03/06/2026
የአከባቢያቸውን ሠላም እና ፀጥታ ለማስከበር ሲሰለጥኑ የነበሩ የሚሊሺያ አባላት ተመረቁ።
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ጋንታ አፈዜ ቀበሌ የአከባቢያቸውን ሠላም እና ፀጥታ ለማስከበር መሠረታዊ የውትድርና ጥበብ የተከታተሉ የሚሊሺያ አባላት ስልጠናቸውን አጠናቀው ከሰሞኑን ለምረቃ በቅተዋል።
በምረቃው ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት አቶ ሎቴ ሎንኬ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ውሃ ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ስንታየሁ ሰማዬ የወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ የአከባቢው ማህበረሰብ ታድመዋል።
ስልጠናውን ተከታትለው የተመረቁ የሚሊሻ አባለት የአከባቢውን ሠላም እና ፀጥታ በመጠበቅ ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንድወጡ እና ከመንግሥት ጎን በመሆንና የህዝብን ሠላም በንቃት በመከታተል መስራት እንደሚገባቸው ተገልጿል።