24/10/2025
የመንግስት ሠራተኞች ተሻሽሎ የወጣው #አዋጅ 1353/2017 ስለደሞዝ ስኬል ምን ይላል?For your understanding.
www.csc.gov.et
++++++++++++++++++++++++++
ክፍል ሶስት አንቀፅ 9 የደሞዝ ስኬል ማስተካከያ
1. የደሞዝ ስኬል ማስተካከያ ዓላማ ከፍተኛ እውቀትና ችሎታ ያለውን ባለሙያ ለመሳብ፣ለማቆየትና ሠራተኛውን ለማትጋት የሥራ ውጤቱን ለማሻሻል የሚያስችል የደሞዝ አከፋፈል ሥርዓት ለመወሰን ነው፡።
2. ኮሚሽኑ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ሰኬል ማስተካከያ የመንግስትን የፋይናስ አቅም ፣የሕዝቡን አጠቃላይ የኑሮ ሁኔታ፣የዋጋ ደረጃዎችና ግሽበት እና አግብብነት ያለውን ሌሎች ሁኔታዎች ባገናዘበ መንገድ በየጊዜው እያጠና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል ፣መመሪያ በማውጣት አፈፃፀሙን ይቆጣጠራል፡፡
3. የደመወዝ ስኬል ለያንዳንዱ የሥራ ደረጃ መነሻ እና ከፍተኛ መድረሻ ደመወዝ እንዲሁም በየጊዜው የሚደረገውን የደመወዝ ጭማሪ የሚያመለክቱ እርከኖች ይኖሩታል፡፡
4. ኮሚሽኑ የሥራ ደረጃ ዝቅተኛ ደመወዝ እና ከፍተኛ ደመወዝ ጣሪያ በየአራት አመቱ አጥንቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣አፈፃፀሙን ይቆጣጠራል፡፡