صالح عبد الله Salih Abdella

صالح عبد الله
Salih Abdella ▒F░O░L░L░O░W▒
┊ ▕▔╲▂▂▂╱▔|
━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭
╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃
┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕
┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕
┃⠀╰▓▒░M░E░▒

✴️ በቴህራን የሚገኘው የተግባራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሞስታፋ ኾሽቼሽም ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከት...
11/07/2026

✴️ በቴህራን የሚገኘው የተግባራዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ሞስታፋ ኾሽቼሽም ለአልጀዚራ እንደተናገሩት በቀድሞው ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢራናውያን የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀው እየጠየቁ ይገኛሉ። ፕሮፌሰሩ ይህን ያሉት የቀድሞው መሪ የሽኝት ስነ-ስርዓት ከመካሄዱ በፊትም ህዝቡ ቁጣውን ሲገልጽ እንደነበር በማስታወስ ነው።

አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ግድያ ለመበቀል የገቡትን ቃል በተመለከተ ፕሮፌሰሩ ሲያብራሩ፣ ኢራናውያን በየምሽቱ አደባባይ በመውጣት እያሰሙ ያሉት ድምጽ እያደገ ለመጣው የህዝብ የበቀል ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መሆኑን ገልጸዋል።

"አሜሪካውያን የኢራንን መሪ እና ከፍተኛ ጄኔራሎች መግደላቸው ትክክል ነው፣ ኢራናውያንም ይህን አምነው ዝም ብለው መቀመጥ አለባቸው የሚል ማንም ሰው በዓለም ላይ ይኖራል ብዬ አላምንም" ያሉት ኾሽቼሽም፣ አሜሪካውያን ለፈጸሙት ጥቃት ተገቢውን ዋጋ ካልከፈሉ፣ በአደባባይ እያስጠነቀቁ እንዳሉት አዲሱንም ጠቅላይ መሪ ከመግደል ወደኋላ እንደማይሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

አሜሪካውያን ከኢራን ጋር ለሚደረግ ለማንኛውም ዓይነት ስምምነት ታማኝ ሆነው ስለማያውቁ፣ በቀጣይ ቀናት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግጭት እና ወታደራዊ ውጥረት መባባሱ ፈጽሞ የማይቀር ጉዳይ መሆኑን ምሁሩ አክለው አስጠንቅቀዋል" ስል የዘገበው አልጀዚራ ነው
صالح عبد الله
Salih Abdella

የህወሓት ስራ አስፈጻሚና የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) ዛሬ በወቅታዊና ተለዋዋጭ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች...
30/06/2026

የህወሓት ስራ አስፈጻሚና የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) ዛሬ በወቅታዊና ተለዋዋጭ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በሰጡት መግለጫም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በክልሉ የነበረውን ግልጽ ተኩስና ደም መፋሰስ እንዲቆም ማድረጉ የሚታወስ ቢሆንም፣ የዚሁ ስምምነት ውጤት የሆነው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ግን የትግራይ ህዝብ በረቂቅና በሰላሕታ የመጥፋት አደጋው እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ያመቻቸበትና የተሰራበት አግባብ እንደነበር በምሬት ገልጸዋል።
ኃላፊዋ አክለውም፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ውስጥ የሕግ የበላይነትንና ሥርዓትን ለማስከበር እንዲሁም የሕዝቡን ህልውናና ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ የሚደረገው ዘርፈ ብዙ ጥረት በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ቁመናና አቋም ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በተያያዥም በተለያዩ አጋጣሚዎችና ምክንያቶች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የጠላቶች መጠቀሚያና መገልገያ በመሆን ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ፣ ከዚህ ድርጊታቸው ተቆጥበው ወደ ቀያቸውና ወደ ሀገራቸው በመመለስ ከሕዝባቸው ጋር በሰላም እንዲኖሩ ጥሪ አቅርበዋል።

صالح عبد الله
Salih Abdella follow me 🙏🙏

19/06/2026

Celebrating my 3rd year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

ኢራን ሶሰተኛውን አያቶላህ መረጠችየአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሁለተኛው ልጅ ሞጅታባ ኻሚኔ ቀጠዩ ሁለንተናዊ መሪ ሆነዋል።ባለ88 ዓባላቱ አሰምብሊ ለአዲሱ ተመራጭ የኢራን ህዝብ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ...
08/03/2026

ኢራን ሶሰተኛውን አያቶላህ መረጠች

የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሁለተኛው ልጅ ሞጅታባ ኻሚኔ ቀጠዩ ሁለንተናዊ መሪ ሆነዋል።

ባለ88 ዓባላቱ አሰምብሊ ለአዲሱ ተመራጭ የኢራን ህዝብ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

ህዝቡ የአገሪቱን በሄራዊ አንድነትም እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦለታል።

ሶስተኛው ጠቅላይ መሪ የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ቦታውን መረከብ የቻሉ ሲሆን ለቴህራን አንድነት ይሰራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በሞጅታባ ሀሳብ እና አሰራር ውስጥ ህዝቡ ተገዥ ሆኖ እንዲያልፍም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ኢራናውያን ፖለቲካዊ መረጋጋት ሊፈጠርላቸው ይችላል ቢባልም አዲሱ አያቶላህ በአሜሪካ ዒላማ ይሆናል በሚል ፕሬዚዳንት ትራምፕ መዛታቸው ይታወሳልና ሌላ ስጋት ጋርጧል።

በሰሜን ምስራቅ ማሻሀድ በ1961 ዓ.ን የተወለዱት ሙጅታባ ትልቅ ሀላፊነትን ተቀብለዋል ተብሏል።

በ17 ዓመታቸው በኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ወታደራዊ አገልግሎትም ሰተዋል።

አልጀዚራ እንዳስነበበው።

Qafar agatih inkiinoh uguugumoh fooca ゚

ቀን 5፡ የአምስት ቀናት ጦርነት፣ አምስት ቢሊዮን ዶላር መክሰር፡ አሜሪካውያን ለዋሽንግተን የኢራን ቁማር ዋጋ እየከፈሉ ነውበግጭቱ የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ (እስከ መጋቢት 4 ቀን ...
05/03/2026

ቀን 5፡ የአምስት ቀናት ጦርነት፣ አምስት ቢሊዮን ዶላር መክሰር፡ አሜሪካውያን ለዋሽንግተን የኢራን ቁማር ዋጋ እየከፈሉ ነው

በግጭቱ የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ (እስከ መጋቢት 4 ቀን 2026 ድረስ) ባለው መረጃ መሠረት፣ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የአጸፋ ጥቃት እና ተያያዥ ክስተቶች ምክንያት ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የቀጥታ ወታደራዊ ቁሳቁስ ኪሳራ እንደደረሰባት ተዘግቧል። የዋና ዋና የአሜሪካ ወታደራዊ ኪሳራዎች ዝርዝር፤ አጠቃላይ የሚገመተው የቁሳቁስ ውድመት በግምት 1.902 ቢሊዮን ዶላር ነው፦

1.1 ቢሊዮን ዶላር የራዳር ሲስተም፦ በኳታር አል ኡዴይድ የአየር ጦር ሰፈር የሚገኝ የ AN/FPS-132 Block 5 ቅድመ ማስጠንቀቂያ ራዳር በየካቲት 28 በኢራን ሚሳኤል ጥቃት ወድሟል።

500 ሚሊዮን ዶላር የሚሳኤል መከላከያ፦ በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ አል-ሩዋይስ ኢንዱስትሪ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የ THAAD (Terminal High Altitude Area Defense) ሲስተም የራዳር አካል ወድሟል።

282 ሚሊዮን ዶላር የአውሮፕላን ኪሳራ፦ በመጋቢት 1 ቀን ከኩዌት የአየር መከላከያ ጋር በተያያዘ በደረሰ የ"friendly fire" (በስህተት በባልደረባ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት) አደጋ ሶስት F-15E Strike Eagle ጄቶች ወድመዋል።

20 ሚሊዮን ዶላር የባህር ኃይል መገናኛ፦ በባህሬን የሚገኘው የአሜሪካ ባህር ኃይል 5ኛው የጦር መርከብ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሁለት የሳተላይት መገናኛ ተርሚናሎች እና በርካታ ሕንፃዎች በኢራን ጥቃት ተመትተዋል።

ለግብር ከፋዩ ህዝብ ያለው አጠቃላይ የጦርነት ወጪ
ከቀጥታ የቁሳቁስ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የ"Operation Epic Fury" (ዘመቻ ኢፒክ ፊውሪ) ሰፊ የኢኮኖሚ ተፅእኖ በፍጥነት እየጨመረ ነው፦

5 ቢሊዮን ዶላር የመጀመሪያ ድምር፦ የ"Center for American Progress" ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2026 ድረስ ለአሜሪካ ግብር ከፋዮች የደረሰው አጠቃላይ ወጪ ከ5 ቢሊዮን ዶላር አልፏል።

የዕለት ተዕለት የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች፦ በክልሉ ውስጥ ሁለት የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን ማቆየት በቀን ከ13 ሚሊዮን እስከ 22.8 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል።

የጥይት እና የትጥቅ ወጪ፦ የአሜሪካ ጦር በዘመቻው የመጀመሪያ 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ 200 የሚጠጉ ቶማሃውክ (Tomahawk) ሚሳኤሎችን ጨምሮ ለጥይትና ትጥቅ በግምት 779 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉ ተዘግቧል።

የረጅም ጊዜ ግምቶች፦ የ"Penn Wharton Budget Model" የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚገምቱት፣ እንደ ጦርነቱ ቆይታ በቀጥታ በግብር ከፋዩ ላይ የሚደርሰው ወጪ ከ40 ቢሊዮን እስከ 95 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል።

የሰው ኃይል እና የዲፕሎማሲ ኪሳራዎች (ሰብአዊ ጉዳት)፦

ቢያንስ ስድስት የአሜሪካ የጦር አባላት በውጊያ ላይ ተገድለዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ አራቱ በኩዌት ሹአይባ ወደብ ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት ነው።

የኤምባሲዎች መዘጋት፦ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኩዌት እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ተልእኮዎች ኢላማ ተደርገዋል ወይም በሁኔታው መባባስ ምክንያት ተዘግተዋል።

የአፋሩ ኤርኔስቶ ቼጉቬራ (ሃጂ Ebrahim Usman Aliyu   ) ✊================================ ሰው ስትሆን እንደ ሀጂ ኢብራሂም ማሰብ ትጀምራለህ!!! ሀጂ ኢብራሂ...
30/01/2026

የአፋሩ ኤርኔስቶ ቼጉቬራ (ሃጂ Ebrahim Usman Aliyu ) ✊
================================

ሰው ስትሆን እንደ ሀጂ ኢብራሂም ማሰብ ትጀምራለህ!!!

ሀጂ ኢብራሂም የአፋር ክልል ብልፅግና ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረ ሰው ነው። የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የአርብቶአደርና ግብርና ቢሮ ኃላፊም ነበር።

ይህ ቢሮ ከ 700 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የሚያንቀሳቅስ፣ በስሩ ደግሞ ብዙ ፕሮጀክቶችንና NGO'S ይመራል። እነ አለም ባንክ፣ አፍሪካ ልማት ባንክ ብቻ ቢሮው በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ በጀቶችን ያንቀሳቅሳል። እነዚህ ብሮች በሙሉ በሀጂ ኢብራሂም ፊርማ ነው የሚንቀሳቀሱት።

በክልሉ ከሚገኙ ሴክተር ቢሮዎች ከየትኛውም ቢሮ በላይ ብር ለመዝረፍ አመቺ የሆነውም ይኸው ቢሮ ነው። አይደለም ተዝረክርከህ ሲስተማቲካሊ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነህ ራሱ እንደልብ ብር የሚታፈስበት አረ እንዲያውም ብር የሚታተምበት ቢሮ ነው። ብዙዎች ወደዚች ቢሮ ለመምጣት ጥሩ የአወል አርባ ገረድ ህነዋል። አስቀውታል፣ ቡና አጣጥተውታል፣ እጅ አስታጥበውታል። ዘፍነውለታል፣ ተረትና ምሳሌ ነግረውታል። ይኼ ሁሉ የግርድና ፉክክር የሚደረገው እዚች ቢሮ ላይ ለመሾምና የቋመጡለትን በጀት ለመዝረፍ ሲሉ ነው ራሳቸውንና ክብራቸውን አሳልፈው ለአወል አርባ የሰጡት። ይሁንና አወል አርባ እዚህ ቢሮ ላይ የማያሸረግደውንና ኩሩውን ባለ ግርማ ሞገሱ ሀጂ ኢብራሂምን ሾመ። ሀጂ ኢብራሂም ማለት በጣም እጅግ የተማረ ነው። መማር ብቻ አይደለም የእውቀት ባለቤትም ጭምር ነው። ሁሉም ሰው የተማረ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ግን አዋቂ መሆን አይችልም። በዚህም መሠረት መማርና ማወቅ ልዩነት እንዳለው ልብ በሉልኝ።

ሀጂ ኢብራሂም በክልላችን ውስጥ ካሉ ካቢኔዎች በሙሉ በእውቀት የላቀ ነው። ያወቀውንም ወደ መፅሀፍት በመቀየር እውቀቱን ለህዝቡ አካፍሏል። በአፋርኛ ቋንቋ ከ 3 በላይ መፅሀፍቶችንም ፅፏል። ለአብነት ከዛሬው ርዕሴ ጋ ስለሚሄዱት ሁለት መፅሀፍቶቹ ልጥቀስ...

አንደኛው 'Madma Le Miraaca' በአማርኛ ሲተረጎም "ውጤማ መሪ" የሚል ሲሆን መፅሀፉ አንድ መሪ ውጤታማ መሆን የሚችልባቸውን መንገዶችና ጥበቦችን የሚያትት ሲሆን፣ ሁለተኛው መፅሀፍ ደግሞ 'Carbi Haxxisso Kee Kalali Makcá gur' "በጦርነት የማሸነፍ ስልት እና የመከላከል ስትራቲጂ" የሚል ሲሆን። ቻይናዊውን የጦር ሊቅ ሱን ዙ The Art of War መፅሀፍን መነሻ ዋቢ ከማድረግ በተጨማሪም ተጨባጭ የሆነውን የራሱ የረጂም አመታት የጦር ሜዳ ልምድና ተሞክሮዎች የተካተቱበት፣ ሁለቱን አንድ ላይ በመጭመቅ ምርጥና ለቀጣይ ትውልድ እንደመማሪያ የሚያገለግል መፅሀፍ ሆኖ ይቀጥላል። ይህም በአፋር ታሪክ በጦርነት ዙሪያ የተፃፈ ብቸኛው የአፋርኛ መፅሀፍ ይመስለኛል።

ሀጂ ኢብራሂም እንደ አወል አርባ ተግባር የሌለው ወሬ እያወራ የራሱንም ሆነ የሰዎችን ጊዜ አያባክንም።
እንደ አወል አርባ ሰው የሌለበትን ድክመት ሰው ላይ አያላክም! እንደ አወል አርባ የሰውን ስም አያጠፋም! እንደ አወል አርባ የሰውን ክብር አያጎድፍም! እንደ አወል አርባ በህዝብ ፊት አይቀልም። ሀጀ ኢብራሂም ግርማን ከነሞገሱ የተቸረ የመልካም ስብዕና ባለቤት ነው!

ያ ዞል ኢስማዕኒ አሹፈክ አልፈርቁ በይነል በጠል ወ-ደዩስ.. ... አል አድምጠኝ ቢል-ጥሞና ....
ሀጂ ኢብራሂም ትንሽ ይናገራል ብዙ ይፈፅማል። አቶ አወል ደግሞ ብዙ ያወራል ምንም አይፈፅምም! ውሸት ብቻ! ቱሪናፋ... ውታፍ ነቃይ፣ ስራው ወሬ ማሳመር ብቻ ነው። አወል 40 የመድረክ ላይ ቼጉቬራ ነው። በፊት አብረው ሳሉ ለካቢኔው ስለ ሀጂ ኢብራሂም ውጤታማ አመራርነት ደጋግሞ ያወራ ነበር። ሁሉም ካቢኔዎች የሱን ፈለግ እንዲከተሉና አርአያቸው እንዲሆን ይመክር ነበር። አሁንስ ካልን...... ስሙን ለማጥፋት መምራት አይችልም ብሎ ለማስወራት የሄደበትን ርቀት ብታዩ የሰውየውን ክፋት ትረዳላችሁ። ዛሬ በሀሳብ ስለተለየው፣ ተው አካሄድህን አስተካክል ስላለው የትናንቱን ምስክርነት ረስቶ ተገልብጦ ስሙን ለማጥፋት ሞከረ። ሆኖም አልተሳካም። ምክንያቱም ሀጂ ኢብራሂም ማን እንደሆነ ሁሉም ያውቃል። በአለም ላይ ያሉ ጭቃዎችን በሙሉ እየቀባህ ልታቆሽሸው ብትሞክር እንኳን የሚቆሽሽ ስም የለውም። ስሙን በደማቅ የወርቅ ብዕር ማንም ከማይደርስበት ከፍታ ላይ የሰቀለ የአፋርነት (የአፋርዮ) መገለጫ ነው።

ሰውየው የአመራር ሊቅ ብቻ አይደለም። ምርጥ የወታደራዊ እውቀት ባለቤት ነው። ለሱ የውጊያ ስትራቴጂን መንደፍ አፍ ውስጥ ምግብ እንደመጉረስ ይቀለዋል። በካርታ ብቻ አይደለም በነደፈው የጦርነት ስልት ውጤታማም ጭምር ነው። ከወታደሮቹ ጋ እንደወታደር በየጫካው፣ በየጢሻው፣ በየበረሃው አዳሩንና ውሎውን አድርጎ ከምቾት ቀጠና ወጥቶ ለህዝቡ ህይወቱንም ጭምር ለመስጠት ሁለቴ የማያስብ እጂግ ደፋር ጦረኛ ነው። በህወሐትና በጂቡቲ ኢሳ የወረራ ጊዜ በተግባር አሳይቷል። አቶ አወል አርባ ከነቤተሰቡ ወደ አአ ሸሽቶ በቀን 10 ጊዜ ሀጂ ኢብራሂም ጋ እየደወለ ነበር የጦርነት ዜናውን ከሀጂ ኢብራሂም አንደበት የሚሰማው። አየህ እዚህ ጋ ነው የሁለቱ ልዩነት የሚገባህ። ይሄኛው ህዝቡን ለማዳን በህዝቡ ላይ የመጣውን ጠላት ከፊት ሆኖ ይመክታል። ሞትም ከመጣ ለአፋር ህዝብ ለመሠዋት ዝግጁነቱን በተግባር ሲያሳይ ያኛው ደግሞ ህዝብን መመከት ሲገባው ከነቤተሰቡ አምልጦ ዳጉ በስልክ ያደርጋል። ታዲያ የአፋር ህዝብ ከአወል አርባ በላይ ለሀጂ ኢብራሂም ህይወቱንም ጭምር ለመስጠት እንዴት ይሳሳል። ለነሱ እንደሚያስብ ስለነሱ ሲል ጊዜያዊ ጥቅሙንና የሚወዳቸውን ቤተሰቦች ጥሎ እንደመጣ 200% እርግጠኞች ስለሆኑ ነው። በህዝብ ዘንድ እምነት ከማግኘት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር ይሆን..?!!!!

ይቀጥላል .....

በክፍል ሁለት ሀጂ ኢብራሂም ወደትጥቅ ትግል እንዲገባና ህዝቡም ንቅቅልል ብሎ ወደሱ በመሄድ የትጥቅ ትግሉን የተቀላቀለበት መንገድ ሰፋ ባለ መልኩ የምንዳስስ ይሆናል።

Address

Awash

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when صالح عبد الله Salih Abdella posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to صالح عبد الله Salih Abdella:

Shortcuts

Share