com/profile.php?id=61562204634443

የቲክቶክ ገፅ (https://vm.tiktok.com/ZMkhEJbMb/

የቴሌግራም ገፅ (https://t.me/SNNPRS_Revenue_Bereau

የዩቲዩብ ገፅ (https://youtube.com/?si=ELneJRp2Lj7xJ8GK

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

Address

Snnprsrevenuea@gmail. Com
Awassa
1709

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ:

Share