Gammo Zone Dita Woreda Government Communication Affairs Office

Gammo Zone Dita Woreda Government Communication  Affairs Office ዲታ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት/Dita Woreda Government Communication Service Office

ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ተምሳሌት ሀገር ሆነች፤ ዶ/ር አሸናፊ ኦይዳግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደዉ ታሪካዊው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክ...
02/06/2026

ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ተምሳሌት ሀገር ሆነች፤ ዶ/ር አሸናፊ ኦይዳ

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደዉ ታሪካዊው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ በስኬት በመጠናቀቁ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

መላው የወረዳችን ህዝቦች በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ቀን እና አሁን ደግሞ በድህረ ምርጫ ወቅት ለሀገራችን መፃይ ብሩህ ተስፋ ቀና በመሆን በሚታሳዩት ትጋት እና ፅናት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዟችንን በማፅናት ዳግም አሸናፊ እንድንሆን አስችሎናል።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና እጩዎች ህዝብ በነፃነት የሰጠውን ድምፅ እና የገለጸውን ፍላጎት ሁሉም በፀጋ እና በክብር በመቀበል በጋራ በመተባበር ሀገርን ለማሻገር ትልቅ አደራ ተቀብለናል።

የምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኛ በመሆን የህዝባችን ድምጽ ወደ ስርዓተ መንግስት ለመቀየር ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋና አለኝ።

ዶ/ር አሸናፊ ኦይዳ
የዲታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

ኢትዮጵያ በታሪክ ሰሪ ልጆቿ ዳግም አሸንፋለች!በትላንትናው ዕለት የተካሄደዉ ታሪካዊው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ በስኬ...
02/06/2026

ኢትዮጵያ በታሪክ ሰሪ ልጆቿ ዳግም አሸንፋለች!

በትላንትናው ዕለት የተካሄደዉ ታሪካዊው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ በስኬት በመጠናቀቁ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

መላው የክልላችን ህዝቦች በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ እና አሁን ደግሞ በድህረ ምርጫ ወቅት ለሀገራችን መፃይ ብሩህ ተስፋ ቀናኢ በመሆን በምታሳዩት ትጋት እና ፅናት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዟችንን በማፅናት ዳግም አሸናፊ እንድንሆን አስችሎናል።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና እጩዎች ህዝብ በነፃነት የሰጠውን ድምፅ እና የገለጸውን ፍላጎት ሁሉም በፀጋ እና በክብር በመቀበል በጋራ በመተባበር ሀገርን ለማሻገር ትልቅ አደራ ተቀብለናል።

በዚህ አጋጣሚ በክልላችን እንደ ሀገር ለምናልመው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዕውን መሆን በምርጫው በነቂስ በመሳተፍ ድምጻችሁን የሰጣችሁ ዜጎች እንዲሁም በምርጫው የተሳተፋችሁ የተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች የምርጫው ሂደት ሰላማዊ፤ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት ላበረከታችሁት ጉልህ አስትዋጽኦ በክልሉ ህዝብና መንግስት ስም ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

እንደዚሁም የምርጫ አስፈጻሚዎች፤ ታዛቢዎች፤ የሲቪክ ማህበራትና ሚዲያዎች እንዲሁም የፀጥታና ደህንነት አካላት የምርጫው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እጅግ ሰላማዊ፤ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከታችሁት የላቀ አስትዋጽኦ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

በመጨረሻም በቅድመ ምርጫና በምርጫው የታየዉ ህዝባዊ አንድነት የድህረ ምርጫው ሂደትም እጅግ በሰከነና በሰላማዊ በሆነ መንገድ በማስኬድ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ስኬት በጋራ በመረባረብ የህዝባችን ተጠቃሚነት እዉን ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ‎7ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በዞኑ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክተው የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ፦  ‎‎7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ  ዞ...
02/06/2026

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) ‎7ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በዞኑ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክተው የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ፦

‎7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ ዞን በሁሉም የምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ተጠናቋል።

‎ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የማይተካ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለመላው የዞናችን ሕዝቦች ላቅ ያለ ምስጋና በዞኑ አስተዳደር ስም አቀርባለሁ።

‎ገና ከመንጋቱ ቀደም ብላችሁ በየምርጫ ጣቢያው በመገኘት መብታችሁን እና ሀገራዊ ግዴታችሁን በሚገባ ተወጥታችኋል።

‎ዝናብና ፀሀይ ሳይበግራችሁ ኃላፊነታችሁን ለተወጣችሁ አባቶች፣ እናቶች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች በአጠቃላይ ለመላው የዞናችን ሕዝብ ያለኝን ልዩ ክብርና አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ።

‎እንዲሁም የፀጥታ አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት ተቋማትእና ሌሎችም ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ከልብ አመሰግናለሁ።

‎በቀጣይም ምርጫ ቦርድ ውጤት ሲገልጽ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ዞናችን የሚታወቅበትን ሠላምና መቻቻልን በማጽናት ለህዝባችን ጋራ ተጠቃሚነት በሚፈይድ መልኩ በአንድነት መንቀሳቀስ ይኖርብናል። አመሰግናለሁ!!

‎ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)
‎የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት*********************** ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
***********************

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት። ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች። ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል። ዛሬ የተደገመውም ይኸው ነው።

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች። ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር።

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል። እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው።

ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም። ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል። ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች።

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች።

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣ አዲስአበባ፣ ኢትዮጵያ

‎በዲታ ምርጫ ክልል የምርጫው ሂደት ፍትሃዊ ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች ገለፁ ‎‎ዛዳ ፡ ግንቦት 24፣2018 ዓ.ም(ዲታ ወረዳ መ/ኮሚዩኒኬሽን)‎‎አሸና...
01/06/2026

‎በዲታ ምርጫ ክልል የምርጫው ሂደት ፍትሃዊ ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች ገለፁ

‎ዛዳ ፡ ግንቦት 24፣2018 ዓ.ም(ዲታ ወረዳ መ/ኮሚዩኒኬሽን)

‎አሸናፊ ኦይዳ (ዶ/ር) ፤ በዲታ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ናቸው ።

‎የምርጫው ሂደት ሰላማዊ መሆኑን የጠቆሙት አሸናፊ ኦይዳ (ዶ/ር) ፤ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ይመራናል ብሎ ላሰበው የፖለቲካ ፓርቲ በነፃነት ድምፁን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል ።

‎ከማለዳው ጀምሮ የምርጫው ሂደት ፍትሃዊ ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል ።

‎መምህር ተገኝ ፋንጮ በዲታ ምርጫ ክልል የሰላም ኢትዮጵያ ጥምረት የክልል ምክር ቤት ዕጩ ናቸው ።

‎የዘንድሮ ምርጫ ከመቼውም ጊዜ በላይጰሰላማዊ ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ገልፀዋል ።

‎በጋሞ ዞን ዲታ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ድምጽ በመስጠት ያለው ህዝብ ሰልፍ አሁናዊ ሁኔታ፤‎‎ !‎ #ምርጫ2018‎‎‎
01/06/2026

‎በጋሞ ዞን ዲታ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ድምጽ በመስጠት ያለው ህዝብ ሰልፍ አሁናዊ ሁኔታ፤

‎ !
‎ #ምርጫ2018


42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ ሲባል… የዴሞክራሲ ዋነኛ መገለጫው በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሒደት መሳተፋቸው ነው። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ...
30/05/2026

42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ ሲባል…

የዴሞክራሲ ዋነኛ መገለጫው በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሒደት መሳተፋቸው ነው።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

እነዚህ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳቦቻቸውን ለሕዝብ በስፋት ያስተዋወቁ ሲሆን፤ መራጮች ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ በርካታ አማራጭ አግኝተዋል።

ዜጎች ለሀገር ዕድገት ይበጃል የሚሉትን በድምጻቸው ወደ ሥልጣን ለማምጣት ከተለያዩ ፓርቲዎች የሚመጡ ፖሊሲዎችንና እሳቤዎችን እንዲያወዳድሩ ያስችላቸዋል።

በመጪውን ሰኞ በሚካሄደው ምርጫ ፓርቲዎች ነፃ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተወዳድረው አሸናፊው ሕዝቡን ይወክላል።

የሃሳብ ነፃነት፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብቶች ሲከበሩ ብዝሃ ፓርቲ ስርዓት ስኬታማ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሒደት ይህንን እያስተናገደች ትገኛለች።

ጋሞ ዞን ዲታ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነውዛዳ፣ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (ዲታ ወረዳ መ/ኮ)፦ ጋሞ ዞን ዲታ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የም...
30/05/2026

ጋሞ ዞን ዲታ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

ዛዳ፣ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (ዲታ ወረዳ መ/ኮ)፦ ጋሞ ዞን ዲታ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሟላ ዝግጅት በማድረግ የምርጫ ሂደቱ እየተከናወነ ሲሆን ግንቦት 24 እለተ ሰኞ ከማለዳው ጀምሮ ድምፅ የሚሰጥ ይሆናል።

በዛሬው እለት ጋሞ ዞን ዲታ ምርጫ ክልል በሚገኙ 57 የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

የምርጫ የቁሳቁስ ስርጭቱ በምርጫ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የሚያገለግል ሲሆን የየምርጫ ጣቢያ ተወካዮችም የቀረቡላቸውን የምርጫ ቁሳቁሶች እየተረከቡ መሆኑ ታውቋል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ምርጫ ዕለቱ ፍፃሜ ድረስ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር በሁሉም ምርጫ መለያዎች የፀጥታ አካላት መመደባቸውን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር ጋፋሮ ቶማስ ገልፀዋል።

የቁሳቁስ ስርጭቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ሆኖ የምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው ዝግጁ እንደሚሆኑም አረጋግጠዋል።

ግንቦት 24ን በቀን መቁጠሪያዎ ላይ አስምረውበታል?7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።ሰኞ ግንቦት 24፤ አገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ድምፅ የምንሰጥበት ቀን ነው...
29/05/2026

ግንቦት 24ን በቀን መቁጠሪያዎ ላይ አስምረውበታል?

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

ሰኞ ግንቦት 24፤ አገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ድምፅ የምንሰጥበት ቀን ነው!

እርስዎስ የመራጭነት ካርድዎን አዘጋጅተው የድርሻዎን ለመወጣት ተሰናድተዋል?

ዛሬ መተግበር የጀመረው እና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የጥሞና ጊዜ መራጩ ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወስን ይረዳል።ኢትዮጵያ ትመርጣለች
28/05/2026

ዛሬ መተግበር የጀመረው እና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የጥሞና ጊዜ መራጩ ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወስን ይረዳል።

ኢትዮጵያ ትመርጣለች

Address

Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gammo Zone Dita Woreda Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gammo Zone Dita Woreda Government Communication Affairs Office:

Share