31/07/2025
በአሶሳ ከተማ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተካሄዴ፡፡
***************************************
ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም አሶሳ፡-
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡
እንደ ሀገር 700 ሚሊዮን እንደ ክልል 15 ሚሊዮን እንደ ከተማ አስተዳደር 250 ሺ ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል በተያዘው ዕቅድ መሰረት በአምባ 8 እና ኢንዚ ተራራ ላይ የተለያዩ ሀገር በቀልና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል፡፡
በችግኝ ተከላው የአሶሳ ከተማ ከንቲባና ም/ከንቲባ እንዲሁም የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ፣የየሴክተር መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣የወረዳ 1 እና የወረዳ 2 ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣በጎ አድራጎት ወጣቶች፣የጸጥታ አካላት እንዲሁም የኦሎምፒክ ጂም ስፖርተኞች ተሳትፈዋል፡፡
በመትከል ማንሰራራት መሪ ቃል እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአጤጦ ሰልጋ የሚቀጥል በመሆኑ ሁሉም አካላት አሻራውን እንዲያሳርፍ መልዕት ተላልፏል፡፡