Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Fayinansete Biiro.ሲ/ብ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Fayinansete Biiro.ሲ/ብ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ

Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Fayinansete Biiro.ሲ/ብ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Fayinansete Biiro.ሲ/ብ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ, Public & Government Service, Awassa.

የሲዳማ ከልል ገንዘብ ቢሮ የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት እና አስተዳደር  ሥርዓት ላይ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።‎፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨‎‎ኮሙኒኬሽን ዳይሬክ...
29/05/2026

የሲዳማ ከልል ገንዘብ ቢሮ የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት እና አስተዳደር ሥርዓት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
‎፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

‎ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬ - ሀዋሳ

‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ከክልሉ ፕላን ቢሮ ጋር በመቀናጀት ለክልል ማዕከል ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት በዕቅድ፣ በጀት ዝግ/ዳይሬክቶሬቶችና ለበጀት ቡድን መሪዎች የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትእና አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

‎በስልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ሀርሲሳ ዕቅድ ማለት አንድን ግብ ወይም ራዕይ ለማሳካት አስቀድሞ የሚዘጋጅ ዝርዝር የድርጊት መርሃ ግብር ሲሆን፤ ተግባሮችን በዘመናዊ መንገድ ለመስራት፣ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም፣ ውሳኔዎችን ለማሳለጥ እና ስኬትን ለመለካት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሰነድ ወይም አቅጣጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

‎አክለውም የፕሮግራም በጀት ዋና ዓላማው ያለንን ውስን ሀብት ውጤት በሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ማዋልን እና ዕቅድን ከበጀት ጋር ማስተሳሰር መሆኑን ገልፀዋል።

‎የስልጠና መድረኩ ዋና ዓላማ የፕሮግራም በጀት ውጤታማ ለማድረግ የልማት ዕቅድ ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት የመፈጸም አቅማቸውን ለማጎልበት ታስቦ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አስገንዝበዋል።

‎በስልጠና መድረኩ ላይ የፕሮግራም በጀት የሚያመላክት የመወያያ ሠነድ የቀረበ ሲሆን፤ በቀረበው ስነድ ላይ የፕሮግራም በጀት ዝግጅት እና አስተዳደር፣ የፕሮግራም በጀት አሰራር፣ የበጀት ምንነት፣ የበጀት አይነቶች፣ የገቢ እና ወጪ በጀት አይነቶች፣ የበጀት ሚና፣ የዕቅድ ዝግጅት እና አጠቃላይ የፕሮግራም በጀት ፅንሰሃሳብን በሚመለከት በዝርዝር ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

‎የሰልጠና ተሳታፊዎች ከስልጠናው ጠቃሚ ሀሳቦች ማግኘታቸውን ጠቅሰው የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ተግተው እንደሚሠሩ ከሰጡት አስተያዬት ለመረዳት ተችሏል ።

‎በመጨረሻም ከቀረበው ሰነድ በመነሳት ከመድረኩ ተሳታፊዎች በኩል ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው በቢሮው ኃላፊ አቶ ኃይሌ ሀርሲሳ እና የሲዳማ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በዶ/ር ዮሐንስ ዮና መልስና ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበት፤ ለቀጣይ ከክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በቅንጅት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ስልጠና መድረኩ ተጠናቋል፡፡

‎ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

‎ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት:-
‎ፌስ ቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067066834036
‎Telegram: https://t.me/+ou6fpnGJwUEwNmM0
‎Whats App:https://chat.whatsapp.com/BwVha2qdJYkK1WhdgCjffr?mode=wwt
‎Tik tok: 335?
‎Emial: Fananice bureaus @ gmail.com
‎You tube: Sidama Region Fanance Bureau
‎Follow, Share, Like, በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

ሲዳማ ክልል የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ተአማኒ እንዲሆን በጋራ ለመስራት ቃል ገቡ ሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ፣ግንቦት 19/2018 በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚገኙ 2...
27/05/2026

ሲዳማ ክልል የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ተአማኒ እንዲሆን በጋራ ለመስራት ቃል ገቡ

ሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ፣ግንቦት 19/2018

በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚገኙ 23 ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤት የተዘጋጀ ውይይት በማካሄድ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ተአማኒ፣ ነጻ እና ቅቡልነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትብብር ለመስራት ቃል ገብተዋል።

የውይይት መድረኩ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ በክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እና በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ በለጠ ሰጌቦ መሪነት ተካሂዷል። በመድረኩ የተለያዩ ፓርቲ ተወካዮች ተሳትፈው ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ዋና ትኩረት የፖለቲካ ተፎካካሪዎች መካከል መተማመንን ማጠናከር፣ የምርጫ ሂደትን ማሻሻል እና ከቀድሞ ምርጫዎች በተሻለ መልኩ ለማስፈጸም ሁሉም በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

ተሳታፊዎቹ በምርጫ ወቅት ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን በቅድሚያ ለመለየት፣ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ሰላማዊ የፖለቲካ ተወዳዳሪነትን ለማጠናከር በጋራ መሥራት እንዳለባቸው በአጽንኦት አንስተው ልዩነቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል።

በመድረኩ ውስጥ የምርጫ ሕጋዊ ሂደቶችን ማክበር፣ የምርጫ ደንቦችን በትክክል መፈጸም እና ሕዝቡ ፍላጎቱን በነጻነት እንዲገልጽ ማስቻል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ የፖለቲካ ውድድር በኃይል ሳይሆን በሐሳብ መሆን እንደሚገባም በግልጽ ተነስቷል።

በምርጫ ሂደት ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ሕጋዊ አሰራር እንዲጠናከር ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶ የምርጫ መርሆዎች በጥብቅ እንዲከበሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ተሳታፊ ፓርቲዎች 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለህዝብ ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በቀጣይ በትብብር ለመስራት ቃል በመግባት ምርጫው ለሀገራዊ ሰላም ወሳኝ እንደሆነ አስረግጠዋል።

በርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ስድስት ተቋማት በምስልየሲዳማ ክልል ገንዘብ  ቢሮ ግንቦት 19/2018
27/05/2026

በርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ስድስት ተቋማት በምስል

የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ግንቦት 19/2018

በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በሀዋሳ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ ሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ፣ግንቦት 18/2018 በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በስፋት ተሳትፈው የ“ም...
26/05/2026

በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በሀዋሳ በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

ሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ፣ግንቦት 18/2018

በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በስፋት ተሳትፈው የ“ምረጡ” እና የድጋፍ መልዕክቶችን በቄጣላ እንዲሁም በተለያዩ ሁነቶች መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።

“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚደረገው ይህ የ“ምረጡ” ቅስቀሳ የህዝብ ንቃተ ህሊናን ለማጠናከርና የፖለቲካ ተሳትፎን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የምርጫ ቅስቀሳው በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በተደራጀና በደመቀ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች በባነሮች፣ በመፈክሮችና በተለያዩ የድጋፍ ምልክቶች የፓርቲውን አቋም አንጸባርቀዋል ።

የርዕሰ መስተዳደሩ ንግግር በሲዳማ ክልል በክልል አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የ“ምረጡኝ” ቅስቀሳ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ባደረጉት ንግግር፣ ብልፅግና ፓርቲ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሀገሪቱ የተመዘገቡ የልማት፣ የሰላምና የኢኮኖሚ ውጤቶች ለህዝቡ ተጨባጭ ተስፋ እንደፈጠሩ ገልፀዋል።

አቶ ደስታ በንግግራቸው፣ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” የሚለው መሪ ቃል የተሻለች፣ የተረጋጋችና በልማት የበለጸገች ሀገር ለመገንባት የተያዘ ራዕይ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ህዝቡ በ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ጉዞ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

በሀዋሳ በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተሳተፉ የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በአንድነት፣ በሰላምና በልማት ዙሪያ የሚያተኩሩ መፈክሮችን በማሰማት ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም የተካሄደው መርሃ ግብር በተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶች፣ የድጋፍ መልዕክቶችና የህዝብ ተሳትፎ የተደመቀ ሲሆን፣ በክልሉ የፖለቲካ ንቃተ ህዝብን ለማጠናከር ጠቃሚ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በክልል ደረጃ የብልፅግና ፓርቲ የ“ምረጡኝ” ቅስቀሳ  በሀዋሳ ከተማ አባለት፤ደጋፊዎች  ሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተ...
26/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በክልል ደረጃ የብልፅግና ፓርቲ የ“ምረጡኝ” ቅስቀሳ በሀዋሳ ከተማ አባለት፤ደጋፊዎች ሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ወጣቶች፣ ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሴቶች በነቂስ ወጥተው ወደ ሀዋሳ አለማቀፍ እስታዲየም እየተመመ ይገኛሉ ።

ሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ግንቦት 18/2018

ማህበራዊ ተጠያቂነት ኘሮግራም በዕቅድ ዝግጅት እና ቅድመ በጀት ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ።‎‎ግንቦት/15/2018 ዓ.ም‎ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት‎ይርጋዓለም‎‎በሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ በ...
23/05/2026

ማህበራዊ ተጠያቂነት ኘሮግራም በዕቅድ ዝግጅት እና ቅድመ በጀት ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ።

‎ግንቦት/15/2018 ዓ.ም
‎ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
‎ይርጋዓለም

‎በሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ በቻናል አንድ ኘሮግራም ስር በማህበራዊ ተጠያቂነት ኘሮግራም በዕቅድ ዝግጅት እና ቅድመ በጀት ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ አካሂዷል።

‎ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የዳሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባልቻ በላይነህ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚመደቡ ሃብቶች በመንግስት አቅም የማይደረስባቸዉን ቦታዎች በመድረስና ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው በመሆኑ ሀብቶቹን በጥንቃቄና በትኩረት ለታለመለት ዓላማ በማዋል የህብረተሰቡን ችግር መቅረፍ ይቻላል ብለዋል፡፡

‎አቶ ባልቻ አክለውም ማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት የግልፀኝነትና ተጠያቂነት መርህን ለሕዝቡ በማስረጽ ሕዝቡ ከመንግሥት ሊያገኝ የሚገባውን የልማት ተጠቃሚነት ማፋጠን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ገልፀዉ፤ የዕለቱ የውይይት መድረኩ በይፋ መከፈቱን አብስረዋል።

‎በውይይት መድረኩ ላይ በቢሮው የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ስር የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት አስተባባሪ በአቶ ዘለቀ ዶራ መወያያ ሠነድ የቀረበ ሲሆን፤ በቀረበው ስነድ ላይ በማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት (Social Accountability) ያሉ ችግሮችን በመለየት፤ ቅድሚ የሚስጣቸውን ችግሮች መለት እና በተዩት ችግሮች ዙሪያ በጥልቀት መወያየት በሚሉ ይዘቶች ላይ ስፊ ገለፃ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

‎እንዲሁም በአለታ ወንዶ፣በዳሌ እና ደራራ ወረዳዎች በማህበራዊ ተጠያቂነት (Social Accountability) ኘሮግራም የ2018 በጀት ዓመት በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩ ስራዎች እና በወረዳዎቹ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ ቅድሚ የሚስጣቸውን ችግሮች እና የተዩትን ችግሮች በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ መካትት እዳለባቸው የሚያመላክት ሪፖርት በፕሮግራሙ ፎካል ፐርሰኖች ቀርቦ፤ ከቀረበው ስራ አፈፃፀም መነሻነት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

‎ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከውይይት መድረኩ ጠቃሚ ሀሳቦችን ማግኘታቸውን ጠቅሰው ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ተግተው እንደሚሠሩ ከሰጡት አስተያዬት ለመረዳት ተችሏል ።

‎በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦች እና ጥያቂዎች የደራራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳንኤል ዳዬ፣ የዳሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በአቶ በቀለ ሁሞ እና የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮጀክት አስተባባሪ በአቶ ዘለቀ ዶራ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።

‎ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት:-
‎ፌስ ቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067066834036
‎Telegram: https://t.me/+ou6fpnGJwUEwNmM0
‎Whats App:https://chat.whatsapp.com/BwVha2qdJYkK1WhdgCjffr?mode=wwt
‎Tik tok: 335?
‎Emial: Fananice bureaus @ gmail.com
‎You tube: Sidama Region Fanance Bureau
‎Follow, Share, Like, በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።


የህዝብ ሃብት ለታለመለት ዓላማ  ማዋል ይቻል ዘንድ የኢንስፔክሽን እና ውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች በቅንጅት መስራት አለባቸው፦ የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ  ኃላፊ አቶ ሀይሌ ሀርሲሳ‎፨፨፨፨፨፨፨፨...
22/05/2026

የህዝብ ሃብት ለታለመለት ዓላማ ማዋል ይቻል ዘንድ የኢንስፔክሽን እና ውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች በቅንጅት መስራት አለባቸው፦ የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ሀርሲሳ
‎፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

‎ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
‎ ግንቦት 14/2018 ዓ.ም
‎ ይርጋ ዓለም


‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከክልል ፣ ከዞኖች፣ ከተቋማት፣ ከወረዳዎች እና ከከተማ አስተዳደር ለኢንስፔክሽን እና ውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሙያዊ ስልጠና ተጠናቀቀ።

‎በስልጠዉ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ሀርሲሳ በንግግራቸዉ የተሰጣችሁን ሰልጠና ተግባራዊ በማድረግ የኦዲት መመሪያዎች እና ደንቦችን በመተግበር የኢንስፔክሽን እና ውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።

‎አክለውም በኦዲት አፈፃፀም ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን እና ጉድለቶችን በጋራ እያረምን በመሄድ ለሚታዩ ለውጦች ትኩረት ሰጥተን በመስራት የፋይናንስ አስራር ህጉን በጠበቀ መልኩ የህዝባችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መፍታት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

‎በስልጠና መድረኩ ላይ በኦዲት ፅንስ ሀሳብ ፣በፋይናንሻል ኦዲት ፣በክዋኔ ኦዲት እና በተደጋጋሚ የሚገኙ የኦዲት ግኝት ዙሪያ የማያመላክቱ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

‎ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከስልጠናው ጠቃሚ ሀሳቦችን ማግኘታቸውን ጠቅሰው ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ተግተው እንደሚሠሩ ከሰጡት አስተያዬት ለመረዳት ተችሏል ።

‎ከቀረቡት ሰነዶች በመነሳት ከመድረኩ ተሳታፊዎች በኩል ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው በገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ሀርሲሳ፣ በቢሮው ም/ል ኃላፊ እና የመንግስት ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ መንገሻ ቤና እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

‎በመጨረሻም የኦዲት ግኝቶች ላይ ፈጣን የእርምት እርምጃ በመውሰድና እየባከኑ ያሉ ሀብቶች በማስመለስ ረገድ ባለሙያዎቹ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የቢሮው ኃላፊ አሳስበው፤ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች እና ለአሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ የስልጠና መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የ“ይምረጡኝ” ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በገንዘብ ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ  አስተባባሪነት  በድምቀት ተካሄደ። ‎‎  ግንቦት 14 / 2018 ዓ.ም‎  ሀዋሳ‎...
22/05/2026

የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የ“ይምረጡኝ” ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በገንዘብ ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት በድምቀት ተካሄደ።

‎ ግንቦት 14 / 2018 ዓ.ም
‎ ሀዋሳ

‎የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የ“ይምረጡኝ” ቅስቀሳ መርሃ-ግብር በገንዘብ ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ በሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተለያዩ ባላድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

‎የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ም/ል ኃላፊ እና የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸሬ ኡጋ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ፣ ነፃ፣ ተዓማኒ እና በሕዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

‎በዕለቱ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲና የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዘውዲቱ ዘለቀ እንደገለጹት ብልጽግና ፓርቲ ሀገሪቱን መምራት ከጀመረባቸው የለውጥ ዓመታት አንስቶ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን በመግለፅ በእነዚህም የልማት ሥራዎች ሕዝቡ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን መቻሉን አብራርተዋል።

‎ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የተሞክሮና የፈጠራ ማዕከል፣ የተረጋጋና ሰላማዊ እንዲሁም የኅብረብሔራዊነት ማሳያ በማድረግ የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሆን መጠነ-ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

‎ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተጓዙበት መንገድ ፈጽሞ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ማለፋቸውን የገለጹት ወ/ሮ ዘውዲቱ እነዚህ ፈተናዎች ግን የብልፅግና ራዕይን ከማጨለም ይልቅ የኢትዮጵያዊነትን ፅናት በተግባር እንዲለማመዱ ማድረጋቸውን አስገንዝበዋል።

‎ለዚህ ስኬት ደግሞ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው ሴት አመራሮችና አባላት ያሳዩት የመሪነት ጥበብና ብቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።

‎ የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ የስብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አመራር ወ/ሮ ሰላማዊት ዘሪሁን ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች ሲበለጽጉ ሀገር ትበለፅጋለች የሚለውን መርህ በተግባር ለማዋል በተደረገው ጥረት የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ከተራ ተሳትፎ ወደ ማዕከላዊ ተዋናይነት ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።

‎ብልጽግና ፓርቲ ትናንትም ሆነ ዛሬ በተግባር ላይ ያለ ፈተናዎችን ወደ ስኬትና ድል የመቀየር አቅም ያለው መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ሰላማዊት ነገም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እየሠራ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን በንግግራቸው አረጋግጠዋል።

‎በመጨረሻም በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የመወዳደሪያ ምልክት "የስንዴ ነዶ" መሆኑን እና የስንዴ ምልክቱም የአንድነት፣ የመደጋገፍ፣ የውጤታማነትና የሉዓላዊነት ተምሳሌት መሆኑ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተብራርቷል።

‎ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት:-
‎ፌስ ቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067066834036
‎Telegram: https://t.me/+ou6fpnGJwUEwNmM0
‎Whats App:https://chat.whatsapp.com/BwVha2qdJYkK1WhdgCjffr?mode=wwt
‎Tik tok: 335?
‎Emial: Fananice bureaus @ gmail.com
‎You tube: Sidama Region Fanance Bureau
‎Follow, Share, Like, በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

https://www.facebook.com/share/p/14ig2eajxmT/
20/05/2026

https://www.facebook.com/share/p/14ig2eajxmT/

በተቋማት የሚስተዋለዉን የሀብት አጠቃቀም እና ብክነት ለማዳን ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሲዳማ ክልል ገንዘብ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሌ ሀርሲ ገለፁዘጋቢ፡ ራሄል አሊ #ደሬቴድ ...

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Fayinansete Biiro.ሲ/ብ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share