04/01/2025
ከአንድ ታካሚ ሆድ በቀዶ ሕክምና 57 ብረታ ብረቶች ወጡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀ ቀዶ ሕክምና ከአንድ ታካሚ ሆድ 57 ብረታ ብረቶች ወጡ።
በቀዶ ሕክምናው 28 ሚስማር፣ 8 ብሎን እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች መውጣታቸው ነው የተገለጸው፡፡
የቀዶ ሕክምናው በስኬት መጠናቀቁን የሆስፒታሉ አጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ሐኪም ዶክተር ጌታነህ በላይ ገልጸዋል።
የአንጀት ቀዶ ሕክምናው ከ2 ሰዓት በላይ የፈጀ እንደነበርም የሆስፒታሉ መረጃ ያመላክታል።