Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia

Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia, Government Organization, Arba Mintch.
(1)

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት አካል የሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የከተማው ኮሪደር የምሽት ድባብ በፎቶ......
02/06/2026

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት አካል የሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የከተማው ኮሪደር የምሽት ድባብ በፎቶ......

02/06/2026
02/06/2026
የገሱፓ ከተማ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤታዊ ዲጂታል አገልግሎት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ከፊል ገጽታ በፎቶ..........
27/05/2026

የገሱፓ ከተማ አስተዳደር የማዘጋጃ ቤታዊ ዲጂታል አገልግሎት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ከፊል ገጽታ በፎቶ..........

በገሱባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ ዲጂታል አገልግሎት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ‎በገሱባ ከተማ አስተዳደር  ከ14 ሚሊዮን ብር  በላይ በጀት ወጪ የተደረገባቸው የኮ...
27/05/2026

በገሱባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ ዲጂታል አገልግሎት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ

‎በገሱባ ከተማ አስተዳደር ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ወጪ የተደረገባቸው የኮሪደር ልማት፣ የኅብረተሰብ ፋርማሲ እና የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ማዘመኛ ዲጂታል አገልግሎት በይፋ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

በአገልግሎት ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የዕለቱ ክቡር እንግዳ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሪሁን ፍቅሩ ለከተሞች ዕድገት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረውነጋዴዎች ግብር በጊዜ እንዲከፍሉ አሳስበዋል።

ዶክተር መሪሁን አክለውም ማዘጋጃ ቤቱ ከሌብነት በፀዳ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዳለበትም በመግለጽ አገልግሎቱን የማዘመን የተቀላጠፈ እና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና መንግሥት ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለአገልግሎት እያበቃ እንደሚገኝ ገልጸው ለከተማዋ ዕድገት ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ መንግሥት የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየፈታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ለከተማዋ እና ህዝብ ዕድገት ሁሉም በትብብር መሥራት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

የገሱባ ከተማ ከንቲባ አቶ ደማ ኃይሌ ያለ መላው የከተማው ህዝብ ተሳትፎ ልማት ዕውን አይሆንም ሲሉ ተናግረው ለተባበሩ የከተማው ህዝብ እንዲሁም ለነጋዴው ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

ከተማን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የከተሞች መዘመን ምልክት ነው ሲሉ ተናግረው ለነዋሪዎች ምቹ እና ፅዱ የማድረግ እና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አፈወርቅ ለማን ጨምሮ የዞን የገሱባ ከተማ እና የኦፋ ወረዳ አመራሮች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የአካባቢው ኅብረተሰብ በተገኙበት ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል ሲል የዘገበው የዞኑ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ነው።

በዳዊት ሽፈራው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሣችሁ እያለ  መልካም...
26/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና መሠረተ-ልማት ቢሮ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሣችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

ዒድ- ሙባረክ

አረንጓዴ ከተሞች ክፍል-2የአረንጓዴ ከተሞች ውጥን ሌላኛው የማጠንጠኛ ነጥብ ደግሞ የደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብ እና አወጋገድ ሥርዓት ነው። ግንቦት 18/2018 ዓ.ም(ከመልቢ)በከተማ የ...
26/05/2026

አረንጓዴ ከተሞች
ክፍል-2

የአረንጓዴ ከተሞች ውጥን ሌላኛው የማጠንጠኛ ነጥብ ደግሞ የደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብ እና አወጋገድ ሥርዓት ነው።

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም(ከመልቢ)

በከተማ የሚኖረው ሕዝብ በቁጥርና ገቢ ከማደጉና ከኢንደስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መስፋፋት ጋር የሚመነጨውም ቆሻሻ በዓይነት እና በብዛት እንደሚጨምር ይጠበቃል።

ይህም የሚያስከትለውን የጤናና አካባቢ ደኅንነት ለመከላከል የሚያስችል ዘመናዊ የቆሻሻ አሰባሰብ ፣ አወጋገድ እልፍ ሲልም መልሶ አጠቃቀም ሥርዓትን መተግበርን አስፈላጊ ያደርገዋል።

ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ቀድሞ የነበሩትን የዘፈቀደ ቆሻሻ ማስወገጃ አካባቢዎች የሚተኩ 101 ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ እና የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች ተገንብተዋል። ከነዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ አና አዳማ ህገ-ወጥ የቆሻሻ አወጋገድን ለማስቀረት እነዲያስችሉ ሆነው የተገንቡት አዳዲስ የቆሻሻ ማስተላለፊያ ጣቢያዎች ተጠቃሽ ናቸው።

ቆሻሻን መልሶ ከመጠቀም አንጻርም ከዚህ ቀደም ለዘመናት ለነዋሪዎች የስጋት ምንጭ ሆኖ በኖረው የቆሼ የቆሻሻ መጣያ ቦታ ላይ የረጲ የቆሻሻ ኃይል ማመንጫ አንዱ ጅምር ነው።

በተያያዘም በከተሞቻችን ደረጃቸውን የጠበቁ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና ማስተላለፊያ ጣቢያዎችና መስመሮች፣ የኮምፖስት ማምረቻና የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶች ለመልሶ ጥቅም ማዋያ ፋብሪካዎች ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ይገኛል። የአረንጓዴ ከተሞች ርእይ እንደ ውብና ንጹሕ መልክዓ ምድር ሁሉ ከብክለት የጸዳ ንጹሕ ከባቢ አየርን መፍጠርንም ያካትታል።

ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ በአንድ በኩል በተለይ በንግድ፣ በኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ዘርፎች ላይ የበካይ ጋዝ ቁጥጥር ማዕቀፎችን በማዘጋጀት በሌላ በኩል ታዳሽና አማራጭ የኃይል ምንጮችን በመፈለግ ላይ ተጠምዳለች።

ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2030 የበካይ ጋዝ ልቀትን እንደ ሀገር በ68% እንዲሁም በመዲናችን በ41% ለመቀነስ አቅዳ እየሰራች ነው። ለዚህ መሳካትም የሚያግዙ የአየር ብክለት እና ሐይል አጠቃቀም ዝርዝር የቁጥጥር መመሪያዎች ተዘጅተው ወደ ትግበራ ወርደዋል። ሌላኛው የንጹሕ ከባቢ አየር የመፍጠር ግብ ዋነኛ አካል የሆነው ከአረንጓዴ ከተማነት እሳቤ ጋር የተጣጣመ የትራንስፖርት ዘርፍን መፍጠር ነው።

የትራንስፖርት ዘርፍ በባሕሪው ግዙፍ የኃይል ፍጆታን የሚጠይቅና ከፍተኛ የአየር ብክለትን 46 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ሊያስከትል የሚችል ዘርፍ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥትም ይህንን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያግዙ ጠንካራ መመሪያና አዋጆችን አውጥቶ ለመተግበር በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

እ.አ.አ ከጥር 2024 ጀምሮ ኢትዮጵያ የነዳጅ መኪኖች ሙሉ ለሙሉ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የከለከለች የመጀመሪያዋ ሀገር ስትሆን በአንጻሩ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በሯን ክፍት አድርጋለች። ሀገር ውስጥ በሥራ ላይ ያሉትንም የነዳጅ መኪኖች የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን ተለክቶ ቁጥጥርና ማስተካከያ እንዲደረግባቸው የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ለመግባት ተቃርቧል።

በተጨማሪም በቅርቡ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ መመረት መጀመሩን ተከትሎ ከባድ ተሽከርካሪዎችን እና የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶችን በአንጻራዊነት ርካሽ ፣ ኃይል ቆጣቢ በሆኑና የአየር ብክለት ተፅዕኖአቸው ዝቅተኛ በሆኑ በተፈጥሮ ጋዝ በሚሠሩ መኪኖች ለመለወጥ እየተሰራ ይገኛል።

የከተሞች የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የኪነጥበብ፣ የቴክኖሎጂ እና ዕውቀት ማዕከልነት ፥ ጤናማ፣ ንጹሕ፣ ውብ፣ ለአደጋ አይበገሬ እና ለመኖር ምቹ የሆኑ አረንጓዴ ከተሞችን ሳይገነባ ዘላቂነት ሊኖረው አይችልም።

በመሆኑም በከተሞች የአረንጓዴና የወንዝ ዳር ልማቶች ፣ በዘመናዊ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት እና በበካይ ጋዝ ልቀት ቁጥጥር የሚገለጸው የአረንጓዴ ከተሞች ልማት ግዙፍ ርእይ ሰንቆ እንደመነሣቱ የሚያጋጥሙትን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ተቋቁሞ ተጨባጭ ለውጦችን እያስገኘ ቀጥሏል ሲል የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል።

በዳዊት ሽፈራው

አረንጓዴ ከተሞች ክፍል-1በፈጣን የከተሞች እድገት እና መስፋፋት፥ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፉ መዘመን ትልቁን ድርሻ በወሰደበት በዚህ ጊዜ የአረንጓዴ ከተሞች እሳቤ ለከተሞች እድገት ዘላቂ...
25/05/2026

አረንጓዴ ከተሞች
ክፍል-1

በፈጣን የከተሞች እድገት እና መስፋፋት፥ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፉ መዘመን ትልቁን ድርሻ በወሰደበት በዚህ ጊዜ የአረንጓዴ ከተሞች እሳቤ ለከተሞች እድገት ዘላቂነትና ፈተናን የመቋቋም አቅም (resilience) የሚመዘንበት አንዱና ዋነኛው መስፈርት ነው።

ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

አረንጓዴ ከተሞች የኢኮኖሚ እድገትን ከተፈጥሮ ጥበቃ እና ከማኅበረሰብ ደኅንነት ጋር ያስማሙ ናቸው። እድገታቸውም የሥነ ምኅዳሩን ጤንነት በመጠበቅ እና የቀጣይ ትውልዶችን ሕይወት ታሳቢ ባደረገ መልኩ ነው።

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ገና በመልማት እና በመከተም ላይ ያሉ ሀገራት ደግሞ ከተሞቻቸውን በዚህ እሳቤ ለማልማት የሚቻልበት ዕድል ሰፊ ነው። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ10 ዓመት ዕቅድ ውስጥ አረንጓዴ ከተሞችን የመፍጠር ትልም አጽንኦት ተሰጥቶት ይገኛል። ይህ ትልም ኢትዮጵያ ከከተማ ልማት እና የኃይል አጠቃቀም አኳያ የምታማትርበትን የለውጥ አቅጣጫ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

ከተሞቻችን ሀገራዊ የብልጽግና እና ኢኮኖሚያዊ የስበት ማዕከላት እንደመሆናቸው መጠን ለነዋሪዎችም ምቹ ፣ ውብ ፣ ንጹሕ እና ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ላይ ይገኛል። አረንጓዴ ከተሞችን የማልማት አስፈላጊነት በተለይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም።

ፈጣን የሆነው የሀገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ፣ የከተሞች መስፋፋት እና በከተሞች ያለው የሕዝብ ቁጥር መጨመር ከተሞችን በአየር ንብረት ለውጥና በአከባቢ ብክለት ምክንያት ለሚከሰቱ ችግሮች ይበልጥ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።

ለዛም ነው በአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ (Ethiopia’s Climate-Resilient Green Economy Strategy) ሰነድ ላይ ኢትዮጵያ እንደ ጎርፍ ፣ ድርቅ እና መሬት መሸርሸር ላሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች ያላትን ጉልህ ተጋላጭነት አስምሮ የሚነሳው።

ጠንካራ መሠረተ ልማት ያላቸው አረንጓዴ ከተሞች ይህን ተጋላጭነት በመከላከልና በመቀነስ ዘላቂነት ያለው ልማትን ለማረጋገጥ እድሉን ይፈጥራሉ።

ከዚህም ባሻገር የአረንጓዴ ከተማ መሰረተ ልማቶች በራሳቸው የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ ቱሪዝምን በማሳደግ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት በማሻሻል የኢኮኖሚ እድገትን ያነቃቃሉ። አረንጓዴ ከተሞችን የማልማት አስፈላጊነት በተለይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ነዋሪ፥ በከተማ የሚኖር፤ ነገር ግን ከተሜነት ሊሰጠው ይገባ ከነበሩት ትሩፋቶች የራቀ ሆኖ እናገኘዋለን።

በዝቅተኛ ጥራትና እቅድ የተገነቡ፣ የተጨናነቁ፣ እልፍ ሲልም ለጎርፍና መሰል የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ጉድለቶች እና አየር ብክለት ከተሞችን ለዜጎች ጤናማ እና ምርታማ ህይወት አመቺ እንዳይሆኑ አድርጓቸው ቆይቷል።

ስለዚህም ይህን በመቀየር አመቺ የኑሮ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊነትም አንዱ እና ዋነኛው የአረንጓዴ ከተሞች ርዕይ መገለጫ ሆኖ እናገኘዋለን።

የጽዳት፣ የአረንጓዴና የተፋሰስ ልማት፣ በግንባታ፣ ምርትና ትራንፖርት ዘርፎች ላይ የሚደረጉ የአከባቢ ብክለት ጥበቃና ቁጥጥር ማዕቀፎች በሙሉ የዚህ ርእይ እውናዊ መንበሪያዎች ናቸው።

በአረንጓዴና ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክቶች ለከተሞች ሳንባ የሚሆኑ አረንጓዴ ቦታዎችን ማስፋፋት፣ ወንዞችን መታደግና የጎርፍ ተጋላጭነትን መቀነስ ተችሏል።

ከተሞች ከጥቅማዊ ፋይዳቸው ባለፈም የሥነ ውበት ዕሤትን የተጎናጸፉ፤ ለመኖር ምቹና ለእይታ ውብ እንዲሆኑ ተሠርቷል እየተሠራም ነው።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ 69 ኪ.ሜ በሚሸፍኑ ተመጋጋቢና ገባር ወንዞች ላይ የሚተገበረው የሸገር ወንዞች ልማት ፕሮጀክት ወንዞቹን ከመጠበቅ፣ ከማጽዳትና ማልማት ባለፈ ከ1.3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በአረንጓዴ አሻራ ባለፉት 5 ዓመታት ብቻ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለው 90% ማጽደቅ የተቻለ ሲሆን በዚህም የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እ.አ.አ በ2018 ከነበረው 17.2% በእ.አ.አ በ2023 ወደ 23.6% አድጓል።

የአዲስ አበባን የደን ሽፋን ብቻ ለይተን ብንመለከት እንኳን ከ11% ወደ 20% ደርሷል። እኚህና መሰል ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ መልክዓ ምድሮች የከተማ ልማት ዕቅድ አንድ አካል ወደሆኑበት ሥነ ምኅዳራዊ (ecological) የከተማ ንድፍ እየተደረገ ላለው ሽግግር ሕያው ማሳያዎች ናቸው ሲል የጽሁፍ ምንጭ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል።

በዳዊት ሽፈራው

በጋሞ ዞን በብርብር ከተማ አስተዳደር ዲጅታል የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በይፋ ተጀመረበብርብር ከተማ የገቢና ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ዘመናዊ ሕንፃ ምረቃ እና የ“አንድ መሶብ” ግንባታ ስራ ማጅመ...
25/05/2026

በጋሞ ዞን በብርብር ከተማ አስተዳደር ዲጅታል የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

በብርብር ከተማ የገቢና ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ዘመናዊ ሕንፃ ምረቃ እና የ“አንድ መሶብ” ግንባታ ስራ ማጅመሪያም መርሐ ግብር ተካሄዷል

ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተጋበዙ እንግዶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት የብርብር ከተማ አስተዳደር ዲጅታል የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በይፋ ተጀምሯል።

በጋሞ ዞን ብርብር ከተማ አስተዳደር በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ የልማት ትሩፋቶችን የሚያሳዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የምረቃና የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተጋበዙ እንግዶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት የከተማዋን የፋይናንስ አቅምና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በላቀ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ የሚጠበቀው ዘመናዊ የገቢና ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ሕንፃ በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በዕለቱ የተካሄደው የምረቃ ፕሮግራም የለውጡ መንግሥት የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተግባር ለመመለስ፣ የመንግሥት የገቢ አሰባሰብ ሥርዓትን ለማዘመን እና ለነዋሪዎች ዘመናዊና ምቹ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

ከምረቃ መርሃ ግብሩ ጎን ለጎን የከተማዋን ባህላዊ፣ ታሪካዊና ሕዝባዊ እሴቶች የሚያጎላው የ“አንድ መሶብ” ፕሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትም በልዩ ሁኔታ ተከናውኗል።

ለከተማዋ መለያና ውበት ይሆናል ተብሎ የታመነበትን ይህን ታላቅ ፕሮጀክት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ደምሴ አድማሱ እና የብርብር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብረሃም አይካ በጋራ በመሆን መሠረተ ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

የገቢና ፋይናንስ ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱና የ“አንድ መሶብ” ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ በብርብር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ያለውን ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እና ከተማዋን ወደ ተሻለ ብልጽግና የማሸጋገር ጉዞ በግልፅ የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።

የብ.ከ.አስ.መን.ኮ

የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን መሠረተ ልማት ከማዘመን ባለፈ  ለከተማዋ አዲስ ገጽታን የሚሰጥ መሆኑ ተጠቆመ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ በክቡር አቶ ብርሃኑ ዘው...
23/05/2026

የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን መሠረተ ልማት ከማዘመን ባለፈ ለከተማዋ አዲስ ገጽታን የሚሰጥ መሆኑ ተጠቆመ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ በክቡር አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የኮሪደር ልማት ባለድርሻ አካላት አፈፃፀም መድረክ አካሄዱ።

አ.ምንጭ ግንቦት 15/2018(ከመልቢ)

የከተማ ነዋሪውን ለኑሮ ምቹ በማድረግ ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ፣ የንግድ ማዕከል በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ የታመነበት የኮሪደር ልማት ሥራ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት እየተከናወነ ይገኛል።

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረውንና ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ውብ የማድረግ ሀገራዊ ራዕይ መነሻ በማድረግ የኮርደር ልማት ባለድርሻ አካላት አፈፃፀም መድረክ ተካሄደ።

ከተማዋን ከአፍሪካ ካሉ አስር የቱሪስት መዳረሻ ከተሞች መካከል በቀዳሚነት የምትጠራና ተመራጭ የቱሪስት ማዕከል እንድትሆን የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን መሠረተ ልማት ከማዘመን ባለፈ ለከተማዋ አዲስ ገጽታን የሚሰጥ መሆኑ ተጠቆመ ።

በአርባምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን መሠረተ ልማት ከማዘመንም ባለፈ ስታንዳርድን ተከትሎ መከናወኑ ለግንባታው ጥራትና ለሥራው ቀጣይነት ትልቅ ዋስትና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ በበኩላቸው የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሳሳረ ልማት ነው። ልማቱ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ ልማት ለዜጎች ለማቅረብ በማለም የተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የከተማ ነዋሪው በባለቤትነት የመሰረተ ልማት ጥበቃ በማድረግ እንዲሁም የፅዳት ባህሉን እንዲያጠናክር አሳስበዋል።

በመድረኩም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ፣ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ክቡር ዶ/ር መስፍን መንዛን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈፃሚ እና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የአርባምንጭ ከተማ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ነው።

Address

Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share