Zada Construction and Industrial College

Zada Construction and Industrial College Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zada Construction and Industrial College, Zada; Gamo, Arba Minch'.

07/09/2026
ሚዲያ ጥቆማ ዛሬ2/13/2018 ማታ 1:00 እና 3:00 የጋሞ ቴሌቭዥን ዜና ላይ የዛዳ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ምረቃ ስነ-ሥራዓት እንድከታተሉ እጦቅማለሁኝ።
07/09/2026

ሚዲያ ጥቆማ ዛሬ2/13/2018 ማታ 1:00 እና 3:00 የጋሞ ቴሌቭዥን ዜና ላይ የዛዳ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ምረቃ ስነ-ሥራዓት እንድከታተሉ እጦቅማለሁኝ።

የዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ የአካባቢውን ፀጋ ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ለለውጥ መትጋት እንደሚገባቸው ተገለፀ‎‎ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠ...
06/09/2026

የዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ የአካባቢውን ፀጋ ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ለለውጥ መትጋት እንደሚገባቸው ተገለፀ

‎ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ዛዳ፥ ነሐሴ 30/2018 ዓ/ም( ዛዳ ቴ/ሙ/ትም/ሥ፣/ኮሌጅ)

‎የዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን አስመርቋል።

‎በምረቃው ስነስርዓት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጋሞ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ተወካይና የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ደመላሽ ንጉሴ፤ ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ስራ በመፍጠር የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

‎ተመራቂዎች በንድፈ ሀሳብና በልምምድ የቀሰሙትን ዕውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ከትንሽ ተነስተው ለቴክኖሎጂ ሽግግር ደረጃ ለመድረስ መትጋት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

‎ኮሌጁን ከማስፋፋትና ለሰልጣኞች ለስራ ፈጠራ ምቹ ሁኔታን ከማመቻቸት ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑን አቶ ደመላሽ አስታውቀዋል።

‎ተመራቂዎቹ ጠንክረው ሰርተው ውጤታማ በመሆን ለሌሎች ወጣቶች የለውጥ አርአያ መሆን እንዳለባቸውም መክረዋል።

‎የዲታ ወረዳ አስተዳዳሪና የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ አሸናፊ ኦይዳ(ዶ/ር)፤ ኮሌጁ ብዙ ፈተናዎችን በመቋቋም ለመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞችን ማስመረቁ አዳዲስ ሰልጣኞችም ከቤተሰብ ሳይርቁ በአካባቢው ሰልጥነው ሙያዊ ዕውቀት መቅሰም እንዲችሉ መነሳሳት ይፈጥራል ብለዋል።

‎በኮሌጁ የሚሰጠው ስልጠና በአካባቢው ያለውን ፀጋ በማዳበር ወደ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መቀየር የሚያስችል መሆኑንንም አስገንዝበዋል።

‎ኮሎጁ በአካባቢው መከፈቱ ህብረተሰቡ ለወጪ ሳይጋለጥ ሙያዊ ዕውቀትን እንዲያጎለብት ዕድል የከፈተ መሆኑንንም አስረድተዋል።

‎ኮሌጁ በ2015 ዓ/ም በሦስት የሙያ ዘርፎች ስልጠና መጀመሩን ያስታወሱት የዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ዲን ተወካይ አቶ ትግራይ ዋሾ፤ በአጭር ጊዜ የስልጠና መስኮችን በማሳደግ በአሁን ጊዜ በ9 የሙያ ዘርፎች የማሰልጠን ፈቃድ አግኝቶ በ8 ሙያ ዘርፎች እያሰለጠነ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

‎ተመራቂዎቹ በሰለጠኑበት የሙያ መስኮች ወደ ስራ በመሰማራት ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ ለአካባቢው ለውጥ መትጋት ይገባቸዋል ብለዋል።

‎በአራት የሙያ መስኮች የሰለጠኑ 40 ሰልጣኞች ለምረቃ መብቃታቸውንም ተናግረዋል።

‎በ7ኛው የአገር አቀፍ ምርጫ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአካባቢው ተወካይ ሆነው የተመረጡት አቶ መስፍን ኢልታሞ፣ የጋሞ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና የኮሌጁ መስራች አቶ ግንሶ ግዛው፣ የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት ዲን አቶ በዛብህ ባርዛን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና የአገር ሽማግሌዎች በምረቃው ስነስርዓት ተግኝተዋል።

HASHSHU HASHSHU   #አስደሳች ዜና:- የምሪቃ_ጥሪ!!❤❤  የዛዳ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ከ2015 ጀምሮ ሲያስለጥናቸው የቆዩትን ተማሪዎቻቸውን/ሰልጣኞቻችን በነገው ዕለት ነሐሰ 30 /20...
04/09/2026

HASHSHU HASHSHU
#አስደሳች ዜና:- የምሪቃ_ጥሪ!!❤❤
የዛዳ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ከ2015 ጀምሮ ሲያስለጥናቸው የቆዩትን ተማሪዎቻቸውን/ሰልጣኞቻችን በነገው ዕለት ነሐሰ 30 /2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል ።
ዛዳ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በየደረጃቸው በተለያዩ 4 ዲፓርትመንቶች ሲያሰለጥናቸው ቆይቶ ሰልጣኞችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ለማስመርቅ
ቅድሜ ዝግጅቱን አጠናቆ እንግዶችን እየተጠባበቀ ይገኛል።
በነገው ዕለት ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም በሚከበረው የኮሌጁ የበኩር ልጆች ምርቃ ላይ የተማሪዎች ወላጆች፣አስመራቂዎች፣ጥሪ የተደገላችሁ እንግዶች ሁላችሁም ኮሌጁ ጋብዛችኋል።
🌹🌹🌹
እንኳን ደስ አላችሁ/ደስ አለን!!
Congragulations!!

BREAKING NEWSየ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና መረጃዎች!  #የማለፊያ ውጤት• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።• 565 ...
22/08/2026

BREAKING NEWS

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና መረጃዎች!

#የማለፊያ ውጤት

• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።

• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።

• 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

#100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች

• አምና — 62
• ዘንድሮ — 88

➡️ በዚህ ዓመት 26 ትምህርት ቤቶች ጨምረዋል።

💻 በፈተና አሰጣጥ ዘዴ

• በኦንላይን የተፈተኑ — 18.37% አልፈዋል።
• በወረቀት የተፈተኑ — 4.2% አልፈዋል።

🏆 የክልሎች የማለፊያ ምጣኔ

🥇 አዲስ አበባ — 32.4%
🥈 ሀረሪ — 22.76%
🥉 አማራ — 15%
• ድሬዳዋ — 11.92%
• ትግራይ — 11.2%
• ጉምዝ — 10.53%
• ደቡብ — 9.2% ኦሮሚያ -- 10.53
• ሶማሌ — 9%
• ሲዳማ — 6.95%
• ጉምዝ — 6.1%
• ደቡብ ኢትዮጵያ — 4.2%
• 3.74% — የክልሉ ስም አልተጠቀሰም።

🎯 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ

• 591/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ወንድ — ኦዳ ትምህርት ቤት

• 583/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ሴት — አገው ምድር ትምህርት ቤት

• 576.25/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ወንድ — ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት

• 569/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ሴት

#በአጠቃላይ

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ምጣኔ 12.8% ሲሆን፣ አዲስ አበባ 32.4% በማስመዝገብ ከፍተኛውን የክልል ደረጃ ይዟል።

በተጨማሪም 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ከ62 ወደ 88 ከፍ ብለዋል።

ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል ተብሏል፡፡

Additional Informationየ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና መረጃዎች!  #የማለፊያ ውጤት• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ...
22/08/2026

Additional Information

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና መረጃዎች!

#የማለፊያ ውጤት

• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።

• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።

• 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

#100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች

• አምና — 62
• ዘንድሮ — 88

➡️ በዚህ ዓመት 26 ትምህርት ቤቶች ጨምረዋል።

💻 በፈተና አሰጣጥ ዘዴ

• በኦንላይን የተፈተኑ — 18.37% አልፈዋል።
• በወረቀት የተፈተኑ — 4.2% አልፈዋል።

🏆 የክልሎች የማለፊያ ምጣኔ

🥇 አዲስ አበባ — 32.4%
🥈 ሀረሪ — 22.76%
🥉 አማራ — 15%
• ድሬዳዋ — 11.92%
• ትግራይ — 11.2%
• ጉምዝ — 10.53%
• ደቡብ — 9.2% ኦሮሚያ -- 10.53
• ሶማሌ — 9%
• ሲዳማ — 6.95%
• ጉምዝ — 6.1%
• ደቡብ ኢትዮጵያ — 4.2%
• 3.74% — የክልሉ ስም አልተጠቀሰም።

🎯 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ

• 591/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ወንድ — ኦዳ ትምህርት ቤት

• 583/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ሴት — አገው ምድር ትምህርት ቤት

• 576.25/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ወንድ — ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት

• 569/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ሴት

#በአጠቃላይ

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ምጣኔ 12.8% ሲሆን፣ አዲስ አበባ 32.4% በማስመዝገብ ከፍተኛውን የክልል ደረጃ ይዟል።

በተጨማሪም 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ከ62 ወደ 88 ከፍ ብለዋል።

ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል ተብሏል፡፡

ዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት  ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጀመረ፣ዛዳ፣ ነሐሴ  15/2018 ዓ.ም (ዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ )...
21/08/2026

ዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጀመረ፣

ዛዳ፣ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም (ዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ )

ዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019ዓ/ም መነሻ ዕቅድ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ለማስፋት፣ ተሞክሮዎችን ለመቀመር እንዲሁም የተስተዋሉ ድክመቶችን ለማረም ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በኮሌጁ በ2018 የበጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በመፈተሽ ለቀጣይ ተልዕኮ የማዘጋጀት ዓላማ እንዳለዉም ተጠቁሟል።

በመድረኩ ዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ዲን ተወካይ ኢ/ር ትግራይ ዋሾ ተገኝተው የበጀት ዓመቱ ስራዎች አፈፃፀም ጥሩ ዉጤት የተገኘበት ዓመት ነዉ ብለዋል።

ተቋሙ ሁለንተናዊ ለውጥ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን በስነ-ምግባር፣ በአመለካከትና በተግባር የላቀ አፈፃፀም ያላቸዉን ሠራተኛ ለመፍጠር እየሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የ2018 በጀት ዓመት ተቋማዊ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት የዛዳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ልማት ዕቅድ ባለሙያ በአቶ አለማየሁ ዋና በኩል ቀርቧል።

በመድረኩ የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አካላት እና አጠቃላይ የኮሌጁ ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛል።‎

በመጨረሻም የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ መድረኩ ተደምድሟል።

Address

Zada; Gamo
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zada Construction and Industrial College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share