25/08/2026
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሜቴ ሊቀመንበር በመሆን ተመረጡ
____________
ዶ/ር መቅደስ ሊቀመንበርነቱን ከማሊ የጤና እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ኮሎኔል አሳ ባዲያሎ ቱሬ ተረክበዋል።
በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ የዛሬ ውሎ ሁለት የኮሚቴው ምክትል ሊቀ መንበሮችንም ሾሟል። የኒጀር የፐብሊክ የህዝብ ጤና እና ንፅህና ሚኒስትር ዶ/ር ጋርባ ሃኪሚ እና የዚምባብዌ የጤና እና የህፃናት እንክብካቤ ሚኒስትር ዶ/ር ዳግላስ ሞምቦሾራን ምክትል ሊቀመንበርነት አፅድቀዋል።
በጉባኤው ዘላቂነት ያለው የጤና ፋይናንስን በአፍሪካ በ2035 ማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የአፍሪካ የጤና የሰው ኃይል አጀንዳ የሰው ሃብት እጥረትን በ2035 ለመቅረፍ የባለሙያዎች ስልጠና ላይ ትኩረት ማድረግን እንደሚጠይቅ በመድረኩ ተገልጿል።
በተጨማሪም በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ነሀሴ 19/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
👇👇👇👇 ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/1EUdJhqmFM/
https://www.facebook.com/1000649355740¡57/posts/1065870482254128/
Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
https://chat.whatsapp.com/K7W4vwM1mqG8SyGz4PYC71
YouTube:
https://youtube.com/?si=bjGP9rGIpwIlZWQX
Tik Tok:
https://vm.tiktok.com/ZMBCWXXxa