Minjar Shenkora Wereda Industry and Investment Office

Minjar Shenkora Wereda Industry and Investment Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Minjar Shenkora Wereda Industry and Investment Office, Government Organization, Arerti.

28/08/2026
28/08/2026
የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ‎ጽ/ቤት የካቲት 01/2018 "ኢትዮጲያ ታምርት እኛም እንሸምት" በሚል በተካሔደው  ዞናዊ ፎረም ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና አቅጣጫዎቹ ዙሪያ ከአ...
16/02/2026

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ‎ጽ/ቤት የካቲት 01/2018 "ኢትዮጲያ ታምርት እኛም እንሸምት" በሚል በተካሔደው ዞናዊ ፎረም ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና አቅጣጫዎቹ ዙሪያ ከአጠቃለይ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሔደ ።

በውይይቱም የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ዘካርያስ ተክሉ ‎የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አማረ ሙሉጌታ ውይይቱን የመሩት ሲሆን ሌሎችም አመራሮች፣ባለሙያዎችና የእለቱ አስተባባሪ ኮሜቴዎች ተገኝተዋል።

‎በውይይቱም በእለቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ጥሩ ጎኖቹን ጨምሮ ኮሚቴው አስተያየት በመስጠት ለቀጣይ ስራዎች ተነሳሽነት እንዲፈጥር አላማ ያደረገ ነው ተብሏል ።

‎በእለቱ ከመድረክ ዝግጅት እንግዶችንተቀብሎ እስከ መሸኘት ያለውን መልካም ነገርና ችግሮች ጨምሮ እንዲሁም የፎረሙ መካሔድ ያመጣው ትሩፍቶችና ገጽታን ከመገንባት አኳያ ኮሜቴው በቂ አስተያየት በመስጠት በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ዝግጅት ማዘጋጀት እንደሚቻል መግባባት ላይ በመድረስ ዝግጅቱ የተሳካና ችግር ፈች እንዲሆን አስተዋጾ ላደረጉ አካላት የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ዘካሪያስ ተክሉ በወረዳውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

‎ በመጨረሻም መድረኩ የተሳካና ያማረ እንዲሆን የድረሻቸውን ለተወጡ አካላት የምስጋናና የምስክር ወረቀትና ልዩ ልዩ ሽልማቶችን በማበርከት የእለቱን ውይይት ማጠናቀቅ ተችሏል ።

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም በአረርቲ ከተማ በአማረና በደመቀ መልኩ አካሔደ  ።‎‎ በፎረሙ ላይም  የፌዴ...
09/02/2026

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም በአረርቲ ከተማ በአማረና በደመቀ መልኩ አካሔደ ።

‎ በፎረሙ ላይም የፌዴራል ፣የክልል ፣የዞንና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ወረዳዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ተወላጆች ፣ ባለሀብቶች የተገኙ ሲሆን አቶ ዝናቡ ይረጋ የኢትዮጲያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ፣ደ/ር ደመቀ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ፕላን ቢሮ ሀላፊ ፣አቶ እንድሪስ አብዱ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁና ሌሎችም በየዘረፍ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።

‎በእለቱም በአረርቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተሻለ ጥላሁን የእንኳን ደና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቂና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ማለትም የመንገድ፣ የውሀ ፣የመብራትና ሌሎችንም ጥያቄዎች አንስተዋል ።

‎የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ድንቅ የስራ ባህል ወዳለባት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ና አረርቲ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ በሰላም መጣችሁ በማለት በጥቅሉ ሰሜን ሸዋ ለኢንቨስትመንት የተመቸ ሰላም ወዳድና ታታሪ ማህበረሰብ ያለበት ዞን ሲሆን ለኢንቨስትመንት በቂ ግብአት ያለው በመሆኑ ከ23 በላይ ማእድናት መኖሩን በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን ለአልሚዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥረም ተናግረዋል ።

‎ምንጃር ለኢንቨስትመንት ጥያቄ ፈጥኖ ምላሽ የሚሰጥና ባለፍት አመታት እንደዞን ከ250 በላይ አልሚዎችም ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸውም ጠቅሰዋል ።ምንጃር ለአዲስ አበባ ቅረብ መሆኑ ባለሀብቶች እንክብካቤ ስለሚፈልጉ ልማታቸው ተጠብቆ ምረታማ እንዲሆኑ ሰላም ወዳድ የሆነው ማህበረሰብ መጠበቅ እንደሚኖርበትም ገልጸዋል ።

‎በእለቱም በሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በአቶ ደምሰ ዞናዊ የመወያያ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት በማድረግ ከማህበረሰቡ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የፊደራል የክልልና የዞን አካላት በተገኙበት ምላሽ በመስጠት በግባባት ላይ በመድረስ የእለቱን የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ዞናዊ የንቅናቄ ፎረም ማጠናቀቅ ተችሏል ።

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ጥር 17/2018 ለሚካሔደው ኢትዮጲያ ታምርት ንቅናቄ ከአብይ ና ንኡስ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሄደ። ውይይቱን የመራው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አ...
26/12/2025

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ጥር 17/2018 ለሚካሔደው ኢትዮጲያ ታምርት ንቅናቄ ከአብይ ና ንኡስ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሄደ።

ውይይቱን የመራው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለምሸት ሞላ ሲሆን ለንቅናቄው መድረክ መሳካት በቅድመ ዝግጅት ስራዎችና እስካሁን በተሰሩ ስራዎች ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ የቀጣይ ስጋቶች ላይ ውይይት በማድረግ ለችግሮቹ መፍትሔ በማስቀመጥ የንቅናቄ መድረኩ አላማውን በማስገንዘብ ስራዎችን ከፋፍሎ በመስጠት የቀጣይ አቅጣጨ በማስቀመጥ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ኑ ምንጃርን በጋራ እናልማ የእለቱ መልእክት ነው ።

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ማዕድን ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት በወረዳው ውስጥ የሚገኙትን የማዕድን ሃብት ዝርዝርና ጥቅሞቻቸውን ይፉ አደረገ ። ከተለዩት ማዕድናት መካክል ፑሚስ አንደኛው ሲሆን በቆ...
23/12/2025

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ማዕድን ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት በወረዳው ውስጥ የሚገኙትን የማዕድን ሃብት ዝርዝርና ጥቅሞቻቸውን ይፉ አደረገ ።

ከተለዩት ማዕድናት መካክል ፑሚስ አንደኛው ሲሆን በቆላው ክፍል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ/አሞራቤት ቀበሌ ፤ክትቻ ቀበሌ፤ ፊናናጆና ከንቦልሻ ቀበሌዎች / በሰፊው ክምችት ይገኛል፡፡
ጥቅምና አይነቱም
1. የኮንስትራክሽን/ የግንባታ ማዕድናት/:- ጥቁር ድንጋይ /Basalt/
* ለጠጠር ምርት ለተለያዩ ግንባታዎች
* ለኮንክሪት ስራና ለድልድይ
* ለኮንክሪት ቀለበቶች
* ለውሃ ታንከሮች ስራ
* ለአስፓልት ስራ ወዘተ

# ነጭ የግንብ ድንጋይ / Ignimbright/

*ለተለያዩ የግንባታ ስራዎች

# የወንዝ አሸዋ / River saned/

* ለተለያዩ የግንባታ ስራዎች

# የወንዝ ጠጠር / River Gravel/
*ለወንዝ ውሃ ማጣሪያ
* ለተለያዩ ግንባታዎች ማስጌጭያ

# ጥቁር ባልጩት / Obsidian/
* ለተለያዩ ግንባታዎች ማስጌጭያ

# የተመረጠ አፈር / Selected matrial /
* ለተለያዩ ግንባታዎች የመሰረት ሙሌት

# ቀይ ሾክሾኬ / scoria/
*ለኮብል ድንጋይ የመሰረት ሙሌት
* ለወለል ምንጣፍ ወይም ቴራዞን ምርት

# ነጭ ሾክሾኬ / Pumic/

* ለብሎኬት ምርት ግብአት

2. የኢንደስትሪ ማዕድናት :- ፊልድስፓር / fildspar/

* ለሴራሚክ ምርት ግብአት
* ለመስተዋት ምርት ግብአት ወዘተ

# ቤንቶናይት / Bentonit/ ተጨማሪ ጥናት የሚፈልግ

* ለሴራሚክ ምርት ግብአት
* ለመዋቢያ /ኮስሞቲከስ/ ምርት ግብአት
* ለንክብል / Tabelt/ መድሀኒት ምርት ግብአት

# ነጭ ሾክሾኬ / pumic/

* ለሲሚንቶ ምርት ግብአት
*ለሳሙና ምርት ግብአት
* ለመዋቢያ /ኮስሞቲክስ/ ምርት ግብአት
* ለተገጣጣሚ ቤቶች የግርግዳ ምርት ግብአት

3. ለጌጣጌጥ :- ጥቁር ባልጩት
* ለአንገት ሀብል ፈርጥ በብርና በወርቅ
*ለጣት ቀለበት ፈርጥ በብርና በወርቅ

እነዚህን ማዕድናት ተጥቅሞ እንቨስት ለሚያደርግ አልሚ ባለሃብት ብቅንነት ተቀብለን የምናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

መረጃውን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ማዕድን ሀብት ልማት ጽ/ ቤት የማዕድን ስራዎች ፍቃድ አስተዳደር ቡድን አድርሰውናል ።
!!! ኑና ምንጃር ሸንኮራ ወረዳንና አረርቲ ከተማ አስተዳደርን በጋራ እናልማ!!!
የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት

‎"ለአንድ ሀገር ፣ክልል፣ ዞንና  ወረዳ  የኢኮኖሚ እድገት  የአምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ሚናቸው ከሁሉም የጎላ ነው"‎                        አቶ ዘካርያስ ተክሉ‎የምንጃር...
24/11/2025

‎"ለአንድ ሀገር ፣ክልል፣ ዞንና ወረዳ የኢኮኖሚ እድገት የአምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ሚናቸው ከሁሉም የጎላ ነው"

‎ አቶ ዘካርያስ ተክሉ
‎የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት
‎ ጽ/ቤት ኃላፊ

‎ህዳር 12/2018 ዓ.ም(ምሸወመኮ)

‎በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ተክሉ በወረዳ ላይ ያሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ኢንዲስትሪዎች ያሉበት አጠቃላይ አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴ ምን ላይ እንዳሉና ባጋጠሟቸውም ችግሮዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

‎አቶ ዘካሪያ ተክሉ እንደገለጹት የምንጃ ሸንኮራ ወረዳና የአረርቲ ከተማ አስተዳደር በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለየ ተፈላጊ በጣም ውጤታማ ከሚባሉ አካባቢዎች ከዞን ካሉ ወረዳዎች ተቋም ካለባቸው አንዱ ነው ብለዋል ፡፡

‎እስካሁንም እንደ ወረዳ በአሁን ሰዓት 36 አልሚ‎ ባለሀብቶች ፍቃድ አግኝተው መሬት የወሰዱ እንዳሉ የገለፁት ኃላፊው ከ36 አልሚ ባለሀብቶች ውስጥ 12(አስራ ሁለቱ) ምርት ጀምረው ምርታቸውን ለገበያ እያቀረቡ ያሉ ናቸው ብለዋል ፣ 9(ዘጠኙ) በግንባታ ላይ ያሉ ሲሆን 15(አስራ አምስቱ) ደግሞ በቅድመ ግንባታ ላያ ማለት ለግንባታ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅት፣የሰነድ፣የግንባታ ፍቃድ፣ የዲዛይን የመሳሰሉት ያሉ ተግባራትን እያሟሉ ያሉ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

‎በወረዳችን ላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች በዋናነት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ አልሚ ባለሀብቶች ከ36ቱ ውስጥ 20 የሚጠጉት በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ግብርናና የግብርና ውጤትን ማቀነባበር ላይ ያተኮሩ ናቸውም ብለዋል፡፡

‎ይህ ራሱን የቻለ ቡርቃ ክላስተር በሚባል የራሱ ክላስተር በ20 መካከለኛና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደተደራጀና ከእነዚህም ውስጥ የወተትና ወተት ተዋፅዖ ማቀነባበር ፣ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበር ፣የዘይት ማምረት፣የዶሮ ስጋ ማምረትና ማቀነባበር አሳ ሀብት ልማት ተጠቃሽ ሲሆኑ በግብርና ምርት ላይ ያተኮሩ በግብርናው ጤፍ፣ስንዴ ምንጃር እንደሚታወቅ በሰፊው የሚመረትበት ውጤታማ አካባቢ ስለሆነ እነዚህን የግብርና ውጠቴቶች ሊጠቀም የሚችንል አምራች ኢንዱስትሪ ስለሚያስፈልግ ይህን ታሳቢ ያደረገ አግሮ ፕሮሰሲንግ ክላስተር በመከለል በክላስተር ውስጥ ያሉ አሁን ላይ በግንባታ ላይ ያሉ አብዛኛዎቹ ያሉት በዚያ ላይ የሚሳተፉ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

‎በተጨማሪም በኬሚካልና ኮንስትራክሽን፣ የአረርቲ ሴራሚክ የከተማችን ብራንድ ተጠቃሽ ሲሆን በተመሳሳይ አለኝታ ከረጢት ማምረቻ ፣ እንጨትና ብረታ ብረት ፣ በአገልግሎት ዘርፍ ስራ ያልጀመሩ በቀጣይ የተያዙ ሆቴልና ቱሪዝም አንዱ እንደሆነና ምንጃር በሁሉም ዘርፍ የኢንቨስትመንት እንቅስቃስ የተዋጣለት የሚባል ወረዳ ነውም ብለዋል፡፡

‎ በቀጣይም እንጨትና ብረታ-ብረት በባልጪ፣ ኬሚካልና ኮንስትራክሽን በቦሎ፣ ከከተማው በተጨማሪ ቡርቃ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ በክላስተር እያደራጀን አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ክላስተር ለማስገባት ጥረት እያደረጉም እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

‎በመሆኑም ለእነዚህ አልሚ ባለሀብቶች እስካሁን ባለው ሁኔታ እስከ 130.36 ሄክታር መሬት ወረዳው በሊዝም በካሳም ለአልሚ ባለሀብቱ እንደተላለፈና ይህንን ሀብት ተጠቅመው 8 ቢሊየን 3 መቶ 59ሺ ሚሊየን 1መቶ 92 ሺ 6 መቶ16 ብር የሚጠጋ ካፒታል በ36ቱ አልሚ ባለሀብቶች ተመዝግቧል ብለዋል አቶ ዘካርያስ፡፡

‎እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራውም በቋሚነት ለ2 ሺ 90 በጊዜያዊነት ለ2 ሺ 7

22/11/2025

‎"ለአንድ ሀገር ፣ክልል፣ ዞንና ወረዳ የኢኮኖሚ እድገት የአምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ሚናቸው ከሁሉም የጎላ ነው"

‎ አቶ ዘካሪያስ ተክሉ

‎እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራውም በቋሚነት ለ2 ሺ 90 በጊዜያዊነት ለ2 ሺ 7መቶ18 ለሚሆኑ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን በድምሩ 4ሺ 8 መቶ 08 ለሚጠጋ የሰው ኃይል በኢንዱስትሪው ዘርፍ ወይም በወረዳው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት በሚደገፉ አልሚ ሀብቶች ስራ ላያ ያሉ ስራ አጥ ወጣች ናቸው ብለዋል ፡፡

‎በመሆኑም በወረዳ ደረጃ በመንግስት አቅም ካለው የሰራተኛ ቁጥር አኳያ በእጥፍ የሚበልጥ የሰው ኃይል ያቀፈ ዘርፍ ስለሆነ በሚፈለገው ልክ ከሄድንበት ምናልባትም የወረዳችን ኢኮኖሚ በተጨባጭ ሽግግር የሚያድግበት አሁን ከተመዘገቡበትም ካፒታል አኳያ በወረዳ ደረጃ የሚንቀሳቀስበት ሀብት መኖሩ ቀላል ሀብት እንዳልሆነም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

‎ መሬት ወስደው ያላለሙ ባለሀብቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ ግንባታቸውን አጠናቀው ወደ ማምረት ባልገቡት የተሰጣቸውን መሬት ከፕሮጀክት አላማ ውጪ ለመጠቀም ወይም ደግሞ በጊዜው ካለማልማት ጋር በተገናኘ እንደ ጽ/ቤት 8(ስምንት) የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ መሬት ወስደው አጥርው ላስቀመጡ የቃል ማስጠንቀቂያ፣ ለ4 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም ለአንድ 0.7 ሄክታር መሬት ነጥቀን ወደ መሬት ባንክ ገቢ አድርገናል ብለዋል፡፡

‎ ምን አልባት መሬት መንጠቅ ግብ ላይሆን ይችላል ያሉት አቶ ዘካርያስ ነገር ግን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳና በሚፈለገው መንገድ አልምቶ ካልተገኘ መሬት መያዙ ለወረዳውም ሆነ ለባለ ሀብቱም ምንም የሚሰጠው ፋይዳ ስለሌለ ጠንክረን እየሰራን እንዲሁም ከአልሚ ባለሀብቱ ጋር ብቻ መሬት ወሰደው እያለሙ ካሉትና ማምረት ላይ ያሉትን ወረዳው ላይ ያሉ ባለሀብቶችን ጠርተን የኢንቨስትመንት አጭር ፎረም አዘጋጅተን ምክክር አድርገን አቅጣጫ አስቀምጠናል ስለዚህ ያለሙትን እንደግፋለን የማያለሙትን ደግሞ ያለ ምንም ድርድር እየነጠቅን እንሄዳለን ብለዋል ፡፡

‎ በመልዕክታቸውም ወረዳችን እንደሚታወቀው በጣም ምቹ መሬት ያለበት አካባቢ ለአልሚ ባለ ሀብቱ በጣም በአጭር ጊዜ ሀብት የሚያካብትበት አካባቢ የተማረ የሰው ሀይል በሰፊው ቁጥር ያለበትና በተጨባጭ ከ8000 በላይ በስራ አጥ መዝገብ ተመዝግበው ያሉበት ስለሆነ ይህንን ፀጋ ተጠቅሞ ማልማት እንደሚያስፈልግና በተለይ መሬት ወስደው የተቀመጡ ባለሀብቶች 1ኛ ወረዳው በሚጠበቀው ልክ ሀብት እንዳያገኝ 2ኛ ባለ ሀብቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚፈጠረው የዋጋ ንረት ሰርቶ ባለማግኘቱ እኛም እርሱም እየተጠቀምን ስላልሆነ ይህን ለነገ የማንለው ተግባር ስለሆነ እነዚህ ላይ ርብርብ ማድረግ የባለ ድርሻው ሚና አብሮ ከተቋሙ ጋር ተባብሮ መሄድ እንደሆነም አሳስበዋል፡፡

‎በመሆኑም በወረዳው እንደሚታወቅ 36 አልሚ ባለሀብቶች መሬት የወሰዱበት 28 የሚጠጉ ደግሞ የመሬት ፍላጎት አቅርበው በሂደት ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ በጣም ከፍ ከፍ ያሉ ባለሀብቶች የመሬትም የማልማት ጥያቄ እየጠየቁ ስለሆነ ለልማት እንቅፋት የሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ የመብራት ሰብስቴሽን ጉዳይ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ በማምረት ላይ ያሉት እንኳን በአቅማቸው ልክ እያመረቱ አይደለም ስሳልሆነ በአፅንኦት ሊታሰብበት ይገባል ሲሉ በቁጭት ገልፀዋል፡፡

‎ስለዚህ በቂ የሆነ የሃይል አቅርቦት ስለ-ሌለ፣ያለውም ስለሚቆራረጥ ከላይ እስከ ታች ያለ የአካባቢው ልማት ይመለከተኛል የሚል ባለ ድርሻ አካል ርብርብ አድርጎ ወረዳው የሰብስቴሽን ተጠቃሚ ማድረግ አለበት።ያ ካልሆነ ያለ ሀይል አማራጭ ኢንቨስትመንት ሊሳለጥ አይችልምና ኢንቨስትመንትን ማሰብ ከንቱ ነው ብለዋል ፡፡

‎ ሁለተኛ በተመሳሳይ የፌደራል የመንገድ ጥገናው በተለይ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለመውሰድ በጣም የተቸገሩበት ከባባድ መኪናዎች ይመጣሉ በመንገዱ ምክንያት የጫኑትን እቃ እየሰበሩ በሚልዬን የሚከስሩበት ችግር ሰለገጠማቸው ወደ ሌላ አማራጭ ቦታ በመፈለግ የሄዱብን ትላልቅ አምራች ኢንዱስትዎች ስላሉ የመሰረተ ልማት ችግሮቻችንን የሚመለከተው አካል ከፌደራል እስከ ወረዳ ተቋማት ርብርብ አድርገው መፍታት ቢቻል ሌሎች ጥቃቅኖቹን በጽ/ቤት እየፈታን እንሰራለን ብለዋል ኃፊው፡፡

‎በዋናነት በግንባታና በቅድመ ግንባታ ላይ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የግንባታ ውሃ እጥረት እና የክልሉ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ በአምራቾቹ ላይ ደግሞ የመብራት ሀይል እጥረት እንደ ችግር እዳጋጠሟቸው መሰዳት እንደቻሉና ከባለሀብቱ ጎን በመሆን ለመፍታት ጥረት እንዳደረጉም ጠቅሰዋል፡፡

‎ በአጠቃላይ የወረዳችን ህዝብ ለኢንቨስትመንቱ ያለው አመለካከት ጥሩና ሊመሰገን የሚገባው ደጋፊና ምስጉን ማህበረሰብ በመሆኑ አመስግነው ተጠናክሮ ይቀጥል ብለው እንደ መንግስት ያለው ጥሩ ጎን እንዳለ ሆኖ ለቀጣይ ነፃ መሬት ለባለሀብቶች ስለሚያስፈልግ መሬቶችን ከሦስተኛ ወገን ነፃ አድርጎ መጠበቅ ክፍተቶች ስላሉ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ሲሉ በጽ/ቤቱ ስም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Address

Arerti

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Minjar Shenkora Wereda Industry and Investment Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share