ጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

ጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ Control thr market and increase the export items

ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚረዳ የ9 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ የምክክር መድረክ በዞን ማዕከል ተደረገ፡፡ንግድና ገበያ ልማት ተቋም የተጣለበትን የህዝብ አደራ በብቃት ለመወጣት በተቋም ደረጃ ...
01/04/2023

ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት የሚረዳ የ9 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ የምክክር መድረክ በዞን ማዕከል ተደረገ፡፡

ንግድና ገበያ ልማት ተቋም የተጣለበትን የህዝብ አደራ በብቃት ለመወጣት በተቋም ደረጃ የሚስተዋሉ ችግሮችን ተመካክሮ ለመፍታት ያለመና ጽ/ቤቶች ላይ አዳዲስ አመራሮች ተልዕኮ ተቀብሎ ከመሚጣታቸዉ ጋር ተያይዞ ወጥ የሆነ አቋም ለመያዝና በመዋቅሮች አለመቀናጀት ምክንያት የሚከሰት ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል ያለመ ምክክር ተደርጓል፡፡
በምክክር መድረኩ የዞኑ ማኔጅሜንት አካላት፣ የወረዳና ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የአ/ምንጭ ከተማ ቀበሌያት ን/ገ/ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ በንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር በአቶ ተስፋዬ ዩካ በኩል ሁሉንም መዋቅሮች የዳሰሰ የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም የቀረበ ሲሆን፡፡ በቀረበዉ ሪፖርት ላይ በጥልቀት ምክክር ተደርጎ የጋራ ማግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ምክክሩን የመሩት የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት መስከረም ዛፉ እንደገለፁት የኑሮ ዉድነቱን ለመቀነስ እንደ ተቋም ለብቻችን የምንወጣዉ ነገር ስላልሆነ ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ቅንጂታዊ ሥራዎችን መስራት ይጠበቃል፡፡ አምራች ግለሰቦችን/ማህበራትን እንዲሁም ጅምላ ነጋዴዎችን በቀጥታ ከሸማቹ ማህበራት ጋር ለማገናኘት መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ቅዳሜና እሁድ ገበያ ማመቻቸት ይጠበቃል ያሉት የመምሪያዉ ኃላፊ ለዚህም ስኬት ከመዋቅሩ ፊት አመራሮች ጋር መቀናጀት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ወቅቱ በዓላትን የምንቀበልበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የገበያ መረጃዎችን በአግባቡ በማሰባሰብና በመተንተን መዋቅር ከመዋቅር ጋር በመናበብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት እንዲደርስ የትስስር ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
እንደ ተቋም ህገ-ወጥነትን ለመከላከል በዉስጥም ሆነ በዉጪ ኢንስፔክሽን ሥራዎች መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ያለ ፈቃድ የሚሰሩትን፣ ባልጸና ፈቃድ የሚሰሩትን፣ ዋጋ ዝርዝር ያልለጠፉትን፣ ፈቃድ ያልለጠፉትን፣ ከተፈቀደላቸዉ ዉጪ የሚሰሩትን በአዋጁ መሰረት ወደ ህጋዊ መስመር ማስገባት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሪት መስከረም ዛፉ የሚዛን ምርመራ ሥራዎችን በመስራት ህብረተሰቡን ከመበዝበዝ መታደግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሸማች ክበባትን በየተቋማት ማደራጀት/ማጠናከር፣ ለገበያዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲዘጋጅ ማድረግና ገበያዉ እንድዘምን መስራት ያስፈልጋል ያሉት የመምሪያዉ ኃላፊ የንግድ ሥርዓቱ እንድዘምንና/E-trade/ ወደ ትግበራ የገቡ መዋቅሮች በምንም ዓይነት ሰበብ ሥራዉ እንዳይቀለበስ በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል፡፡
በሰብልም ሆነ በቁም እንስሳት ዘርፍ የድልልና ፈቃድ ያወጡ በተሻሻለዉ ፈቃድ መስጫ መደብ መሰረት ፈቃዱ ተመላሽ እንድደረግ ያሳሰቡት ኃላፊዋ ለቁም እንስሳት ነጋዴዎች የባጅ ሥርዓቱ ተጠናክሮ እንድቀጥል አሳስበዋል፡፡
ከቤቱ በተነሱ በተለያዩ ጉዳዮች ከሚመለከተዉ አካል ጋር ለመነጋገርና ችግሮቹን ለመፍታት ይሰራል ያሉት ኃላፊዋ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ሁሉም በቅንጂት ርብርብ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
መጋቢት 23/2015 አ/ምንጭ

በነዳጅ ማደያዎች አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ዉይይት ከማደያ ባለቤቶች ጋር ተደረገመንግስት በከፍተኛ ድጎማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርበዉ የነዳጅ ምርት ግብይት በተገቢ ሁኔታ ሊመራ...
01/04/2023

በነዳጅ ማደያዎች አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ዉይይት ከማደያ ባለቤቶች ጋር ተደረገ
መንግስት በከፍተኛ ድጎማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርበዉ የነዳጅ ምርት ግብይት በተገቢ ሁኔታ ሊመራ እንደሚገባ የመምሪያዉ ኃላፊ አሳሰቡ፡፡
በርካታ ችግሮች ከነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ተነስቶ ዉይይት የተደረገ ሲሆን በዞንና በታችኛዉ መዋቅር የሚፈቱ ችግሮችን ለመስራት መስራት እንደሚያስፈልግ የመምሪያዉ ኃላፊ መስከረም ዛፉ አሳሰቡ
ኮድ-4 ሞቴር የያዙ ግለሰቦች በተቀመጠዉ ፕሮግራም መሰረት ብቻ እንዲጠቀሙ ከፕሮግራም ዉጪ ከቀጅዎች ጋር አላስፈላጊ ግብግብ በመፍጠር የግብይት ሥርዓቱን ለማዛባት የሚሰሩት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል፡፡
መጋቢት/2015
አ/ምንጭ

በነዳጅ ምርቶች ዝዉዉር ስርጭት እና ግብይት ላይ የሰዓት ገደብ እንደተቀመጠ ተገለፀ;..........................................................የሀገራችንን ወ...
01/12/2020

በነዳጅ ምርቶች ዝዉዉር ስርጭት እና ግብይት ላይ የሰዓት ገደብ እንደተቀመጠ ተገለፀ;..........................................................
የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በምርቶች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ሰዉ ሰራሽ የሆኑና ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪ እና ያለአግባብ የምርት ክምችት በመፍጠር እጥረቶች እንዳይፈጠሩ ለመከላከል ከመቸዉም ጊዜ በላይ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን የጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ዩካ ገለፁ።

አቶ ተስፋዬ እንደገለፁት የነዳጅ ምርቶች ዝዉዉር ስርጭት እና ግብይትን በጥብቅ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር እንዲቻል በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማዴያዎች ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ እና ከምሳ በፊት በጊዜ የመዝጋት እና ከምሳ በኃላም ዘግይቶ የመክፈት እንዲሁም 12:00 ሰዓት ሳይሞላ የመዝጋቱ ሁኔታ በአንዳንድ ማደያዎች የሚታየዉ ክፍተት እንድስተካከል አሳስበዋል።

አስተባባሪዉ አክለዉም የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦትና ስርጭት በሚመለከት ከዚህ ቀደም ሲል በወንዶ ኩባንያ አማካኝነት የሚቀርበዉ ስኳር ኩባኒያዉ ከትስስር በመዉጣቱ ምክንያት ምርቱ በአርባምንጭ ሸማቾች ህብረት ስራ ዩኒየን እና በህዶታ ገበሬዎች ሰብል አምራቾች ግብይት ህብረት ስራ ዩኒየን አማካኝነት እንደምቀርብ አስረድተዋል።

የዘይት ስርጭት በሚመለከት የህዳር ወር 2013 ዓ.ም ኮታ 72% እንደተመደበ ገልፀዉ ሁሉም ወረዳና ከተማ መዋቅሮች በወቅቱ ኮታዉን እንዲያነሱ አሳስበዉ የስንዴ ዱቄት በተመለከተ ከሰኔ ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱ መቆሙን ጠቁመዉ በቀጣይ አቅርቦቱ በሚኖርበት ወቅት ለህዝቡ የሚናሳዉቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ህገ ወጥ ንግድን በጋራ እንከላከል!
የጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

ህዳር/21/2013 ዓ.ም
አርባምንጭ

12/2/2012መረጃ ለጥንቃቄደህንነታቸዉ ያልተረጋገጡ የተለያዩ ምርቶች።ህብረተሰቡ ባለመጠቀምና ሌላዉንም እንዲያስተምር እንጠይቃለን
22/10/2020

12/2/2012
መረጃ ለጥንቃቄ
ደህንነታቸዉ ያልተረጋገጡ የተለያዩ ምርቶች።
ህብረተሰቡ ባለመጠቀምና ሌላዉንም እንዲያስተምር እንጠይቃለን

13/10/2020
ቀን 3/2/2013 ዓ.ምየጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ "ከኮሮና ቫይረስ ራሳችንን እየተከላከልን ጤናማ የንግድና ግብይት ስርዓት እንድሰፍን እንረባረብ" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀዉ ዓመታ...
13/10/2020

ቀን 3/2/2013 ዓ.ም

የጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ "ከኮሮና ቫይረስ ራሳችንን እየተከላከልን ጤናማ የንግድና ግብይት ስርዓት እንድሰፍን እንረባረብ" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀዉ ዓመታዊ የሴክቶሪያል ጉባኤ በስኬት አጠናቀቀ። በጉባኤዉ የጋሞ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘዉዴን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ቀጣይ መሰራት ያለበትንም ነገሮች አስመረዋል። በዚህ ጉባኤ ከየመዋቅሩ ስምንት ግለሰቦችና የተቋሙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ የተሳተፉ ሲሆን በዚህ ጉባኤ የ2012 በጀት ዓመት አፈፃፀም በጥልቀት ተገምግሟል በ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በ2012 የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የእዉቅና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸዉም ሲሆን ባሳለፍነዉ በጀት ዓመት 1ኛ, ገረሰ ወረዳ 2ኛ, ም/ዓባያ ወረዳ 3ኛ, አርባምንጭ ከተማ ሲሆኑ ቦንኬ ወረዳ አዲስ የተፈጠረ መዋቅር ሆኖ አመርቂ ዉጤት በማስመዝገብ ልዩ የእዉቅና ሰርቴፍኬት ተሰጥቶታል። በጉባኤዉ መምሪያዉ ላስመዘገበዉ ዉጤት ጉልህ ሚና የተጫወተዉ የቀድሞ መምሪያ ሀላፊ ለአቶ ተስፋዬ ታሪኩ የእዉቅና ሰርቴፍከት የተበረከተለት ሲሆን የጉባኤዉ ተሳታፊ እዉቅና ሰጥቷል። ጉባኤዉን በአንደኛ ደረጃ ኦሞቲክ ጠቅላላ የንግድ ስራ ድርጅት በሁለተኛ ደረጃ አቶ አለማየሁ ጎንጮ አቶ ሽፈራዉ አሊ ባይራ ዱቄት ፋብሪካ/ኤብሶ/ እና አቶ አክሊሉ አድማሱ ስፎንሰር አድርገዋል። መድረኩ በክነ ጥበብ ቡድኖች ደምቆ የዋለ ሲሆን ሁሉም መዋቅሮች ዕቅድ በመፈራረም በመምሪያዉ ሀላፊ በአቶ አሸናፊ ናና የስራ ስምሪት ተሰጥቶ ጉባኤዉ ፍፃሜዉን አግኝቷል።
ህገ ወጥ ንግድን በጋራ እንከላከል!!
የጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ
ጥቅምት/3/2013
አርባምንጭ

13/10/2020

Address

Arba Minch'

Telephone

+251468814822

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጋሞ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share