የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council

የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council የቻግኒ ከተማ ምክር ቤትንና ከተማዊ
አጠቃላይ እንቅስቃሴ እናደርሳለን፡፡
ለእውነተኛና ፈጣን መረጃዎች ይወዳጁን፤ ይከታተሉን!

01/06/2026
‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ  የቀበሌ ምክር  ቤቶች የ2018  በጀት አመት የግንቦት  ወር  ጉባኤ በቀረበዉ አጀንዳ ላይ  በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል///////////////...
29/05/2026

‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ የቀበሌ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት አመት የግንቦት ወር ጉባኤ በቀረበዉ አጀንዳ ላይ በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል/////////////////////
‎ግንቦት 21/2018 ዓ ም (ቻግኒ ከተማ ምክርቤት)
‎የጉባኤ አጃንዳ፡-
‎አጀንዳ1:- ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝእና የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች በተመለከተ
‎ በአጠቃላይ የቀበሌ ምክርቤቶች በወቅታዊ የወባ ወረርሽኝና የአካባቢ የቁጥጥር ስራዎች አስመልክቶ ውይይት አደርገው እና በቀጣይ በየአካባቢዉ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ የጋራ አቅጣጫ በመያዝ እንዲሁም ከቀበሌ ም/ቤት አባላት በሚጠበቁ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ዉይይት በማድረግ በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት የቀረበዉን አጀንዳ በማፅደቅ ጉባኤውን በስኬት አጠናቀዋል።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን መልዕክት አስተላለፉ!‎‎ግንቦት 19/09/2...
27/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን መልዕክት አስተላለፉ!

‎ግንቦት 19/09/2018 ዓ.ም ቻግኒ ከተማ ምክር ቤት

‎አቶ ተዋበ ምህረት በመልዕክታቸው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 447ኛዉ ዒድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

‎በዓሉን ስናከብር ቅንነትን፣ መልካምነትን፣ መታዘዝን፣ በጎ አድራጊነትንና ትኅትናን በሕይወታችን ተግባራዊ በማድረግ ሊሆን ይገባል።

‎በዓሉ፤ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

‎​መልካም_በዓል!!
‎ኢድ_ሙባረክ!!

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀጣይ አቅጫዎችን ‎አስቀመጠ *************************‎‎ግንቦት 08/09/2018 ዓ.ም ቻግኒ ከተማ ምክ...
16/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀጣይ አቅጫዎችን
‎አስቀመጠ *************************

‎ግንቦት 08/09/2018 ዓ.ም ቻግኒ ከተማ ምክር ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ተዋበ ምህረት በቀረበው የ2018 በጀት አመት የተመረጡ የተቋማት የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ያቀረቧቸው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች
‎~የንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የሚያደርገው ጥራት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንዲሚገባ አፈ ጉባኤው አስገነዘበ።
‎~ አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻል አለበት ?
‎~ማደያዎች በአግባቡ ነዳጅና ቤንዚን በህጋዊ መንገድ እንዲሰራጩ በትኩረት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል ።
‎ ~ የግብዓት አቅርቦት በተመለከተ በተለይ ኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት።
‎~ከንግድ አኳያ ህገወጥ ንግድን ከመቆጣጠር አኳያ በትኩረት ስራ መሰራት አለበት?
‎~ ከንግድ አኳያ የነዳጅና የቤንዚን ስርጭት በትኩረት መሰራት ?
‎~ከትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አኳያ የትራንስፖርት አገልግሎት በደንብና አሰራር መሰረት መመራት አለበት?
‎~የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ በትኩረት ስራ መሰረት አለበት ?
‎~ ትራንስፖርት አኳያ ያለአግባብ ከታሪፍ ውጭ ከሚቀበሉት አሽከርካሪዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ስራ መሰራት አለበት በማለት አሰስቧል ? የቀረበው ሪፖርት በሙሉ ድምፅ በእለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። የአንድ ቀን ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ።

‎የቻግኒ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ/////////////////‎      ‎  ግንቦት 08/09/2018ዓ.ም‎   ቻግኒ ከተማ ም/ቤት ‎‎➢በዚህ...
16/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ/////////////////

‎ ግንቦት 08/09/2018ዓ.ም
‎ ቻግኒ ከተማ ም/ቤት

‎➢በዚህ ጉባኤ የሚመከርባቸው አጀንዳዎቹም:-
‎1.የዕለቱን አጀንዳዎች ማፀደቅ
‎2.የ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 46ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ
‎3.በ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 46ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ማዳመጥ
‎4.የቻግኒ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት አመት የተመረጡ ተቋማት የ3ኛው ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት መገምገም
‎~ የቋሚ ኮሚቴዎች የክትትልና ቁጥጥር የውሳኔ ሀሳብ ይቀርባል። ስለዚህ በአጠቃላይ ምክር ቤቱ የአንድ ቀን ውይይት ያድርገል የቀረቡ አጃንዳዎችም በዕለቱ በተገኙ ምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።


‎የቻግኒ ከተማ ም/ቤት በ07/09/2018 ዓ ም የሴቶች ፎርም የቻግኒ ከተማ አስተዳደር የ2018  በጀት አመት የተመረጡ የተቋማት የ3ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት  ግምገመ አካሄዱ።...
15/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ም/ቤት በ07/09/2018 ዓ ም የሴቶች ፎርም የቻግኒ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት አመት የተመረጡ የተቋማት የ3ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገመ አካሄዱ።


‎ግንቦት 07/09/2018ዓ.ም
‎ ቻግኒ ከተማ ም/ቤት



‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ  አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ  ዛሬ ተጀመረ ////////////...
08/05/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬ ተጀመረ ////////////////////////

‎ሚያዚያ 30/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት አመት የ9ወር የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ።

‎የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት አመት የ9ወር እቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርትም በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ፈንታሁን ደማም በኩል ቀርቧል።

‎ሰለሆነም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎~ ያለአግባብ ዋጋ በመጨመር ኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለ እርምጃ ካለ ቢገለፅ?
‎~ወቅታዊ የነዳጅ እጥረትን ምክንያት በማድረግ ህገወጥ ተግባራትን የሚያከናውኑ አካላትን በመቆጣጠር ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው እንዲስተካከሉ ከማድረግ አኳያ እየተሰራ ስራ ካለ ቢገለፅ ?
‎~ የሰንበት ገበያን በማመቻቸት አምራቾችንና ሸማቹን በማገናኘት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እየተሰራ ስራ ካለ ቢገለፅ
‎~ጋርቾን በመደገፍና የገበያ ትስስር በመፍጠር ገበያ እንዲያረጋጋ ከማድረግ አኳያ የተሰራ ስራ ይብራራ
‎~ነዳጅ ከማደያ ከቀዱ በኋላ ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይሰጡ ነዳጁን በህገወጥ መንገድ በመሸጥ ተግባር የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ከትራንስፖርት ተቋም ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራ ምን ይመስላል ?
‎~የሚመጣውን ናፍጣና ቤንዚን በአግባቡ እንዲሰራጭ እንዲሁም ስራ ላይ እንዲውል ተቋም እያደረገ ያለው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ይብራራ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባላት በኩል ምላሽና ማብራሪያ እየተሰጠባቸው ይገኛል።

‎‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ ቀበሌ ምክር  ቤቶች የ2018  በጀት አመት የሚያዚያ ወር  ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች  በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል//////////////////...
01/05/2026


‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ ቀበሌ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት አመት የሚያዚያ ወር ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል/////////////////////
‎የሚያዚያ 23/2018 ዓ ም
‎የጉባኤ አጃንዳዎች፡-
‎አጀንዳ1:- የትምህርት ስራዎች በተመለከተ
‎አጃንዳ2:- የፀጥታ ስራዎች ሁኔታ በተመለከተ
‎አጃንዳ3፡- የጤና ሰራዎች አኳያ፡-ወቅታዊ የወባ ወረርሽኝ ፣የትራኮማ በሽታ እና መንስኤ በተመለከተ
‎አጀንዳ4:- የቀበሌ የ9ወር የማህበራዊ ፍርድ ቤት በተመለከተ
‎ በአጠቃላይ በቀበሌ ምክርቤቶች ሰፊ ማብራሪያና ውይይት አደርገው በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀዋል።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት  ‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች  ለትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።‎‎ቻግኒ ፡ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም ...
10/04/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት
‎ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

‎ቻግኒ ፡ሚያዝያ 3/2018 ዓ.ም አቶ ተዋበ ምህረት መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

‎ በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ ፤በዓሉ በሚከበርበት ጊዜ ደጋፊና ረዳት የሌላቸዉን ወገኖቻችንን በማሰብና በማገዝ በአሉን ማክበር ይኖርብናል በማለት አሳስበዋል ።

‎በመጨረሻም የትንሳኤ በዓሉን የመተሳሰብና የመረዳዳት መንፈስ እንድናሳልፍ ጥሪን አስተላልፋለሁ።

‎በድጋሚ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

‎ ታምፁናስ!

‎ ***መልካም ፋሲካ በዓል ***

‎አቶ ተዋበ ምህረት የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

‎‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ 5ቱ የቀበሌ ምክር  ቤቶች የ2018  በጀት አመት የመጋቢት ወር  ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች  በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል//////////////...
31/03/2026


‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ 5ቱ የቀበሌ ምክር ቤቶች የ2018 በጀት አመት የመጋቢት ወር ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል///////////////////////////////
‎በመጋቢት 22/2018 ዓ ም
‎የጉባኤ አጃንዳዎች፡-
‎አጀንዳ1:- የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በተመለከተ
‎አጃንዳ2:-የቀበሌ ስራ አስፈፃሚ ሹመት ማፅደቅ
‎አጃንዳ3፡- የጤና ሰራዎች አኳያ
‎አጀንዳ4፡-የሰላምና የድህንነት ስራዎችን መገምገም
‎አጀንዳ5:-የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ በተመለከተ
‎ በአጠቃላይ በ5ቱ ቀበሌ ምክርቤቶች ሰፊ ማብራሪያና ውይይት አደርገው በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀዋል።

Address

Chagni
Amhara Region

Telephone

+251582250761

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share