የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና  ማህበራዊ  ጉዳይ ቢሮ  BG.Bureau of Women and Social Affairs TO CONVEY MESSAGE ABOUT WOMEN ,CHILDREN,YOUTH ,ELDERS and Disable .

በአሶሳ ሆሃ እና አሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ለድምጽ መስጫ የሚሆኑ የቁሳቁስ ስርጭት ተጠናቋልአሶሳ፤ ግንቦት 23/2018(ኢዜአ)፦ በአሶሳ ሆሃ እና አሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ ...
31/05/2026

በአሶሳ ሆሃ እና አሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ለድምጽ መስጫ የሚሆኑ የቁሳቁስ ስርጭት ተጠናቋል

አሶሳ፤ ግንቦት 23/2018(ኢዜአ)፦ በአሶሳ ሆሃ እና አሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ለድምጽ መስጫ የሚሆኑ የቁሳቁስ ስርጭት መጠናቀቁን የምርጫ ክልሎቹ አስተባባሪዎች ተናገሩ።

የአሶሳ መገሌ ምርጫ ክልል አስተባባሪ ሀብታሙ ተስፋዬ እንደገለፁት፤ በምርጫ ክልሉ በሚገኙ 48 የምርጫ ጣቢያዎች ላለፉት ሁለት ቀናት የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ሲካሄድ ቆይቷል።

በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መድረሱን ገልፀው፥ ቁሶቹ አስፈላጊውን ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

የአሶሳ መገሌ ምርጫ ክልል አስተባባሪ እሱባለው ንጋቱ በኩላቸው፤ በምርጫ ክልሉ በሚገኙ 68 የምርጫ ጣቢያዎች ሲከናወን የቆየው የቁሳቁስ ስርጭት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በአሶሳ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ባደረግነው ቅኝት የድምጽ መስጫ ሳጥን፣ የመራጮች ድምጽ መስጫ መከለያ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች በወቅቱ ደርሰዋል።

#ኢዜአ

ድምፅ ለመስጠት አንድ ቀን ብቻ ቀረው! ድምፄ ዋጋ ስላለው እኔ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ፤ እናንተስ?
31/05/2026

ድምፅ ለመስጠት አንድ ቀን ብቻ ቀረው! ድምፄ ዋጋ ስላለው እኔ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ፤ እናንተስ?

የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ወደ ዴሞክራሲያዊ ብስለት መሸጋገርን የሚያሳይ ነው******************* ጎህ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሲፈነጥቅ፣ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚ...
30/05/2026

የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ወደ ዴሞክራሲያዊ ብስለት መሸጋገርን የሚያሳይ ነው
*******************

ጎህ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሲፈነጥቅ፣ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በምርጫ ሳጥን አማካኝነት ድምፃቸውን ለማሰማት ዋዜማ ላይ ይገኛሉ።

ከሰፊዋ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር፣ ከተጨናነቁ ከተሞች እስከ ርቀው ከሚገኙ የገጠር ማኅበረሰቦች ድረስ ለዚህ ታሪካዊ ኩነት የሚደረጉ ዝግጅቶች የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል።

በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው ሂደት ከተለመደ የምርጫ ተግባር ባሻገር፤ ከአፍሪካ ግዙፍ እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ተቋማዊ ብስለቷን የምታስመሰክርበት ታሪካዊ ወቅት ነው።

ከ54 ሚሊዮን በላይ የተመዘገቡ መራጮች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ምርጫ፤ በአህጉሪቱ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከታዩት እጅግ ጉልህ ዴሞክራሲያዊ ሂደቶች አንዱ ነው። ይህም የፖለቲካ ውድድርን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋማት እያሳዩ የመጡትን ተግባራዊ የአሠራር ብስለትን ጭምር የሚያንጸባርቅ ነው።

ከምርጫው አስቀድሞ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ ታሪካዊ ድምፅ አሰጣጥ አስፈላጊ የሆኑ ሁሉንም የቁሳቁስ እና የተግባር ዝግጅቶች በስኬት አጠናቆቀ በየምርጫ ጣቢያዎች እያሰራጨ ይገኛል።

እንደ ቦርዱ ገለጻ የፊታችን ሰኞ የሚካሄደው ድምፅ አሰጣጥ ካለፉት የምርጫ ዑደቶች ጋር ሲነጻጸር ሰፊ የፖለቲካ አካታችነትን፣ የተሻሻሉ የቴክኖሎጂ አሠራሮችን፣ ጠንካራ የአስተዳደር ቅንጅትን እና የላቀ የሕዝብ ተሳትፎን ያካተተ በመሆኑ ከፍተኛ ተቋማዊ ዕድገት የታየበት ነው።

በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመጠቆምም ሆነ ሲያጋጥምዎ ሪፖርት ለማድረግ የቦርዱ ነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥሮች በሆኑት 7555 እና 6214 በመደወል ጥቆማ መስጠት ይችላሉ...
29/05/2026

በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመጠቆምም ሆነ ሲያጋጥምዎ ሪፖርት ለማድረግ የቦርዱ ነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥሮች በሆኑት 7555 እና 6214 በመደወል ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

Website: https://l1nq.com/n5amd66

X (Twitter): https://t.ly/o2nM9

Telegram: https://t.ly/BmT_4

YouTube: https://t.ly/N80Eo

LinkedIn: https://t.ly/zntYV

WhatsApp: https://t.ly/3Gfih

TikTok: https://surl.li/rrtdog

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው*******************በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የቁሳቁስ ስርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል። የአ...
29/05/2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው
*******************

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የምርጫ ክልሎች የቁሳቁስ ስርጭት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የአሶሳ ሆሃ እና የአሶሳ መገሌ የምርጫ ክልሎች ለየምርጫ ጣቢያዎቻቸው የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ሥራ እየሠሩ ነው።

የአሶሳ ሆሃ የምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ እሱባለው ንጋቱ እና የአሶሳ መገሌ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንዳሉት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅድመ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ እስከ ግንቦት 22 ቀን ድረስ በሁሉም ጣቢያዎች ቁሳቁሶችን አሰራጭተው ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

እነዚህን የምርጫ ክልሎች ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሁሉም አካባቢዎች ከሚገኙ ማዕከላት ወደ ሁሉም ጣቢያዎች ቁሳቁሶችን በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

ኢቢሲ

ግንቦት 24ን በቀን መቁጠሪያዎ ላይ አስምረውበታል?******************7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።ሰኞ ግንቦት 24፤ አገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር...
29/05/2026

ግንቦት 24ን በቀን መቁጠሪያዎ ላይ አስምረውበታል?
******************

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

ሰኞ ግንቦት 24፤ አገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ድምፅ የምንሰጥበት ቀን ነው!

እርስዎስ የመራጭነት ካርድዎን አዘጋጅተው የድርሻዎን ለመወጣት ተሰናድተዋል?

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ

ለምርጫ 4 ቀን ብቻ ቀረው !ካርደዎን ይጠቀሙ ! #በምርጫብቻ
28/05/2026

ለምርጫ 4 ቀን ብቻ ቀረው !
ካርደዎን ይጠቀሙ !
#በምርጫብቻ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 5 ቀናት ብቻ ቀሩት ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ በይፋ ይካሄዳል።  #ኢትዮጵያ  #ምርጫ    #በምርጫብቻ
27/05/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 5 ቀናት ብቻ ቀሩት

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ በይፋ ይካሄዳል።

#ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ

1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብረ**************1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ...
27/05/2026

1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብረ
**************

1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብሯል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ኢብራሂም ሲራጅ በ1 ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል አከባበር ላይ ባስተላለፉት መልዕክ፣ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የቀደመ አብሮነቱን እና አንድነቱን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

በዓሉንም ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች በመጠየቅና ኃይማኖታዊ አስተምህሮቱ በሚያዘው መሰረት ማክበር እንደሚገባም ነው ሼህ ኢብራሂም ሲራጅ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

የበዓሉ ታዳሚዎች በበኩላቸው፣ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አንድነቱን በማጠናከርና በመደጋገፍ ማክበር እንዳለበት ተናግረዋል።

በዓሉንም ያለው ለሌለው በማካፈል እና እርስ በርስ በመጠያየቅ ማክበር እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።

1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በሶላትና በተለያዩ ሀይማኖታዊ አስተምህሮ በድምቀት መከበሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ዘግቧል።

‎ብሔራዊ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ ጾታ እኩልነት ረቂቅ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ጥበቃና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ድርሻው የላቀ ነው‎...
26/05/2026

‎ብሔራዊ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ ጾታ እኩልነት ረቂቅ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ጥበቃና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ድርሻው የላቀ ነው
‎************
‎በ1986 ዓ.ም የተቀረፀውና ለረጅም ጊዜ በስራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፖሊሲ ለሀገራችን ሴቶች መልካም አጋጣሚዎችንና ዕድሎችን የመፍጠሩን ያህል በርካት ክፍተቶች እንደነበሩበት በተካሄደ የግምገማ ጥናት ለመገንዘብ ተችሏል።

‎በመሆኑም ካለፈው ትምህርት በመውሰድና የሌሎች ሀገራትን ልምድና ተሞክሮ በመፈተሽ እንዲሁም ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተጣጣመ መልኩ ፖሊሲውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

‎ለዚህም የተለያዩ መንግስታዊ እና አለም አቀፍ ተቋማት፣ የሴቶች አደረጃጀቶችና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተሳተፉበት አግባብ የረቂቅ ሰነድ ዝግጅት ሲካሄድና በየደረጃው ግብዓት ሲሰጥበት መቆየቱ ይታወቃል።

‎ፖሊሲው ለስርአተ ጾታ መዛባት ስር ነቀል የሆኑ ጉዳዮች ላይ በቂ ትኩረት ለመስጠት፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን በአግባቡ ለመከላከል እና ጥበቃና ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ልዩ ትኩረት ለሚሹ ሴት አካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ስርአተ-ጾታን መሰረት ካደረጉ አለም አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶች ጋር በማጣጣም ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ሊቀርብ ችሏል፡፡

‎ምክር ቤቱ በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

‎ፖሊሲው አሁን ላይ ያለውንና የወደፊቱን የሴቶች ፍላጎት፣ ጥያቄና ተግዳሮት ሊፈታ በሚችል መልኩ የተዘጋጀ እንደመሆኑ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ጥበቃና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መረጋገጥ ድርሻው የላቀ እንደሆነ ይታመናል።

‎በመሆኑም በፖሊሲ ዝግጁት ላይ የተሳተፉ እና ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱት አካላት በሙሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረበ፤ የፖሊሲው ዝግጅት ረጅም ሂደት አልፎ ለዚህ ደረጃ በመብቃቱ ለመላው የኢትዮጵያ ሴቶች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።

‎በቀጣይም ለፖሊሲው ስኬታማ አተገባበር ባለድርሻና አጋር አካላት በጋራ እንድትረባረቡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል።

Address

Asdoss
Asosa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ BG.Bureau of Women and Social Affairs:

Share