South Ethiopia Region Revenue Bureau /የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ/

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • South Ethiopia Region Revenue Bureau /የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ/

South Ethiopia Region Revenue Bureau /የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Ethiopia Region Revenue Bureau /የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ/, Public & Government Service, Limat, Arba Mintch.

በተከታታይነት ውጤት የተመዘገበባቸው 8ቱ ዓመታት ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)የገቢዎች ሚኒስቴር በ8 ዓመታት ውስጥ ማለትም (ከ2011 እሰከ 2018 ዓ.ም)  ተከታታይነት ...
04/06/2026

በተከታታይነት ውጤት የተመዘገበባቸው 8ቱ ዓመታት

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር በ8 ዓመታት ውስጥ ማለትም (ከ2011 እሰከ 2018 ዓ.ም) ተከታታይነት ያለው እና የተሳካ የገቢ አፈጻጸም ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

የየሶስት ወሩ የቅድመ ግብር ክፍያ መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ 4 ቀናት ቀርተውታል። እስከዚያው ድረስ ክፍያዎን በማጠናቀቅ ግዴታዎን ይወጡ።
04/06/2026

የየሶስት ወሩ የቅድመ ግብር ክፍያ መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ 4 ቀናት ቀርተውታል። እስከዚያው ድረስ ክፍያዎን በማጠናቀቅ ግዴታዎን ይወጡ።

የየሶስት ወሩ የቅድመ ግብር ክፍያ መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ቀርተውታል። እስከዚያው ድረስ ክፍያዎን በማጠናቀቅ ግዴታዎን ይወጡ።
03/06/2026

የየሶስት ወሩ የቅድመ ግብር ክፍያ መክፈያ ጊዜው ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ቀርተውታል። እስከዚያው ድረስ ክፍያዎን በማጠናቀቅ ግዴታዎን ይወጡ።

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፣ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት ማለትም የ2017 ግብር ዘመን በነበረው የከፈሉትን ግብር 25%(ሃያ አምስት በመ...
02/06/2026

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፣

ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት ማለትም የ2017 ግብር ዘመን በነበረው የከፈሉትን ግብር 25%(ሃያ አምስት በመቶ) ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በሚቆጠር በየሶስት ወሩ የሶስት ወሩ በተጠናቀቀ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ አስቀድመው መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
👉የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ጊዜ ከህዳር 01 እስከ 30 ይሆናል፣
👉የሁለተኛ ዙር ክፍያ ጊዜ የካቲት 01 እስከ 30 ይሆናል፣
👉የሶስተኛ ዙር ክፍያ ጊዜ ከግንቦት 01 እስከ 30 ሲሆን በየግብር ዓመቱ ሐምሌ ወር መጨረሻ ሊከፍሉ ከሚገባው ግብር ላይ በየሶስት ወሩ የከፈሉት ተቀንሶ ቀሪውን ይከፍላሉ፡፡

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ መያዝ ግዴታ የለለባቸው ሲሆን በፍቃደኝነት መያዝ ይችላሉ፡፡ የያዙት የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት ካገኘ የሚከፍሉት ግብር በሂሳብ መዝገባቸው ሠንጠረዥ ሐ መሰረት ይሆናል፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ቢኖርም ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢ ግብር የሚከፍሉ አዲስ ግብር ከፋዮች የመጀመሪያውን የግብር ዓመት በተመለከተ ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በሚከተለው አኳኋን ይሆናል፤

ሀ) የደረጃ "ሀ" አዲስ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ገቢያቸውን ማስታወቅ ባለባቸው ጊዜ በግብር ዓመቱ ሊከፍሉት የሚገባውን ግብር መክፈል አለባቸው፡፡

ለ) የደረጃ "ለ" አዲስ ግብር ከፋዮች ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30 ቀን ባለው ጊዜ ዉስጥ ግብሩን መክፈል አለባቸው::

የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብር ክፍያ፦በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 መሠረት፤ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብራቸዉን (1/4ኛ) ክፍያ...
02/06/2026

የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብር ክፍያ፦

በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 መሠረት፤ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ቅድመ ግብራቸዉን (1/4ኛ) ክፍያ ሲፈጽሙ በሩብ ዓመቱ ተቀናሽ የተደረገባቸው 3% ቅድመ ግብር (Withholding) ታሳቢ ይደረጋል።

የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ፦
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🌐 ድረ-ገጽ
https://serb.gov.et

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1CK8kqAM58/

ቴሌግራም ፦
https://t.me/South_ethiopia_revenue

ቴሌቪዥን_ፕሮግራም ፡-
📺 ጋሞ ቴሌቪዥን ቅዳሜ ቀን ከ6:40 እስከ 7:00

፡-
📻 በወላይታ ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ አርብ ጧት ከ4፡40 -5:00

አስተማማኝ የልማት አቅም እንፈጥራለን !

02/06/2026
ባለፉት 10 ወራት በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ከ281 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ                  ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ...
01/06/2026

ባለፉት 10 ወራት በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ከ281 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ተጠቅመው ግብራቸውን የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን በገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ሂሳቦች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የገቢ ሂሳብ ማጠቃለያ ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ኤልሳቤት አሸናፊ ገለጹ፡፡

በዚህም በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 10 ወራት ከ 281 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ በኢ-ፔይመንት የኤሌከትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

እንደ ቡድን አስተባባሪዋ ገለፃ ግብር ከፋዮች ይህንን የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ተመራጭ ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን አገልግሎቱ ተመራጭ ሊሆን የቻለበትን ምክንያት ሲያስረዱም ፈጣን እና ግብር ከፋዮች ወደ ታክስ ማእከላት በአካል መምጣት ሳያስፈለጋቸው በቀላሉ ባሉበት ቦታ ክፍያቸውን ለመፈፀም ስለሚያስችላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ እና ለአጠቃቀም ቀላል በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ኤልሳቤት አክለውም ወደ ኤሌክትሮኒክስ ታክስ ስርዓት ያልገቡ እና ተጠቃሚ መሆን ያልጀመሩ ግብር ከፋዮች ወደዚህ ስርዓት በመግባት ግብራቸውን የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ዘዴን በመጠቀም አሳውቀው እንዲከፍሉ እና ውድ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

31/05/2026

የሆቴል ክፍል ይዞታ ክፍያ የሚከፍለው ማን ነው?

በኢ-ክሊራንስ መተግበሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶች ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)"ኢ-ታክስ" ታክስን ለማሳወቅ፣ ክፍያን ለማከናወን፣ ከዕዳ ነጻ ማረጋገጫ (Tax Clearance)...
30/05/2026

በኢ-ክሊራንስ መተግበሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶች

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

"ኢ-ታክስ" ታክስን ለማሳወቅ፣ ክፍያን ለማከናወን፣ ከዕዳ ነጻ ማረጋገጫ (Tax Clearance) ፣ የተለያዩ ታክስ ነክ ማብራሪያዎች እና ግብር ከፋዮች የራሳቸውን የታክስ መረጃ ለማየት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማግኘት የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡

በዚህ ሥርዓት ከሚሰጡ አገልግሎቶች ውስጥ ግብር ከፋዩ በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ (ሰዓት) የኢ-ክሊራንስ አገልግሎትን ማግኘት ይችላል፡፡

የታክስ ግንዛቤዎን ለማሳደግ እና ፈጣንና ትክክልኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ፦ድረ-ገጽ ፡-  https://serb.gov.etፌስቡክ፡- https://www.faceb...
29/05/2026

የታክስ ግንዛቤዎን ለማሳደግ እና ፈጣንና ትክክልኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ፦
ድረ-ገጽ ፡-
https://serb.gov.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/share/1CK8kqAM58/
ቴሌግራም፦
https://t.me/South_ethiopia_revenue
ቴሌቪዥን_ፕሮግራም፡-
ጋሞ ቴሌቪዥን ቅዳሜ ቀን ከ6:40 እስከ 7:00
የሬድዮ_ፕሮግራም፡-
በወላይታ ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ አርብ ጧት ከ4፡40 -5:00
አስተማማኝ የልማት አቅም እንፈጥራለን!

Address

Limat
Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Region Revenue Bureau /የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share