Gofa Zone Oyda Woreda Water Irrigation and Mineral Development Office.

Gofa Zone Oyda Woreda Water Irrigation and Mineral Development Office. ውሃ ህይወት ነው!!!

29/03/2026
24/02/2026
26/11/2025
 😭😭😭😭😭የጽ/ቤታችን የአማራጭ ኢነርጅ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አነቦ ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል።ለቤተሰቦቻቸውንና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።
24/06/2025


😭😭😭😭😭

የጽ/ቤታችን የአማራጭ ኢነርጅ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አነቦ ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል።
ለቤተሰቦቻቸውንና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።

 #የሚኒስትሩ ምላሽ ለትራምፕ!  | የውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ ለፕሬዘዳንት ትራምፕ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ግድባችን በህዝባችን ገንዘብ እንጅ በውጭ ብድር አልተሰራም ብለዋል ዶክተር ኢንጅነር ሀብ...
22/06/2025

#የሚኒስትሩ ምላሽ ለትራምፕ!

| የውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ ለፕሬዘዳንት ትራምፕ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ግድባችን በህዝባችን ገንዘብ እንጅ በውጭ ብድር አልተሰራም ብለዋል ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ፡፡

አወዛጋቢው ፕሬዚዳንት በአሜሪካ በሞኝነት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ግዙፉ የኢትዮጵያ ግድብ፣ ወደ አባይ ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ በእጅጉ ይቀንሳል፣" ሲሉ በትሩዝ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት ፅሁፍ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው አሜሪካን በመሩበት የስልጣን ዘመን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ " ኢትዮጵያና ግብፅ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አድርጌ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች። ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት። በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም " ብለው ነበር።

ትራምፕ አክለውም " ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም ሲሉ መከላከላቸው ይታወሳል።

“ኢትዮጵያ ስምምቱን አፍርሳለች ግብጽ በዚህ ሁኔታ መኖር አትችልም ፤ ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች " የሚል ንግግርም ተናግረው ነበር።

የትላንቱ ግድቡ በአሜሪካ ልገሳ የተገነባ ነው ማለታቸው ግን ሀሰተኛ እና የሚያበሳጭ ስለመሆኑ እየተገለፀ ይገኛል፡፡

እስካሁን ከወደ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል ይፋዊ ምላሽ ባይሰጥም የውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ግዙፍ ግዳባችን ህዳሴ ሀገረ በቀል ፕሮጀክት ነው ያሉ ሲሆን በህዝባችን አንጡራ ሀብት ለህዝባችን ጥቅም የተገነባ እንጅ በውጭ እርዳታ የተሰራ አይደለም ሲሉም ነው ለአወዛጋቢው የትራም ገለፃ በX ገፃቸው ላይ ምላሽ የሰጡት።

06/04/2025
31/10/2024
  ⚠️ ⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️በቀጣዮቹ ቀናት ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የሚያስከትል ዝናብ ይኖራል - የኢትዮጵያ ሜቲዎሪዮሎጅ ኢንስቲትዩትበቀጣዮቹ 11 ቀናት የሚኖረው ተደጋጋሚነት ያለው ከባ...
21/08/2024


⚠️ ⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️

በቀጣዮቹ ቀናት ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የሚያስከትል ዝናብ ይኖራል - የኢትዮጵያ ሜቲዎሪዮሎጅ ኢንስቲትዩት

በቀጣዮቹ 11 ቀናት የሚኖረው ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት የማስከተል አቅም ስለሚኖረው የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ፡፡

በዚህም በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንካራ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በፀሐይ ኃይል ታግዞ ከሚፈጠረው ጠንካራ የደመና ክምችቶች ላይ በመነሳት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በመካከለኛው የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ በረዶና ነጎድጓድ የቀላቀለ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የሚኖረው ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የማስከተል አቅም ስለሚኖረው የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡

በአጠቃላይ በሚቀጥሉት 11 ቀናት ከትግራይ ክልል ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኽምራ፣ አዊ፣ ባህርዳር ዙሪያ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፤ ከአፋር ክልል ቅልበቲ፣ ፈንቲ፣ አውሲ፣ ማሂ፣ ሃሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ፣ ማኦ ኮሞ እና ካማሺ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ አኝዋክ፣ ማዣንግ እና የኢታንግ ልዩ ዞን ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉአባቦር፣ ጅማ፣ ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ)፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋና ሐረሪ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ሃዲያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ፣ ስልጤ፣ የየም ዞኖች፣ ጠምባሮ፣ ቀቤና እና ማረቆ ልዩ ወረዳ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ኮንታ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ጌዲኦ አማሮ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹት አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል መባሉን ኤፍ.ቢ.ሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኤረር፣ አካባቢዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

ከሰልን ሲጠቀሙ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎችአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለይም ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሲኖር ከሰልን በአማራጭ የኃይል ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ተግባር ነ...
10/07/2024

ከሰልን ሲጠቀሙ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለይም ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሲኖር ከሰልን በአማራጭ የኃይል ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም ከሰልን ሰዎች ለተለያየ አገልግሎት ሲጠቀሙ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ምክንያቱም አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ የከሰሉ ጭስ ሞትን ጨምሮ የዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአዕምሮ ጉዳትና የልብ በሽታ ስለሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመላክቱትም÷ የከሰል ጭስ በዓይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ አለው፡፡

ይህ ጋዝ የሚፈጠረውም ጋዝ፣ ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

የከሰል ጭስ ባለበት አካባቢ አየር ወደ ውስጥ በሚሳብበት ጊዜ÷ በደም ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ኅዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለተያዩ የሰውነት ክፍሎች ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ጉዳት ያስከትላል፡፡

ይህን ተከትሎም ደም ኦክስጅን መሸከሙን ያቆማል፤ በዚህ የተነሳ የኅዋሶቹ አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ ብሎም ይሞታሉ፡፡

• በከሰል ጭስ (በካርበን ሞኖክሳይድ) የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች

የራስ ምታት፣ ራስ ማዞርና መታመም፣ የድካም ስሜትና ግራ መጋባት፣ ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር፣ የዕይታና የትውስታ ማጣት፣ ራስን መሳት፣ በአንድ ነገር ላይ አትኩሮት ማጣት፣ የሆድ ህመም እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር ምልክቶች ሊታዩበት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
• የከሰል ጭስን እንዴት መከላከል ይቻላል?

በከሰል ምግብ ማብሰል ሲያስፈልግ በቂ አየር እንዲያገኝ ከተቻለ ከቤት ውጭ ማብሰል፤ ከቤት ውጭ ማብሰል ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በመሉ ከተቀጣጠለና ጭሱ መጥፋቱ ሲረጋገጥ ወደ ቤት ማስገባት ይመከራል፡፡

በተጨማሪም የከሰል ምድጃ እየተጠቀሙ በር እና መስኮት አለመዝጋት፣ በከሰል ምግብ አብስለው ሲጨርሱ በውኃ ማጥፋትና በርና መስኮት በመክፈት ቤቱን ማናፈስ እንዲሁም ከሰል ቤት ውስጥ አለማቀጣጠልን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም ከሰል ቤት ውስጥ አቀጣጥሎ ማሸለብ ወይም መተኛት አደጋው የከፋ በመሆኑ ከእነዚህ ድርጊቶች ይቆጠቡ።

አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ትስስር ኮንፍረንስ  እየተካሄደ ነውአዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ተኛው አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ...
15/06/2024

አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ትስስር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ተኛው አመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ቀጠናዊ ትስስር ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

ኮንፍረንሱ"የጋራ ሀብት ለጋራ መጻኢ ጊዜና ለጋራ ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲቲዩት፤በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋን ጨምሮ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ወሌ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ፣የናይል ተፋሰስ ሀገራት ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

መድረኩ በናይል ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስለሚኖር ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

Address

Oyda
Arba Minch'
P2030

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa Zone Oyda Woreda Water Irrigation and Mineral Development Office. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share