23/04/2026
የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) online Course's ስልጠና በሁሉም ዘርፊ ባለመዘናጋት ሊወሰድ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡
ኤዞ፦15/082018 ዓ.ም (ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ
የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኅላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል አበበ የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) online Course's ስልጠና በሁሉም ዘርፊ ባለመዘናጋት ሊወሰድ እንደሚገባ ያሳሰቡ ሲሆን ጠቀሜታው ዘረፈ ብዙ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ተነሳሽነት በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳደግና ለዜጎች የቴክኖሎጂ ክህሎትን ለማጋራት የታለመ ታላቅ ብሔራዊ ፕሮጀክት ሲሆን ይህ ስልጠና በዋናነት በኢፌዴሪ መንግሥት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት በጋራ ትብብር የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የሥልጠናው ዓላማ 5 ሚሊዮን ኮደሮችን 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በኮዲንግ (Coding) እና በዲጂታል ክህሎቶች ማሰልጠን እና በዘርፉ ወጣቶች በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና በራሳቸው የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን እንዲፈጥሩ ማስቻል ይገኙበታል።
የሚሰጡ ስልጠናው አይነቶች በዋናነት በነዚህ አራት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሆኖ :-የሞባይል መተግበሪያዎችን (Apps) ለመስራት፣ : መረጃዎችን በመተንተን ውሳኔ ሰጪነትን ማሳደግ፣ : የኮምፒውተር ፕሮግራም መሰረታዊ ዕውቀት እና ወይም AI ፡-ኮምፒውተሮች ወይም ማሽኖች እንደ ሰው የማሰብ፣ የመማር፣ ችግሮችን የመፍታት እና ውሳኔ የመስጠት ችሎታ እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሰሩበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ በማወቅ እውቀትን እንድንቀስም እናንዲሁም አለማችን በቴክኖሎጂው ያለችበትን ደረጃ ተረድተን አብረን እንድንጓዝ የሚረዳን ስለሆነ በየዘርፉ ስልጠናዎች ባለመዘናጋት ሊወሰዱ ይገባል ብለዋል፡፡
👍ለመመዝገብ፦ የድረ-ገጹን ሊንክ Ethiocoders.et ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።