Gamo Zone Health Department ጋሞ ዞን ጤና መምሪያ

Gamo Zone Health Department ጋሞ ዞን ጤና መምሪያ Disease prevention and control
Maternal and child health
Nutrition
Health care financing

 #የፈተና ጊዜ ማስታወቅያ
18/09/2026

#የፈተና ጊዜ ማስታወቅያ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የወባን ወረርሽኝን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል የኮምፒተር መተግበሪያ ማዘጋጀቱ ተገለጸ ‎‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 8/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)‎‎አርባ...
18/09/2026

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የወባን ወረርሽኝን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል የኮምፒተር መተግበሪያ ማዘጋጀቱ ተገለጸ

‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 8/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)

‎አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የሚከሰት የወባን ወረርሽኝን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የኮምፒተር መተግበሪያ ማዘጋጀቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢንጂነር አብደላ ከማል አስታወቁ።

‎በጉዳዩ ላይ ለሁለት አመታት ሲካሄድ የቆየው ፕሮጀክት የማጠቃለያ ወርክሾፕ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።

‎የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በወርክሾፑ መክፈቻ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች ለህብረተሰቡ ችግሮች በምርምር የታገዘ መፍትሔ ማስቀመጥ አንዱ ኃላፊነታቸው ነው።

‎አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ያሉት ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቅበት ከውሃ ምህንድስና ባሻገር በጤና፣ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና እና በሌሎችም የተከናወኑ ውጤታማ የምርምር ስራዎች በአብነት ጠቅሰዋል።

‎ባለፉት ሁለት አመታት ሲካሄድ ቆይቶ የተጠናቀቀውን የአየር ንብረት ለውጥ ተከትሎ የሚከሰት የወባን ወረርሽኝን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችለው መተግበሪያም ዘላቂ የልማት ግቦች አፈጻጸም የሚደግፍ ነው ብለዋል።

‎በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተክሉ ወጋየሁ በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ተላላፊ በሽታዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ጠቅሰዋል።

‎የኮምፒዩተር ፕሮግራሙ ወባን ጨምሮ በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎ፕሮጀክቱ በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፎማ ለውጤት መብቃቱን ጠቅሰው ለስኬቱ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ ዶክተር ተክሉ አመስግነዋል።

‎የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር መሀመድ አበበ መተግበሪያው በተለይ ለጤና አስተዳደር፣ ለመረጃ ተንታችኞችና ለህብረተሰቡ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

‎በወርክሾፑ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዞን ጤና መምሪያዎች፣ የክልል ጤና ቢሮና የክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተወካዮች፣ ባለሙያዎችና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ተሳታፊ ናቸው።

‎ስኳር መጠቀም ብናቆም ወይም ብንቀንስ ምን ይፈጠራል?‎1. የስኳር ፍላጎትዎ ይጠፋል።‎ስኳር መቀነስ ሲጀምሩ የደም ውስጥ ስኳር መውጣትና  መውረድ ስለሚቆም፣ ፍላጎቱ ቀስ በቀስ ይጠፋል።‎2....
18/09/2026

‎ስኳር መጠቀም ብናቆም ወይም ብንቀንስ ምን ይፈጠራል?
‎1. የስኳር ፍላጎትዎ ይጠፋል።
‎ስኳር መቀነስ ሲጀምሩ የደም ውስጥ ስኳር መውጣትና መውረድ ስለሚቆም፣ ፍላጎቱ ቀስ በቀስ ይጠፋል።
‎2. ብዙ አይርብዎትም — ያለ ምግብ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት ይችላሉ። የረሃብ ሆርሞኖች ይረጋጋሉ።
‎3. ብዙ ጉልበት ይኖርዎታል፣ ምክንያቱም ሰውነትዎ ስብን በማቃጠል ጉልበት ያመነጫል።
‎አካልዎ ሲላመድ፣ ፈጣን ስኳር ከመጠቀም ይልቅ ስብን በማቃጠል የተረጋጋ ጉልበት ይሰጥዎታል።
‎4. ክብደት ይቀንሳል።
‎ስኳር ማስወገድ ባዶ ካሎሪዎችን ይቀንሳል፣ ኢንሱሊንንም ዝቅ ያደርጋል፤ ይህም ስብ እንዲቃጠል ያግዛል።
‎5. ስሜትዎ ይሻሻላል።
‎ተጨንቀው ከነበረ ደስተኛ ይሆናሉ። የተረጋጋ የደም ስኳር ማለት የተረጋጋ ስሜት መኖር ማለት ነው።
‎6. በተሻለ ማሰብ ይጀምራሉ ፦ ትኩረት፣ ትውስታ ይሻሻላል። አንጎልዎ በተረጋጋና በተሻለ ይሰራል።
‎7. ቆዳዎ በጣም ይሻሻላል ጤናማና ንጹህ ይሆናል።
‎ስኳር እብጠትና መጎዳት ያመጣል፤ ይህም ብጉር ያስከትላል። መተው ቆዳን ያጸዳል።
‎8. በሰውነትዎ ውስጥ እብጠትና glycation ህመም በጣም ይቀንሳል። መቀነሱ የመገጣጠሚያ ህመምና የጡንቻ ህመም ያቃልላል።
‎9. ተረጋጋ የደም ስኳር ጥሩ እንቅልፍ በፍጥነት እንዲተኙ ያግዛል።
‎10. ስኳር መቀነስ ጥርስ መበስበስንና የድድ በሽታን ይቀንሳል።
‎11. ጠንካራ የበሽታ መከላከያ፦ ብዙ ስኳር ነጭ የደም ሴሎችን ያዳክማል፤ መቀነሱ ኢንፌክሽንን ለመዋጋት ያግዛል።
‎12. ጤናማ ልብ። ስኳር መቀነስ የደም ግፊት፣ ትሪግሊሰራይድና የልብ በሽታ አደጋን ይቀንሳል።
‎13. የጉበት ስብ አደጋ ይቀንሳል። ቆሽትና ጉበትን በማሳረፍ ሜታቦሊክ በሽታን ይከላከላል።
‎14. ጤናማ የአንጀት ስርዓት። ስኳር ጎጂ ባክቴሪያና እርሾን ይመግባል፤ መቀነሱ ጥሩ ባክቴሪያ እንዲበለጽግ ያግዛል።
‎15. የእርጅና መጠን ይቀንሳል።

  17  (World Patient Safety Day) የታካሚውን የጤና ችግር የመለየት ሂደት ትክክለኛ የምርመራ ውጤት (Diagnosis) ይባላል። ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ላይ ለመድረስ ብዙው...
18/09/2026

17 (World Patient Safety Day)

የታካሚውን የጤና ችግር የመለየት ሂደት ትክክለኛ የምርመራ ውጤት (Diagnosis) ይባላል። ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ላይ ለመድረስ ብዙውን ጊዜ ታካሚዎች እና የጤና ባለሙያዎች አብረው ውስብስብ እና አንዳንዴም ረጅም ሂደቶችን ማለፍ ይጠይቃቸዋል።
‎​የምርመራ ውጤት ሲዘገይ፣ ሲሳሳት ወይም ሳይታወቅ ሲቀር ከባድ አደጋዎችን ሊያስከትል ይችላል፤ ይህም ለረጅም ጊዜ በሽታ፣ ለአካል ጉዳት ወይም ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
‎​በ የዓመቱ September 17 ዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀን (World Patient Safety Day) ታስቦ ይውላል፣
‎የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ለማግኘት የሚረዱ ተግባራዊ ምክሮችን አቅርቧል፦
‎​✅ የሕክምና ታሪክዎን ያጋሩ
‎✅ ጥያቄዎችን ይጠይቁ
‎✅ የላቦራቶሪ እና የምርመራ ውጤቶችን ይከታተሉ
‎✅ የቀጠሮዎችን እና የሕክምና ሂደቶችን መረጃ ይያዙ ይከታተሉ
‎✅ አስፈላጊ ሲሆን የሌላ ሕክምና ባለሙያ አማራጭ አስተያየት (Second opinion) ይጠይቁ

በባስኬቶ ዞን ላስካ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሶስት ህጻናትን በሰላም ተገላገለች።‎‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ) ‎‎ወ/ሮ ካሰች እውነቱ ...
17/09/2026

በባስኬቶ ዞን ላስካ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሶስት ህጻናትን በሰላም ተገላገለች።

‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)

‎ወ/ሮ ካሰች እውነቱ የተባለች እናት በሆስፒታሉ በተደረገላት አገልግሎት ሶስት ወንድ ልጆቿን በሰላም መገላገሏን በባስኬቶ ዞን የላስካ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ታሪኩ ገልጸዋል።

‎በሆስፒታሉ ሶስት ህጻናትን በአንድ ጊዜ ሲወለዱ የመጀመሪያ
‎እንደሆነና በተጨማሪ ከወሊድ በኋላም በቂ አገልግሎት እየተሰጣት እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

‎በፅንስ ጊዜ እናቲቱ በቂ የህክምና ክትትል በማድረግ ሦስት መንትያ ልጆቿን አምጣ በሠላም መውለዷን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ገልጸዋል።

‎ህጻናቱ በጨቅላ ህጻናት ክፍል ጤና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አክለዋል።

የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከመላዉ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገለፀ‎‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ...
17/09/2026

የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከመላዉ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገለፀ

‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)

‎በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና በ2019 ዓ.ም ዕቅድ ፈፃሚ ማዘጋጃ ሲካሄድ የነበረዉ የምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡

‎የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ባንጌ ባንጃ የኤች አይቪ/ኤዲስ እና ቫይራል ሄፓታይትስ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከአጋር ድርጅቶችና ከመላዉ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

‎በልማት ኮሪደሮች አከባቢ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለበሽታዉ ተጋላጭነታቸዉ ከፍ ያለ በመሆኑ ስርጭቱን ለመከላከል በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበትም ወ/ሮ ባንጌ አሳስበዋል፡፡

‎የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ መምሪያው ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ስላዘጋጀዉ የምክክር መድረክ በማመስገን መድረኩ አቅማቸዉን የፈተሹበትና ብዙ ልምድ የቀሰሙበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‎በሌላ በኩል የመድረኩ ተሳታፊዎች በዘርፊ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከርና ክፍተቶችን በመሙላት የተሻለ አፈጻፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

‎በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎቸና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የዘርፈ ብዙ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የጉበት በሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፤‎‎አርባ ምንጭ፡-...
17/09/2026

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የዘርፈ ብዙ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የጉበት በሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፤

‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 7/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)

‎የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ በበጀት ዓመቱ በዘርፈ ብዙ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የጉበት በሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡

‎የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ባንጌ ባንጃ ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው በጤናው ዘርፍ የተነደፉትን የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሣካት በዞኑ ጤና መምሪያ በኩል ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ሲከናውኑ መቆየታቸውን አውስተው በበጅት ዓመቱ በርካታ ሃገራዊ እና ክልላዊ የዘመቻ ስራዎች ላይ እንዲሁም በዞኑ የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት አደጋና የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር በስፋት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

‎ወ/ሮ ባንጌ በንግግራቸው አክለው በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች የሚላኩ የኮማንድ ፖስት ሪፖርቶች በአበዛኛው ወቅታዊነት እና ጥራት የትጓደለባቸው ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ ተግዳሮት እየሆኑ የመጡ መሆኑን ጠቁመው በየደረጃው የሚላኩ ሪፖርቶችን ገምግሞ መላክ ላይ ትኩረት መሰጠት ይገባል ብለዋል።

‎ይህ በእንዲህ እንዳለ የዳይሬክቶሬቱ ሪፖርት በዳይሬክቶሬቱ ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት በአቶ እሸቱ ሙአ በኩል የቀረበ ሲሆን በዚህም በበጀት ዓመቱ 65 ሽህ 432 ሰዎች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክርና ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ምርመራ ካደረጉ መካካል 183 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏ፡፡ በሌላ በኩል በበሽታው ከተያዙ ግለሠቦች መካከል 164 ሰዎች የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እንዲጀምሩ ማድረግ ተችሏል፡፡

‎በአጠቃላይ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት እየተከታተሉ ከሚገኙ ወገኖች መካከል ለ3 ሺህ 199 ሰዎች የቫይራል ሎድ ምርመራ የተካሄደላቸው ሲሆን በዚህም 3 ሺህ 050 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ከ 50 ኮፒ በታች እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል ይህም ሶስተኛው 95 አፈጻጸም 95 በመቶ ያህል መድረሱን ያሣያል፡፡

‎ከኤ.ች.አይ.ቪ/ኤድስ የመከላከል ተግባር ጋር በተያያዘ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ለሚገኝ ወገኖች እና ወላጃቸውን ላጡ ህጻናት በአጠቃላይ ለ 4 ሺህ 364 ወገኖች ቢያንስ አንድ አይነት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድሩግ ተችሏል፡፡ በበጀት ዓመቱ 250 ሺህ 811 ኮንዶም ማሰራጨት ተችሏል፡፡

‎በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት ላይ እና በኮማንድ ፖስት ሪፖርት አደራረግ ላይ ከተሣታፊዎች ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት እንደሚካሄድ የሚጠበቅ ሲሆን በሌላ በኩል የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ተግባቦት ይፈጸማል ተብሎ ይገመታል፡፡

በሣምንቱ 3ኛ ቀን የድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር እና የመሠረታዊ ጤና ተግባራት በበይኔ መረብ ተገመገመ፡፡‎‎በሣምንቱ የተከናወኑ መሠረታዊ ጤና፣ ወባ እና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት በሽታን ጨምሮ...
16/09/2026

በሣምንቱ 3ኛ ቀን የድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር እና የመሠረታዊ ጤና ተግባራት በበይኔ መረብ ተገመገመ፡፡

‎በሣምንቱ የተከናወኑ መሠረታዊ ጤና፣ ወባ እና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት በሽታን ጨምሮ ድንገተኛ አደጋዎችና ምላሽ ሥራ እና የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ክንውን ሪፖርት ተደምጧል፡፡

‎አርባ ምንጭ፡-መስከረም 6/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)

‎በክልሉ የዞን እና የሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች የጤና መዋቅር አመራር አካላት በበየኔ መረቡ በመሳተፍ ለውይይት በቀረቡ ሪፖርቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

‎ወቅታዊ የአየር ፀባይ በአንፃራዊነት እርጥበታማ እየሆነ ስለሚመጣ የአካባቢ ጽዳትና ውሃ የሚተኛባቸው አካባቢዎችን ወባ በሽታን ለመከላከል ማፋሰስና ማዳፈን ይጠበቃል ሲሉም ጤና አመራሩ አሳስበዋል፡፡

‎በሽታ መከላከል ሥራዎች፣ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና አጠባበቅ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስ ልየታና ህክምና እንዲሁም ሌሎች ጤና ተግባራት ዙሪያ መክረዋል፡፡

‎የእናቶች፣ ህፃናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ እና ክትባት አገልግሎት በአንዳንድ የወረዳ መዋቅሮች ትኩረት የሚፈልግ ሲሆን፤ የተመዘገቡ መሻሻሎችን ለማስቀጠል ሁሉም የጤና አመራርና ባለሙያ መጠናከር እንዳለባቸው አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

‎በጤና ክረምት በጎ ተግባራት በህክምናና ልዩ ልዩ ድጋፍ ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገ ሲሆን፤ በጎነትና ሰው ተኮር ተግባራትን ማስቀጠል እንደሚገባም በበይኔ መረቡ ተመክሯል፡፡

‎የህፃናት ሥርዓት ምግብ አለመመጣጠን በሽታን ለመከላከል በሁሉም አከባቢዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የልየታ ሥራው ከIMS ወረዳዎች በተጨማሪ ማጠናከር እንደሚገባ አመራሩ በአስተያየት አዳብሯል፡፡

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ ወቅታዊ የአየር ፀባይን መነሻ በማድረግ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን በመከታተል ከወዲሁ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

‎ከጤናና ጤና ነክ አገልግሎት አንፃር ጤና ተቋማትን ኦዲት በማድረግና ክትትልን በማጠናከር ህገወጥ የመዲሃኒት ዝውውርን መከላከል እንደሚገባም አቶ አጉኔ አስታውቀዋል፡፡

‎በክረምት በጎ ተግባራት የተሻሉ አፈፃፀሞች የተከናወኑ ሲሆን በቀጣይ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እሳቤን ተግባራዊ በማድረግ በጤና ተቋማት አከባቢ ለእርሻ ሥራ ምቹ ቦታ በመምረጥ ማልማት እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አጉኔ አሾሌ አስታውቀዋል፡፡

‎በበይኔ መረብ ውይይቱ ጤና ቢሮ አመራሮች፣ የጤና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የዞንና ሪጂዮ ፖሊስ ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

‎ከመጠን በላይ ስኳር፣ ጨው እና ስብ የያዙ ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በቂ ውሃ በየቀኑ በመውሰድ ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ!‎‎...
16/09/2026

‎ከመጠን በላይ ስኳር፣ ጨው እና ስብ የያዙ ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በቂ ውሃ በየቀኑ በመውሰድ ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ!


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ሕክምና ቡድን (EMT) ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና አገኘ__________የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና ስጋት ሲከሰት ዜጎቻችንን ቀድሞ ለመጠበቅና ...
16/09/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ሕክምና ቡድን (EMT) ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና አገኘ
__________

የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና ስጋት ሲከሰት ዜጎቻችንን ቀድሞ ለመጠበቅና ሲከሰትም በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መምጣቱን እና ውጤታማ መሆኑን የሚያረጋግጥ እውቅና ነው፤ ለኢትዮዽያ የህክምና ዘርፍ ልዩ የኩራትና የደስታ ቀንም መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።

የተገኘው ስኬት በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና በባለድርሻና አጋር አካላት የጋራ ቅንጅትና ትብብር አማካኝነት ለዓመታት በተከናወነ አመራርነት፣ ኢንቨስትመንት፣ ሥልጠናና እና ድጋፍ የተገኘ በመሆኑ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሁሉንም አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሯ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይም የተገኘውን ውጤት በማላቅ እና ትጋታችንን በመጨመር ለሌሎች የጤና ግቦች መሳካት ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

እውቅናው በጥብቅና ገለልተኛ በሆነ አካል ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ ሂደቶችን በበርካታ መመዘኛዎች ተፈትሾ መረጋገጡን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ናቸው። የኢትዮጵያ ቡድንም በበሽታ ወረርሽኞች፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና በሰብዓዊ ቀውሶች ወቅት በጥራት፣ በዝግጁነት፣ በፈጣን የማሰማራት አቅምና በድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ምላሽ በመመዘን የተገኘ ውጤት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የWHO ተወካይ ዶ/ር ፍራንሲስ ቺሳካ ካሶሎ በበኩላቸው ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ማህበረሰቦቿን ከድንገተኛ የጤና ስጋት በተጠናከረ ዝግጁነትና ፈጣን ምላሽ አቅም ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያ መንግስትንና ጤና ሚኒስቴርን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኅዳር 3–5 ቀን 2019 ዓ.ም. (3–5 November 2026) በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 7ኛውን ዓለም አቀፍ የEmergency Medical Teams Meeting ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች። በWHO የአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ የመጀመሪያው ጊዜ ይሆናል።

Address

Shecha Sub City, Beside Zone Administration
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Health Department ጋሞ ዞን ጤና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share