የቤ/ጉ/ክ/መ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን BGRS Disaster Risk Management Commishine

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • የቤ/ጉ/ክ/መ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን BGRS Disaster Risk Management Commishine

የቤ/ጉ/ክ/መ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን BGRS Disaster Risk Management Commishine Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የቤ/ጉ/ክ/መ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን BGRS Disaster Risk Management Commishine, Government Organization, ASSOSA, Asosa.

በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች /ገጠርና ከተማ/ የአደጋ ስጋቶችን በጥናት በመለየት በሴክተሮች የልማት ዕቅድ እንዲካተቱ በማስቻል እና የተጠናከረ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በመዘርጋት ለዘላቂ ልማት አስተዋፅዖ ማድረግና የአደጋ ክስተት ስጋትንና አደጋ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት መቀነስ፡፡

15/10/2025

እንኳን ለዓለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን አደረሳችሁ!

“ከአደጋ ይልቅ ለአደጋ አይበገሬነት ግንባታ ትኩረት እንስጥ”
“Fund Resilience, Not Disaster” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የአደጋ ስጋት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመስክ ጉብኝት፣ በልምድ ልውውጥና በምክክር እየተካሄደ ይገኛል።
"ከተረጂነት ወደ ማምረት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት!"

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም.

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን ለመሸፈን ከ26 ሄክታር መሬት በላይ እየለማ ነው።(ግልገል በለስ:- ጥቅምት 4/2018) በዞኑ ዳንጉር ወረዳ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ ለ...
14/10/2025

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን ለመሸፈን ከ26 ሄክታር መሬት በላይ እየለማ ነው።

(ግልገል በለስ:- ጥቅምት 4/2018) በዞኑ ዳንጉር ወረዳ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ ለመሸፈን እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ከ26 ሄክታር መሬት በላይ በዘር መፈሸኑን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ገልጿል።

የዳንጉር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገናነው ዳኘ፤እንደ ክልል ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት ያለውን የተረጅነት ቅነሳ ፕሮግራም እና ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ እንቅስቃሴ በተቀናጀ መልኩ በመስራት በወረዳው ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በወረዳው ይሄን ተግባራዊ ለማድረግ ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑ ሰብሎችን በመለየት አበረታች የግብርና ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል።

የዳንጉር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ደስታየሁ አብሾክ እንደገለጹት እንደ ሀገር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲከሰቱ በራሱ አቅም ድጋፎችን ለመሸፈን እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ 26 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ገልጸዋል።

መንግስት የጀመረውን የድህነት ቅነሳ መርሃ ግብር እውን ለማድረግና ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ቀድሞ ለመከላከል 14 ነጥብ 4 ሄክታር በቆሎ እና 12 ሄክታር መሬት ደግሞ በአኩሪ አተር መሸፈኑን ሃላፊው ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት ወረዳው ባካሄደው የቅድመ ምርት ትንበያ መሰረት ከሁለቱም የሰብል አይነቶች ከ1 ሺ ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

በወረዳው ከተረጅነት ለመላቀቅ እየለማ ያለውን የአኩሪ አተርና የበቆሎ ሰብል ተሞክሮ የወረዳው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የዞንና የወረዳ ባለሙያዎች እንዲሁም አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቢሮ በዚገም ወረዳ በፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደረሻ ምግብ ድጋፍ አደረገ።(ድባጢ፦ጥቅምት 3/2018 ዓ,ም)የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አደጋ...
13/10/2025

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቢሮ በዚገም ወረዳ በፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ደረሻ ምግብ ድጋፍ አደረገ።

(ድባጢ፦ጥቅምት 3/2018 ዓ,ም)የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከአማራ ክልል ዚገም ወረዳ ተፈናቅለው በድባጢ ወረዳ አንግቶክ ቀበሌ ለሚገኙ ዜጎችን በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፉም የድባጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ተገኘ በአማራ ክልል አዊ ዞን በተለያዩ ወረዳ ላይ በፀጥታ ችግር ተፈናቅለው በድባጢ ወረዳ አንግቶክ ቀበሌ ለሚገኙ 238 የህብረተሰብ ክፍሎች ከክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል።

በአማራ ክልል በአዊ እና በምዕራብ ጉጃም ዞኖች በሚገኙ ዚገም እና ወንበርማ ወረዳዎች 482 አባወራና እማወራዎች 3ሺ 4መቶ 10 ቤተሰብ አባላት ተፈናቅለው በወረዳው ስር እንደሚገኙም ገልፀዋል።

አክለውም በቀጣይም በወረዳው ታች ዶበን፣ጉልፈን፣ገፈሬ፣አልበሳ፣ሙዘን ቀበሌዎች ላይ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የዕለት ደራሽ ምግብ አቅርቦት ድጋፍቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ በፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ 238 የህብረተሰብ ክፍሎች ምግብ ነክ እህል ድጋፍ እንደተደረገ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምግብ ዋስትና የስራ ሂደት አቶ ሽባባው ቡሸን ተናግረዋል።

ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራዊ አንድነት እና የኀብረ ብሔራዊነት መገለጫ ዓርማችን ነው፦ የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ‎***************‎‎ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራዊ አንድነት...
11/10/2025

ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራዊ አንድነት እና የኀብረ ብሔራዊነት መገለጫ ዓርማችን ነው፦ የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ
‎***************

‎ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራዊ አንድነት እና የኀብረ ብሔራዊነት መገለጫ ዓርማችን ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ ተናገሩ።

‎18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል።

‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ በዓል ላለፉት 17 ዓመታት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ሲከበር መቆየቱን ገልጸዋል።

‎ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራዊ አንድነት እና የኀብረ ብሔራዊነት መገለጫ ዓርማችን ነው ያሉት ወ/ሮ አስካለች፣ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠት ይገባል ብለዋል።

‎የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ዜጎች ለሀገራቸው እና ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸውን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

‎የዘንድሮው 18ኛው የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን፣ ቀኑ ዜጎች ለሀገራዊ አንድነትና ሉዓላዊነት መጠበቅ ቃለ መሐላቸውን ዳግም የሚያድሱበት መሆኑንም ጭምር አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።

‎በዕለቱም የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ሥነ- ስርዓት ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት ላይ እንደሚካሄድ ጠቁመው፣ በተመሳሳይ ሰዓት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሰንደቅ ዓላማ አሰቃቀል ሥነ-ሥርዓት በማካሄድ በድምቀት ይከበራል ብለዋል።

‎የዘንድሮው 18ኛው የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጲያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል።

መረጃው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው

11/10/2025
የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ''ብሔራዊ ጥቅምና የጂኦስትራቴጂ ቁመና'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ።               (አሶሳ:-መስከ...
02/10/2025

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ''ብሔራዊ ጥቅምና የጂኦስትራቴጂ ቁመና'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄዱ። (አሶሳ:-መስከረም 21/2018 ዓ/ም) የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች እንደ ሀገር በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል። ሰነዱን ያቀረቡት የኮምሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ባንቲ አባሹ ፤ያለ ብሄራዊ ጥቅም ሀገር እንደማትቀጥል በመገንዘብና የሰራተኞች ውጤታማነት የጅኦስትራጅያዊ ተዕጽኖ ከፍተኛ በመሆኑ ማወቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በብሔራዊ ጥቅሞች ላይ መለያየት ሳይኖር የጂኦ እስትራተጅያዊ ቁመናን በግልፅ በመረዳት እና በየተቋማት የሚጠበቅብን ሀላፊነት በመወጣት ለተገልጋዮች የሚያረካ አገልግሎት በመስጠት፣ሀገርን ወደ ትልቅ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ በስፋት ተገልጿል።''ብሄራዊ ጥቅምና ጅኦስትራቴጂ ቁመና'' ያለውን አጠቃላይ ሀገራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ማስከበር ከሰራተኞ ጋር የተጠናከረ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ከአማራ ክልል ተፈናቅለው በግልገለ በለስ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ከዳንጉር ወረዳ ጃቫ ቀበሌ ተፈናቅለው ማንቡክ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃች የክልሉ አደጋ ስጋት ...
25/09/2025

ከአማራ ክልል ተፈናቅለው በግልገለ በለስ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ከዳንጉር ወረዳ ጃቫ ቀበሌ ተፈናቅለው ማንቡክ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃች የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራረር ኮሚሽን ምግብ እና ምግብነክ ያልሆኑ ድጋፎችን አደረግ፡፡
*****************
በቀን 13/1/2018 ዓ.ም ግልገል በለስ
ከአማራ ክልል ተፈናቅለው በግልገለ በለስ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ከዳንጉር ወረዳ ጃቫ ቀበሌ ተፈናቅለው ማንቡክ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃች የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራረር ኮሚሽን ምግብ እና ምግብነክ ያልሆኑ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
ድጋፉን ለዳንጉር ከዳንጉር ወረዳ ተፈናቃዮች የዕለት ቀለብ የሚውል ቦቆሎ እና አልሚ ምግብ ለወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከአማራ ክልል ተፈናቃዮች ለቤት መስሪያ አገልግሎት የሚውል 100 እሽግ ሸራ ለግልገል በለስ ከተማ አስተዳደደር ከንተባ አሳየ አበበ አማረ አመራሮች ያበረከቱት የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልአዚዝ እና ምክትል ኮሚሽነር ባንቲ አባሹ አስረክበዋል፡፡
በድጋፉ ወቅት እንደኮሚሽነሮቹ ገለጻ እየተደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ ቀጣይነት የሌለው፣ሊቆም ስለሚችል እና የመንግስት ዋነኛ ትኩረት ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም ስራ በመስራት ምርት እና ምራታማነትን በማሳደግ በምግብ አቅም ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነ የቀረበው ድጋፍ ይበልጥ ተጋላጭ እና ተጎጂ ለሆኑ አካል ጉዳተኛ፣ለአጥቢ እና ለነፍሰጡር ፣ለሕጻናት፣ለአረጋውያን ዜጎች የቅድሚያ ቅድሚያ መስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡ አመራሮች ለተፈናቃይ ዜጎች እየተደረጉ ያሉ ድጋፍች በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በተያያ ዜና ኮሚሽኑ በግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን ለመሸፈን እየተከናወነ ያለውን የሩዝ እና የአኩሬ አተር የእርሻ ስራ በአካል በመገኘት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን ለመሸፈን እየተከናወነ ያለውን   እና   አተር   ስራ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮ...
24/09/2025

በግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን ለመሸፈን እየተከናወነ ያለውን እና አተር ስራ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮምሽነር መሃመድ አብዲልአዚዝ : ምክትል ኮሚሽነር ባንቲ አባሹ እና የግልገልበለስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሳየ አበበ በአካል በመገኘት ያደረጉት የመስክ ምልከታ በፎቶ።

  ወረዳ በማንቡክ ከተማ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለሁለት አቅመ ደካማ ዜጎች 2 ቤቶችን በመገንባት  እና አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶችን በማሟላት እንዲሁም ለ6ወራት የሚሆን ምግብ...
23/09/2025

ወረዳ በማንቡክ ከተማ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለሁለት አቅመ ደካማ ዜጎች 2 ቤቶችን በመገንባት እና አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶችን በማሟላት እንዲሁም ለ6ወራት የሚሆን ምግብነክ ድጋፎችን ጨምሮ ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልዓዚዝ በትለንትናው እለት በአካለ በመገኘት ለነዋሪዎቹ ቁልፍ አስረክበዋል።

በሚቀጥሉት አስር ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ - ኢንስቲትዩቱበሚቀጥሉት አስር ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ...
23/09/2025

በሚቀጥሉት አስር ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ - ኢንስቲትዩቱ

በሚቀጥሉት አስር ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚቀጥሉት አስር ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ገልጿል።

በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ እንዲሁም መካከለኛ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

የምዕራብ፣ መካከለኛው እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ደረጃ ያለው የዝናብ መጠን እንደሚያገኙ ይጠበቃል ብሏል።

በሚቀጥሉት አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ እንዲሁም በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ርጥበት ይኖራቸዋል ብሏል።

ይህም በአመዛኙ ለግብርና ስራ እንቅስቃሴ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ጠቁሟል።

በአብዛኞቹ ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚጠበቅ ትንበያዎች እንደሚያሳዩ ተመላክቷል።

የአባይ፣ የባሮ አኮቦና የኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ርጥበት የገጸ ምድር ውሃ እንደሚያገኙም አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ገናሌ ዳዋ፣ ዋቤ ሸበሌ፣ የታችኛው ኦሞ ጊቤና የአዋሽ ተፋሰስ ከቀላል እስከ መካከለኛ ርጥበት እንዲሁም የዋቤ ሸበሌ ተፋሰስ ቀላል መጠን ያለው የገጸ ምድር ውሃ እንደሚኖራቸው ጠቅሷል።

ኢዜአ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሁለት የአቅመ ደካማና የአረጋውያን ቤቶች በመገንባት አስረከበ።(ግልገል በለስ:-መስከረም 12...
22/09/2025

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሁለት የአቅመ ደካማና የአረጋውያን ቤቶች በመገንባት አስረከበ።

(ግልገል በለስ:-መስከረም 12/2018 ዓ/ም) ኮሚሽኑ እንደ ክልል በክረምት የዘጠና ቀናት የተሰጠውን እቅድ መሰረት ሁለት የአቅመ ደካማና አረጋውያን ቤቶችን ገንብቶች ለግለሰቦች አስረክቧል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልዓዚዝ፤ኮሚሽኑ
ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍን ከመሸፈን ባለፈ በክረምት ወራት ያከናወናቸውን የአቅመ ደካማ ቤቶችን መገንባቱን ገልጸዋል።

በዚህ መሰረት በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በማንቡክ ከተማ ለሚገኙ ሁለት አረጋውያን ቤቶችን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመገንባት የተሟላ የቤት ቁሳቁስና ለስድስት ወራት የሚሆን የምግብ እህል ድጋፍ ማበረከቱን ኮሚሽነር መሃመድ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ባንቲ አባሹ፤ኮሚሽኑ የክልሉ መንግስት በዘጠና ቀናት ባስቀመጠው የትኩረት አቅጣጫ መሰረት አመራሮችና ሰራተኞች በተለያዩ ወረዳዎች በማሰማራት የተለያዩ የሰብዓዊ አገልግሎት ስራዎችን ማከናወኑን አመላክተዋል።

ይሄን ተግባር በቀጣነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ተቋማትና የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በወረዳው ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር  ኮሚሽን ለአንድ መቶ ተማሪያዎች የመማሪያ ቁሳቁስ  እና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።(ግልገል በለስ:-መስከረም 12/2018 ዓ/ም) ኮሚሽኑ ...
22/09/2025

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ለአንድ መቶ ተማሪያዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

(ግልገል በለስ:-መስከረም 12/2018 ዓ/ም) ኮሚሽኑ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አንድ መቶ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብዱላዚዝ፤እንደ ክልል የተያዘውን ኢንሼቲቭ ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገው ርብርብ በዳንጉር ወረዳ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ እንደ ሀገር የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን እውን ለማድረግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አንድ መቶ ተማሪዎች የተሟላ የመማሪያ ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ የራሱን ሰራተኞች በማስተባበር ለተማሪዎች ከመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ባለፈ የአልባሳት ሰብዓዊ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፍቃዱ ደበሎ፤ኮሚሽኑ በዞኑ ውስጥ እያደረገ ያለው ድጋፍ በርካታ ተማሪዎችን በትምህርት ገበታቸው እንዲገኙ አስችሏል ብሏል።

አቶ ፍቃዱ አክለው ለተደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ይህ የመረዳዳትና የአብሮነት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ባንቲ አባሹ በበኩላቸው፤ኮሚሽኑ በዘጠና ቀናት ያቀደቻውን የበጎ አድራጎት ስራዎች በየደረጃው ካለው አካል ጋር በማስተባበር ተፈጻሚ ማድረጉን ገልጸው ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

Address

ASSOSA
Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቤ/ጉ/ክ/መ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን BGRS Disaster Risk Management Commishine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share