Gamo Zone Prosperity Party - የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ

Gamo Zone Prosperity Party - የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጤና ይስጥልን! ይህ የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው፡፡

በብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባየብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ጅ...
06/06/2026

በብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡



የጋሞ ዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በመንግስታዊ ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉአርባምንጭ፦ ግንቦት 29/2018 ዓ.ም ( የጋሞ ዞን ብልፅግና ...
06/06/2026

የጋሞ ዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በመንግስታዊ ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉ

አርባምንጭ፦ ግንቦት 29/2018 ዓ.ም ( የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ )

በጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የተመራ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ በሚገኘው ፀሐዬ ሎጅ በመንግስታዊ ስራዎች ሪፖርትና ቀጣይ ወራት አቅጣጫዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ፣ የመድረኩ ዓላማ በመንግስት የልማት ስራዎች የ100 ቀናት አፈፃፀምን መገምገም እና ለቀጣይ ወራት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና ኢኒሼቲቭ ስራዎች ዙሪያ ለመምከር መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የዞኑ አስተዳደር አማካሪ አቶ ተስፋፅዮን ዘነበ የ100 ቀናት የአፈፃፀም ሪፖርት እና ለቀጣይ ወራት የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራትና ኢኒሼቲቭ ስራዎች ዕቅድ እያቀረቡ ሲሆን፣ በቀጣይም በቀረቡት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በምክክር መድረኩ የጋሞ ዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው በተለያዩ የልማትና የአስተዳደር ጉዳዮች ላይ ሃሳብ እየተለዋወጡ ይገኛሉ።



"7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ህዝቡም በነፃነት የፈለገውን የመረጠበት ነው" የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትአርባምንጭ: ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ( የጋሞ ዞን ብልፅ...
04/06/2026

"7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ህዝቡም በነፃነት የፈለገውን የመረጠበት ነው" የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

አርባምንጭ: ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ( የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ )

የምርጫው ውጤትን ቦርዱ ይፋ እስኪያደርግ ድረስ ፓርቲዎችና ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጥሪ ቀርቧል።

የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በዞኑ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

በምክር ቤቱ መግለጫ ፣ ምርጫው ህዝቡ በነፃነት የተሳተፈበትና ዴሞክራሲያዊ መብቱን በአግባቡ የተጠቀመበት ሂደት እንደነበር ተመላክቷል።

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ መምህር ቴዎድሮስ ፋንታዬ በሰጡት መግለጫ፣ ምርጫው በጋሞ ዞን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

እንደ መምህር ቴዎድሮስ ገለጻ፣ ህዝቡ የሚደግፈውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም በነፃነት ድምፁን የሰጠ ሲሆን፣ ምርጫውም ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቋል።

በድህረ ምርጫ ሂደትም ሁሉም አካላት ሰላማዊ መንፈስን እንዲጠብቁ እና የምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውጤትን ይፋ እስኪያደርግ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ምርጫው ህዝቡ መብቱን በአግባቡ የተጠቀመበት ሰላማዊ ሂደት በመሆኑ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሆኑ ህዝቡ የምርጫውን ውጤት በፀጋ እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

ከምርጫው ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ በህግና በደንብ መሰረት በምርጫ ቦርድ እንዲታዩ እና የሚሰጠውን ውሳኔ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተመስገን እዩኤል በጋሞ ዞን 13 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት ምርጫ 725 የምርጫ ጣቢያዎች በቂ ዝግጅት አድርገው ወደ ምርጫው መግባታቸውን ገልጸዋል።

ህዝቡም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ጠቅሰው፣ ለሁሉም ተሳታፊ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ሀሳባቸውን የሰጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችም በበኩላቸው፣ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደነበር ጠቅሰው፣ የውጤት ማዳመር ሥራዎች ተጠናቀው በምርጫ ቦርድ ይፋ እስኪደረጉ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።

እንዲሁም ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በፀጋ መቀበል እንዳለበት አስገንዝበው፣ ለሀገራችንና ለዞናችን ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግና በጋራ መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫው ወቅት በቂ ታዛቢዎችን ለማሰማራት የፋይናንስ እጥረት እንደገጠማቸው የገለጹ ሲሆን፣ ምርጫውን ባያሸንፉም ለሀገሪቱ ሰላም፣ መረጋጋት፣ እድገትና ለተለያዩ የፖሊሲ አማራጮች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የዞኑ መንግስት፣ የፀጥታ ኃይሎች፣ የምርጫ አስፈፃሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህዝብ ምርጫው ሰላማዊና የተሳካ እንዲሆን ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።



የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ልዩ ድምቀቶች7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም የዜጎች የሀገር ፍቅር፣ ልዩ መስዋዕትነት እና አስገራ...
04/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ልዩ ድምቀቶች

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የፖለቲካ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም የዜጎች የሀገር ፍቅር፣ ልዩ መስዋዕትነት እና አስገራሚ የሕይወት አጋጣሚዎች በደመቀ ቀለም የተጻፉበት ታሪካዊ መድረክ እንጂ።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተስተዋሉ አንዳንድ ክስተቶች የምርጫውን ሂደት ከፖለቲካዊ ክንውንነት ባለፈ፣ የሰው ልጅን የፅናት ጥግ እና ለሀገር የመቆርጠጥን ሚስጥር ያሳዩ ነበሩ።

የምርጫ ጣቢያው ታዳሚዎችን ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገሪቱን ህዝብ ያስደመመው ክስተት የተመዘገበው በአካል ጉዳት ምክንያት ሁለት እጆቹን ያጣው ወገናችን ነው። እርሱ ግን እጆች ባይኖረኝም መምረጥ እችላለሁ በሚል መንፈስ፣ የምርጫ ወረቀቱን በአፉ በመያዝ ድምጹን በምስጢር ሳጥን ውስጥ ከቷል።

በሌላ በኩል እናትነትና ሀገራዊ ግዴታ ፊት ለፊት የተጋፈጡበት አስደናቂ ታሪክ ተመዝግቧል። አንዲት ጀግና እናት አዲስ ህጻን ልጅ ወደዚህች ምድር ባመጣች በሁለት ሰዓት ልዩነት ውስጥ፣ በምጥና በድካም ዝላ ሳለች ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፅ መስጠጥ ችላለች ።

ለብዙዎች የሰርግ ቀን ከጭፈራ፣ ከፎቶግራፍ ውጭ ሌላ ነገር አይታሰብበትም። ለነዚህ አዲስ ተጋቢዎች ግን የሰርጋቸው ምርጥ ማስታወሻ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ ነበር።
የትዳራቸውን መጀመሪያ በሀገር የወደፊት እጣ ፈንታ ውሳኔ የባረኩት እነዚህ ሙሽሮች፣ የዕለቱ ደማቅ ድምቀት ነበሩ።

በዱላ እየተደገፉ፣ በልጆቻቸውና በልጅ ልጆቻቸው እየተመሩ ወደ ምርጫ ጣቢያ የጎረፉት አባቶችና እናቶች ሌላው የምርጫው ውበት ነበሩ።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኮሮጆ ውስጥ የገቡ ድምፆች ብቻ ሳይሆኑ፣ የዜጎች ተስፋና ህያው ታሪኮች የተሰነዱበት ክስተት ሆኖ ያልፋል።



"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትግንቦት 27/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓር...
04/06/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው 7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከነበሩ የምርጫ ሂደቶች ሕብረተሰቡ በነፃነት ተሳትፎ ያደረገበት መሆኑን ገልጿል።

በክልሉ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 2 የግል ዕጩዎች ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ወደ ምርጫው መግባታቸውን አስታውቋል።

በቅድመ ምርጫው ሂደትም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገራዊና ክልላዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በምርጫ ቦርድ በተመደበላቸዉ ነፃ የአየር ሰዓት መሠረት ፕሮግራሞቻቸውን ማስተዋወቃቸዉን ጠቁሟል።

በምርጫዉ ዕለት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ 3 ሺህ 941 የምርጫ ጣቢያዎች ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ህብረተሰቡ ለመረጠው የፖለቲካ ፓርቲ በሠላም ድምፅ ሲሰጥ መዋሉ መረጋገጡን በመግለጫው ጠቅሰዋል።

ምክር ቤቱ በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የሚሰጠውን የመጨረሻ ዉጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ በምርጫዉ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ ለሚያገኘዉ ፓርቲ ከወዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ጎበዜ አበራ የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ዉጤታማና ተሞክሮ የተወሰደበት እንደሆነ ተናግረዋል።

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ሳጌ ሻምባ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ተቋም በመሆን ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ የነበሩ ሂደቶችን በስኬትና መምራቱን ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ የጀመራቸውን የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች በቀጣይም በተሻለ ተቋማዊ ጥንካሬ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

የክልሉ መንግስትን ጨምሮ አጠቃላይ የምርጫው ሂደት ሰላማዊና የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ አካላት የጋራ ምክር ቤቱ ምስጋና አቅርቧል።



ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል። ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ...
03/06/2026

ሕዝቡ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል!

ግንቦት 24/2018 ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል። ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ጉዞ ለማፅናትና ለማስቀጠል ያለውን ፅኑ ፍላጎት በግልፅ ያሳየበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ይመዘገባል። ሕዝቡ የምርጫ ካርዱን በጥንቃቄ አስቀምጦ በመያዝ በምርጫዉ እለት ድምፅ በመስጠት ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱን በተግባር አረጋግጧል።

የፖለቲካ ሥልጣን ምንጭ ሕዝብ ብቻ መሆኑንም ዳግም ለመላው ዓለም በማሳየት፣ ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ ተችሏል። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው አሸናፊ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው። መራጩ ሕዝብ ሳይሰለች ከነጋት 10:00 ሰአት ጀምሮ ረጅም ሰልፎችን በመያዝ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምፁን የሰጠው የፓርቲዎችን ድል ለመወሰን ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር ከፍ ለማድረግ ነው። እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ እድሜ ጠገብ አዛዉንቶች፣ ሙሽሮች ሳይቀሩ በነቂስ ወጥተው ዲሞክራሲን ለማፅናት ያሳዩት ትዕግስት የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነትና ጥንካሬ ለዓለም ያሳየ ታላቅ የድል ምዕራፍ ነው።

የዘንድሮው የምርጫ ሂደት ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ስልጡን እና ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ለሀገራችን ትልቅ የሞራል ድል ሲሆን ሕዝቡ ያሳየው የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል፣ መቻቻልና እርስ በርስ የመከባበር እሴት ኢትዮጵያን ሊከፋፍሉና ሊያዳክሙ ለሚፈልጉ ሀይሎች ሁሉ ግልጽ ምላሽ የሰጠ ታሪካዊ ድል ነው። ይህ ስልጡን የዲሞክራሲ ልምምድ አካሄድ ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የደረሰችበትን ጀረጃ በተግባር ያሳየና የሀገሪቱን ገጽታ በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ልዩ ክስተት ነው።

ይህ ምርጫ ለአዲሲቷና ለበለፀገችው ኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት በመጣል ለነገዋ የበለፀገችና የተረጋጋች ሀገር ጠንካራ መሰረት የጣለ ታላቅ የስኬት ምዕራፍ ነው። 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የልዩነት ሳይሆን የኅብረት፣ የብጥብጥ ሳይሆን የሰላም መገለጫ በመሆኑ የሀገሪቱን የነገ ተስፋ ብሩህ አድርጎታል።

በመጨረሻም በተለያዩ ጫናዎች እና ፈተናዎች ሳይበገሩ ድምፄ ዋጋ አለዉ በማለት በታላቅ ሀገራዊ ክብር ፀንተዉ በመቆም በትዕግስት እስከ ሌሊት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለሰጡ እና የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ታላቅነት በተግባር ላገዘፉ ዜጎች ሁሉ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል።

ኢትዮጵያ መርጣለች!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ታሸንፋለች!




የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁየአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡ምርጫውን አ...
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡



7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቅቋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድግንቦት 25፣ 2018 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቅቋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክ...
02/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቅቋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 25፣ 2018

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቅቋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ÷ በግንቦት 24 ቀን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ ሲሰጥ የዋለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቅቋል ብለዋል።

በድምጽ ምስጫ ሂደቱ በአዲስ አበባ ከተማ በጣም ረጃጅም ሰልፎች እንደነበሩ አንስተው÷ በሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ አማራ፣ ሶማሌ ክልሎች የድምጽ ቆጠራ አለመጠናቀቁን ገልጸዋል።

በዚህም የመራጮች ቁጥር እስካሁን ተጠቃleሎ አለመግባቱን ተናገረዋል።

ቦርዱ የተለያዩ ቅሬታዎች በተለያየ መንገድ ሲያስተናግድ መቆየቱን አንስተው÷ በሕግ ክፍል በኩል በቀጥታ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ የስራ ክፍል አማካይኝነት በቅድመ ማስጠንቀቂያ 6412 ስልክ ቁጥር የመጡ ጥቆማና ቅረታዎች እንደነበሩ አመልክተዋል።

በዚህም ጥቆማውን በመከተል ከስር ከስር አስፈላጊውን የእርምት ርምጃ ቦርዱ ሲሰጥ መቆየቱን እንዲሁም የማጣራት፣ የማረጋገጥና ማስረጃ ማጠናቀር በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።



7ኛው ሀገራዊ አጠቃላይ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ የተላለፈ የምስጋና መልዕክት!!ትላንት ​ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ "ኢትዮጵያ  ትመርጣለች" በሚል ...
02/06/2026

7ኛው ሀገራዊ አጠቃላይ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ የተላለፈ የምስጋና መልዕክት!!

ትላንት ​ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ "ኢትዮጵያ ትመርጣለች" በሚል መሪ ቃል፣ አርአያነት ባለው መልኩ በስኬት ተጠናቋል። ከዳር እስከ ዳር የተካሄደው ይህ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት፣ ከዴሞክራሲያዊ እሴቶች አንዱ የሆነውን መሪን በድምፅ የመምረጥ መብት በተግባር የታየበትና ሀገራችንን አሸናፊ ያደረገ ታሪካዊ ክስተት ነው።

​የተፎካካሪን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ህዝቡ የሰጠንን ትልቅ አደራ ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በላይ መስራትና መትጋት ይጠበቅብናል።የጋራ ራዕያችን የሆነው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዕውን እንዲሆን፣ በሂደቱ የየበኩላችሁን ሚና ለተወጣችሁ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡-

• ​ለመላው መራጭ ህዝብ፡ በምርጫው ቀን በነቂስ በመውጣትና ድምፃችሁን በመስጠት ላሳያችሁት የላቀ ሀገራዊ ተሳትፎ፤

• ​ለተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የምርጫው ሂደት ሰላማዊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላበረከታችሁት ገንቢ አስተዋፅዖ፤

• ​ለምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች የድምፅ አሰጣጡ ሂደት ፍትሃዊና ግልፅ እንዲሆን የቦርዱን የምርጫ ህግና ደንብ ተከትላችሁ ላደረጋችሁት ያላሰለሰ ጥረት፤

• ​ለሲቪክ ማህበራትና የሚዲያ ተቋማት ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃ በማድረስና ግንዛቤ በመፍጠር ለተጫወታችሁት የላቀ ሚና፤

• ​ለፀጥታና ደህንነት አካላት፡ ሂደቱ እጅግ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲከናወን በከፍተኛ የሙያ ስነ-ምግባር ኃላፊነታችሁን ስለተወጣችሁ።

​በመጨረሻም፤ በቅድመ-ምርጫና በምርጫው ሂደት የታየው ደማቅ ህዝባዊ አንድነት፣ በድህረ-ምርጫውም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ቀጣዩን ጊዜ በሰከነና ሰላማዊ መንገድ በመምራት፣ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ስኬት በጋራ እንረባረብ፤ የህዝባችንንም ተጠቃሚነት ዕውን ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

አቶ ገዛኸኝ ጋሞ
በብልፅግና ፓርቲ የጋሞ ዞን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ



በትናንትናው ዕለት በክልላችን የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ስኬታማ በሆነ መንገድ ተጠናቋል። ይህ ታላቅ አገራዊ ኩነት በድል እንዲሳካ የላቀ ድርሻ ላበረከቱ መላው አካላት የ...
02/06/2026

በትናንትናው ዕለት በክልላችን የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ስኬታማ በሆነ መንገድ ተጠናቋል። ይህ ታላቅ አገራዊ ኩነት በድል እንዲሳካ የላቀ ድርሻ ላበረከቱ መላው አካላት የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ይህ ታሪካዊ ኃላፊነት በውጤታማነት ይሳካ ዘንድ ግንባር ቀደም ሚና ለተጫወቱት የክልሉ አመራሮች፣ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ የጸጥታ አካላትና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ እንዲሁም በከፍተኛ ጨዋነትና በዳበረ የዲሞክራሲ ባህል ድምፃቸውን ለሰጡ መራጮች፣ ለምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎችና ታዛቢዎች በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስ።

በምርጫው ዕለት የታየው አኩሪ ትብብርና የስኬት ጉዞ በድህረ-ምርጫው ሂደትም ላይ እንዲደገም፤ መላው የህብረተሰቡ አካላት የተጣለባቸውን ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት በቁርጠኝነት እንዲወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።



Address

Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Prosperity Party - የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share