ጋጮ ባባ ወረዳ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት G/B/W Labor and Social Affairs Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • ጋጮ ባባ ወረዳ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት G/B/W Labor and Social Affairs Office

ጋጮ ባባ ወረዳ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት G/B/W Labor and Social Affairs  Office ይህ ትክክለኛ የጋጮ ባባ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ፌስቡክ ገጽ ነው።

06/10/2025
27/08/2025
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባካሄደው 4ኛው ሴክቶሪያል የጋራ ጉባኤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበጀት አመቱ በማህበራዊ ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች  ከፍተኛ ...
14/08/2025

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባካሄደው 4ኛው ሴክቶሪያል የጋራ ጉባኤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበጀት አመቱ በማህበራዊ ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ

ጂንካ :-ነሐሴ 7/2017)

ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮችን እንደ አፈፃፀማቸው በድጋፍ ክትትልና ሱፐርቪዥን ባደረገው ምልከታ መሠረት በጣም ከፍተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ ብሎ የፈረጀ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በማህበራዊ ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች ከፍተኛ በሚል መፈረጁ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ስቡስቤ ቡናቤ እንደገለፁት ቢሮው በበጀት አመቱ የአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁለንታዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተቀናጀ መልኩ በተሰራው ስራ የተመዘገበው ውጤት እጅግ አስደሳችና በቀጣዩ የ2018 በጀት አመት ይበልጥ ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

የቢሮ ኃላፊው አክለውም ቢሮው ላስመዘገበው የላቀ ውጤት
የክልሉ መንግስትና ፓርቲ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች፣ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦም በቢሮው ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመደገፍና ለመንከባከብ እንዲሁም በዘላቂነት ለማቋቋም የሚሰራው ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የተለመደውን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
South Ethiopia Region Labour & Social Affairs
ጋሞ ዞን ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ/Gamo zone Labour & Social Affairs Department

13/08/2025
13/08/2025
08/07/2025

!

ለመላው የጋጮ ባባ ወረዳ ግብር ከፋዮች በሙሉ እንኳን የ2017 ዓመታዊ የግብር መክፈያ ወቅት በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን።

በወረዳችን የ2017 ግብር ዘመን ዓመታዊ ግብር ሐምሌ 1/2017 ዓም በይፋ ይጀመራል።

ግብር የዜጎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለማሟላትና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያግዝ ቁልፍ መሳሪያ ነው።

ስለሆነም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ከሀምሌ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚጠበቅባችሁን ግብር በተገቢው በመክፈል የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ የጋጮ ባባ ወረዳ ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ብሩክ ቡፃ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

Mr. Biruk Butsa Gita

Address

Gacho Baba
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጋጮ ባባ ወረዳ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት G/B/W Labor and Social Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share