Machakel Woreda Government Communication Affairs Office

Machakel Woreda Government  Communication Affairs Office ራዕይ ፦
በመረጀ የበለጸገ ህብረተሰብ መገንባት!!
የማቻክል ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ፌስቡክ ገፅ

"ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው" በምስራቅ ጎጃም ዞን የ7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በአማኑኤል ምርጫ ክልል  በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እየመረጠ ነው።
01/06/2026

"ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው"

በምስራቅ ጎጃም ዞን የ7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በአማኑኤል ምርጫ ክልል በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እየመረጠ ነው።

ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ።የምስራቅ ጎጃም ዞን ...
31/05/2026

ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር በሃይሉ ታከለ የፀጥታ መዋቅሩን በማደራጀት እና በየምርጫ ጣቢያዎች ስምሪት በመስጠት ለምርጫው ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ ነገ ግንቦት 24/ 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው ምርጫ ህብረተሰቡ ለቀጣይ ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምፁን በነፃነት እንዲሰጥ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ሃላፊው አያይዘው ማህበረሰቡ እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለፀጥታ ስራው ግንባር ቀደም ሚናቸውን በመወጣት ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

  _ማቻክል!‎‎በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል  ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች "ከሞፈር ወደ ትራክተር" በሚል መሪ ሃሳብ የትራክተር እርሻ በልዩ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው።‎‎በወረዳው የሰብል ምርትና ...
29/05/2026

_ማቻክል!

‎በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች "ከሞፈር ወደ ትራክተር" በሚል መሪ ሃሳብ የትራክተር እርሻ በልዩ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው።

‎በወረዳው የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን የላቀ ተቃሚነት ለማረጋገጥ ለግብርና ሜካናይዜሽን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

"የሥላሴ ከብቶች አስደናቂ ሰዋዊ ባህሪ"ቦታው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ነው፤ ታሪካዊው ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም።በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተመሠረተው ታሪካዊው ማኅ...
27/05/2026

"የሥላሴ ከብቶች አስደናቂ ሰዋዊ ባህሪ"

ቦታው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ነው፤ ታሪካዊው ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም።

በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በተመሠረተው ታሪካዊው ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ውስጥ ታዲያ "የሥላሴ ከብቶች" የሚባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የከብት መንጋዎች ይገኛሉ።

እነዚህ ከብቶች ከተለመደው የእንስሳት ባህሪ ውጭ በኾነ ረቂቅ ሥርዓት እና ፍቅር ይመራሉ።

የገዳሙ አፈ-መምህር አባ አማሃ ኢየሱስ ወልደ ሥላሴ እንደሚያብራሩት በእነዚህ እንስሳት እና በሰዎች መካከል አስገራሚ ተግባቦት አለ ይላሉ።

"ላምራስ" በመባል የሚታወቁት የገዳሙ መነኮሳት ከብቶቹን የሚመሩት በዱላ ሳይኾን በለስላሳ ቃል እና የፍቅር ቃና ነው።

እረኛው "ተመለስ" ወይም "ቁም" ሲላቸው ወዲያውኑ ይታዘዛሉ። ጥጃዎችን ከእናቶቻቸው ለይቶ ወደ ግጦሽ ለመውሰድ ሲፈለግም ላምራሱ "ወገን" እያለ ሦሥት ጊዜ ሲያጨበጭብ ጥጃዎቹ ያለምንም ግርግር ተለይተው በሰልፍ ይጓዛሉ።

በሺዎች በሚቆጠሩ መንጋዎች መካከል እያንዳንዱ ላም እና ጥጃ የሰው ጆሮ የማይለየው ልዩ የድምጽ ቃና አላቸው። ጥጃዎቹ ወተት ጠብተው ሲጨርሱ እረኛው "አጎዶ" (ማደሪያ በረት) እያለ ሦሥት ጊዜ ሲያጨበጭብ የራሳቸውን ማደሪያ አውቀው በፈቃዳቸው ይገባሉ።

መንጋውን ወደ ሌላ የግጦሽ ቦታ ለማዛወር ላምራሱ "ጉዞ" እያለ ሦሥት ጊዜ ሲያጨበጭብ ጉዟቸውን ይጀምራሉ። መድረሻቸው ላይ ሲደርሱም "ሠፈር" በሚል የሦሥት ጊዜ ጭብጨባ በአንድነት ይቆማሉ።

በተጨማሪም በገዳሙ የጸሎት እና የቅዳሴ ደወል ሲሰማ በእንስሳቱ ላይ ልዩ ጸጥታ ይሰፍናል።

"ሰው እግዚአብሔርን ሲታዘዝ፣ ፍጥረት ሁሉ ደግሞ ሰውን ይታዘዛል፤ የገዳሙ ሕግ እና ሥርዓት በእኛ ላይ ብቻ ሳይኾን በእነሱም ላይ ይሠራል" ይላሉ አባ አማሃ ኢየሱስ።

የማኅበረ ሥላሴ ከብቶች ታሪክ፣ ፍጥረት ሁሉ በፈጣሪ እና በሰው ልጅ ፍቅር ሲገራ ምን ያህል ውብ እና ሰላማዊ ሥርዓት ሊኖረው እንደሚችል የሚያሳይ ድንቅ የሕይወት ትምህርት ነው።

#መተማ #ኢትዮጵያ!

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዋች  "ከሞፈር ወደ ትራክተር " በሚል እሳቤ የትራክተር እርሻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።መረጃው የጎዛምን ወረዳ  ኮሙዩኒኬሽን ነው።
27/05/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዋች "ከሞፈር ወደ ትራክተር " በሚል እሳቤ የትራክተር እርሻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መረጃው የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው።

 #የከተማው ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም በማስከበር  ለምርጫው  ስኬታማነት የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ ይገባል።አቶ ጌታቸው ሞሴ የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ሰላም...
27/05/2026

#የከተማው ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም በማስከበር ለምርጫው ስኬታማነት የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ ይገባል።

አቶ ጌታቸው ሞሴ የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ
****
የምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጂት ማድረጉን አስታወቀ።

የከተማ አስተዳድሩ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ሞሴ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የፀጥታ ኃይሉ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጂት ማድረጉን በመግለጽ
የፀጥታ ሃይሉ በሰላማዊ መንገድ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲካሄድ ህግና ስርዓትን ከማስከበር ጀምሮ ምርጫው በስኬታማነት እንዲከናወን በገለልተኛነት የሚጠበቅበትን ኀላፊነት እንዲወጣ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው አያይዘው በከተማው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ከፌዴራል የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን አንስተው የከተማው ማህበረሰብ ማህበረሰቡ ይመራኛል የሚለውን የፓለታካ ፓርቲ በነፃነት ወጥቶ እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

 #ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም በማስከበር  ለምርጫው  ስኬታማነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ።******************የምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻ...
27/05/2026

#ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም በማስከበር ለምርጫው ስኬታማነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ።
******************
የምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጂት ማድረጉን አስታወቀ።

የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዘውድ ደምስ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የፀጥታ ኃይሉ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጂት ማድረጉን በመግለጽ
የፀጥታ ሃይሉ በሰላማዊ መንገድ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲካሄድ ህግና ስርዓትን ከማስከበር ጀምሮ ምርጫው በስኬታማነት እንዲከናወን በገለልተኛነት የሚጠበቅበትን ኀላፊነት እንዲወጣ ተናግረዋል።

አቶ ዘውድ አያይዘው በወረዳው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ከፌዴራል የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን አንስተውማህበረሰቡ ይመራኛል የሚለውን የፓለታካ ፓርቲ በነፃነት ወጥቶ እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

 #የፖሊስ ተቋም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትኃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እንዲወጣ  ጥሪ ቀረበ።*****************************በምስራቅ ጎጃም...
27/05/2026

#የፖሊስ ተቋም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትኃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ።
*****************************
በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ እና የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤቶች በጋራ በመሆን" ለምርጫ የፖሊስ ሚና" በሚል መሪ መልዕክት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ለፖሊስ አመራሮች እና አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው ላይ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ መንገድ ደህንነት ዋና ክፍል ሃላፊ ኮማንደር የሽዋስ አከለ፣የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ሽታው የሻነህ፣የማቻክል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አንዷለም*እናውጋው፣የጸጥታ አመራሮች፣የፖሊስ አመራሮች እንዲሁም የፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።

ስልጠናው ፖሊስ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በመሆን፣ ለህገ-መንግስቱና ለህዝብ ደህንነት ብቻ ታማኝ በመሆን የህዝብን አመኔታ እንዲያገኝ ዓለማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ፖሊስ በምርጫ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የተለያዩ የጸጥታ ስጋቶችን በጥንቃቄ በመፍታት፣ የዜጎችን የመምረጥ መብትና ደህንነት በማስጠበቅ የተጣለበትን ኃላፊነት በታማኝነት እንዲወጣ የማያስችል ስልጠና እንደሚሆን ይጠበቃል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

ለኢትዮጵያችን የዴሞክራሲ ጉዞ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ሊከፈት... 5 ቀናት ብቻ ቀሩትዛሬ ግንቦት 19 ነውሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ በይፋ ይካሄዳል።የእርስዎ አን...
27/05/2026

ለኢትዮጵያችን የዴሞክራሲ ጉዞ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ሊከፈት... 5 ቀናት ብቻ ቀሩት

ዛሬ ግንቦት 19 ነው

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ በይፋ ይካሄዳል።

የእርስዎ አንድ ድምፅ የአገርን አቅጣጫ የመወሰን ትልቅ አቅም አለው።

በዚህ ታሪካዊ ቀን ድምፅዎን ሰጥተው ኃላፊነትዎን ለመወጣት እና አሻራዎን ለማሳረፍ ዝግጁ ነዎት?

Ethiopian Broadcasting Corporation

"ብልጽግና ትላንትን አክሞ ነገን አልሞ እየሰራ ያለ  ፓርቲ ነው" አቶ አንዷለም እናውጋው የማቻክል ወረዳ አስተዳዳሪ****************************የማቻክል ወረዳ አስተዳድር  "...
26/05/2026

"ብልጽግና ትላንትን አክሞ ነገን አልሞ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው"
አቶ አንዷለም እናውጋው የማቻክል ወረዳ አስተዳዳሪ
****************************
የማቻክል ወረዳ አስተዳድር "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትኃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አንዷለም እናውጋው ብልጽግና የልዕልና ምልክት የእድገትና የአንድነት ማሳያ መሆኑን አንስተውፓርቲው ትላንትን አክሞ ዛሬን ሰርቶ ነገን አቅዶ እየሰራ ያለ መሆኑን በመግለጽ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ አሻጋሪ እና ተምሳሌት ኢትዮጵያን የመገንባት ልዩ ምዕራፍ ነው ብለዋል።

አቶ አንዷለም አያይይዘው ፓርቲው በተስፋ ቃል ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ተግባር ላይ ቆሞ ኢትዮጵያን ያሻገረ ሲሆን በግብርና፣በጤና እና በትምህርት ዘርፎች ከፍተኛ ለውጥን ያሳየ መሆኑ በአካባቢያችን የተገነቡ ያሉ የትምህርት፣የመድሃኒት ቤት፣ በበጋ መስኖ በአትክልትና ፍራፍሬ የታየው ውጤት ህያው ምስክር መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላው በውይይቱ ላይ የተገኙት የማቻክል ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዘውድ ደምስ ዛሬም ብልጽግናን በመምረጥ የዘመናት የልማት ጥያቄዎቹ ዘላቂ መልስ እንዲያገኙ የቀደመ መንግስት የመመስረት ታሪኩን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መድገም እንደሚገባ በመግለጽ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትኃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ ማህበረሰቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም መልዕክት አስተላልፈዋል።

Address

Amanuel, East Gojjam
Amanu'el

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Machakel Woreda Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Machakel Woreda Government Communication Affairs Office:

Share