ሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ This is the Selamber Polytechnic College official page.

ቅጥር ማስታወቂያ ፦
26/02/2026

ቅጥር ማስታወቂያ ፦

የቴክኖሎጂ ሰነድ ዝግጅት እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት   ሰነድ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።*\\*ጥር 19/2018 ዓ/ም ሠላም በር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅበሰላ...
27/01/2026

የቴክኖሎጂ ሰነድ ዝግጅት እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ሰነድ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።
*\\*
ጥር 19/2018 ዓ/ም ሠላም በር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
በሰላም በር ፖሊ ቴክኒክ ኮልጅ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጃ ሽግግር ዳይሮክቶሬት በቴክኖሎጂ ሰነድ ዝግጅት እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ማሰተግበሪያ ሰነድ ላይ ለኮሌጁ አሰልጣኞች ፣ አስተዳደር ሠራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

🌏✈️የውጪ ሀገር የስራ እድል 🚀በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማ...
14/01/2026

🌏✈️የውጪ ሀገር የስራ እድል
🚀በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት በተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል። አሁንም በዚሁ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ወደተባበሩት አረብ ኤምሬትስ/UAE/ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የሰው ሃይል ይፈለጋል።
የስራ ዘርፍ ብዛት
📍BIK DRIVER 350
📍CLEANER 520
📍CONSTRUCTION LABORERS 1050
📍MEP WORKERS 600
📍GARDENERS 700
📍LIFEGUARDS 200
📍WAREHOUSE WORKERS(PICKERS) 700
📍FEMAIL CLEANINERS 200
📍MALE CLEANERS 200
📍CATERING WORKERS 200
📍DALIVERY RUNNER/CYCLIST 400
📍SECURITY GUARDS 200
📍FACTORY WORKERS 400
📍CIVIL CHARGEHANDS 200
📍CHARGEHAND 100
📍CARPENTERS 100
📍PAINTER 20
📍COOK 20
📍SELSMAN 100
📍CHECKER PICKERS 30
📍FISHERY STAFFS 20
📍BUCHERY STAFFS 20
📍SECURITY 40
📍POT WASHERS 40
📍LOADING AND UPLOADING STAFF 40
📍BRICK MASON 100
📍BRICKLAYER ASSISTANT 100
📍BUILDING CLEANERS 200
📍LIMOUSINE DRIVER 100
📍DIGGER 500
📍IRRIGATION PIPE FITTER 500

🏫ስለሆነም ይሆንን እድል ለትጠቀሙ የምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/uae-new/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
☎️አስተያየት እና ጥቆማዎን በ9138 ነፃ የሥልክ መስመር በመደወል እንዲያደርሱን እናሳስባለን።

የጋሞ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት  ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብረሃኑ አራያ እና የሠልጣኝ አ...
02/01/2026

የጋሞ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኢንዳስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብረሃኑ አራያ እና የሠልጣኝ አሰልጣኝ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ እንዮ ካዲኦ ጋር በጋራ በመሆን በቀን 24/04/2018 ዓ.ም በሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኮሌጁ ማኔጅመንት ጋር የኮሌጁ አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታ፣የ6 ወር ሥራ አፈፃፀም እና የሠልጣኝ ቅበላ ነባሪና አድስ የደረሰበትን ሁኔታ በመገምገምና ቀጣይ ከቦርዱ ጋር በመናበብ በሦስቱም መዋቅር በልዩ ትኩረት ሠልጣኞችን በመለየት ወደ ኮሌጁ የመመጡበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ ልሰሩና ልተገበሩ የሚገቡ ነጥቦችን በመለየት መሰራት እንደለበትና ከማኔጅመንቱም በተነሱ ሐሳቦች ለይ በጥልቀት በመወያየት ሀሳባቸውን አስቀምጧል።

✈️ውጪ ሀገር/UAE የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕድል 👉በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ...
25/12/2025

✈️ውጪ ሀገር/UAE የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕድል

👉በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት በተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል።

👉አሁንም በዚሁ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ወደተባበሩት አረብ ኤምሬትስ/UAE/ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የሰው ሃይል ይፈለጋል።

📌የኮንትራት ቆይታ:ሁለት አመት
📌ተፈላጊ ፃታ:ወንድ

🚧የሞያ ዘርፎች:-
1.Construction Laborers (የኮንስትራክሽን ሰራተኛ / ረዳት)
2.Mason(ግንበኛ)
3.እስቲል ፊክሰር (ፌራዩ)
4.Shuttering Carperter (አናፂ)
5. Delivery Boy (ሞተረኛ)
6. Walkers (እግረኛ ተላላኪ)
7. Plumber (የቧንቧ ሰራተኛ)
8. Electrician (የኤሌክትሪክ ሰራተኛ)
9. Scaffholders (የብረት መወጣጫ ባለሞያ)
10. Ductmen (የቬንትሌሽን ባለሞያ)
11. Supervisors and Foreman
12. Timekeepers (የሰራተኛ ሰአት ተቆጣጣሪ)
13. Camp Boss Assistant (የካምፑ አለቃ ተጠሪ)

☝️በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች ለመወዳደር https://forms.lmis.gov.et/triple-one-uae/ በመግባት ፓስፓርት፣ የሰራተኛ መለያ ቁጥር/Labor id/፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና አስፈላጊ መረጃዎችን በማስገባት ከታህሳስ 08 እስከ ታህሳስ 14 2018 መወዳደር ይቻላል።

💰የትኬት፣ የጤና ምርመራ እና ቪዛ በአመልካቾች የሚሸፍኑ ወጪዎች መሆኑን እንገልፃለን። ሌሎች በስራ ቆይታ ላይ የሚያስፈልጉ የመኖርያ ቤት፣የማብሰያ ክፍልእና ከነማብሰያ እቃዎች፣ኢንሹራንስ እና የህክምና ወጪ በአሰሪው የሚሸፈኑ ወጪዎች ይሆናል።

✅ ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ 9138 ነፃ የሥልክ መስመር ይጠቀሙ

ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

የተሻሻለዉ የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ክልላዊ ሥልጠና ለሚመለከታቸዉ የባለ ድርሻ አካላት እየተሰጠ ይገኛል።ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም አርባምንጭየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ...
25/12/2025

የተሻሻለዉ የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ክልላዊ ሥልጠና ለሚመለከታቸዉ የባለ ድርሻ አካላት እየተሰጠ ይገኛል።

ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም አርባምንጭ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ የተሻሻለው የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ላይ ለተለያዩ የባለድርሻ አካላት ሥልጠና መስጠት ጀምሯል።

በመድረኩ ክቡር አቶ ማሄ ቦዳ የክልሉ ምክትል ርዕሰምተዳድር አማካሪና የጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ የተከበሩ አቶ እንቁ ዮሐንስ የምክር ቤት ፕላን መሠረተ ልማትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚተ ሰብሳቢ፣ወ/ሮ ፀሐይ ኃይለሚካኤል የርዕሰ መስተዳድር ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪን ጨምሮ የዞንና የሪጅኦ ፖሊ ከተሞች የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች፣ፖሊ ቴክኒክና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ዋናና ምክትል ዲኖች፣ የመንግስት፣ የግል እና የመያድ ሥልጠና ኮሌጅ ዲኖች እንዲሁም የቢሮ ምክትል ኃላፊዎችና ማኔጅመነት አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘገባዉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮማኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነዉ።

ለኮሌጁ አሰልጣኞችና አሰተዳደር ሰራተኞች ተግባራዊ ጥናትና ምርምር አሰራር  ላይ   ሥልጠና ተሰጠ፡፡ታህሳስ 16/4/2018 ዓ.ም (ሰላም በር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ) በሰላም በር ፓሊ ቴክኒክ ኮ...
25/12/2025

ለኮሌጁ አሰልጣኞችና አሰተዳደር ሰራተኞች ተግባራዊ ጥናትና ምርምር አሰራር ላይ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ታህሳስ 16/4/2018 ዓ.ም (ሰላም በር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)

በሰላም በር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለኮሌጁ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዝግጅትና አተገባበር ላይ በኮሌጅ በሁለቱም ዘርፍ የሚሰሩ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚረዳ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር /Action Resarch induction training/ በኢ/ር ታምራት ታይሳ የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል።
የኮሌጁ የቴክኒካልና ክህሎት አቅም ግንባታ ቡድን መሪ ዳንኤል ጉልታ /ኢ/ር ስልጠውን ሲከፍቱ አሰልጣኞች ስልጠናውን ሰልጥነው ወደፊት በኤንድስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሥልጠና ዘርፍ ተግባራት በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ችግሮችን በመለየት ውጤታማ ስራ ለመስራት ቁርጠኛ እንዲሆኑ አደራ ብለዋል።

09/12/2025
"ስብዕናቸው የዳበረ ብቁ ክህሎት ያላቸውን ሰልጣኞች በማፍራት የስራ ስምሪት እንዲያገኙ ይሰራል" አቶ ሀኪሜ አየለሠላምበር፦  ህዳር  30/2018 ዓ.ም (ሠ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ)በጋሞ ዞን ሥራና ክህ...
09/12/2025

"ስብዕናቸው የዳበረ ብቁ ክህሎት ያላቸውን ሰልጣኞች በማፍራት የስራ ስምሪት እንዲያገኙ ይሰራል" አቶ ሀኪሜ አየለ

ሠላምበር፦ ህዳር 30/2018 ዓ.ም (ሠ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ)

በጋሞ ዞን ሥራና ክህሎት መመሪያ በ2018 ዓ.ም ሠልጣኝ ቅበላ ዙሪያ የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ የተለያዩ ኮሌጆች ዲኖችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀኪሜ አየለ ባስተላለፉት መልዕክት የሠልጣኝ ቅበላ ላይ ትኩረት በማድረግ በሙያ የተካነ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ሁለንተናዊ ስብዕናው የተጠበቀ፣ በክህሎት የዳበረ ሰልጣኝ በማፍራት የስራ ስምሪት እንዲያገኝ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ከፖሊሲ ጉዳዮች አኳያ ተገቢነት፣ ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን በጠንካራ ተቋማዊ አሰራር ሊተገበሩ እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ሀኪሜ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማጎልበት የወንድ ሰልጣኝ ቁጥር ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አክለውም በቴክኒክና ሙያ የሚሰጠው ስልጠና ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ እንዳይል የሰልጣኞችና የማሕበረሰቡ የአመለካከት ችግር ጎልቶ መታየቱን አውስተው በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች የሚያቀርቡትን ምርቶች በመጠቀም ማበረታታት ይገባልም ብለዋል።

በብድር አመላለስ፣ በሒሳብ ዝርጋታ፣ በኦዲትና በደረጃ ሽግግር የታዩ ጉድለቶችን መፍታት እንደሚገባ ያብራሩት አቶ ሀኪሜ ቁጠባንና አጫጭር ስልጠና በማጠናከር የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር የስራ ስምሪት ለማመቻቸት በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
ምንጭ፦ (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)

የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ግርማ የክልሉ መንግስት የሕብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መከፈታቸውን ገልፀው መዋቅራዊ ሽግግርና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሙያ ሰልጣኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።

የስራ አጥን ቁጥር መቀነስ የሁሉም ባለድርሻ የማያቋርጥ የሁልጊዜ ተግባር መሆን እንደሚገባ የተናገሩት አቶ አዲሱ የስራና ክህሎት ተቋማት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የብድር ስርጭትና ተዘዋዋሪ ፈንድ አጠቃቀም ማሻሻል ይገባልም ብለዋል።

የሰልጣኝ ቅበላ ለተከታታይ 3 አመታት ከ50 በመቶ ማለፍ አለመቻሉ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጠንካራ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ በአከባቢው ባሉ ፀጋዎች ሰልጣኞችን ማሰማራትና የሙያ ብቃት ምዘና በአግባቡ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የተለያዩ ተቋማት ከመምሪያው ጋር የግብ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት አዲሱን የሲቪል ሰርቪስ መመዘኛ መሠረት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሌጆች፣ የስራ ሂደቶችና ለፈጻሚዎች እውቅና ተሰጥቶዋቸዋል።

የሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አርማ /logo/ በታች በቀረበው መነሻ መሠረት በአጠቃላይ በሎጎ ሥራና ዲዛይን ላይ የሚጨመርና የሚስተካከል የተኛውም ሀሳብና ቀለም ምርጫ ከኮሌጁ ራዕይና ዓላማ ...
26/11/2025

የሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አርማ /logo/ በታች በቀረበው መነሻ መሠረት በአጠቃላይ በሎጎ ሥራና ዲዛይን ላይ የሚጨመርና የሚስተካከል የተኛውም ሀሳብና ቀለም ምርጫ ከኮሌጁ ራዕይና ዓላማ አንጻር ተሠርቶ ለኮሌጁ ቦርድ ቀርቦ ከመጽደቁ በፊት ለህዝብ አስተያየት ያቀረብን ስሆን ከአከባቢው ፀጋ መነሻ ታሳቢነት እንድሁም ከቀለም ምርጫ ጀምሮ የሚሰጡ ሀሳቦችና አስተያየቶች ገንቢና ኮሌጁን መስሎ መግለጽ በሚቻለው መልክ መስራት ጥሩ፣ መልካምና የቀጣይ ጉዞን ለማሳየት ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም የቁጫ 3ቱ መዋቅር ማህበረሰብና የጋሞ ዞን ህዝብ እንዲሁም ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሙያዊ አስተያየት በመሰብሰብ የሁላችንም የሆነውን ተቋም ሀሳብ መስጠት ከሚችሉት ከሁሉም ህዝብ በጋራ የጋራ ለማድረግ የእናንተን ሀሳብና አስተያየት መቀበል ወሳኝ ስለሆነ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ በአክብሮት እንጠይቃለን ።
ልዩ ሙያዊ እገዛና አስተያየት ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ሀሳብ በውስጥ መስመርም ጭምር ሀሳብ መስጠት የሚቻል መሆኑንም መሆኑን በቀን 04/03/2018ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ መግለጻችን ይታወሳል ።

በዚህ መሠረት በርካታ አስተያየቶች የተሰጡ ስሆን አሁን የተሻሻለው ላይ ያለው ሀሳብ አስተያየት ተቀብለን ለማስተካከል ዝግጁ መሆናችንን እየገለጽን በድጋሜ በአክብሮት እናሳውቃለን ።
ከታች የመጀመሪያውንና የተሻሻለው ቀርቧል።
ለሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሚከተሉት መገናኛ አማራጮች መረጃ መስጠት የሚቻል መሆኑን በትህትና እንገልፃለን ።

Website: 🌐 https://stvet.edu.et/ https://www.facebook.com/profile.php?id=100075884746891
https://www.facebook.com/profile.php?id=61571119977837
Telegram: ?? https://t.me/+CJ8RAOOP6FEzNWU0
Email : 📱 [email protected]
WhatsApp: https://wa.me/+251901701626
የኮሌጁ ስልክ ቁጥር 0464590676/0464590685
Mob.+251916757601
+251926533334
+251916591139

ህዳር 18/03/2018ዓ.ም
የሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሠላምበር

የሰላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማናጅመንት በ2018 በጀት ዓመት የበጀት ድልድል ዙሪያ  ተወያየ‎‎ህዳር 17/2018 ዓ.ም‎ሠላም በር ፖ/ቴ/ኮሌጅ‎የኮሌጁ ማናጅመንት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ውይ...
26/11/2025

የሰላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማናጅመንት በ2018 በጀት ዓመት የበጀት ድልድል ዙሪያ ተወያየ

‎ህዳር 17/2018 ዓ.ም
‎ሠላም በር ፖ/ቴ/ኮሌጅ

‎የኮሌጁ ማናጅመንት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ውይይት በ2018 የበጀት ዓመት የበጀት ድልድል እና ቀጣይ በሚኖረው የተቋሙ የበጀት አጠቃቀም ስርአት ዙሪያ በመወያየት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

‎የኮሌጁ ዲን ኢን/ር ድርጅት ድንበሩ በውይይቱ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት ኮሌጁ ወደ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያደገእና አዲስ የተከፈቱ እና ግብዓት በሚፈልጉ ዲፓርትመንቶች ተቋሙ ላይ በጀት እንዲደለደል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎በሌላ በኩል ሁለቱም ዘርፎች ሆኑ ደጋፊ ሥራ ሂደቶች በበጀት አስደግፈው የያዟቸውን ተግባራት በቲውአር አስደግፈው እንዲያቀርቡና ከቲውአር ውጪ በመሀል የሚቀርቡ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስበዋል።

‎አንደ ኮለጅ ኮሌጅን ከፍ አድርገው ለሚያሳዩ ተግባራት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ዲኑ ለውጤታማነቱም የሁሉንም የኮሌጅ ማንጅመንት እና ባለሙያዎች ርብርብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

‎የኮሌጁ ምክትል ዲንና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ኃላፊና ም/ዲን ኢ/ር መኮንን ካባ በበኩላቸው በፖሊ ደረጃ በአዲሱ ለተሻሸሉ ሥልጠና ዘርፎችና በአዲስ ለተከፈቱ ሙያዎች ግብዓት መሠረት ባደረገ መልኩ መሸንሸን እንዳለበት አሳስበዋል።

‎ሌሎች የማናጅንነቱ አካላት ባነሱት ሀሳብ በጀት ለታለመለት አላማ ካልዋለ በጀትን መምራት አስቸጋሪ መሆኑን በማንሳት የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ ስርአቱ ላይ ያሉ ችግሮችን ለይቶ በጥንቃቄ መምራት እንደሚገባ አንስተዋል።

‎በሌላ በኩል ወጪዎችን በአግባቡ እና በወቅቱ አይቤክስ ላይ መዝግቦ ካልተያዘ ሊረሳና እዳ ሊሆን ስለሚችል በዚህ ዙሪያም ልዩ ትኩረት እንደሚሻ አንስተዋል፡፡
‎ የሥልጠና ግብዓት በጀቶች ለታለመላቸው አላማ መዋል እንደሚገባቸው ያነሱት የማናጅመንቱ አካላት የኮሌጁን ተልዕኮ ለመፈፀም የውስጥ ገቢ አቅም በማሳደግ በጀት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ሥራ ቢሠራ የተሻለ እንደሆነም ጠቁመዋል።

‎የበጀት ድልድሉ ማናጅንነቱ በጋራ የተግባባቸውን ነጥቦች በማካተት ተግባራዊ እንዲሆን በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል።

ብቁ የሆኑ ሥራ ፈጣሪ ዜጋ እናፈራለን!!!!
ሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሚከተሉት መገናኛ አማራጮች መረጃ መስጠት የሚቻል መሆኑን በትህትና እንገልፃለን ።

Website: 🌐 https://stvet.edu.et/ https://www.facebook.com/profile.php?id=100075884746891
https://www.facebook.com/profile.php?id=61571119977837
Telegram: ?? https://t.me/+CJ8RAOOP6FEzNWU0
Email : 📱 [email protected]
WhatsApp: https://wa.me/+251901701626
የኮሌጁ ስልክ ቁጥር 0464590676/0464590685
Mob.+251916757601
+251926533334
+251916591139

ህዳር 17/03/2018ዓ.ም
ሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሠላምበር

ዓለምአቀፍ ኢንተርፕርነርሺፕ በዓል እየተከበረ ነው።ህዳር 13/2018 (ሠላምበር)፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ  ዞን ሠላምበር  ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ  ዓለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሺፕ "በጋራ...
24/11/2025

ዓለምአቀፍ ኢንተርፕርነርሺፕ በዓል እየተከበረ ነው።

ህዳር 13/2018 (ሠላምበር)፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ሠላምበር ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ዓለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሺፕ "በጋራ እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የፓናል ውይይት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እና በተለያዩ መርሐ-ግብሮች አከበረ።

#የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንቱ አላማ የኢንተርፕረነርሺፕ ፅንሰ-ሀሳብ በሁሉም በኮሌጁ ማህበረሰብ በሆኑት ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች በኩል እንዲሰርፅ ለማድረግ እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን በመፍጠር ችግር ፈቺ ተግባራትን ለማከናወንና በሰለጠኑበት የሙያ መስክ በመሰማራት የራሳቸውን ህይወት ከመለወጥ ባለፈ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሀገራችን እየተገነባ ላለው ኢንተርፕሪነራል ማህበረሰብ ምስረታ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ታሳቢ ያደረገ ነው።

በዚህ መሰረት የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሰልጣኞች ሸቀጣሸቀጦችን ለግቢው ማህበረሰብ እንዲሸጡ በማድረግ፣ ሞንታርቦ በመጠቀም ለግቢው ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ኢንተርፕሪነርሺፕ ላይ ግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነዶች ላይ ከኮሌጁ ማህበረሰብና ከባለድርሻ አካላት ጋርየፓናል ውይይት በማድረግ፣ በኮሌጁ እየሰሩ በትርፍ ጊዜያቸው ስራ በመፍጠር ለሌሎችም የስራ እድል የፈጠሩ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግ፣ እና በሌሎችም መሰል መርሐ-ግብሮች በድምቀት ተከብሯል።

Address

Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ሠላምበር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ:

Share