23/04/2026
ዛሬ የዓለም መጽሐፍ ቀን ነው
የዓለም መጽሐፍ ቀን፤ የዓለም መጽሐፍ እና ኮፒራይት ቀን ወይም ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን በሚል ስያሜም የሚታወቅ ሲሆን፤ በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት) የሚዘጋጅ ዓመታዊ ኹነት ነው፡፡
ዓላማውም ንባብን፣ ህትመትንና የቅጂ መብት ጥበቃን ማስፋፋትና ማጎልበት ነው፡፡
የመጀመሪያው የዓለም መጽሐፍ ቀን የተከበረው እ.ኤ.አ. አፕሪል 23 ቀን 1995 ዓ.ም ሲሆን፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ በዚሁ ቀን መከበሩን ቀጥሏል፡፡
የዓለም መጽሐፍና ኮፒራይት ቀን ኹነት ላይ ዩኔስኮ ከመጽሐፍ ኢንዱስትሪው ትላልቅ ዘርፎች ከተውጣጣ አማካሪ ኮሚቴ ጋር በመሆን፣ ለአንድ ዓመት የዓለም መጽሐፍ መዲናን ይመርጣሉ፡፡ ለዓመቱ የተሰየመ የዓለም መጽሐፍ መዲናም መጽሐፍትንና ንባብን ለማክበርና ለማስፋፋት የተለያዩ መርሃግብሮችን ዓመቱን ሙሉ ያከናውናል፡፡
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!!!
"ዛሬም በንባብ፣ ለንባብ፣ ስለንባብ እንተጋለን!!!"