08/03/2026
ኢራን ሶሰተኛውን አያቶላህ መረጠች
የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሁለተኛው ልጅ ሞጅታባ ኻሚኔ ቀጠዩ ሁለንተናዊ መሪ ሆነዋል።
ባለ88 ዓባላቱ አሰምብሊ ለአዲሱ ተመራጭ የኢራን ህዝብ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።
ህዝቡ የአገሪቱን በሄራዊ አንድነትም እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦለታል።
ሶስተኛው ጠቅላይ መሪ የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ቦታውን መረከብ የቻሉ ሲሆን ለቴህራን አንድነት ይሰራሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በሞጅታባ ሀሳብ እና አሰራር ውስጥ ህዝቡ ተገዥ ሆኖ እንዲያልፍም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ኢራናውያን ፖለቲካዊ መረጋጋት ሊፈጠርላቸው ይችላል ቢባልም አዲሱ አያቶላህ በአሜሪካ ዒላማ ይሆናል በሚል ፕሬዚዳንት ትራምፕ መዛታቸው ይታወሳልና ሌላ ስጋት ጋርጧል።
በሰሜን ምስራቅ ማሻሀድ በ1961 ዓ.ን የተወለዱት ሙጅታባ ትልቅ ሀላፊነትን ተቀብለዋል ተብሏል።
በ17 ዓመታቸው በኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ወታደራዊ አገልግሎትም ሰተዋል።
አልጀዚራ እንዳስነበበው።
Qafar agatih inkiinoh uguugumoh fooca ゚