23/10/2025
በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ የአቡራሞ ቀበሌ ፂዎ ጎጥ ማህበረሰብ ክፍሎች የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል ተከበረ፤
************************************************************************************
(ጥቅምት13/02/2018 ዓ.ም አቡራሞ) በአቡራሞ ወረዳ የአቡራሞ ቀበሌ ፂዎ ጎጥ ማህበረሰብ ክፍሎች በሞዴል አርሶ አደሮች እየተሰሩ ያሉ የቬርሚ ኮምፖስት ስራዎችን እንዲሁም በLLRP ፕሮጄክት ድጋፍ በአርሶ/ከፊል አርብቶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት A.P.F.S (Agro Pastoral Field School) ፕሮግራም የተተገበሩ የተለያዩ ማሳዎችንና ሰርቶ ማሳያዎችን ማዕከል ያደረገ የመስክ ጉብኝት ተካሄዷል።
በመስክ ምልከታው የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የተለያዩ የስራ ዘርፎች ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የል/ጣቢያ ሰራተኞችን ጨምሮ የቀበሌው አርሶ/ከፊል አርብቶ አደሮች ተሳትፈዋል።
በእለቱ በተካሄደው የመስክ ምልከታ ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም በቀበሌው ተከስቶ በነበረው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የወደሙ ሰብሎችን በአንፃራዊ መልኩም ቢሆን ቀድመው በሚደርሱ (Cash Crop,s) እንዲሁም በተለያዩ የአትክልት ዘር ዓይነቶች ለመተካት አርሶ/ከፊል አርብቶ አደሮች ያደረጉትን ጥረት ለመመልከት ተችሏል።
በጉብኝቱ ወቅት ሞዴል አርሶ አደር አቶ አባስ ሰሌማን እንደገለፁት ከዚህ በፊት ጳጉሜ 1/2017 ዓ.ም በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የእርሳቸውን ጨምሮ አጠቃላይ በቀበሌው የሚገኙ አርሶ/ከፊል አርብቶ አደሮች ሰብሎቻቸው መውደሙ እንዳሳዘናቸው ጠቅሰው ነገር ግን ቀጣይ የግብርና ባለሙያዎችን ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ በማድረግ በዘርፉ አዋጭ የሆኑ የስራ መስኮች ላይ በመሰማራት የደረሰውን የተፈጥሮ አደጋ የሚያካክስ ስራ ላይ መሰማራት ይኖርብናል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
አቶ አባስ ከመደበኛ የግብርና ስራዎች በተጨማሪ በተለይም በቬርሚ ኮምፖስት ዝግጅት ስራ ተሰማርተው አሁን ላይ ከ 30ኩ/ል ቬርሚ ኮምፖስት ብር 90,000 ሺህ: ከ Vermi worm ሽያጭ ብር 18,000 እንደሸጡ እና ከ30 ኩ/ል በላይ ቬርሚ ኮምፖስት ደግሞ የተለያዩ ሰብሎችንና ከደቡብ ክልል ያመጧቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘሮችን ለመዝራት እንደተጠቀሙበት ገልፀው በቀጣይም ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት ጠቁመዋል።
በመጨረሻም የአርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት ቤት አባላትና አጠቃላይ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ባለድርሻ አካላት በመካከላቸው ተገኝተው በመሳተፋቸውና ለሰጧቸው ሙያዊ አስተያየቶችና ምክሮች ሁሉ አክብሮት እንዳላቸው ገልፀው በቀጣይ በሚያከናውኗቸው ማናቸውም የግብርና የልማት ስራዎች እንደተለመደው ሁሉ ወረዳው ከጎናቸው እንደሚሰለፍ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልፀው የዕለቱ የመስክ ምልከታ ተጠናቅቋል።