በጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • በጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት

በጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት, Government Organization, Secha, Arba Minch'.

ጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ ፍርድ ቤት የግብረስጋ ድፍረት በደል የፈጸመው ተከሳሽ  በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጥቷልተከሳሽ  አቶ  ቱካ ቱጋሞ ዕድሜ  45 ስሆን በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህ...
28/08/2024

ጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ ፍርድ ቤት የግብረስጋ ድፍረት በደል የፈጸመው ተከሳሽ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጥቷል
ተከሳሽ አቶ ቱካ ቱጋሞ ዕድሜ 45 ስሆን በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 627(5) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የዲታ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የግብረስጋ ግንኙነት በመፈጸሙ ነሀሴ 5/ 2016ዓ.ም ዕሁድ ከቀኑ 9:00 የሚሆንበት ጊዜ በዲታ ወረዳ ዛዳ ከተማ ቀበሌ የ3አመት ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ ዕድሜ ሦስት ዓመት የሆነችው ልጅ ከሌሎች ልጆች ጋር ከብቶችን በሚያግዱበት ቦታ ተከሳሽ አንቀላፍታለች በማለት አቅፎ ወደ ተበዳይ ወላጅ አባቷ ቤት ድረስ በማምጣት አስገድዶ በመድፈር የከባድ አካል እና ሥነ ልቦና ጉዳት ያደረሰባት በመሆኑ የፈፀመው በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ አቅርቧል።
ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያሰረዳ ሲሆን ተከሳሽም ወንጀሉን ስላለመፈጸሙ ማስረጃ አቅርቦ ያላሰተባበለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እዲቀጣ ተወስኖበታል ፡፡
በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላክል እና አጥፊዎችንም ለሕግ ለማቅረብ በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ሁሉም ዜጎች እና ተቋማት ከፍተህ ተቋማት ጋር ሊሰሩ ይገባል፡፡

09/08/2022

የተደጋገሙ የወንጀል ጥቆማዎችና አቤቱታዎች እየደረሡን በመሆኑ ከባንክ ነው በሚል የሚደርሦዎትን መልዕክት ከሚመለከተው ባንክ ሣያጣሩ እንዳይፈጽሙ!

03/06/2022
--------ከችሎት መልስ-------------------ወደ አ/ምንጭ ጫካ ምንጮችን ለማየት በሚል በሄዱ የሐገር ዉስጥ ጎብኝዎች ላይ የዉንብድና ተግባር የፈጸመ    ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ ...
13/04/2022

--------ከችሎት መልስ---------
----------ወደ አ/ምንጭ ጫካ ምንጮችን ለማየት በሚል በሄዱ የሐገር ዉስጥ ጎብኝዎች ላይ የዉንብድና ተግባር የፈጸመ ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ***-----
ተከሳሽ ማንያዘዋል አወቀ ለጊዜዉ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ፊታቸዉን ጭምብል በመሸፈን በእጃቸዉ ቆንጨራና ጩቤ በመያዝ በቀን 02/08/2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡30 በሚሆንበት ጊዜ፤አርባ ምንጮችን ጎብኝተዉ ሲመለሱ የነበሩ በቁጥር 05 ተበዳዮች/የሐገር ዉሰጥ ጎብኝዎችን/ በያዙት ቆንጨራና ጩቤ በማስፈራራት መሬት ላይ እንዲንበረከኩ ካደረጉ በኋላ በወቅቱ ጎብኚዎች የያዟቸዉን ስልኮችና ታብሌቶችን እንዲሰጧቸዉ ሲያስገድዱ፤ እማይሰጡ ከሆነ ግን በያዙት ስለት እንደሚገድሏቸዉ በመዛት ጎብኝዎቹ በወቅቱ የያዟቸዉን ስልኮችና ታብሌቶች በመቀበል ከአካባቢዉ ከሸሹ በኋላ፤ ተበዳዮች የወንጀሉን መፈጸምና አፈጻጸሙን ለአ/ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ሪፖርት በማድረጋቸዉ፤ የወንጀል ሪፖርት የደረሰዉ የአ/ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ከአ/ምንጭ ከተማ ፖሊስ ጋር ባደረገዉ ክትትል ተከሳሽ ማንያዘዋል አወቀን በዉንብድና ወንጀል ከወሰዷቸዉ ንብረቶች ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል የመርመራ መዝገብ ያደራጀ ሲሆን፣ የተደራጀዉንም ምርመራ መዝገብ የደረሰዉ ዐ/ህግ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም በቀረቡ ማስረጃዎች ግራ ቀኙን ሲያከራክር ከቆዬ በኋላ ተከሳሽ በዐ/ህግ በኩል የቀረበበትን ክስና ከክሱ ጋር የቀረበዉን የሰዉ፣ የሰነድና የኤግዚብት ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በሁሉም ክሶች ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት የ10 ዓመት ጽኑ አስራት ቅጣት እንዲቀጣ ሲል ዉስኗል፡፡
ህብረተሰቡ በዚህ ጉዳይ ተጠርጥረዉ ያልተያዙ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጠቁሞ በማስያዝ እንዲሁም በዞኑና በከተማዋ ያሉ ሰዉ ስራሽም ሆነ የተፈጥሮ መስህብ ቦታዎች ላይ እና እነኝህኑ ለመጎብኘት ሲሉ ከሐገር ዉስጥም ሆነ ከሐገር ዉጭ የሚመጡ ጎብኝዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከልም ሆነ ተፈጽመዉ ሲገኙ ፈጻሚዎችን ለህግ አካላት አሳልፎ በመስጠት የራሱን አሰተዋጽኦ እንዲያበረክት ማሳሰብ እንወዳለን፡፡

11/12/2021
* ምርጫ የአንዲት ሀገር ዜጎች ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ኩነት ነው፣   * ሥለሆነም ፍፁም ሠላማዊና የተረጋጋ  እንዲሆን ይጠበቃል፣    * እርሥዎም በመምረጥ ሥልጣ...
20/06/2021

* ምርጫ የአንዲት ሀገር ዜጎች ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ኩነት ነው፣
* ሥለሆነም ፍፁም ሠላማዊና የተረጋጋ እንዲሆን ይጠበቃል፣
* እርሥዎም በመምረጥ ሥልጣን ከዜጎች የሚመነጭ ዜጎችን ለማገልገል እሚውል መሆኑን ያረጋግጡ!
* ሠላም የሁሉ ነገር መሠረት ነውና የመምረጥ የመመረጥ ሂደቱ በሠላም ተጀምሮ በሠላም ይጠናቀቅ ዘንድ የራሥዎትን አሥተዋጽዎ ያበርክቱ!
* በአቅራቢያዎ ለሠላምዎ መድፍረሥ መንሤኤ ሊሆን ይችላል ብለው ያመኑት እንግዳ ነገር ሢያጋጥምዎ በፍጥነት በእቅራቢያዎ ላለ የጸጥታ አካል በማሣወቅ በምንም ሊለካ እማይችል ሠላምዎን ያሥጠብቁ!!!

15/05/2021

***ለዋጋ ማናርና ሸቀጦችን የመደበቅ ተግባር የሕግና የሞራል ተጠያቂነት***
----------//--------------------//----------------
ሠላም ሠላም ውድ የገጻችን ተከታታዮች ዛሬም አንድ የገጻችን ተከታይ የሆኑ ግለሠብ ተገቢ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪ እና ሥላለው የህግ ተጠያቅነት ማብራሪያ ብትጽፉልን በሚል በገጻችን መልዕክት ማቀመጫ ላይ ያኖሩልን በመሆኑና በኛም እምነት ሥለዚህ ጉዳይ መረጃ መሥጠቱ ተገቢ መሥሎ ሥለታየን ለዚህ ገጽ በማሥማማት ተከታዪን ጽሁፍ ማጋራት ወደድን//---------------------
-----------------------------------------
ተገቢ ያልሆነ ዋጋ መጨመር
-------------------------
በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት ከተከሰተ የቆየ
ቢሆንም የኮቪድ-19 ቫይረስ በዓለማችን ብሎም በሀገራችን ከገባ ጀምሮ
በተለየ መልኩ የሸቀጦች የዋጋ ንረት በተለይም የምግብ ነክና የንፅሕና
መጠበቅያ ቁሳቁስ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ በሕብረተሰቡ ዘንድ
ምሬትን ፈጥሮ ይገኛል፡፡
ለአንድ ሀገር የዋጋ ንረት መከሰት በዋነኝነት ሁለት ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ገፊ
ምክንያቶች ያሉ መሆናቸውን የስነ-ቁጠባ ባለሞያዎች ይገልፃሉ። እነዚህም
ከፍላጎት መጨመር የመነጨ የዋጋ ንረት(demand push inflation) እና
የማምረቻ ዋጋ መጨመር(cost push inflation) ናቸው። ከእነዚህ
ምክንያቶች አንፃር ሲመዘን በሀገራችን የተከሰተው የዋጋ ንረት እዚህ ደረጃ
ሊደርስ የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ አመክንዮ የለውም ወደሚለው ድምዳሜም
ይደርሳሉ ምሁራኑ።
ሀገራችን የምትከተለው የኢኮኖሚ ስርዓት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ስርዓት ቢሆንም
በየትኛውም ሀገር ቢሆን መንግስት ጣልቃ የማይገባበት የገበያ ኢኮኖሚ የለም።
መጠኑ ይለያይ እንጂ ነፃ የገበያ ኢኮኖሚ የሚከተሉ የበለጸጉትም ሆኑ ታዳጊ
ሀገራት የገበያ ጉድለት ሲያጋጥማቸው መንግስት ጣልቃ ገብቶ ጉድለቱን
የሚሞላበት አሰራር አለ። ኢትዮጵያም ከዚህ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ ልትሆን
አትችልም።
በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/06 በአንቀፅ 25 ሥር
“አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የንግና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግባቸው
የሚገቡ መሰረታዊ የንግድ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ጥናት አድርጎ
ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ በማስፈቀድ ዝርዝራቸውንና ዋጋቸውን በሕዝብ
ማስታወቅያ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡
” በማለት ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም የንግዱ ማሕበረሰብ ይህ አሰራር ያለ መሆኑን
ተገንዝቦ በተለይም በእንደዚህ ዓይነት አስቸጋሪ ወቅት ሊተገበር የሚችል
በመሆኑ ነቅቶ መከታተልና መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ የንግድ ሚኒሰቴርም
ለሸማቹ ሕብረተሰብ የራስ ምታት የሆኑትን ምርቶች የዋጋ ቁጥጥር
እንዲደረግባቸው እየለየ ሕጉ ባስቀመጠለት ሥልጣንና ኃላፊነት መሰረት
እንዲሰራበት ለመጠቆም እንወዳለን፡፡
በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች ካላቸው ጥቂት ነገር ለተቸገረው በማካፈል ለወገን
አለኝታነታቸውን በማስመስከር ላይ ይገኛሉ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ወረርሽኙን
እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር በእጃቸው ላይ ያለን የግድ ዕቃ በሕገ-ወጥ
መንገድ በመደበቅ ገበያው ላይ ሰው ሰራሽ ዕጥረት እንዲፈጠር በማድረግ
ሸማቹ እንዳይረጋጋና አማራጭ እንዲያጣ ካደረጉ በኋላ ባሻቸው ዋጋ የሚሸጡ፤
በወቅቱ ወደገበያ ያቀረቡትን ዕቃም ቢሆን ተመሳጥረው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ
ተመን በመተመን ተገቢ ያልሆነ ትርፍ የሚያጋብሱ ግልሰቦች አሉ፡፡
ነገር ግን ይህ በሀገር እና በወገን ላይ ከፍተኛ ጫና በሚያሳድር መልኩ
የሚደረግ የዋጋ ማናር ተግባር ከሐይማኖቶች አስተምህሮም ሆነ ከሞራል አንፃር
ብናየው በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለውና አስነዋሪ ድርጊት መሆኑ
እርግጥ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ክፉ ጊዜ ተባብረንና ተደጋግፈን ማለፍ የሚገባን
ሆኖ ሳለ በሀገርና በወገን ላይ ሌላ ተጨማሪ ችግር መፍጠር የአንድ መልካም
ዜጋ መገለጫ አይደለምና በጥብቅ ልናስብበት ይገባል፡፡
የንግድ ዕቃን ስለማከማቸት/መደበቅ
ዕቃን ማከማቸት እና መደበቅ ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር የገቢያ
አለመረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ከሚያስከትሉ ተግባራት መካከል የአንበሳውን
ድርሻ ይይዛል። በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የዕቃውን በገበያ ላይ
ያለውን ተፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአቅርቦት ችግር በሌለበት
ሁኔታ የአቅርቦት ችግር ያለ በማስመሰል በግለሰብ ወይም በቡድን ደረጃ
ሊያከማቹ እና ሰው ሰራሽ እጥረት ፈጥረው በከፍተኛ ዋጋ የመሸጥ ተግባር
ሲፈፅሙ ይስተዋላሉ። ይህ የንግዱ ማህበረሰብም ሆነ ሸማቹ ያለአግባብ
የንግድ ዕቃን የማከማቸት ተግባር በዜጎች ላይ ወይም እንደ አጠቃላይ በሀገር
ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ በጣም ከባድ ነው።
በበንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት
አንድ ነጋዴ ከመደበኛ የግብይት ስርዓት ውጭ ወይም ነጋዴ ያልሆነ ሰው ለግል
ወይም ለቤተሰብ ፍጆታ ከሚውል መጠን በላይ በንግድ እና ኢንዱስትሪ
ሚኒስቴር በገቢያ ላይ እጥረት ያለበት መሆኑ በወጣ የህዝብ ማስታወቂያ
የተገለፀ የንግድ ዕቃን ማከማቸት ወይም መደበቅ ክልክል መሆኑ ተደንግጓል።
ነገር ግን ከተገቢው የንግድ አሰራር ውጪ ማከማቸትም ሆነ መደበቅ
የማይቻለው በገበያ ላይ ዕጥረት ያለበትን የንግድ ዕቃ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም
የንግድ ዕቃ መሆኑን የአዋጁን አንቀፅ 23(3) እና 24ን በጣምራ በማንበብ
መገንዘብ ይቻላል፡፡
ይኼውም በአንቀፅ 23(3) ላይ “ሚኒስቴሩና ቢሮዎች በነጋዴዎች የሚፈፀም
የንግድ ዕቃዎች ክምችት ወይም የመደበቅ ተግባር ላይ ቁጥጥር ያደርጋሉ”
ተብሎ መደንገጉ ሲታይ የተጠቀሱት ተቋማት በሕገወጥ ነጋዴዎች የሚደረግን
የምርት ማከማቸትና መደበቅ እየተቆጣጠሩ የንግድ ሥርዓቱን ሚዛን
የማስጠበቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም የንግዱ
ማሕበረሰብ ማንኛውንም ዓይነት የንግድ ዕቃ መደበቅ ወይም ማከማቸት
ክልክል መሆኑን ተገንዝቦ እራሱን ከእንደዚህ ዓይነት ተግባር መቆጠብ
ይጠበቅበታል፡፡
የማከማቸት እንዲሁም የመደበቅ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን
በተመለከተ የአዋጁ አንቀፅ 43 ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ላይ የተቀመጡ
ድንጋጋጌዎች የተከማቸውን እቃ እንዲሁም ማጓጓዣውን መውረስን ጨምሮ
እስከ አምስት አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣቶችን
አስቀምጠዋል።
---------------//-----------------//-----------
በጋሞ ዞን ዐ/ሕግ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት//-----
----------------=-====--------
ምንጮች፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግና ኢትዮ ሕግ*****
------------------------------------------//----------

--------ከችሎት መልስ----------     ***ባለቤቱ ላይ የጊዲያ ሙከራ የፈጸመ ተከሳሽ በ20 ዓመት ጽኑ እሰራት ተቀጣ***-----ነገሩ የሆዉ እንዲህ ነዉ:- ተከሳሽ ተሰማ ዲታ የተ...
04/05/2021

--------ከችሎት መልስ----------
***ባለቤቱ ላይ የጊዲያ ሙከራ የፈጸመ ተከሳሽ በ20 ዓመት ጽኑ እሰራት ተቀጣ***-----

ነገሩ የሆዉ እንዲህ ነዉ:- ተከሳሽ ተሰማ ዲታ የተባለ ግለሰብ በአ/ምንጭ ከተማ ዉሃ ምንጭ ቀበሌ ከተበዳይ ባለቤቱ ጋር በኪራይ መልክ በያዙት መኖሪያ ቤት በትዳር ተጣምረዉ አብረዉ ይኖራሉ፣ በትዳራቸዉም አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል፤ ወጀሉ በተፈጸመበት እለትም በቀን 14/8/2012 ዓ.ም ምሽት ለ2 ሰዓት እየቆጠረ ሳለ ባል/ተከሳሽ/ተበዳይን ያለኔ ፍቃድ እናትሽን ለመጠየቅ በሚል ስለምን ወደ ወርዳ ሄድሽ በማለት ይጠይቃታል፣ ሚስትም በምትችለዉ ሁሉ እናቷ ስለመታመማቸዉ ገልጻ እርሷን ለመጠየቅ መሄዷን ታስረዳለች፣ ነገሩ ለባል አልተዋጠለትም ፣ በጉዳዩ ተጨቃጨቁ፤ ሚስትም የተረዳት ምስሏት ወደ መኝታዋ ትሄዳለች ባል ቁጭ ባለበት ስልኩን መጎርጎሩን ይቀጥላል ፣ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ባል/ተከሳሽ ቢላዋ ይዞ ሚስት ወደተኛችበት ክፍል ያመራል፣ ሚስት/ተበዳይ ሀገር አማን ብላ በታኛችበት አሁን ወደ እናትሽ ጋር አትሄጅም በማለት በያዘዉ ቢላዋ የተለያዬ የሰዉነት ክፍሏ ላይ መዉጋት ይጀምራል፤ በሁኔታዉ የተደናገጠችዉ ሚስት የይድረሱልኝ ጩሄት ታሰማለች፣ ነገሩ ያላማረዉ ባል/ተከሳሽ ሚስትን ከቤት ጎትቶ በማዉጣት ከቤታቸዉ ፊት ለፊት ባለ የቆሻሻ መጣያ ላይ ጥሏት ከአካባቢዉ ይሸሻል፤ ጩሄቱን የሰሙ የአካባቢዉ ሰዎችን ደርሰዉ ረሷን ስታ የወደቀችዉን ሚስትን ወደ ህክምና ተቋም አድርሰዉ ሕይወቷን ያተርፋሉ፤ ከሚስት ያገኙትንም መረጃ ለፖሊስ ያደርሳሉ ፖሊስም ተጠርጣሪዉን ፍለጋ ይቀጥላል፣ ከብዙ ጥረትም በኋላ ፖሊስ ተጠርጣሪዉን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራዉን በማስረጃዎች በማደራጅት መዝገቡን ለዐ/ህግ ያደርሳል፣ ዐ/ህግም በተጠርጣሪዉ ላይ በከባድ ነፍስ ግዲያ ሙከራ ክስ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀርባል፤ ፍ/ቤቱም በቀረበዉ ክስ ላይ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ከቆዬ በኋላ በቀን 19/7/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽን በተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ ጥፋተኛ በማለት በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
***የዉሳኔዉ ማስተማሪያ መልዕክት****
ወድ የገጻችን ቤቴሰቦች፤ ቤት ዉስጥ የሚፈጠሩ የእለት ግጭቶችንና አለመግባባቶችን በተቻለ መጠን በንግግርና በዉይይት መፍታት ቢቻል፤ ከዚያም ቢያልፍ እንኴ በቤተዘመድ እና በቅርብ ጎረቤት አደራዳሪነት መቅረፍ የከፋም አለመግባባት ሲኖር ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤቶቻችን ወሰዶ የመጨረሻ እልባት ማሰጠት ቢቻል እየተበራከተ የመጣዉን ቤቶሰብ መካከል የሚፈጸም ወንጀልን መቀነስ ይቻላል መልዕክታችን ነዉ፡፡
--------------------------------------------

Address

Secha
Arba Minch'

Telephone

+251468810405

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጋሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና ሥራ ሂደት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share